ምዕራፍ 4

1 ያን የምለው ህጻን ሳለ ምንም እንኳ ሁሉም የእርሱ ቢሆንም ወራሹ ከባሪያ አይለይም። 2 ነገር ግን አባቱ የወሰነልት ቀን እስኪደርስለት ድረስ በተንከባካቢዎቹና በሞግዚቶቹ ስር ይቆያል። 3 እኛም ልጆች ሳለን በዚህ ዓለም ዋና ትምህርቶች እስራት ሥር ነበርን። 4 ነገር ግን በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር በህግ ሥር ያሉትን 5 ነጻ እንዲያወጣና የልጅነትን መብት እንዲኖረን ከሴት የተወለደውንና በህግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ። 6 ልጆች ስለሆናችሁ «አባ አባት» እያለ የሚጣራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ። 7 በዚህም ምክንያት ከእንግዲህ ልጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም፥ ልጆች ከሆናችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ። 8 ነገር ግን እግዘአብሔርን በማታውቁበት በቀድሞው ዘመን በባህሪያቸው ፈጽሞ አማልክት ላልሆኑት ተገዝታችሁ ኖራችሁ። 9 አሁን ግን እግዚአብሔርን አውቃችኋል ይልቁኑም በእግዚአብሔር ታውቃችኋል፥ ታዲያ እንዴት ወደ ደካማና ዋጋ ወደሌለው የዚህ ዓለም ዋና ትምህርት ተመለሳችሁ።እንደገና ባሮች መሆን ትፈልጋላችሁ? 10 ልዩ ቀናትን፥አዳዲስ ጨረቃዎችን፥ ወራትና ዓመታትን ታመልካላችሁ። 11 ስለ እናንተ የደከምኩት ድካም ከንቱ ሆኖብኝ እንዳይሆን ብዬ እፈራለሁ። 12 ወንድሞች ሆይ ልክ እኔ ለእናንተ እንደምሆነው እናንተም ለእኔ እንደዚያው እንድትሆኑ እለምናችኋለሁ። 13 ምንም ክፉ አላደርጋችሁብኝም ነገር ግን ወንጌልን በመጀመሪያ በሰብኩላችሁ ጊዜ የሥጋ ህመም አሞኝ እንደነበረ ታውቃላችሁ። 14 በሥጋዬ ላይ የነበረው ለእናንተ ከባድ ፈተና ቢሆንም አልተጸየፋችሁኝም አልጣላችሁኝምም፥ ይልቁኑ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ወይም ክርስቶስን በተቀበላችሁብት አቀባበል ተቀበላችሁኝ። 15 አሁን ደስታችሁ በምንድነው? ዓይናችሁን እንኳ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ፈቃደኛ እንደነበራችሁ እኔ ራሴ ምስክር ነኝ። 16 ታዲያ እውነትን ስለነገርኳችሁ የእናንተ ጠላት ሆንኩ ማለት ነው? 17 አጥበቀው ይፈልጓችኋል ነገር ግን ለመልካም አይደለም። እነርሱን እንድትከተሉ ከእኔ ሊለዩዋችሁ ይፈልጋሉ። 18 እኔ ከእናንተ ጋር ስሆን ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ለመልካም ነገር መትጋት ተገቢ ነው። 19 ጨቅላ ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ ስለእናንተ ምጥ ይዞኛል! 20 የእናንተ ነገር ግራ ስለገባኝ በመካከላችሁ ተገኝቼ በቁጣ ልናገራችሁ እመኛለሁ። 21 እስኪ እናንተ በህግ ሥር ለመሆን የምትፈልጉ ንገሩኝ ህጉ ምን እንደሚል አልሰማችሁምን? 22 አብርሃም አንድ ባሪያ ከነበረች ሴት አንድ ደግሞ ነጻ ከነበረች ሴት የተወለዱ ሁለት ልጆች እንደነበሩት ተጽፏል። 23 ነገር ግን ከባሪያይቱ የተወለደው በሥጋ ብቻ የተወለደ ነው፥ ከነጻይቱ የተወለደው ግን በተስፋ የተወለደ ነው። 24 እነዚህ ነገሮች እንደ ምሳሌ ሊገለጹ ይችላሉ።እነኚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ቃል ኪዳኖች ናቸው፥ አንደኛዋ በሲና ተራራ የተሰጠውንና ባርነትን የወለደውን ታመለክታለች፥ እርሷም አጋር ናት። 25 እንግዲህ አጋር በአረቢያ ምድር የሚገኘው የሲና ተራራ ስትሆን ከልጆቿ ጋር በባርነት የምትኖረውን የአሁኗን ኢየሩሳሌምን ትወክላለች። 26 ነገር ግን እናታችን የሆነችው ላይኛይቱ ጽዮን ነጻ ነች። 27 ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል «አንቺ ያልወለድሽና መካን የሆንሽ ሴት ሀሴት አድርጊ፥አንቺ መውለድን ያልተለማምድሽ ውጪና በደስታ ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የመካኗ ልጆች በዝተዋልና»። 28 እንግዲህ እናንተ ወንድሞቼ እንደ ይስሀቅ የተስፋ ልጆች ናችሁ። 29 ነገር ግን እንደ ሥጋ ፈቃድ የተወለደው እንደ መንፈስ ፈቃድ የተወለደውን እንዳሳደደው አሁንም እየሆነ ያለው እንደዚያው ነው። 30 መጽሀፍ ስለዚህ ነገር ምን ይላል« የባሪያይቱ ልጅ ከነጻይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱንና ልጇን አስወጣ»። 31 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ እኛ የነጻይቱ እንጂ የባሪያይቱ ልጆች አይደለንም።