Genesis 47

Genesis 47:3

አምስቱ የዮሴፍ ወንድሞች ለፈርዖን የነገሩት ሥራቸው ምን መሆኑን ነበር?

አምስቱ የዮሴፍ ወንድሞች ሥራቸው በጎችን ማርባት መሆኑን ለፈርዖን ነገሩት

ወንድማማቾቹ የተናገሩት በግብፅ ምድር ምን ዓይነት ነዋሪዎች መሆናቸውን ነበር?

ወንድማማቾቹ በግብፅ ምድር ጊዜያዊ ነዋሪዎች መሆናቸውን ተናገሩ

Genesis 47:5

ፈርዖን፣ የዮሴፍን ቤተሰብ በሚመለከት ዮሴፍ ምን እንዲያደርግ ነገረው?

ፈርዖን በመልካሙ ምድር፣ በጌሤም ምድር ቤተሰቦቹን እንዲያሰፍራቸው ለዮሴፍ ነገረው

Genesis 47:7

ያዕቆብ ከፈርዖን ጋር በተገናኘ ጊዜና ከዚያም ሲለየው ለፈርዖን ምን አደረገለት?

ያዕቆብ ከፈርዖን ጋር በተገናኘ ጊዜና ከእርሱ በሚለይበትም ጊዜ ፈርዖንን ባረከው

ያዕቆብ ከፈርዖን ጋር በተገናኘ ጊዜ ዕድሜው ስንት ነበር?

የያዕቆብ ዕድሜ አንድ መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር

ያዕቆብ፣ ዕድሜው ከአባቶቹ ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ነው አለ?

ያዕቆብ፣ የእርሱ ዕድሜ የአባቶቹን ያህል እንዳልሆነ ተናገረ

ያዕቆብ ከፈርዖን ጋር በተገናኘ ጊዜና ከዚያም ሲለየው ለፈርዖን ምን አደረገለት?

ያዕቆብ ከፈርዖን ጋር በተገናኘ ጊዜና ከእርሱ በሚለይበትም ጊዜ ፈርዖንን ባረከው

Genesis 47:13

ዮሴፍ እህል በመሸጥ ምን ለማድረግ ቻለ?

ዮሴፍ በግብፅና በከነዓን ምድር የነበረውን ገንዘብ ሁሉ መሰብሰብ ችሎ ነበር

Genesis 47:15

ዮሴፍ ለግብፃውያን እህል በመስጠት በምትኩ ምን ለማድረግ ቻለ?

ዮሴፍ ለግብፃውያን በሚሰጣቸው እህል ምትክ ከብቶቻቸውን በሙሉ መውሰድ ቻለ

ዮሴፍ ለግብፃውያን እህል በመስጠት በምትኩ ምን ለማድረግ ቻለ?

ዮሴፍ ለግብፃውያን በሚሰጣቸው እህል ምትክ ከብቶቻቸውን በሙሉ መውሰድ ቻለ

Genesis 47:18

የግብፃውያኑ ገንዘብና ከብቶች ሁሉ በሚሰጣቸው እህል ምትክ ለፈርዖን ከተሰጡ በኋላ የግብፅ ሰዎች ተጨማሪ እህል ለማግኘት ለፈርዖን ምን አቀረቡ?

የግብፅ ሰዎች ተጨማሪ እህል ለማግኘት የፈርዖን አገልጋዮች ይሆኑ ዘንድ መሬታቸውንና ራሳቸውን አቀረቡ

የግብፃውያኑ ገንዘብና ከብቶች ሁሉ በሚሰጣቸው እህል ምትክ ለፈርዖን ከተሰጡ በኋላ የግብፅ ሰዎች ተጨማሪ እህል ለማግኘት ለፈርዖን ምን አቀረቡ?

የግብፅ ሰዎች ተጨማሪ እህል ለማግኘት የፈርዖን አገልጋዮች ይሆኑ ዘንድ መሬታቸውንና ራሳቸውን አቀረቡ

ዮሴፍ ከምርቱ ሁሉ ምን ያህሉ ለፈርዖን እንዲሰጥ ጠየቀ?

ዮሴፍ የምርቱ አንድ አምስተኛ ለፈርዖን እንዲሰጥ ጠየቀ

Genesis 47:27

እስራኤላውያን በግብፅ ምድር ስኬታማ የሆኑት እንዴት ባሉ መንገዶች ነበር?

እስራኤላውያኑ በግብፅ ምድር ሀብት አፈሩ፣ ፍሬአማ ሆኑ፣ እጅግም በዙ

ያዕቆብ በስንት ዓመቱ ሞተ?

ያዕቆብ በአንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመቱ ሞተ

Genesis 47:29

እስራኤል ዮሴፍን ያስማለው ምን እንዲያደርግለት ነበር?

እስራኤል፣ በአባቶቹ የመቃብር ሥፍራ እንዲቀብረው ዮሴፍ ይምልለት ዘንድ ጠየቀው