Genesis 44

Genesis 44:1

ዮሴፍ፣ ወንድማማቾቹ ከመሄዳቸው በፊት ጆንያዎቻቸው ውስጥ ምን እንዲያደርግ ለመጋቢው ነገረው?

የወንድማማቾቹን ጆንያ በእህል እንዲሞላ፣ ገንዘባቸውን በጆንያቸው ውስጥ እንዲያደርግና በታናሽየው ጆንያ ውስጥ የብር ጽዋውን እንዲያደርግ ዮሴፍ ለመጋቢው ነገረው

Genesis 44:3

በመሠረቱ፣ ዮሴፍ ለመጋቢው አስቀድሞ የነገረው፣ ወንድማማቾቹን ከከተማ ውጭ በሚይዛቸው ጊዜ ምን እንዲላቸው ነበር?

መልካም በተደረገላቸው ፈንታ ለምን ክፉ እንደ መለሱ እንዲጠይቃቸውና የዮሴፍን ጽዋ ስለ መስረቃቸው እንዲወቅሳቸው ዮሴፍ ለመጋቢው ነገረው

በመሠረቱ፣ ዮሴፍ ለመጋቢው አስቀድሞ የነገረው፣ ወንድማማቾቹን ከከተማ ውጭ በሚይዛቸው ጊዜ ምን እንዲላቸው ነበር?

መልካም በተደረገላቸው ፈንታ ለምን ክፉ እንደ መለሱ እንዲጠይቃቸውና የዮሴፍን ጽዋ ስለ መስረቃቸው እንዲወቅሳቸው ዮሴፍ ለመጋቢው ነገረው

Genesis 44:8

ወንድማማቾቹ፣ ከእነርሱ አንዱ የዮሴፍን ጽዋ ሠርቆ ከሆነ ምን ለማድረግ ማሉ?

ወንድማማቾቹ፣ ጽዋው የሚገኝበት ሰው እንዲገደልና የቀሩት ባሪያዎች እንዲሆኑ ተናገሩ

መጋቢው፣ ጽዋው ተሠርቆ ከሆነ በምን ዓይነት ቅጣት እንደሚቀጣ ተናገረ?

መጋቢው፣ ጽዋው የሚገኝበት ሰው የእርሱ ባሪያ እንደሚሆንና ሌሎቹ ንጹሐን እንደሚሆኑ ተናገረ

Genesis 44:11

መጋቢው ያገኘው ምንድነው? የወንድማማቾቹ ምላሽስ ምን ሆነ?

መጋቢው ጽዋውን ከብንያም ጆንያ ውስጥ አገኘው፣ ወንድማማቾቹም በኀዘን ልብሳቸውን ቀደዱ

መጋቢው ያገኘው ምንድነው? የወንድማማቾቹ ምላሽስ ምን ሆነ?

መጋቢው ጽዋውን ከብንያም ጆንያ ውስጥ አገኘው፣ ወንድማማቾቹም በኀዘን ልብሳቸውን ቀደዱ

Genesis 44:14

ወንድማማቾቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ውስጥ ተመልሰው በመጡ ጊዜ ምን አደረጉ?

ወንድማማቾቹ በዮሴፍ ፊት በምድር ላይ ሰገዱ

Genesis 44:16

ይሁዳ፣ የወንድማማቾቹን ኃጢአት የገለጠው ማን ነው አለ?

ይሁዳ፣ ኃጢአታቸውን እግዚአብሔር እንደገለጠው ተናገረ

ይሁዳ፣ ወንድማማቾቹ ሁሉ አሁን ምንድናቸው አለ?

ይሁዳ፣ ወንድማማቾቹ ሁሉ አሁን የዮሴፍ ባሪያዎች ናቸው አለ

ዮሴፍ በወንድማማቾቹ ላይ ምን ዓይነት ቅጣት እንደሚፈጽም ተናገረ?

ዮሴፍ፣ ጽዋው በእጁ የተገኘበት ሰው ባሪያው እንደሚሆንና ሌሎቹ በሰላም መሄድ እንደሚችሉ ተናገረ

ይሁዳ፣ አባቱ ታናሽ ወንድማቸውን ስለ መውደዱ የሰጠው ምክንያት ምን ነበር?

ታናሽ ወንድማቸው አባቱ በሽምግልናው የወለደው መሆኑንና ከእናቱ እርሱ ብቻ መቅረቱን ይሁዳ ተናገረ

Genesis 44:20

ወንድማማቾቹ፣ ታናሽየው ከሌለ አባታቸው ምን ይሆናል ብለው ሰጉ?

ወንድማማቾቹ፣ ታናሽየው ከሌለ አባታቸው ይሞታል ብለው ሰጉ

Genesis 44:23

ይሁዳ፣ ወንድማማቾቹ ብንያምን ከእነርሱ ጋር ወደ ግብፅ ለማምጣት የተገደዱት ለምንድነው አለ?

ታናሽ ወንድማቸው ካልመጣ ፊቱን እንደማያዩ ዮሴፍ ተናግሯቸው ስለ ነበረ ብንያምን ለማምጣት መገደዳቸውን ይሁዳ ተናገረ

ይሁዳ፣ ወንድማማቾቹ ብንያምን ከእነርሱ ጋር ወደ ግብፅ ለማምጣት የተገደዱት ለምንድነው አለ?

ታናሽ ወንድማቸው ካልመጣ ፊቱን እንደማያዩ ዮሴፍ ተናግሯቸው ስለ ነበረ ብንያምን ለማምጣት መገደዳቸውን ይሁዳ ተናገረ

Genesis 44:27

እስራኤል የሚያስበው ዮሴፍ ምን ሆኗል ብሎ ነበር?

እስራኤል፣ በርግጥ ዮሴፍ በአውሬ ተቦጫጭቋል ብሎ አሰበ

እስራኤል፣ ብንያም ከእርሱ ከተወሰደ ምን እንደሚሆን ተናገረ?

ወንድማማቾቹ፣ ሽበቱን በኀዘን ወደ መቃብር እንደሚያወርዱ እስራኤል ተናግሮ ነበር

Genesis 44:30

ይሁዳ፣ ያለ ብንያም ከተመለሱ አባቱ ምን እንደሚሆን ተናገረ?

አባቱ እንደሚሞት ይሁዳ ተናገረ

ይሁዳ ስለ ብንያም ዋስትና የሰጠው ምን ለመሆን ነበር?

ይሁዳ ብንያምን ወደ አባቱ ካልመለሰው በደሉን ለዘላለም እንደሚሸከም ተናግሮ ነበር

Genesis 44:33

ብንያም ወደ አባቱ መመለስ ይችል ዘንድ ይሁዳ ዮሴፍን የጠየቀው ምን እንዲያደርግ ነበር?

ይሁዳ፣ ብንያም ወደ አባቱ መመለስ ይችል ዘንድ ዮሴፍ እርሱን ባሪያው እንዲያደርገው ጠየቀው