ምዕራፍ 5

1 ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው ። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፥ እንደገና በባርነት ቀንበር አትጠመዱ። 2 እኔ ጳውሎስ የምለውን ተመልከቱ ብትገረዙ ክርስቶስ በምንም ዓይነት መልኩ አይጠቅማችሁም። 3 የተገረዘ ሁሉ ህግን ሁሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት ብዬ እንደገና እመሰክራለሁ። 4 በህግ ልትጸድቁ የምትደክሙ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆናችኋል፤ከጸጋም ርቃችኋል። 5 ምክንያቱም እኛ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የጽድቅን ዋስትና ስለምንጠብቅ ነው። 6 በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍቅር የሆነ እምነት እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም ትርጉም የለውም። 7 በጥሩ ሁኔታ ትሮጡ ነበር። ታዲያ ለእውነት ከመታዘዝ ያስቆማችሁ ማነው? 8 ይህን እንድታደርጉ የሚያደርግ ጉትጎታ ከጠራችሁ የመጣ አይደለም። 9 ትንሽ እርሾ ሊጡን በሙሉ እንዲቦካ ያደርጋል። 10 በሌላ መልኩ እንደማታስቡ በጌታ እተማመንባችኋለሁ። ግራ የሚያጋባችሁ ማንም ይሁን ማን ፍርዱን ይቀበላል። 11 ወንድሞች ሆይ እስከአሁን ተገረዙ እያልኩ የምሰብክ ቢሆን ለምን እሰደድ ነበር? እንግዲያውስ የመስቀሉ እንቅፋት ይደመሰሳል። 12 የሚያስቷችሁ እራሳቸው ሄደው በተሰለቡ ብዬ እመኛለሁ። 13 ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ። 14 ምክንያቱም ህግ ሁሉ «ባልንጀራህን እንደራስህ ልትወድ ይገባል» 15 በሚለው ትዕዛዝ የተጠቀለለ ነው። 16 በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋን ክፉ ምኞት አትፈጽሙ እላችኋለሁ። 17 ምክንያቱም ሥጋ ከመንፈስ ተቃራኒ መንፈስም ከሥጋ ተቃራኒ ነገር ይመኛሉና ነው። 18 እነዚህ እርስ በእርሳቸው ስለሚቀዋወሙ በውጤቱ እናንተ የምትፈልጉትን ለማድረግ አትችሉም። 19 እንግዲህ የሥጋ ስራዎች የተገለጡ ናቸው። እነዚህም አስቀድሜ እንዳስጠነቀኩዋችሁ 20 ዝሙት፣እርኩሰት፣ክፉ ምኞት፣ጣዖትን ማምለክ፣ምዋርት፣ጥል፣ክርክር፣ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣አድመኛነት፣መለያየት፣ 21 መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ስካር፥ ዘፋኝነትና የመሳሰሉት ናቸው፥ ፥አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ እነዚህን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። 22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥ 23 የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም። 24 የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ስሜቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል። 25 በመንፈስ የምንኖር ከሆነ በመንፈስ እንመላለስ። 26 አንታበይ፣ እርስ በእርሳችን ለክፉ አንነሳሳ፣ አንቀናና።