Genesis 49

Genesis 49:1

ያዕቆብ ወንዶች ልጆቹን የሰበሰበበት ምክንያት ምን ነበር?

ያዕቆብ ወደ ፊት በእነርሱና በዘሮቻቸው ሊሆን ያለውን ይነግራቸው ዘንድ ወንዶች ልጆቹን በአንድ ላይ ሰበሰባቸው

Genesis 49:3

ሮቤል ምን አዎንታዊ አስተዋጽዖ ነበረው?

ሮቤል የክብርና የኃይል አለቃ ነበር

ሮቤል በኩር ቢሆንም አለቅነትን ያጣው ለምንድነው?

ሮቤል የአባቱን መኝታ አርክሶ ስለ ነበረ አለቅነትን አጣ

Genesis 49:7

ሮቤል በኩር ቢሆንም አለቅነትን ያጣው ለምንድነው?

ሮቤል የአባቱን መኝታ አርክሶ ስለ ነበረ አለቅነትን አጣ

Genesis 49:8

ያዕቆብ የተናገረው ሌሎቹ ወንዶች ልጆቹ በይሁዳ ፊት ምን እንደሚያደርጉ ነበር?

ሌሎች ወንዶች ልጆቹ በይሁዳ ፊት እንደሚሰግዱ ያዕቆብ ተናገረ

Genesis 49:10

ይሁዳ ወደ ፊት ስለሚሆኑለት ነገሮች ምን የተስፋ ቃል ተሰጠው?

ሴሎ እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከእርሱ እንደማይርቅና ሕዝቦች እንደሚታዘዙት የተስፋ ቃል ተሰጠው

Genesis 49:13

ያዕቆብ፣ የዛብሎን ዘሮች መኖሪያቸው የት ይሆናል አለ?

የዛብሎን ዘሮች መኖሪያ በባህር ዳርቻ እንደሚሆን ያዕቆብ ተናገረ

Genesis 49:16

ያዕቆብ፣ ዳን የትኛውን እንስሳ ይመስላል አለ?

ያዕቆብ፣ ዳን እንደ መርዘኛ እባብ ይሆናል አለ

Genesis 49:19

ያዕቆብ፣ አሴር በምን ይታወቃል አለ?

ያዕቆብ፣ አሴር ለነገሥታት ጣፋጭ ምግብ በማቅረብ ይታወቃል አለ

Genesis 49:22

ያዕቆብ፣ ዮሴፍ እንዴት ያለውን ተክል ይመስላል አለ?

ዮሴፍ፣ ቅርንጫፎቹ በግድግዳ ላይ የሚወጡ ትንሹን ፍሬአማ ዛፍ እንደሚመስል ያዕቆብ ተናገረ

Genesis 49:24

ያዕቆብ፣ የዮሴፍን ቀስት የሚያጸናና እጆቹን ብልኅ የሚያደርጋቸው ማን ነው አለ?

ኃያሉ የያዕቆብ አምላክ እጆች፣ የእስራኤልም ዓለት የዮሴፍን ቀስት እንደሚያጸናና እጆቹን ብልኆች እንደሚያደርጋቸው ያዕቆብ ተናገረ

Genesis 49:31

ያዕቆብ ለመቀበር በሚፈልግበት ቦታ ቀደም ሲል የተቀበረበት ማን ነበር?

ቀደም ሲል አብርሃም፣ ሣራ፣ ይስሐቅ፣ ርብቃና ልያ በዚያ ተቀብረው ነበር

ያዕቆብ ለልጆቹ በረከትና መመሪያ ከሰጣቸው በኋላ ምን አደረገ?

ያዕቆብ ሞተ፣ ወደ ወገኖቹም ሄደ