Genesis 22

Genesis 22:1

እግዚአብሔር አብርሃምን የፈተነው በምንድነው?

እግዚአብሔር፣ ወደ ሞሪያም ምድር እንዲሄድና ይስሐቅን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ ለአብርሃም ነገረው

እግዚአብሔር አብርሃምን የፈተነው በምንድነው??

እግዚአብሔር፣ ወደ ሞሪያም ምድር እንዲሄድና ይስሐቅን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ ለአብርሃም ነገረው

ለእግዚአብሔር ትዕዛዝ የአብርሃም ምላሽ ምን ነበር?

አብርሃም በማለዳ ተነሥቶ እግዚአብሔር ወደ ተናገረው ቦታ ሄደ

Genesis 22:4

አብርሃም ለሁለቱ ሎሌዎቹ የነገራቸው እርሱና ይስሐቅ ምን እንደሚያደርጉ ነበር?

አብርሃም ለሁለቱ ሎሌዎቹ የነገራቸው እርሱና ይስሐቅ ሰግደው እንደሚመለሱ ነገራቸው

Genesis 22:7

አብረው በመጓዝ ላይ እያሉ ይስሐቅ አብርሃምን የጠየቀው ምን ነበር?

ይስሐቅ አብርሃምን፣ "የመሥዋዕቱ በግ የት አለ?" ብሎ ጠየቀው

አብርሃም የይስሐቅን ጥያቄ የመለሰው እንዴት ነበር?

አብርሃም፣ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ራሱ ያዘጋጃል አለ

ወደ ቦታው በደረሱ ጊዜ አብርሃም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀው ምን ነበር? ያዘጋጀውስ እንዴት አድርጎ ነው?

አብርሃም ይስሐቅን አስሮ በመሠዊያው ላይ በማጋደም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው

Genesis 22:11

አብርሃም በእጁ ቢላዋ ባነሣ ጊዜ የእግዚአብሔር አምላክ መልአክ ለአብርሃም የነገረው ምንድነው?

የእግዚአብሔር አምላክ መልአክ አብርሃም በይስሐቅ ላይ አንዳች እንዳያደርግ ነገረው

መልአኩ፣ አሁን ስለ አብርሃም ምን እንዳወቀ ተናገረ?

መልአኩ፣ አሁን አብርሃም እግዚአብሔርን እንደሚፈራ ማወቁን ተናገረ

Genesis 22:13

ከዚያ፣ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀለት እንዴት ነበር?

ከአብርሃም ጀርባ በቁጥቋጦ የተያዘ በግ ነበረ፣ አብርሃምም ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት አደረገው

አብርሃም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀረበበትን ቦታ ምን ብሎ ጠራው?

አብርሃም ቦታውን፣ "እግዚአብሔር አምላክ ያዘጋጃል" ብሎ ጠራው

Genesis 22:15

የእግዚአብሔር አምላክ መልአክ አብርሃምን ለመባረክ ምን ምክንያት አቀረበ?

የእግዚአብሔር አምላክ መልአክ፣ አብርሃም አንድ ልጁን ስላልከለከለ እንደሚባርከው ተናገረ

የእግዚአብሔር አምላክ መልአክ አብርሃምን ለመባረክ ምን ምክንያት አቀረበ?

የእግዚአብሔር አምላክ መልአክ፣ አብርሃም አንድ ልጁን ስላልከለከለ እንደሚባርከው ተናገረ

Genesis 22:18

የምድር ሕዝቦች ሁሉ የሚባረኩት በማንና ለምንድነው?

የምድር ሕዝቦች ሁሉ በአብርሃም ዘር ይባረካሉ፣ ምክንያቱም፣ አብርሃም የእግዚአብሔር አምላክ መልአክን ድምፅ ታዟልና