Genesis 30

Genesis 30:1

እንደ ያዕቆብ አባባል ራሔል ልጅ ያልኖራት ለምንድነው?

እንደ ያዕቆብ አባባል ራሔል ልጅ ሳይኖራት እንድትቆይ ያደረጋት እግዚአብሔር ነበር

Genesis 30:3

ራሔል ልጆች እንዲኖሯት ምን አደረገች?

ራሔል በእርሷ ምትክ ልጆች እንዲኖሯት አገልጋይዋን ባላን ለያዕቆብ ሰጠችው

Genesis 30:7

ራሔል እህቷን ልያን እንዳሸነፈቻት የተናገረችው ለምንድነው?

አገልጋይዋ ባላ ለያዕቆብ ሁለት ወንድ ልጆችን ስለ ወለደችለት ራሔል እንዳሸነፈች ተናገረች

ራሔል እህቷን ልያን እንዳሸነፈቻት የተናገረችው ለምንድነው?

አገልጋይዋ ባላ ለያዕቆብ ሁለት ወንድ ልጆችን ስለ ወለደችለት ራሔል እንዳሸነፈች ተናገረች

Genesis 30:9

ልያ ልጆች መውለድ ማቆሟን ባየች ጊዜ ምን አደረገች?

ልያ በእርሷ አማካይነት ልጆች እንዲኖሩዋት አገልጋይዋን ዘለፋን ለያዕቆብ ሰጠችው

ልያ፣ "ጉድ" ያለችው ለምን ነበር?

ልያ "ጉድ" ያለችው አገልጋይዋ ዘለፋ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ስለ ወለደች ነበር

ልያ፣ "ጉድ" ያለችው ለምን ነበር?

ልያ "ጉድ" ያለችው አገልጋይዋ ዘለፋ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ስለ ወለደች ነበር

Genesis 30:14

በልጇ እንኮይ ምክንያት ራሔል ለልያ ያቀረበችላት አሳብ ምን ነበር?

በሮቤል እንኮይ ምክንያት በልዋጩ ልያ ከያዕቆብ ጋር እንድትተኛ ራሔል አሳብ አቀረበች

Genesis 30:19

በልጇ እንኮይ ምክንያት ራሔል ለልያ ያቀረበችላት አሳብ ምን ነበር?

በሮቤል እንኮይ ምክንያት በልዋጩ ልያ ከያዕቆብ ጋር እንድትተኛ ራሔል አሳብ አቀረበች

Genesis 30:22

ልያ ለያዕቆብ የወለደችው ስንት ወንዶች ልጆችን ነበር?

ልያ ስድስት ወንዶች ልጆችን ለያዕቆብ ወለደችለት

ራሔል ስድቧ መወገዱን እንድትናገር ያስደረጋት ምን ነበር?

ራሔል ለያዕቆብ ወንድ ልጅ በወለደችለት ጊዜ ስድቧ መወገዱን ተናገረች

Genesis 30:25

ዮሴፍ ከተወለደ በኋላ ያዕቆብ ለላባ ያቀረበለት ጥያቄ ምን ነበር?

ያዕቆብ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ገዛ አገሩና ቤቱ ለመመለስ ላባ እንዲፈቅድለት ጠየቀው

ያዕቆብ እንዲሄድ ላባ ያልፈለገው ለምንድነው?

እግዚአብሔር አምላክ በያዕቆብ ምክንያት ላባን ባርኮት ስለ ነበረ ነው

Genesis 30:31

ያዕቆብ ለላባ በመሥራቱ የተቀበለው ደሞዝ ምን ነበር?

ያዕቆብ ከሚጠብቀው መንጋ ዥንጉርጉር፣ ነቁጣ ያለባቸውንና ጥቁር በጎችን፣ ከፍየሎቹም ዥንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን ወሰደ

Genesis 30:35

የያዕቆብን ደሞዝ በሚመለከት ላባ ያዕቆብን ያታለለው እንዴት ነበር?

ላባ፣ መንጋውን እንዲጠብቅለት ለያዕቆብ ከመስጠቱ በፊት በመጀመሪያ የያዕቆብ ድርሻ መሆን የሚገባቸውን እንስሶች ለይቶ አስቀራቸው

Genesis 30:37

የያዕቆብን ደሞዝ በሚመለከት ላባ ያዕቆብን ያታለለው እንዴት ነበር?

ላባ፣ መንጋውን እንዲጠብቅለት ለያዕቆብ ከመስጠቱ በፊት በመጀመሪያ የያዕቆብ ድርሻ መሆን የሚገባቸውን እንስሶች ለይቶ አስቀራቸው

ያዕቆብ፣ ሽመልመሌ አድርጎ የላጣቸው በትሮች ምን ዓይነት ነበሩ?

ያዕቆብ ልብን፣ ለውዝ፣ ኤርሞን የሚባሉ እንጨቶችን ቅርንጫፍ በመላጥ ሽመልመሌ መልክ እንዲኖራቸው አደረገ

ያዕቆብ በሽመልመሌዎቹ በትሮች ምን አደረገ?

ያዕቆብ መንጋው ውሃ ለመጠጣት በሚመጡበት ጊዜ በፊት ለፊታቸው በውሃ ማጠጫ ገንዳው ውስጥ ሽመልመሌዎቹን በትሮች አስቀመጣቸው

Genesis 30:39

መንጋዎቹ በበትሮቹ ፊት በጸነሱ ጊዜ ምን ሆነ?

መንጋዎቹ በበትሮቹ ፊት በጸነሱ ጊዜ ሽመልመሌ መሳይ፣ ዥንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን ወለዱ

Genesis 30:41

ያዕቆብ እንስሶቹ እንዲህ ባለ መንገድ እንዲወልዱ የማድረጉ ውጤት ምን ነበር?

በውጤቱም የላባ መንጋዎች ሲደክሙ የያዕቆብ በረቱ