Genesis 35

Genesis 35:1

እግዚአብሔር ለያዕቆብ ሄዶ እንዲያደርግ የነገረው ምን ነበር?

እግዚአብሔር፣ ያዕቆብ ወደ ቤቴል እንዲሄድና ለተገለጠለት አምላክ መሠዊያ እንዲሠራ ነገረው

ከዚያም፣ ያዕቆብ ወገኖቹ ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

ያዕቆብ፣ ባዕዳን አማልክትን እንዲያርቁ፣ ራሳቸውን እንዲያነጹና ልብሳቸውን እንዲለውጡ ለወገኖቹ ነገራቸው

Genesis 35:4

በተጓዙ ጊዜ በያዕቆብና በወገኖቹ ዙሪያ ባሉ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ያላሳደዷቸው ለምንድነው?

በዙሪያቸው የሚገኙ ከተሞች ሰዎች እግዚአብሔርን ፈርተው ስለ ነበር አላሳደዷቸውም

Genesis 35:6

ያዕቆብ የመጡበትን ስፍራ ለምን "ኤልቤቴል" ብሎ ጠራው?

ከኤሳው በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ስፍራ ራሱን ገልጦለት ስለ ነበረ ያዕቆብ "ኤልቤቴል" ብሎ ጠራው

Genesis 35:9

እግዚአብሔር ለያዕቆብ ማን የሚል አዲስ ስም ሰጠው?

እግዚአብሔር እስራኤል የሚል አዲስ ስም ለያዕቆብ ሰጠው

Genesis 35:11

እግዚአብሔር ለያዕቆብ እንደገና ያረጋገጠለት የትኛውን ተስፋ ነበር?

ከዘሮቹ መካከል ነገሥታት የሚወጡበት ብዙ ሕዝብ እንደሚያደርገውና እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለይስሐቅ ተስፋ የሰጠውን ምድር ለእርሱና ለዘሩ እንደሚሰጥ የገባለትን ቃል ለያዕቆብ እንደገና አረጋገጠለት

Genesis 35:16

ራሔል ቢንያምን በምታምጥበት ወቅት ምን ሆነች?

ራሔል ቢንያምን ለመውለድ በምታምጥበት ወቅት ሞተች

Genesis 35:21

ራሔል ቢንያምን በምታምጥበት ወቅት ምን ሆነች?

ራሔል ቢንያምን ለመውለድ በምታምጥበት ወቅት ሞተች

Genesis 35:23

እስራኤል የሰማው ሮቤል ምን ማድረጉን ነበር?

ሮቤል ከእስራኤል ቁባት ከባላ ጋር መተኛቱን እስራኤል ሰማ

ያዕቆብ ስንት ወንዶች ልጆች ነበሩት?

ያዕቆብ አሥራ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት

ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ወንዶች ልጆች የትኞቹ ነበሩ?

ዮሴፍና ቢንያም የተወለዱት ከራሔል ነበር

Genesis 35:28

ይስሐቅ ስንት አመት ኖረ?

ይስሐቅ አንድ መቶ ስምንት አመት ኖረ

ይስሐቅን ማን ቀበረው?

ኤሳውና ያዕቆብ ይስሐቅን ቀበሩት