Genesis 43

Genesis 43:1

እስራኤል እንደገና ወደ ግብፅ እንዲሄዱና ጥቂት እህል እንዲገዙ ለልጆቹ የነገራቸው ለምንድነው?

ረሃቡ ጽኑ ስለነበረና በመጀመሪያ ወደ ግብፅ ተጉዘው ያመጡትን እህል በልተው ስለ ጨረሱት ነበር

እስራኤል እንደገና ወደ ግብፅ እንዲሄዱና ጥቂት እህል እንዲገዙ ለልጆቹ የነገራቸው ለምንድነው?

ረሃቡ ጽኑ ስለነበረና በመጀመሪያ ወደ ግብፅ ተጉዘው ያመጡትን እህል በልተው ስለ ጨረሱት ነበር

Genesis 43:3

ይሁዳ፣ እንደገና ወደ ግብፅ የሚወርዱ ከሆነ ምን ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናገረ?

ወደ ግብፅ ለመውረድ ወንድማቸው ብንያም አብሮአቸው መሆን እንዳለበት ይሁዳ ተናገረ

Genesis 43:8

ይሁዳ ለአባቱ ለእስራኤል የማለው ምን ብሎ ነበር?

ብንያምን መልሶ ባያመጣው በደሉ ለዘላለም በእርሱ ላይ እንደሚሆን ይሁዳ ተናገረ

Genesis 43:11

እስራኤል ለወንድማማቾቹ የነገራቸው ወደ ግብፅ ምን ይዘው እንዲሄዱ ነበር?

እስራኤል ለወንድማማቾቹ የነገራቸው ከምድሪቱ ምርጥ ፍሬ ጥቂትና ገንዘቡን እጥፍ አድርገው እንዲወስዱ ነበር

እስራኤል ለወንድማማቾቹ የነገራቸው ወደ ግብፅ ምን ይዘው እንዲሄዱ ነበር?

እስራኤል ለወንድማማቾቹ የነገራቸው ከምድሪቱ ምርጥ ፍሬ ጥቂትና ገንዘቡን እጥፍ አድርገው እንዲወስዱ ነበር

Genesis 43:13

ጉዞውን አስመልክቶ እስራኤል እግዚአብሔርን ስለ ምን ጠየቀ?

ወንድማማቾቹ ሁሉ ይለቀቁ ዘንድ በግብፅ ምድር እግዚአብሔር ምህረትን እንዲሰጣቸው እስራኤል ጠየቀ

Genesis 43:18

ወደ ዮሴፍ ቤት ባመጧቸው ጊዜ ወንድማማቾቹ ምን አሉ? ለምን?

ወንድማማቾቹ፣ በመጀመሪያው ጉዞአቸው በጆንያዎቻቸው ውስጥ ስላገኙት ገንዘብ እንዳይታሰሩና ባሪያ እንዳይሆኑ ፈርተው ነበር

Genesis 43:21

ወንድማማቾቹ ለዮሴፍ ቤት መጋቢ የነገሩት ምን ነበር?

ወንድማማቾቹ በጆንያዎቻቸው ውስጥ ያገኙትን ገንዘብ መልሰው ማምጣታቸውንና እህል ለመግዛትም ገንዘብ እንደ ያዙ ለመጋቢው ነገሩት

ወንድማማቾቹ ለዮሴፍ ቤት መጋቢ የነገሩት ምን ነበር?

ወንድማማቾቹ በጆንያዎቻቸው ውስጥ ያገኙትን ገንዘብ መልሰው ማምጣታቸውንና እህል ለመግዛትም ገንዘብ እንደ ያዙ ለመጋቢው ነገሩት

መጋቢው፣ በጆንያዎቻቸው ውስጥ የተገኘው ገንዘብ ከየት የመጣ ነው አላቸው?

መጋቢው፣ በጆንያዎቻቸው ውስጥ የተገኘው ገንዘብ ከአምላካቸው የመጣ መሆኑን ነገራቸው

Genesis 43:26

ዮሴፍ ወደ ቤት በመጣ ጊዜ ወንድማማቾቹ ምን አደረጉ?

ወንድማማቾቹ ስጦታዎቹን ወደ ቤት አመጡና መሬት ላይ ወድቀው ለዮሴፍ ሰገዱለት

ዮሴፍ ወንድማማቾቹን የጠየቃቸው ስለ ማን ነበር?

ዮሴፍ ወንድማማቾቹን የጠየቃቸው ስለ አባታቸው ደኅንነት ነበር

Genesis 43:30

ዮሴፍ ከክፍሉ ውስጥ ለመውጣት የቸኮለው ለምንድነው? ከወጣስ በኋላ ምን አደረገ?

ዮሴፍ፣ ስለ ብንያም ውስጡ ስለተናወጠ ከክፍሉ በችኮላ ወጣና ወደ ራሱ ክፍል ገብቶ አለቀሰ

Genesis 43:32

ግብፃውያንና ዕብራውያን ለየብቻ የተመገቡት ለምንድነው?

ለግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር መብላት እንደ መርከስ ስለሚቆጠር ነበር

ወንድማማቾቹ ለማዕድ የተቀመጡት እንዴት ባለ ቅደም ተከተል ነበር?

ወንድማማቾቹ እንደተወለዱበት እንደ ዕድሜአቸው በቅደም ተከተል ለማዕድ ተቀመጡ

ወንድማማቾቹ ስለ ተቀበሉት የምግብ ድርሻ ያልተለመደ የሆነው ምን ነበር?

የብንያም ድርሻ ከወንድሞቹ ሁሉ ይልቅ አምስት ዕጥፍ ያህል ነበር