Genesis 29

Genesis 29:4

ያዕቆብ ያነጋገራቸው ሰዎች ከየት ነበሩ?

ሰዎቹ ከካራን ነበሩ

ደግሞም፣ ከበጎች መንጋ ጋር ወደ ውሃው ጉድጓድ የመጣው ማን ነበር?

የላባ ልጅ ራሔል ደግሞ ከበጎች መንጋ ጋር ወደ ውሃው ጉድጓድ መጣች

Genesis 29:9

ለላባ በጎች ያዕቆብ ምን አደረገ?

ያዕቆብ ከጉድጓዱ አፍ ድንጋዩን ገለበጠና በጎቹን አጠጣ

Genesis 29:11

ያዕቆብ ለራሔል ምን ነገራት? እርሷስ ከዚያ በኋላ ምን አደረገች?

ያዕቆብ የአባቷ ዘመድ መሆኑን ለራሔል ነገራት፣ ራሔልም እየሮጠች ሄደችና ለአባቷ ነገረችው

Genesis 29:13

ላባ የያዕቆብን መምጣት በሰማ ጊዜ ምን አደረገ?

ላባ ያዕቆብን ለመገናኘት ሮጠ፣ አቀፈውና ሳመው፣ ወደ ቤቱም አመጣው

Genesis 29:15

ሁለቱን የላባ ሴቶች ልጆች ግለጻቸው፡፡

ልያ ታላቂቱ ልጅ ስትሆን ዓይነ ልም ነበረች፣ ራሔል ግን ታናሽ፣ መልከ መልካምና ውብ ነበረች

ሁለቱን የላባ ሴቶች ልጆች ግለጻቸው፡፡

ልያ ታላቂቱ ልጅ ስትሆን ዓይነ ልም ነበረች፣ ራሔል ግን ታናሽ፣ መልከ መልካምና ውብ ነበረች

Genesis 29:19

የያዕቆብን የሥራ ድርሻ በሚመለከት ላባና ያዕቆብ ምን ስምምነት አደረጉ?

ያዕቆብ ስለ ራሔል ለሰባት አመታት ላባን እንዲያገለግለው ተስማሙ

ለያዕቆብ ሰባቱ አመት እንደ ጥቂት ቀናት ብቻ የሆኑለት ለምን ነበር?

ያዕቆብ ራሔልን ይወዳት ስለ ነበር ሰባቱ አመት እንደ ጥቂት ቀናት ብቻ ሆኑለት

Genesis 29:23

ላባ ያዕቆብን ያታለለው እንዴት ነበር?

በሠርጉ ምሽት ላባ ራሔልን ሳይሆን ልያን ለያዕቆብ ሰጠው

ላባ ያዕቆብን ያታለለው እንዴት ነበር?

በሠርጉ ምሽት ላባ ራሔልን ሳይሆን ልያን ለያዕቆብ ሰጠው

ላባ፣ ልያን እንድታገለግላት ማንን ሰጣት?

ላባ ልጁን ልያን እንድታገለግላት ሴት ባሪያውን ዘለፋን ሰጣት

ላባ ያዕቆብን ያታለለው እንዴት ነበር?

በሠርጉ ምሽት ላባ ራሔልን ሳይሆን ልያን ለያዕቆብ ሰጠው

Genesis 29:26

ላባ ያዕቆብን ለምን እንዳታለለው ተናገረ?

ታላቂቱ እያለች ታናሽቱን መዳር ባህላቸው ያለመሆኑን ላባ ተናገረ

የያዕቆብን የሥራ ድርሻ በሚመለከት ላባና ያዕቆብ ምን ስምምነት አደረጉ?

ያዕቆብ ስለ ራሔል ለሰባት አመታት ላባን እንዲያገለግለው ተስማሙ

Genesis 29:28

ታገለግላት ዘንድ ላባ ለራሔል የሰጣት ማንን ነበር?

ላባ ልጁን ራሔልን ታገለግላት ዘንድ ባላን ሰጣት

Genesis 29:31

ያዕቆብ ልያን እንዳልወደዳት ባየ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ምን አደረገ?

እግዚአብሔር አምላክ ልያን እንድትፀንስ አደረጋት፣ ራሔል ግን ልጅ አልነበራትም

ልያ ወንዶች ልጆችን ለያዕቆብ ከወለደችለት ምን ይሆናል ብላ ተስፋ አደረገች?

ልያ ወንዶች ልጆች ከወለደችለት ያዕቆብ እንደሚወዳት ተስፋ አደረገች

Genesis 29:33

የልያ የመጀመሪያው ወንድ ልጅ ስም ማን ነበር?

የልያ የመጀመሪያው ወንድ ልጅ ስሙ ሮቤል ነበር

Genesis 29:35

ልያ ይሁዳን ከወለደች በኋላ ምን አለች?

ልያ ይሁዳን ከወለደች በኋላ፣ "በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክን አመሰግናለሁ" አለች