Genesis 20

Genesis 20:1

አብርሃም በጌራራ በሚኖርበት ጊዜ ስለ ሣራ ምን ተናገረ?

አብርሃም ሣራ እህቱ እንደሆነች ተናገረ

አብርሃም በጌራራ በሚኖርበት ጊዜ ስለ ሣራ ምን ተናገረ?

አብርሃም ሣራ እህቱ እንደሆነች ተናገረ

Genesis 20:4

ሣራን ከወሰዳት በኋላ እግዚአብሔር አቢሜሌክን ምን አለው?

እግዚአብሔር በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጥቶ የሰውየውን ሚስት በመውሰዱ ምውት መሆኑን ነገረው

Genesis 20:6

አቢሜሌክ፣ አብርሃምና ሣራ ምን እንዳሉት ነበር ለእግዚአብሔር የተናገረው?

አብርሃም፣ ሣራ እህቱ መሆኗን እንደ ነገረው፣ ሣራም አብርሃም ወንድሟ መሆኑን እንደ ነገረችው አቢሜሌክ ለእግዚአብሔር ተናገረ

እግዚአብሔር ለአቢሜሌክ የነገረው ምን እንዲያደርግ ነበር? ባያደርገው ምን እንደሚደርስበት ነገረው?

አቢሜሌክ ሣራን ለአብርሃም እንዲመልስለት ነገረው፤ ያለበለዚያ እርሱና ሕዝቡ ሁሉ ይሞታሉ

Genesis 20:8

እግዚአብሔር ለአቢሜሌክ የነገረውን በሰሙ ጊዜ የአቢሜሌክ ሰዎች ምን አደረጉ?

እግዚአብሔር ለአቢሜሌክ የነገረውን በሰሙ ጊዜ የአቢሜሌክ ሰዎች እጅግ ፈሩ

Genesis 20:10

አብርሃም፣ ሣራ እህቱ እንደ ሆነች ለአቢሜሌክ የነገረው ለምንድነው?

አቢሜሌክ በሣራ ምክንያት እንዳይገድለው ስለ ፈራ መሆኑን አብርሃም ተናገረ

Genesis 20:13

በእርግጥም ሣራ የአብርሃም እህት የሆነችው በየትኛው መንገድ ነበር?

ሣራ የእናቱ ሳትሆን የአብርሃም የአባቱ ልጅ ነበረች

Genesis 20:15

አቢሜሌክ ለአብርሃም የሰጠው ምን ዓይነት እንስሶችንና ሰዎችን ነበር?

አቢሜሌክ ለአብርሃም በጎችንና በሬዎችን፣ ወንዶችንና ሴቶች ባሮችን ሰጠው

አቢሜሌክ ለወንድሟ አንድ ሺህ ጥሬ ብር ስለ መስጠቱ ለሣራ ያቀረበላት ምክንያት ምን ነበር?

ለወንድሟ አንድ ሺህ ጥሬ ብር የሰጠው ከእርስዋ ጋር በነበሩት ሁሉና በሌሎችም ሰዎች ፊት ለጉዳቷ ካሳ እንዲሆን መሆኑን አቢሜሌክ ለሣራ ነገራት

Genesis 20:17

አብርሃም ለአቢሜሌክና ለሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ምን ነገር ሆነ?

አቢሜሌክ፣ ሚስቱና ሴት ባሪያዎቹ መውለድ እንዲችሉ አግዚአብሔር ፈወሳቸው