Genesis 34

Genesis 34:1

የኤሞር ልጅ ሴኬም የልያን ልጅ ዲናን ባያት ጊዜ ምን አደረገ?

ሴኬም ዲናን ወሰዳት፣ ከእርስዋም ጋር ተኛ፣ አስነወራትም

Genesis 34:4

በዲና ላይ የሆነውን ነገር በሰማ ጊዜ ያዕቆብ በመጀመሪያ ምን አደረገ?

ልጆቹ ከመስክ እስኪመጡ ድረስ ያዕቆብ ዝም አለ

Genesis 34:6

የያዕቆብ ወንዶች ልጆች፣ ሴኬም በዲና ላይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ ምን አደረጉ?

የያዕቆብ ወንዶች ልጆች በጣም ተቆጡ

Genesis 34:8

የሴኬም አባት ኤሞር ያዕቆብ ምን እንዲያደርግ ፈለገ?

ዲና ለሴኬም ሚስት እንድትሆነው እንዲሰጥና የያዕቆብ ቤተሰቦች ከኤሞር ቤተሰቦች ጋር እንዲጋቡ ያዕቆብ እንዲፈቅድ ኤሞር ፈለገ

የሴኬም አባት ኤሞር ያዕቆብ ምን እንዲያደርግ ፈለገ?

ዲና ለሴኬም ሚስት እንድትሆነው እንዲሰጥና የያዕቆብ ቤተሰቦች ከኤሞር ቤተሰቦች ጋር እንዲጋቡ ያዕቆብ እንዲፈቅድ ኤሞር ፈለገ

Genesis 34:11

ሴኬም፣ ዲና ሚስት ትሆነው ዘንድ ምን ለማድረግ ፈቃደኛ እንደሚሆን ተናገረ?

ያዕቆብ የሚጠይቀውን ያህል ብዙ ጥሎሽ እንደሚከፍል ሴኬም ተናገረ

የያዕቆብ ልጆች ለሴኬም እንዴት ባለ መንገድ መለሱለት? ለምን?

ሴኬም ዲናን ስላስነወራት የያዕቆብ ልጆች ለሴኬም በተንኮል መለሱለት

Genesis 34:14

የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ከኤሞር ቤተሰቦች ጋር ለመጋባት ከመስማማታቸው በፊት ለኤሞር ያስቀመጡት ቅድመ ሁኔታ ምን ነበር?

የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ከኤሞር ቤተሰቦች ጋር ለመጋባት ከመስማማታቸው በፊት ወንዶቹ ሁሉ እንዲገረዙ ጠየቁ

Genesis 34:22

ኤሞርና ሴኬም ለከተማቸው ወንዶች በሚናገሩበት ጊዜ ከያዕቆብ ቤተሰቦች ጋር ከተጋቡ የእነርሱ እንደሚሆን የተናገሩት ምኑን ነበር?

ከያዕቆብ ቤተሰብ ጋር ከተጋቡ የያዕቆብ ከብቶች፣ ንብረቶቹና እንስሶቹ በሙሉ የእነርሱ እንደሚሆኑ ተናገሩ

Genesis 34:24

የኤሞር ከተማ ሰዎች ለመገረዝ ፈቃደኞች ይሆኑ እንደ ሆነ በተጠየቁ ጊዜ ምላሻቸው ምን ሆነ?

የኤሞር ከተማ ሰዎች ኤሞርንና ሴኬምን ሰሟቸውና ወንዶቹ ሁሉ ተገረዙ

የኤሞር ቤተሰቦች የሆኑ ወንዶች ከተገረዙ በኋላ በሦስተኛው ቀን ስምዖንና ሌዊ ምን አደረጉ?

ስምዖንና ሌዊ በኤሞር ከተማ የሚኖሩትን ወንዶች በሙሉ ገደሏቸው

Genesis 34:27

ከዚያ በኋላ የያዕቆብ ወንዶች ልጆች በሙሉ ምን አደረጉ?

የያዕቆብ ወንዶች ልጆቹ በሙሉ ከተማይቱን ዘረፉ፣ ሀብታቸውን ሁሉ ወሰዱ፣ ሕፃናቶቻቸውንና ሚስቶቻቸውንም ማረኩ

ከዚያ በኋላ የያዕቆብ ወንዶች ልጆች በሙሉ ምን አደረጉ?

የያዕቆብ ወንዶች ልጆቹ በሙሉ ከተማይቱን ዘረፉ፣ ሀብታቸውን ሁሉ ወሰዱ፣ ሕፃናቶቻቸውንና ሚስቶቻቸውንም ማረኩ

ከዚያ በኋላ የያዕቆብ ወንዶች ልጆች በሙሉ ምን አደረጉ?

የያዕቆብ ወንዶች ልጆቹ በሙሉ ከተማይቱን ዘረፉ፣ ሀብታቸውን ሁሉ ወሰዱ፣ ሕፃናቶቻቸውንና ሚስቶቻቸውንም ማረኩ

Genesis 34:30

ስምዖንና ሌዊ ያደረጉትን በተረዳ ጊዜ የያዕቆብ ምላሽ ምን ነበር?

አሁን የአገሪቱ ነዋሪዎች እርሱንና ወገኑን ሊያጠፉ ነውና ስምዖንና ሌዊ መከራ እንዳመጡበት ያዕቆብ ተናገረ

ስምዖንና ሌዊ ይህንን ለምን እንዳደረጉ ተናገሩ?

ልክ በጋለሞታ እንደሚደረገው ሴኬም በእህታቸው በዲና ላይ በማድረጉ ምክንያት ይህንን እንዳደረጉ ስምዖንና ሌዊ ተናገሩ