Genesis 31

Genesis 31:1

ላባና ወንዶች ልጆቹ ያዕቆብ ሀብቱን ሁሉ ያገኘው ከየት ነው ብለው ያምኑ ነበር?

ላባና ወንዶች ልጆቹ ያዕቆብ ሀብቱን ሁሉ ያገኘው ከላባ ንብረት ነው ብለው አመኑ

ላባና ወንዶች ልጆቹ ያዕቆብ ሀብቱን ሁሉ ያገኘው ከየት ነው ብለው ያምኑ ነበር?

ላባና ወንዶች ልጆቹ ያዕቆብ ሀብቱን ሁሉ ያገኘው ከላባ ንብረት ነው ብለው አመኑ

Genesis 31:4

እግዚአብሔር አምላክ ለያዕቆብ የሰጠው መመሪያ ምን ነበር?

ያዕቆብ ወደ አባቶቹና ወደ ዘመዶቹ ምድር እንዲመለስ እግዚአብሔር አምላክ መመሪያ ሰጠው

Genesis 31:7

እግዚአብሔር የላባን ከብቶች ወስዶ ለያዕቆብ የሰጠው እንዴት ነበር?

እግዚአብሔር፣ የያዕቆብ ደሞዝ የሆኑትን እንስሶች ዥንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸው እንዲሆኑ አደረጋቸው

Genesis 31:12

እግዚአብሔር የላባን ከብቶች ወስዶ ለያዕቆብ የሰጠው እንዴት ነበር?

እግዚአብሔር፣ የያዕቆብ ደሞዝ የሆኑትን እንስሶች ዥንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸው እንዲሆኑ አደረጋቸው

Genesis 31:14

ራሔልና ልያ ለአባታቸው ለላባ ምን ዓይነት አመለካከት ነበራቸው?

ራሔልና ልያ፣ ላባ እንደ ባዕዳን እንደ ቆጠራቸውና ሽጧቸው ገንዘባቸውን እንደ በላ ተናገሩ

ራሔልና ልያ ለአባታቸው ለላባ ምን ዓይነት አመለካከት ነበራቸው?

ራሔልና ልያ፣ ላባ እንደ ባዕዳን እንደ ቆጠራቸውና ሽጧቸው ገንዘባቸውን እንደ በላ ተናገሩ

Genesis 31:19

ራሔል ከያዕቆብ ጋር ከመሄዷ በፊት ምን አደረገች?

ራሔል የአባቷን ቤተሰብ አማልክት ሰረቀች

በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ላባን ያታለለው እንዴት ነበር?

ያዕቆብ መሄዱን ለላባ ባለ መንገር አታለለው

Genesis 31:22

ያዕቆብ መኮብለሉ በተነገረው ጊዜ ላባ ምን አደረገ?

ላባ ዘመዶቹን ሰብስቦ ሰባት ቀን ያህል ያዕቆብን ተከታተለው

ያዕቆብ መኮብለሉ በተነገረው ጊዜ ላባ ምን አደረገ?

ላባ ዘመዶቹን ሰብስቦ ሰባት ቀን ያህል ያዕቆብን ተከታተለው

Genesis 31:24

እግዚአብሔር ለላባ በሕልም የነገረው ምን ነበር?

ያዕቆብን በጎም ይሁን ክፉ እንዳይናገረው እግዚአብሔር ለላባ ነገረው

Genesis 31:31

ያዕቆብ ከላባ በድብቅ የኮበለለበት ምክንያት ምንድነው አለ?

ላባ ልጆቹን በኃይል የሚወስድበት መስሎት ስለ ፈራ በድብቅ መኮብለሉን ያዕቆብ ተናገረ

ላባ የቤተ ሰቡን አማልክት ስለ መስረቁ ያዕቆብን በወቀሰው ጊዜ ያዕቆብ ምን አለ?

ያዕቆብ፣ የላባን ቤተሰብ አማልክት የሰረቀ ማንም ቢሆን ይሙት አለ

Genesis 31:34

ላባ የቤተ ሰቡን አማልክት በያዕቆብ ንብረት ውስጥ ፈልጎ ያጣው ለምንድነው?

ራሔል ስለ ተቀመጠችባቸውና የወር አበባዋ ወቅት ላይ በመሆኗ ለመነሣት አለመቻሏን ስለ ተናገረች ላባ የቤተ ሰቡን አማልክት ለማግኘት አልቻለም

ላባ የቤተ ሰቡን አማልክት በያዕቆብ ንብረት ውስጥ ፈልጎ ያጣው ለምንድነው?

ራሔል ስለ ተቀመጠችባቸውና የወር አበባዋ ወቅት ላይ በመሆኗ ለመነሣት አለመቻሏን ስለ ተናገረች ላባ የቤተ ሰቡን አማልክት ለማግኘት አልቻለም

Genesis 31:41

ያዕቆብ ላባን ያገለገለው ለምን ያህል ጊዜ ነበር? ላባስ የእርሱን ደሞዝ የለወጠው ስንት ጊዜ ነበር?

ያዕቆብ ለሃያ አመታት ላባን አገለገለ፣ ላባም ደሞዙን አሥር ጊዜ ለዋውጦት ነበር

Genesis 31:43

ላባ የያዕቆብ ንብረት የእርሱ እንደ ሆነ አሁንም እንደሚያስብ ያሳየው እንዴት ነበር?

ላባ የሚያየው የያዕቆብ ንብረት ሁሉ የእርሱ መሆኑን ተናገረ

Genesis 31:45

ያዕቆብና ላባ ቃል ኪዳን በተገባቡበት ስፍራ ላይ ምን ምልክት አደረገ?

ያዕቆብና ላባ ቃል ኪዳን በተገባቡበት ስፍራ ላይ የድንጋይ ሐውልት በማቆም ምልክት አደረጉ

በያዕቆብና በላባ መካከል የተደረገው ቃል ኪዳን እንዲጠበቅ ምስክር ሆኖ የተጠራው ማን ነበር?

በያዕቆብና በላባ መካከል የተደረገው ቃል ኪዳን እንዲጠበቅ ምስክር ሆኖ የተጠራው እግዚአብሔር ነበር?

Genesis 31:48

በያዕቆብና በላባ መካከል የተደረገው ቃል ኪዳን እንዲጠበቅ ምስክር ሆኖ የተጠራው ማን ነበር?

በያዕቆብና በላባ መካከል የተደረገው ቃል ኪዳን እንዲጠበቅ ምስክር ሆኖ የተጠራው እግዚአብሔር ነበር

Genesis 31:51

ክምሩና ሐውልቱ የሚወክሉት ምንን ነበር?

ላባም ሆነ ያዕቆብ ክምሩን ወይም ሐውልቱን በማለፍ አንዱ ሌላውን እንዳይጎዳ ለገቡት ቃል ኪዳን ምስክር ነበሩ

ያዕቆብና ላባ የገቡት ቃል ኪዳን ምን ነበር?

ያዕቆብና ላባ እርስ በእርሳቸው የተስማሙት የድንጋይ ክምሩን በማለፍ አንዱ ሌላውን እንዳይጎዳ ነበር

ክምሩና ሐውልቱ የሚወክሉት ምንን ነበር?

ላባም ሆነ ያዕቆብ ክምሩን ወይም ሐውልቱን በማለፍ አንዱ ሌላውን እንዳይጎዳ ለገቡት ቃል ኪዳን ምስክር ነበሩ

ያዕቆብ በቃል ኪዳኑ መስማማቱን ለማሳየት ምን አደረገ?

ያዕቆብ በቃል ኪዳኑ መስማማቱን ለማሳየት አባቱ ይስሐቅ በሚፈራው በእግዚአብሔር ማለ

Genesis 31:54

በማግስቱ ላባ ምን አደረገ?

ላባ ተነሣ፣ ሴት ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን ሳማቸውና ባረካቸው፣ ወደ ቤቱም ተመለሰ