Genesis 21

Genesis 21:1

እግዚአብሔር አምላክ ለሣራ ምን አደረገላት?

እግዚአብሔር አምላክ ሣራን ጎበኛት፣ ተስፋ በተሰጠበት ጊዜም ለአብርሃም ወንድ ልጅን ወለደችለት

Genesis 21:5

ይስሐቅ ስምንት ቀን በሆነው ጊዜ አብርሃም ምን አደረገ?

ይስሐቅ ስምንት ቀን በሆነው ጊዜ አብርሃም ገረዘው

ሣራ እግዚአብሔር ምን እንድታደርግ እንዳደረጋት ተናገረች?

እግዚአብሔር እንድትስቅ እንዳደረጋት ሣራ ተናገረች

Genesis 21:8

ይስሐቅ ጡት መጥባት ባቆመ ጊዜ ሣራ ያየችው ምን ነበር?

የአጋር ልጅ በይስሐቅ ሲያሾፍበት ሣራ አየችው

Genesis 21:10

ሣራ፣ አብርሃም በአጋርና በልጇላይ ምን እንዲያደርግ ነገረችው? ለምን?

የአጋር ልጅ ከይስሐቅ ጋር ስለማይወርስ አጋርንና ልጇን እንዲሰዳቸው ሣራ ለአብርሃም ነገረችው

ለሣራ ፍላጎት የአብርሃም ምላሽ ምን ነበር?

አብርሃም በሣራ ፍላጎት አዘነ

Genesis 21:12

እግዚአብሔር፣ አብርሃም ምን እንዲያደርግ ነገረው?

አብርሃም ሣራን እንዲሰማት እግዚአብሔር ነገረው

Genesis 21:14

አብርሃም ከቤት ካስወጣቸው በኋላ አጋርና ልጇ ወዴት ሄዱ?

አጋርና ልጇ ወደ ምድረበዳ ሄዱ

Genesis 21:17

እግዚአብሔር ለአጋር የነገራት ለልጇ ምን እንደሚያደርግለት ነበር?

እግዚአብሔር የአጋርን ልጅ ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገው ተናገረ

Genesis 21:19

አጋርና ልጇ በሕይወት መቆየት የቻሉት እንዴት ነበር?

እግዚአብሔር የአጋርን ዓይኖች ከፈተና የውሃ ጉድጓድ አየች

የአጋር ልጅ ባደገ ጊዜ ምን ሆነ?

የአጋር ልጅ ቀስተኛ ሆነ፣ እናቱም ከግብፅ ሚስት አመጣችለት

Genesis 21:22

የአጋር ልጅ ባደገ ጊዜ ምን ሆነ?

የአጋር ልጅ ቀስተኛ ሆነ፣ እናቱም ከግብፅ ሚስት አመጣችለት

አቢሜሌክ የፈለገው አብርሃም ምን ለማድረግ እንዲምልለት ነበር?

አቢሜሌክ፣ አብርሃም በእርሱ ወይም በልጆቹ ወይም በዘሮቹ ክፉ ላለማድረግ እንዲምልለት ፈለገ፡፡ አቢሜሌክ ለአብርሃም ያሳየውን ቸርነት አብርሃምም ለእርሱ እንዲያደርግለት ጠየቀው

Genesis 21:25

አብርሃም ለአቢሜሌክ ያቀረበው ቅሬታ ምን ነበር?

አብርሃም የአቢሜሌክ ባሪያዎች ስለ ወሰዱበት የውሃ ጉድጓድ ቅሬታውን ለአቢሜሌክ አቀረበ

Genesis 21:28

አብርሃም ሰባት ቄቦች በጎችን ለአቢሜሌክ የላከለት ለምንድነው?

የተከራከሩበትን ጉድጓድ የቆፈረው እርሱ ለመሆኑ ምስክር እንዲሆኑ አብርሃም ሰባት ቄቦች በጎችን ለአቢሜሌክ ላከ

አብርሃም ሰባት ቄቦች በጎችን ለአቢሜሌክ የላከለት ለምንድነው?

የተከራከሩበትን ጉድጓድ የቆፈረው እርሱ ለመሆኑ ምስክር እንዲሆኑ አብርሃም ሰባት ቄቦች በጎችን ለአቢሜሌክ ላከ

አብርሃም ሰባት ቄቦች በጎችን ለአቢሜሌክ የላከለት ለምንድነው?

የተከራከሩበትን ጉድጓድ የቆፈረው እርሱ ለመሆኑ ምስክር እንዲሆኑ አብርሃም ሰባት ቄቦች በጎችን ለአቢሜሌክ ላከ

Genesis 21:31

አቢሜሌክ የተመለሰው ወደ የትኛው ምድር ነበር?

አቢሜሌክ የተመለሰው ወደ ፍልስኤማውያን ምድር ነበር

Genesis 21:33

አብርሃም በቤርሳቤህ ባለው የተምር ዛፍ አጠገብ ምን አደረገ?

አብርሃም የዘላለሙን እግዚአብሔር አምላክ አመለከ

አብርሃም ለብዙ ቀናት የኖረው የት ነበር?

አብርሃም በፍልስጥኤማውያን ምድር ለብዙ ቀናት ኖረ