Genesis 32

Genesis 32:3

ያዕቆብ ወደ ከነዓን በመጓዝ ላይ እያለ መልዕክት የላከው ወደ ማን ነበር?

ያዕቆብ ወደ ከነዓን በመጓዝ ላይ እያለ መልዕክት የላከው ወደ ወንድሙ ወደ ኤሳው ነበር

ያዕቆብ ይህንን መልዕክት የላከበት ዓላማ ምን ነበር?

ያዕቆብ በኤሳው ፊት ሞገስን ለማግኘት ፈልጎ ነበር

Genesis 32:6

ኤሳው ከአራት መቶ ሰዎች ጋር እየመጣ እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ ያዕቆብ ምን ተሰማው? ምንስ አደረገ?

ያዕቆብ ፈርቶ ነበር፣ በመሆኑም ኤሳው አንደኛውን ቡድን ቢያጠቃ ሌላኛው እንዲያመልጥ የእርሱን ሰዎች በሁለት ቡድኖች ከፈላቸው

Genesis 32:9

ኤሳው ከአራት መቶ ሰዎች ጋር እየመጣ እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ ያዕቆብ ምን ተሰማው? ምንስ አደረገ?

ያዕቆብ ፈርቶ ነበር፣ በመሆኑም ኤሳው አንደኛውን ቡድን ቢያጠቃ ሌላኛው እንዲያመልጥ የእርሱን ሰዎች በሁለት ቡድኖች ከፈላቸው

Genesis 32:11

ያዕቆብ ወደ እግዚአብሔር አምላክ ያቀረበው ልመና ምን ነበር?

ያዕቆብ፣ እግዚአብሔር አምላክ ከኤሳው እጅ እንዲያድነው ለመነ

ያዕቆብ እግዚአብሔር አምላክን ያሳሰበው የትኛውን ተስፋ እንዲያስብ ነበር?

ያዕቆብ እግዚአብሔር አምላክን ያሳሰበው፣ ያዕቆብን ለማበልጸግና ዘሩን እንደ ባህር አሸዋ ለማብዛት የሰጠውን ተስፋ ነበር

Genesis 32:19

ያዕቆብ ለወንድሙ ኤሳው ስጦታዎችን በመላክ ምን ለማሳካት እንደሚችል አስቦ ነበር?

ያዕቆብ በሚልክለት ስጦታ ምናልባት የኤሳውን ቁጣ ማብረድ እንደሚችልና ባየው ጊዜም ኤሳው እንደሚቀበለው አስቦ ነበር

Genesis 32:22

በዚያች ሌሊት ያዕቆብ ለብቻው የቀረው እንዴት ነበር?

ያዕቆብ ሚስቶቹን፣ ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቹን ወስዶ የያቦቅን ወንዝ አሻገራቸው

Genesis 32:24

በዚያ ምሽት ጎሕ እስኪቀድ ድረስ ያዕቆብ ያደረገው ምን ነበር?

ያዕቆብ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ ከአንድ ሰው ጋር ታገለ

ሰውየው ያዕቆብን ሊያሸንፈው ባልቻለ ጊዜ ምን አደረገ?

ሰውየው የያዕቆብን ሹሉዳ መታውና ውልቃት እንዲደርስበት አደረገው

ያዕቆብ፣ ሰውየው እንዲሄድ ከመልቀቁ በፊት ምን ጠየቀ?

ሰውየው እንዲባርከው ያዕቆብ ጠየቀ

Genesis 32:27

ሰውየው የተናገረው፣ ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ማን ተብሎ እንዲጠራ ነበር?

ሰውየው፣ አሁን የያዕቆብ ስሙ እስራኤል መሆን አለበት አለ

Genesis 32:29

ያዕቆብ፣ በዚያ ምሽት ፊት ለፊት አየሁት ያለው ማንን ነበር?

ያዕቆብ፣ በዚያ ምሽት እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳየው ተናገረ