Names

ሄሮድያዳ

ሄሮድያዳ መጥምቁ ዮሐንስ ባገለገለበት ዘመን ይሁዳን እየገዛ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ (አንቲጳስ) ሚስት ነበረች።

  • መጀመሪያ ላይ ሄሮድያዳ የሄሮድስ ወንድም የፊልጶስ ሚስት ነበረች፤ ይሁን እንጂ ሕጉ ባይፈቅድም ሄሮድስን አግብታለች።
  • ከሕግ ውጪ በሆነው ጋብቻቸው መጥምቁ ዮሐንስ ሄሮድስንና ሄሮድያዳን ገሠጸ። በዚህ ምክንያት ሄሮድስ ዮሐንስን አሳሰረው በኋላም አንገቱ እንዲቆረጥ አደረገ።

ሄኖክ

ሄኖክ የሁለት የብሉይ ኪዳን ሰዎች ስም ነው።

  • የመጀመሪያው ሄኖድ ከሴት የተወለደው ነው። እርሱ የኖኅ አያት አባት ነበር።
  • ይኸኛው ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ኅብረት ነበረውል 365 ዓመት እንደ ኖረ በሕይወት እያለ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወሰደው።
  • ሌላው ሄኖክ የተባለው የቃየን ልጅ ነበር።

ሆሴዕ

ሆሴዕ ከክርስቶስ 750 ዓመት በፊት የእስራኤል ነቢይ ነበር።

  • የአገልግሎት ዘመኑ ኢየሮብዓምን፣ ዘካርያስን፣ ዖዝያንን፣ አዮአታምንና ሕዝቅያስን በመሳሰሉ የእስራኤልና የይሁዳ ነገሥታት ንጉሥነት ዘመን የዘለቀ በጣም ብዙ ዓመት ነበር።
  • ጎሜር የምትባል አመንዝራ ሴት እንዲያገባና ለእርሱ ታማኝ ባትሆን እንኳ እርስዋን መወደዱን እንዳያቋርጥ እግዚአብሔር ለሆሴዕ ተናገረ።
  • ይህ ለእርሱ ታማኝ ያልሆነውን ሕዝቡን ማለትም እስራኤልን እግዚአብሔር የመውደዱ ምሳሌ ነበር።
  • ሆሴዕ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ትንቢት ተናገር፤ ጣዖቶችን ማምለክ እንዲተዉ አስጠነቀቃቸው።

ሆሺያ (ሆሴዕ)

ሆሺያ (ሆሴዕ) በይሁዳ ነገሥታት በአካዝና በሕዝቅያስ ግዛት ዘመን ለዘጠኝ ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ነበር።

  • ሆሺያ (ሆሴዕ) ከኤፍሬም ነገድ የሆነ የነዌ ልጅ ነበር።
  • እርሱንና ሌሎች አሥራ አንድ ሰዎች ምድረ ከንዓንን እንዲሰልሉ በላከው ጊዜ ሙሴ ይሆሺያን (ሆሴዕን) ስም ኢያሱ ወደሚል ለወጠው።
  • ሙሴ ከሞተ በኋላ ምድረ ከነዓንን እንዲወርሱ የእስራኤልን ሕዝብ የመራው ኢያሱ ነበር።

ሉቃስ

ሉቃስ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ ሁለት መጻሕፍት የሉቃስ ወንጌልና የሐዋርያት ሥራ ጸሐፊ ነው።

  • ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክት ሉቃስ ሐኪም እንደ ነበር ጳውሎስ አመልክቷል። በሌሎች ሁለት መልእክቶቹም ጳውሎስ ሉቃስን ጠቅሷል።
  • ሉቃስ በሁለት ሐዋርያዊ ጉዞዎቹ ከጳውሎስ ጋር አብሮ ነበር፣ በሥራውም ረድቶታል።
  • አንዳንድ የጥንት ቤተ ክርስቲያን ጽሑፎች ሉቃስ የተወለደው በሶርያ ባለችው አንጾኪያ ከተማ እንደ ነበር ያመለክታሉ።

ሊባኖስ

ሊባኖስ ከእስራኤል በስተ ሰሜን ሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ የምትገኝ በጣም የምታምር ተራራማ ቦታ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ይህ አካባቢ ጥቅጥቅ ባሉት ደኖቹም ይታወቅ ነበር።

  • የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥሪያ የሚሆን ዝግባ እንጨት እንዲያመጡለት ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሊባኖስ ሠራተኞች ልኮ ነበር።
  • የሊባኖስ ጥንታዊ ኗሪዎች ሊንቃውያን የተሰኙት ሕዝብ ሲሆኑ በንግዱ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ የዋሉ መርከቦችን የመሥራት ችሎታ ነበራቸው።
  • የጢሮስና የሲዶና ከተሞች ሊባኖስ ውስጥ ነበር። ውድ ዋጋ ያለው ሐምራዊ ቀለም ያለ የተነከረ ጨርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በእነዚህ ከተሞች ነበር።

ላሜሕ

ላሜሕ ዘፍጥረት ውስጥ የተጠቀሱ የሁለት ሰዎች ስም ነው።

  • መጀመሪያ የተጠቀሰው ላሜሕ የቃየን ዘር ነበር። ሰው በመግደሉ ሁለቱ ሚስቶች ፊት ሲፎክር ነበር።
  • ሁለተኛው ላሜሕ ሴት የተባለው ሰው ዘር ነበር፤ የኖኅ አባትም እርሱ ነበር።

ላባን

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ላባን የያዕቆብ አጎትና አማት ነበር።

  • ያዕቆብ ከላባን ጋር በመስጴጦምያ ኖረ፤ ልጆቹን በሚስትነት እንደሚሰጠው ተዋውሎ የላባንን በጎችና ፍየሎች ሲጠብቅ ነበር።
  • የያዕቆብ ምርጫ የላባን ልጅ ራሔልን ማግባት ነበር።
  • ላባን የዕቆብን በማታለል ራሔልን ከማግባቱ በፊት ትልቋ ልጁ ልያን እንዲያገባ አደረገ።

ሌዋታን

“ሌዋታን” የሚለው ቃል በቀደሙት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተጠቀሰ በጣም ግዙፍና አሁን የማይገኝ አውሬ ነው።

  • ሌዋታን በጣም ኀይለኛና ቁጡ በዙሪያው ያለውን ውሃ፣ “እንዲፈላ” ማድረግ የሚችል ግዙፍ ፍጡር እንደ ነበር ተነግሯል። እርሱን በተመለከተ የተሰጡት ገለጻዎች ዳይኖሰርን በተመለከተ ከተሰጡት ጋር ይመሳሰላል።
  • ነቢዩ ኢሳይያስ ሌዋታንን፣ “ተወርዋሪ እባብ” የለዋል።
  • ኢዮብ ሌውታንን በተመለከተ ከነበረው ቀጥተኛ ዕውቀት ይጽፋል፤ ስለዚህም በእርሱ ዘመን ይህ አውሬ ገና ከምድር አልጠፋም ነበር ማለት ነው።

ሌዋዊ፣ ሌዊ

ሌዋዊ የሌዊ ዘር የሆነ የእስራኤል ማኅበረ ሰብ አባል ነው።

  • ቤተ መቅደሱንና ሃይማኖታዊ ሥርዐቶቹን ኀላፊነቱ የሌዋዋን ነበር።
  • ምንም እንኳ ሌዋውያን ሁሉ ካህናት ነበሩ ማለት ባይቻልም፣ እስራኤላውያን ካህናት ሁሉ ከሌዊ ነገድ የተገኙ ነበሩ።
  • ሌዋውያን ካህናት ቤተ መቅደሱ ውስጥ እግዚአብሔርን ለማገልገል ልዩ ሥራ የተለዩና የተቀደሱ ነበር።

ልስጥራ

ልስጥራ በአንዱ ሐዋርያዊ ጕዞው ጳውሎስ የጎበኛት ታናሽ እስያ ውስጥ የነበረች ከተማ ስም ነው። የምትገኘው የአሁንዋ ቱርክ ባለችበት ሊቃኦንያ አካባቢ ነበር።

  • ወንጌላዊና ቤተ ክርስቲያን መሥራች ከሆነው ከጢሞቴዎስ ጋር ጳውሎስ የተገናኘው ወደ ልስጥራ በሄደ ጊዜ ነበር።
  • ጳውሎስ አንካሳውን ሰው ከፈወሰ በኋላ በልስጥራ የነበሩ ሰዎች ጳውሎስና በርናባስን ለማምለክ ሞክረው ነበር፤ ሐዋርያቱ ግን ያንን እንዳያደርጉ አጥብቀው ተቃወሙ።

ልያ

ልያ ከያዕቆብ ሚስቶች አንኳ ነበረች። የዐሥር ወንዶች ልጆች እናት ስትሆን ዐሥሩ ልጆች ከእስራኤል ነገዶች የተወሰኑት ነበሩ።

  • የልያ አባት የይስሐቅ ሚስት የነበረችው የራሔል ወንድም ነበር።
  • ምንም እንኳ ልያ የእኅቷ የራሔልን ያህል ያዕቆብ የሚወዳት ሴት ባትሆንም፣ እግዚአብሔር ባርኳታል፤ ብዙ ልጆችም ሰጥቷታል።

ሎጥ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሎጥ የአብርሃም ወንድም ልጅ ነበር።

  • ሎጥ የሞዓባውያንና ይአሞናውያን ጥንተ አባት ነው።

ሐማት፣ ሌቦ ሐማት

ሐማት ከምድረ ከነዓን በስተ ሰሜናዊ ሶርያ ውስጥ ትገኝ የነበረች በጣም ጠቃሚ ከተማ ናት። በዚህ ዘመን የከተማዋ ስም ሐማ ይባላል።

  • “ሌቦ ሐማት” የሚለው ቃል ሐማት ከተማ አጠገብ የሚገኝ የተራራ መሻገሪያን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
  • አንዳንድ ትርጕሞች “ሌቦ ሐማት” የሚለውን፣ “ወደ ሐማት መግቢያ” ብለውታል።
  • “ሐማታውያን” የኖኅ ልጅ የካምና የልጅ ልጁ የከነዓን ዘሮች ናቸው።
  • ንጉሥ ዳዊት የሐማት ንጉሥ የቶዑን ጠላቶች ድል በማድረጉ በሁለቱ መካከል ወዳጅነት ተመሠረተ።
  • ሐማት አስፈላጊ ነገሮች የሚከማቹበት ከንጉሥ ሰሎሞን ግምጃ ቤት ከተሞች አንዷ ነበረች።
  • ንጉሥ ሴዴቅያስ በንጉሥ ናቡከደነፆር የተገደለውና ንጉሥ ኢዮአካዝ በግብፃዊው ፈርዖን የተያዘው በሐማት ምድር ነበር።

ሐራን

ሐራን የአብርሃም ታናሽ ወንድምና የሎጥ አባት ነበር።

  • ሐራን (ካራን) ከዑር ተነሥተው ወደ ከነዓትን ሲጓዙ አብራምና ቤተ ሰቡ ለአጭር ጊዜ የነበሩበት ቦታም ነበር።

ሐና

ሐና ከ6-15 ዓ፤ም ከ10 ዓመት በእየሩሳሌም የነበረ አይሁዳዊ ሊቀ ካህን ነው፤ይሁን እንጂ በኋላ ላይ ሮማውያን ከሊቀ ካህንነቱ አንስተውታል፤ያም ሆኖ በአይሁድ ዘንድ የነበርው ተደማጭነት መሪ በመሆን ቀጥሎ ነበር።

  • ሐና እየሱስ ባገለገለበት ዘመን ሕጋዊ ሊቀ ካህን የነበረው የቀያፍ አማች ነበር።
  • ሊቀ ካህናት ጡረታ ከወጡ በኋላ እንካ በዚያው ስም ይጠሩ ነበር፤አንዳንድ የካህነት ሥራዎችንም ይሠሩ ነበር፤ስለዚህም በቀያፋና በሌሎችም ሊቀ ካህናት ዘመን ሊቀ ካህን ተበሎ ተጠርቱል፤
  • በአይሁድ መሪዎች ፊት ለፍርድ በቀረበ ጊዜ እየሱስ በመጀመሪያ ለጥያቄ የመጥው ሐና ዘንድ ነበር።

ሐና

ሐና ብሉይ ኪዳኑ ውስጥ የነቢዩ ሳሙኤል እናት ናት። ከሕልቃና ሚስቶች አንዷ ነበረች።

  • ሐና ልጅ መውለድ አለመቻልዋ ከባድ ሐዘን ሆኖባት ነበር።
  • ሐና እግዚአብሔር ወንድ ልጅ አንዲሰጣት ቤተ መቅደስ ውስጥ አጥብቃ ጸለየች፣ ያ ልጅ ለእግዚአብሔር አገልግሎት እንደሚለይም ቃል ገባች።
  • እግዚአብሔር የለመነችውን ሰጣት፤ ሕፃኑ ሳሙኤል ካደገ በኋላ በካህኑ በዔሊ መሪነት ሥር ቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግል አመጣችው።
  • ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ለሐና ሌሎች ልጆችንም ሰጥቷታል።

ሐጌ

ሐጌ እስራኤል ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ የነበረ የይሁዳ ነቢይ ነበር።

  • ሐጌ ትንቢት እየተናገረ በነበረበት ዘመን ይሁዳን እየገዛ የነበረው ንጉሥ ዖዝያን ነበር።
  • ሐጌ እንደ ገና ቤተ መቅደሱን መሥራት እንዲጀምሩ አይሁድን አበረታታ።

ሔዋን

ይህ የመጀመሪያዋ ሴት ስም ነበር። የስሟ ትርጉም፣ “ሕይወት” ወይም፣ “ሕያው” ማለት ነው።

  • እግዚአብሔር ሔዋንን የፈጠራት ከአዳም ጎድን ከወሰደው አጥንት ነበር።
  • ሔዋን የተፈጠረችው የአዳም “ረዳት” እንድትሆን ነው። እግዚአብሔር በሰጠው ሥራ እርሱን ለመርዳት ከአዳም ጎን ትሆናለች።
  • ሔዋን በእባቡ (ሰይጣን)ተፈተነች፣ እንዳይበሉ እግዚአብሔር የከለከለውን ፍሬ በመብላት የመጀመሪያውን ኀጢአት ፈጸመች።

ሕዝቅኤል

ሕዝቅኤል ብዙ አይሁድ ወደባቢሎን በተወሰዱበት የምርኮ ወቅት የነበረ የእግዚአብሔር ነብይ ነው።

  • እርሱና ሌሎች ብዙ አይሁዳውያን በባቢሎን ሰራዊት ከመያዛቸው በፊት ሕዝቅኤል በይሁዳ መንግሥት ውስጥ የሚኖር ካህን ነበር።
  • እርሱና ሚስቱ ባቢሎን ወንዝ አጠገብ ከሃያ ዓመት የበለጠ እየኖሩ እያለ የትንቢት ቃል ለመስማት አይሁድ ወደእርሱ መጡ።
  • ከትንቢቶቹ መካከል ሕዝቅኤል ስለኢየሩሳሌምና ቤተመቅደሱ መደምሰስና እንደገና መሠራት ትንቢት ተናግሮ ነበር።
  • ስለየወደፊቱ የመሲሕ መንግሥትም ትንቢት ተናግሮአል።

ሕዝቅያስ

ሕዝቅያስ 13ኛው የይሁዳ ንጉሥ ነበር። በእግዚአብሔር የሚታመንና ለእርሱ የሚታዘዝ ንጉሥ ነበር።

  • በጣም ክፉ ንጉሥ ከነበረው ከአባቱ ከአካዝ በተለየ መልኩ ንጉሥ ሕዝቅያስ የጣዖት አምልኮን ከይሁዳ በማስወገድ እውነተኛ የእግዚአብሔር አምልኮ እንደ ገና እንዲታደስ አደረገ።
  • ንጉሥ ሕዝቅያስ አጥብቆ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር ከጽኑ ሕመም ፈወሰው፤ በዕድሜውም ላይ 15 ዓመት ጨመረለት።
  • ወደ ፊት የሚሆነውን በተመለከተ ለሕዝቅኤል ምልክት እንዲሆን ጥላው አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመልሶ ነበር።

መልከጼዴቅ

አብርሃም በነበረበት ዘመን መልከጼዴቅ፣ በኋላ፣ “ኢየሩሳሌም” ተብላ የተጠራችው የሳሌም ከተማ ንጉሥ ነበር።

  • የመልከጼዴቅ ስም ትርጉም፣ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ “የሳሌም ንጉሥ” የተሰኘው መጠሪያውም፣ “የሰላም ንጉሥ” ማለት ነው።
  • “የልዑል አምላክ ካህን” ተብሎም ተጠርቷል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልከጼዴቅ መጀመሪያ የተጠቀሰው አብራም የወንድሙን ልጅ ሎጥን ብርቱ ከህልኑ ነገሥታት እጅ አስጥሎ ሲመለስ፣ ለአብራም እንጀራና ወይን የሰጠው ጊዜ ነበር። አብራምም ከድሉ ካገኘው ሁሉ አንድ አሥረኛውን ለመልከጼዴቅ ሰጠው።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ መልከጼዴቅ አባትና እናት እንደሌለው ተነግሯል። እርሱ ካህንና ለዘላለም የሚነግሥ ንጉሥ ነው። በእግዚአብሔር ልጅ፣ “ተመስሎ” እንደሚኖርም ተነግሯል።
  • ኢየሱስ፣ “በመልከጼዴቅ ክህነት” መሠረት ካህን እንደ ሆነ አዲስ ኪዳን ይናገራል። እንደ ሌሎቹ እስራኤላውያን ካህናት ኢየሱስ ከሌዊ ዘር አልተወለደም። የእርሱ ክህነት በቀጥታ ከእግዚአብሔር ነበር።
  • እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥያሉ ገለጻዎችን መሠረት በማድረግ መልከጼዴቅ ዘላለማዊ የሰላምና የጽድቅ ንጉሥ የሆነውንና ሊቀ ካህናችን የሆነውን ኢየሱስ እንዲወክል በእግዚአብሔር የተመረጠ ሥጋ ለባሽ ካህን እንደ ነበር እንረዳለን።

መርዶክዮስ

መርዶክዮስ በፋርስ አገር ይኖር የነበረ አንድ አይሁዳዊ ስም ነው። በኋላ ላይ የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ሚስት የሆነችው የአጎቱ ልጅ የአስቴር ጠባቂ ነበር።

  • ቤተ መንግሥት ውስጥ እየሠራ እያለ ሰዎች ንጉሥ አርጤክስስን ለመግደል ሲመካከሩ ሰማ። ይህን በመናገሩ ንጉሡ ከሞት ተረፈ።
  • ከግዙ ጊዜ በኋላም መርዶክዮስ በፋርስ መንግሥት ውስጥ የነበሩ አይሁድን በሙሉ ለመግደል የወጣውን ዕቅድ ሰማ። ሕዝቧን ለማዳን ለንጉሡ አቤቱታ እንድታቀርብ አስቴርን መከራት።

መስጴጦምያ፣ አራም ናሐራይም

መስጴጦምያ በኤፍራጥስና በጤግሮስ ወንዞች መካከል ያለ ምድር ነው። ስፍራው የዘመኑ ኢራቅ ያለችበት ቦታ ነበር።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህ አካቢ አራም ናሐራይም ይባል ነበር።
  • “መስጴጦምያ” ማለት፣ “በሁለት ወንዞች መካከል” ማለት ነው። “አራም ናሐራይም” ማለት፣ “ባለ ሁለት ወንዞች” ማለት ነው።
  • ወደ ምድረ ከነዓን ከመንቀሳቀሱ በፊት አብርሃም ዑር እና ካራን በተባለት የመስጴጦምያ ከተሞች ይኖር ነበር።
  • ባቢሎን መስጴጦምያ ውስጥ የነበረች ጠቃሚ ከተማ ናት።
  • “ከለድ” ተብሎ የሚጠራውም አካባቢ መስጴጦምያ ውስጥ ነበር።

መቄዶንያ

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን መቄዶንያ ከጥንቱ ግሪክ በስተ ሰሜን የነበረች የሮም አውራጃ ነበረች።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ አንዳንድ ሁነኛ የመቄዶንያ ከተሞች ቤርያ፣ ፊልጵስዩስና ተሰሎንቄ ናቸው።
  • ሐዋርያት ወንጌል ለምስበክና አዲሶቹ አማኞች ለአምልኮና የእግዚአብሔርን ትምህርት ለሌሎች የሚያካፍል ክርስቲያን ማኅበረ ሰብ እንዲመሠረቱ ለመርዳት ወደ እነዚህ ከተሞች ሄደው ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጳውሎስ ለፊልጵስዩስና ለተሰሎንቄ አማኞች የጻፋቸው መልእክቶች አሉ።

መዓካ

መዓካ የአብርሃም ወንድም ናሆር ከወለዳቸው ልጆች አንደኘው ነው። በብሉይ ኪዳን ሌሎችም ሰዎች ይህ ስም ነበራቸው።


ሙሴ

ሙሴ ለ40 ዓመት የእስራኤል ሕዝብ ነቢይና መሪ ነበር።

  • እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ነጻ እንዲያወጣና ወደ ተስፋው ምድር እንዲመራቸው እግዚአብሔር ሙሴን መረጠ።
  • እግዚአብሔር ለሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲሆን የእርሱ ሕጎች የተጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠው።
  • ሕይወቱ ማብቂያ ላይ ሙሴ ለእግዚአብሔር ባለ መታዘዙ ወደ ተስፋው ምድር ወደ ከንዓን ሳይገባ ቀረ።

ሚልክያስ

ሚልክያስ ወደ እስራኤል ከተላኩት የእግዚአብሔር ነቢያት አንዱ ነው።

  • ሚልክያስ ትንቢት የተናገረው ከባቢሎን ምርኮ መልስ በኋላ የእስራኤል ቤተ መቅደስ እንደ ገና እየተሠራ በነበረበት ዘመን ነበር።
  • ሚልክያስ የነበረው ምናልባት ነህምያና ዕዝራ በሕይወት በነበሩበት ዘመን እንደ ሆነ ይታሰባል።
  • ትንቢተ ሚልክያስ የመጨረሻው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ሲሆን፣ “ታናናሾቹ ነቢያት” ከሚባሉት አንዱ እንደ ነበር ትውፊት ያመለክታል።

ሚሳኤል

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሚሳኤል ተብለው የተጠሩ ሦስት ሰዎች አሉ።

  • ሚሳኤል ከአሮም ወንድም ልጆች አንዱ ሲሆን፣ መሠዊያውን ያረከሱ ሁለት ሰዎችን እንዲያወጡ የተነገራቸው ለእርሱና ለአንድ ሌላ ሰው ነበር።
  • ሌላው ሚሳኤል የተባለው ሰው ሕጉ በተገኘ ጊዜ በአደባባይ ለሕዝቡ ሲነበብ ዕዝራ አጠገብ ቆሞ የነበረው ነው።
  • ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን ተወስደው ከነበሩት ሦስቱ የዳንኤል ጓደኞች አንዱ ሚሳኤል ይባል ነበር፤ በባቢሎናውያን ግን ሚሳቅ በማለት ጠሩት ሲድራቅና አብድናጎ ከሚባሉት ጓደኞቹ ጋር አብሮ ንጉሡ ላቆመው ምስል መስገድ አልፈለገም ስለዚህም እሳት ውስጥ ተጣለ

ሚካኤል

ሚካኤል ቅዱሳንና ታዛዦች ከሆኑት የእግዚአብሔር መላእክት ዋናው ነው። የእግዚአብሔር፣ “ሊቀ መልአክ” ተብሎ የተጠራ እርሱ ብቻ ነው።

  • “ሊቀ መልአክ” – “ዋና መልአክ” ወይም፣ “ገዢ መልአክ” ማለት ነው።
  • እስራኤላውያንን በፋርስ ሰራውቲ ላይ የመራ ሚካኤል ነበር፤ በዳንኤል በተነገረው መሠረት በመጨረሻው ዘመን ከክፋት ኀይሎች ጋር በሚደረገው ውጊያ የእስራኤልን ሰራዊት የሚመራም እርሱ ነው።
  • የእግዚአብሔርን ሕዝብ በተመለከተም በእግዚአብሔር ፊት እንደሚማልድ የተነገረበ ሁኔታም አለ።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የተጠሩ አንዳንድ ሰዎች አሉ።

ሚክያስ

ሚክያስ ነቢዩ ኢሳይያስም በይሁዳ እያገለገለ በነበረ ጊዜ ከክርስቶስ 700 ዓመት በፊት የነበረ የይሁዳ ነቢይ ነበር።

  • ትንቢተ ሚክያስ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መጨረሻ አካባቢ ይገኛል።
  • ሚክያስ ሰማርያ በአሦራውያን እንደምትደመሰስ ትንቢት ተናገረ።
  • ሚክያስ ለእግዚአብሔር ባለ መታዘዛቸው የአይሁድን ሕዝብ ገሠጸ፤ ጠላቶቻቸው እንደሚያጠቋቸውም አስጠነቀቃቸው።
  • ትንቢቱ የሚያበቃው ሕዝቡን ለማዳን ታማኝ በሆነው በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ እንደሚግባ በማሳስብ መልእከት ነው።

ሚጽጳ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሚጽጳ ተብለው የተጠሩ ጥቂት ቦታዎች አሉ። ትርጕሙ፣ “መመልከቻ ቦታ” ወይም፣ “ቅጥር መጠበቂያ” ማለት ነው።

  • ሳኦል ዳዊትን ባሳደደው ጊዜ ሚጽጳ ከነበረው የወላጆቹ ቤት ወደ ሞዓብ ንጉሥ ሸሽቶ በዚያ ጥገኝነት ጠየቀ።
  • ሚጽጳ የሚባለው ሌላው ቦታ በይሁዳና በእስራኤል መንግሥታት መካከል ድንበር ላይ የነበረው ነው። ዋና የወታደር ማዕከል ነበር።

ማርታ

ማርታ ቢታንያ በተባለ ቦታ ትኖር የነበረ የኢየሱስ ተከታይ ሴት ናት።

  • ማርታ ማርያም የምትባል እኅትና አልዓዛር የሚባል ወንድም ነበራት፤ ሁለቱም የኢየሱስ ተከታዮች ነበር።
  • አንድ ጊዜ እኅቷ ተቀምጣ ኢየሱስ ሲያስተምር ስትሰማ ማርታ ግን ምግብ ለማዘጋጀት ወዲያ ወዲህ እያለች ነበር።
  • አልዓዛር ሞቶ በነበረ ጊዜ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንደምታምን ማርታ ለኢየሱስ ተናገረች።

ማርያም

ማርያም የአሮንና የሙሴ ታላቅ እኅት ነበረች።

  • ማርያም ትንሽ ልጅ እያለች በቅርጫት ዐባይ ወንዝ ዳር ቄጤማዎች መካከል የተጣለው ታናሽ ወንድሟ ሙሴን በዐይኗ እንድትከታተል እናቷ ነግራት ነበር። የፈርዖን ልጅ ሕፃኑን አግኝታ የሚያሳድገው ሰው እየፈለገች በነበረች ጊዜ ማርያም፣ የሙሴን እናት አመጣችላት።
  • እስራኤላውያን ከግብፃውያን አምልጠው ቀይ ባሕርን ሲሻገሩ እስራኤላውያንን ወደ ደስታና ወደ ምስጋና ሽብሸባ የመራች ማርያም ነበርች።
  • ከዓመታት በኋላ እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት በማግባቱ ማርያምና አሮን ደስ አልተሰኙም፣ እርሱን በተመለከተ መጥፎ ነገር መናገር ጀመሩ።
  • ሙሴ ላይ ክፉ በመናገር ባሳየችው ዐመፅ እግዚአብሔር ማርያም ላይ ለምጽ እንዲወጣ አደረገ። በኋላ ግን ሙሴ ለእርሷ በመማለዱ እግዚአብሔር ፈውሷታል።

ማርያም (የማርታ እኅት)

ማርያም ቢታንያ በሚባል ቦታ ትኖር የነበረ የኢየሱስ ተከታይ ናት።

  • ማርያም ማርታ የምትባል እኅትና አልዓዛር የሚባል ወንድም ነበራት፤ ሁለቱም የኢየሱስ ተከታዮች ነበር።
  • ለእርሱ ምግብ ለማዘጋጀት ወዲያ ወዲህ ከማለት ይልቅ እርሱን መስማት ስለ መረጠች አንድ ጊዜ ኢየሱስ ማርያምን አመስግኗት ነበር።
  • አንድ ጊዜ ኢየሱስ በቢታንያ ምግብ ለመብላት ተቀምጦ እያለ፣ እርሱን ለማምለክ ማርያም ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ እግሩ ላይ አፈሰሰች፤ ይህን በማድረጓም ኢየሱስ አመስግኗታል።

ማርያም መግደላዊት

ማርያም መግደላዊት ኢየሱስን መከተል የጀመረችው ሰባት አጋንንት ከእርሷ ካስወጣ በኋላ ነበር።

  • ማርያም መግደላዊትና ሌሎች ሴቶች ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን በገንዘብ ይረዷቸው ነበር።
  • ኢየሱስ ከሞት በተነሣ ጊዜ እርሱን በመጀመሪያ ያዩት ማርያም መግደላዊትና ሌሎች ጥቂት ሴቶች ነበሩ።

ማርያም የኢየሱስ እናት

ማርያም የዮሴፍ እጮኛና የኢየሱስ እናት ናት።

  • ማርያም ድንግል እያለች መንፈስ ቅዱስ በተአምር እንድትፀንስ አደረገ። እርሷ የፀነሰችው ሕጻን የእግዚአብሔር ልጅ ነበር።
  • ሚስቱ እንድትሆን ዮሴፍ ማርያም ወሰዳት፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስን እስክትወልድ ድረስ ማርያም ድንግል ነበረች።
  • ሕጻን ሲወለድ፣ ማርያምና ዮሴፍ ኢየሱስ አሉት።

ማቴዎስ፣ ሌዊ

ማቴዎስ ለእልፍዮስ ልጅ ለሌዊ የተሰጠ ስም ነው። ማቴዎስ ሐዋርያቱ እንዲሆኑ ኢየሱስ ከመረጣቸው አሥራ ሁለት ሰዎች አንዱ ነበር።

  • ከኢየሱስ ጋር ከመገናኘቱ በፊት ማቴዎስ በቅፍርናሆም ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር።
  • ማቴዎስ ስሙን የያዘ ወንጌል ጽፎአል።

ሜምፊስ

ሜምፊስ ዐባይ ወንዝ መደዳ የምትገኝ ጥንታዊ ግብፅ ውስጥ የነበረች ከተማ ነበረች።

  • ሜምፊስ ትገኝ የነበረው በየትኛው ግብፅ የዐባይ ወንዝ ደለል ላይ ሲሆን፣ በዚያ ዐፈሩ በጣም ለም ነበር፤ ብዙ እህልም ይመረት ነበር።
  • የነበረችበት ሁነኛ ቦታ ሜምፊስን ዋና የንግድና የግብይት ከተማ አደረጋት።

ሜዶን፣ ሜዶናውያን

ሜዶን ከአሦርና ከባቢሎን በስተ ምሥራቅ፣ ከኤላምና ከፋርስ በስተ ሰሜን የነበረ ትንታዊ መንግሥት ነው። የነበረበት ቦታ በአሁኑ ዘመን ቱርክ፣ ኢራን፣ ሶርያ፣ ኢራቅና አፍጋኒስታን ያሉበትን በክፊል ያካትት ነበር።

  • በሜዶን መንግሥት የነበሩ ሰዎች ሜዶናውያን ይባሉ ነበ።ር
  • ሜዶናውያን ከፋርስ ጋር በጣም ይቀራረቡ ነበር፤ ሁለቱ መንግሥታት በአንድነት ሆነው የባቢሎንን መንግሥት አሸንፈዋል።
  • ሜዶናዊው ዳርዮስ በባቢሎን የወረረው ነቢዩ ዳንኤል እዚያ እያለ ነበር።

ምሳሕ

ምሳሕ የኖኅ ልጅ የያፌት ልጅ ነው። ሌላው ሞሳሕ ተብሎ የተጠራ ሰው የኖኅ ልጅ የሴም የልጅ ልጅ ነው።

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው የየለያዩ ሰዎች ስም የአካባቢ ወይም የአገር ስም ሆነዋል። ሞሳሕ የተባለውም ምድር ከእነዚህ ሰዎች በአንዱ ተጠርቶ ሊሆን ይችላል።
  • ይህ ስም የተለያዩ ነገሮችን እንደሚያመለክት ግልጽ ለማድረግ እንደ ዐውዱ አገባብ፣ “ሞሳሕ የተባለው ቦታ” ወይም፣ “ሞሳሕ የተባለው ሰው” ማለት ይቻላል።

ምናሴ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ምናሴ ተብለው የተጠሩ አምስት ሰዎች ነበር።

  • ምናሴ የዮሴፍ መጀመሪያ ልጅ ስም ነው።
  • ምናሴንና ታናሽ ወንድሙ ኤፍሬምን የዮሴፍ አባት ያዕቆብ እንደ ገዛ ራሱ ልጆች ተቀብሎአቸዋል፤ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ውስጥ የመሆንን መብትም ሰጥቷቸዋል።
  • የምናሴ ነገድ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ ሆኗል።
  • የምናሴ ነገድ ብዙውን ጊዜ፣ “የምናሴ ነገድ ዕኩሌታ” ተብሎ ተጠርቷል፤ ምክንያቱም ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በምድረ ከነዓን የሰፈረው የነገዱ ግማሽ ብቻ ስለ ነበር ነው። የነገዱ ሌላው ግማሽ የሰረፈው ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ነበር።
  • ከይሁዳ ንጉሦች አንዱ ምናሴ ይባል ነበር።
  • ንጉሥ ምናሴ የገዛ ልጆቹን እንኳ ለሐሰተኛ አማልክት መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበ ክፉ ንጉሥ ነበር።
  • በጠላት ሰራዊት እጅ እንዲወድቅ በማድረግ እግዚአብሔር ንጉሥ ምናሴን ቀጣው። ምናሴ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ጣዖቶች ይመለኩባቸው የነበሩ መሠዊያዎች አፈራርሷል።
  • በዕዝራ ዘመን የነበሩት ምናሴ የሚል ስም የነበራቸው ሁለት ሰዎች ሁለቱም የባዕድ አገር ሴቶች አግብተው ነበር። ባዕዳን አምልኮቶቻቸው ካሳደሩት ተፅዕኖ የተነሣ እነዚህ ሰዎች ሚስቶቻቸውን እንዲፈቱ ተጠይቀው ነበር።
  • ሌላው ምናሴ የተባለው ሰው የሐሰተኛ አማልክት ካህናት የነበሩ የዳን ወገኖች አያት ነበር።

ምድያማዊ፣ ምድያማውያን

ምድያማውያን ከከነዓን በስተ ደቡብ ሰሜናዊው የአረቢያ ምድረ በዳ ይገኙ የነበሩ ሕዝብ ናቸው።

  • ምድያማውያን የነበሩት ከ19ኛው እስከ 11ኛው ዓቅክ ነበር።
  • ዮሴፍን ወደ ግብፅ የወሰዱት ምድያማውያን ባሪያ ነጋዴዎች ነበር።
  • ከብዙ ዓመታት በኋላ ምድያማውያን ምድረ ከንዓን ውስጥ የነበሩ እስራኤላውያንን መበውረር አሸነፏቸው።
  • በዚህ ዘመን ያሉት አብዛኞቹ የአረብ ነገዶች ከምድያማውያን የተገኙ ናቸው።

ሞሎክ

ሞሎም ከነዓናውያን ከሚያመልኳቸው ሐሰተኛ አማልክት የአንዱ ስም ነበር።

  • ሞሎክን የሚያመልኩ ሰዎች ለእርሱ መሥዋዕት እንዲሆኑ ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ነበር።
  • አንዳንድ እስራኤላውያንም ከእውነተኛ አምላክ ከያህዌ ይልቅ ሞሎክን አምልከው ነበር።

ሞዓብ፣ ሞዓባዊ፣ ሞዓብዊት

ሞዓብ የኖኅ ታላቅ ሴት ልጅ ልጅ ነበር። ዘሮቹ ሞዓባውያን ሲባሉ የሰፈሩበት ቦታ ሞዓብ ተባለ።

  • የሞዓብ አገር ከይሁዳ በስተ ምሥራቅ ከሙት ባሕር ፊት ለፊት ባለው ቦታ ነበር። የኑኃሚን ቤተ ሰብ ከነበረበት ከይሁዳ ከተማ ከቤተ ልሔም ከተማ ደቡብ ምሥራቅ ላይ ነበረች።
  • “ሞዓባዊት” የሚለው ቃል፣ “የሞዓብ አገር ሴት” ወይም፣ “ከሞዓብ አገር የሆነች ሴት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ሠሪ

አጠቃላይ በሆነ አነጋገር፣ “ሠሪ” ነገሮችን የሚፈጥር ወይም የሚሠራ ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንዴ፣ “ሠሪ” የሚለው የያህዌ ስም ወይም መጠሪያ ነው፤ ምክንያቱም እርሱ የሁሉም ሠሪና ፈጣሪ በመሆኑ ነው።
  • ብዙ ጊዜ ቃሉ፣ “የእርሱ” ወይም፣ “የእኔ” ወይም፣ “የአንተ” ከተሰኙት ጋር ተያይዞ ቀርቧል።

ሣራ፣ ሦራ

  • ሣራ የአብርሃም ሚስት ነበረች
  • መጀመሪያ ላይ የሣራ ስም ሦራ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ወደ ሣራ ለወጠው
  • ሣራ ለእርሷና ለአብርሃም እንደሚሰጥ እግዚአብሔር ቃል የገባላቸውን ልጅ ወለደች

ረባት

ረባት በጣም ጠቃሚ የአሞራውያን ከተማ ነበረች።

  • ከአሞራውያን ጋር በተደረጉ ጦርነቶች ብዙ ጊዜ የተጠቃች ረባት ነበረች።
  • የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት መጨረሻ ላይ ካገኛቸው ድሎች አንዱ ረባትን መያዙ ነበር።
  • ረባት በአሁኑ ዘመን ዮርዳኖስ አማን ከተማ ያለችበት ቦታ ላይ ነበረች።

ረዓብ

ረዓብ እስራኤላውያን ኢያሪኮን ሲያጠቁ እዚያ የነበረች ሴት ነበረች። አመንዝራም ነበረች።

  • እስራኤላውያን ኢያሪኮን ከማጥቃታቸው በፊት ኢይሪኮን ለምሰለል ሲመጡ ረዓብ ሁለቱን እስራኤላውያን ደበቀች። አምልጠው ወደ እስራኤላውያን ሰፈር እንዲመለሱም ረዳቻቸው።
  • ረዓብ በያህዌ አመነች፤ ኢያሪኮ ስትደመሰስ እርሷና ቤተ ሰቧም ዳኑ። ከእስራኤላውያን ጋር አብረው ኖሩ።

ሩት

ሩት መሳፍንት እስራኤላውያንን እየመሩ በነበረ ዘመን የነበረች ሞዓባዊት ሴት ናት። ጥንታዊ የኢየሱስ ክርስቶስ መገኛ ነበረች

  • ሩት ይበልጥ የምትታወቀው ለአማቷ ለኑኃሚን በነበራት ታማኝነት ነው። ሩት ከእርሷ ጋር ወደ እስራኤል በመመለስ በሚያስፈልጋት ረድታታለች
  • አንዱንና እውነተኛውን የእስራኤል አምላክ ወደማመን መጥታለች
  • ሩት አንድ እስራኤላዊ ሰው በማግባት ወንድ ልጅ ወልዳለች፣ ያም ልጅ የንጉሥ ዳዊት አያት ሆኗል

ሪሞን

ሪሞን የአንድ ሰው እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሳቸው ጥቂት ቦታዎች ስም ነው። ሪሞን የሚባል ጣዖትም ነበር። ቃል በቃል ትርጉሙ፣ “ሮማን” ማለት ነው።

  • ሮሞት ዛብሎን ውስጥ በሚገኘው በአሮት ከተማ ይኖር የነበረ ብንያማዊ ነው። የዚህ ሰው ልጆች ኢያቡስቴ የሚባለውን አንካሳ የዮናታን ልጅ ገድለዋል።
  • ሪሞን በደቡባዊው የይሁዳ አካባቢ የነበረች ከተማ ነች። የሪሞት ዐለት ብንያማውያን ከመገደል ያመለጡበት መደበቂያ ቦታ ነበር።
  • ሪሞት ፌሬዝ የይሁዳ ምድረ በዳ ውስጥ ያልታወቀ ቦታ ነው።

ራሔል

ራሔል ከያዕቆብ ሚስቶች አንዷ ነበረች። እርሷና እኅቷ ልያ የያዕቆብ አጎት የላባን ልጆች ነበሩ።

  • ራሔል ከእስራኤል ነገዶች ሁለቱ የሆኑት የዮሴፍና የብንያም እናት ነበረች።
  • መጀመሪያ ላይ ራሔል ልጅ መውለድ አልቻለችም ነበር። ሆኖም፣ እግዚአብሔር ዮሴፍን መውለድ አስቻላት።
  • ከዓመታት በኋላ ብንያምን በመውለድ ላይ እያለች ራሔል ሞተች፤ ያዕቆብም ቤተ ልሔም አጠገብ ቀበራት።

ራማ

ራማ ከኢየሩሳሌም በስተ ሰሜን 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ጥንታዊ የእስራኤል ከተማ ነበረች።

  • ራማ ትገኝ የነበረው የያዕቆብ ሚስት ራሔል ዘሮች የነበሩበት አካባቢ ነበር።
  • እስራኤላውያን በምርኮ ወደ ባቢሎን ሲወሰዱ፣ ወደዚያ ከመሄዳቸው በፊት መጀመሪያ የመጡት ወደ ራማ ነበር።
  • ራማ የሳሙኤል እናትና አባት አገር ነበረች።

ራሞት

ራሞት ገለዓድ ተራሮች ላይ የምትገኝ በጣም ጠቃሚ ከተማ ነበረች። ራሞት ገለዓድም ትባላለች።

  • ራሞት የጋድ ድርሻ ነበረች፤ የመማጸኛ ከተማም ነበረች።
  • የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ከአራም ንጉሥ ጋር የተዋጉት በራሞት ነበር። አክዓብ በጦርነቱ ተገደለ።
  • በኋላ ላይ ንጉሥ አካዝያስና ንጉሥ ኢዮራም ከአራም ንጉሥ ራሞትን ለመውሰድ ሞክረው ነበር፤ ሆንም ንጉሥ ኢዮራም ቆሰለ። የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን በራሞት ተቀብቶ በነበረው በኢዩ ሁለቱም ተገደሉ።

ርብቃ

ርብቃ ከአብርሃም ወንድም ልጆች አንዷ ነበረች፤ የእርሷ አያት የአብርሃም ወንድም ነበር።

  • የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ሚስት እንድትሆን እግዚአብሔር ርብቃን መረጠ።
  • ይስሐቅን ለማግባትና ከእርሱ ቤተ ሰብ ጋር ለመኖር ርብቃ ወደ ይስሐቅ አገር ለመሄድ አግሯን ትታ ክአብርሃም አገልጋይ ጋር ሄደች።
  • ለረጅም ዓመታት ርብቃ ልጅ አልነበራትም፤ በኋላ ግን ኤሳውና ያዕቆብ በሚባሉ መንታ ልጆች እግዚአብሔር ባረካት።

ሮም፣ ሮማዊ

በዚህ ባለንበት ዘመን ሮም የኢጣልያ ዋና ከተማ ናት።

  • ኢየሱስና ሐዋርያቱ ባገለገሉበት ዘመን ሮም የሮም መንግሥት ማዕከል ነበረች።
  • የሮም መንግሥት እስራኤልን ጨምሮ ሜዲትራንያን ባሕር ዙሪያ የነበረውን አካባቢ ሁሉ ይገዛ ነበር።
  • “ሮማዊ” የሚለው ቃል ሮማውያን ዜጎችንና ባለ ሥልጣኖችን ጨምሮ የሮም መንግሥት ከሚገዛው አካባቢ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ሁሉ ያመለክታል።
  • ሐዋርያው ጳውሎስ የኢየሱስን የምሥራች በመስበኩ እስረኛ ሆኖ ወደ ሮም ከተማ ተወስዶ ነበር።

ሮቤል

ሮቤል የመጀመሪያው የያዕቆብ ልጅ ነበር። እናቱ ልያ ትባላለች።

  • ወንድሞቹ ታናሽ ወንድማቸው ዮሴፍን ለመግደል ሲማከሩ፣ ከዚያ ይልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንዲጥሉት በመናገር የዮሴፍን ሕይወት ያዳነ ሮቤል ነበር።
  • በኋላም ተመልሶ በመምጣት ሮቤል ዮሴፍን አዳነ ሌሎች ወንድሞቹ ግን በዚያ በኩል እያለፉ ለነበር ነጋዴዎች ለባርነት ሸጡት።
  • የሮቤል ዘሮች ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ሆነዋል።

ሮብዓም

ሮብዓም ከንጉሥ ሰሎሞን ልጆች አንዱ ሲሆን፣ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ንጉሥ ሆኗል.

  • ሮብዓም የእስራኤልን ሕዝብ በሚያስመርር ሁኔታ በመናገሩ አሥሩ ነገዶች እርሱ ላይ ዐመፁ። ከዚህም የተነሣ የእስራኤል መንግሥት ለሁለት ተከፈለ፤ በሰሜን ያለው የእስራኤል መንግሥት ሲባል፣ በደቡብ ያለው የይሁዳ መንግሥት ተባለ።
  • ሮብዓም በእርሱ ታማኝ የሆኑ ሁነቱን ነገዶች በያዘው የይሁዳ መንግሥት ንጉሥ መሆኑን ቀጠለ።
  • ሮብዓም ለእግዚአብሔር የማይታዘዝ ክፉ ንጉሥ ነበር፤ የተለያዩ አማልክትንም ያመልክት ነበር።

ሰሎሞን

ሰሎሞን ከንጉሥ ዳዊት ልጆች አንዱ ነበር። የእናቱ ስም ቤርሳቤህ ይባል ነበር

  • ሰሎሞን በነገሠ ጊዜ ከእርሱ ማንኛውንም ነገር እንዲለምን እግዚአብሔር ነግሮት ነበር። ስለዚህም ሰሎሞን ሕዝቡን በአግባቡና በፍትሕ ማስተዳደር የሚችልበት ጥበብ እንዲሰጠው ጠየቀ። ሰሎሞን በቀረበው ጥያቄ እግዚአብሔር ደስ ስለተሰኘ ጥበብንና ብዙ ሀብትን ሰጠው
  • ሰሎሞን አባቱ ዳዊት ለመሥራት ፈልጎ የነበረውን በኢየሩሳሌም የነበረውን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሠራ
  • ምንም እንኳ ሰሎሞን በመጀመሪያው የአገዛዝ ዘመኑ በጥበብ ቢያስተዳድርም፣ በኋላ ግን በመታለል ባዕድ ሴቶች አገባ፤ አማልክቶቻቸውንም ማምለክ ጀመረ
  • ሰሎሞን ታማኝነትን በማጉደሉ፣ ከእርሱ ሞት ብኋላ እስራኤላውያን ለሁለት መንግሥታት ተከፈሉ፤ እስራኤልና ይሁዳ። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ መንግሥታት እርስ በርስ ይዋጉ ነበር

ሰማርያ፣ሳምራዊ

ሰማርያ ለእስራኤል ሰሜናዊ አካባቢ ላለው ከተማና አካባቢው የተሰጠ ስም ነው። ይህ አካባቢ በምዕራብ በሳሮን ሜዳማ ቦታና በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ይገኛል

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰሜናዊ እስራኤል መንግሥት ዋና ከተማ ነበር። በኋላ ላይ ዙሪያውን ያለው አካባቢም ሰማርያ ተባለ
  • አሦራውያን ሰሜናዊውን የእስራኤል መንግሥት ባሸነፉ ጊዜ እዚያ የነበሩ እስራኤላውያን ወደ ተለያዩ የአሦር ከተማ ወሰዷቸው።
  • አሦራውያን ብዙ የባዕድ አገር ሰዎች ወደሰማርያ በማምጣት ከዚያ የተወሰዱ እስራኤላውያን ቦታ ላይ አሰፈሯቸው
  • አንዳንድ እስራኤላውያን ከእነዚያ ከባዕድ አገር ከመጡ ሰዎች ጋር ተጋቡ፤ ከእነርሱ የተወለዱት ሳምራውያን ተባሉ
  • ከፊል አይሁድ በመሆናቸውና የአረማውያን አማልክትን ያመልኩ ስለነበር አይሁድ ሳምራውያንን ይንቋቸው ነበር
  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ሰማርያ በሰሜን ከገሊላ ጋር፣ በደቡብ ከይሁዳ ጋር ይዋሰን ነበር

ሰሜኢ፣ ሳሚ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሰሜኢ ተብለው የተጠሩ ጥቂት ሰዎች ነበሩ።

  • የጌራ ልጅ ሳሚ ብንያማዊ ሲሆን፣ ልጁ አቤሴሎም ከኢየሩሳሌም ባሳደደው ጊዜ ንጉሥ ዳዊትን እየተራገመ ድንጋይ ወርውሮበት ነበር
  • ብሉይ ኪዳን ሰሜኢ በማለት የጠራቸው አብዛኞቹ ሰዎች ሌዋውያን ካህናት ነበሩ

ሰናክሬም

ሰናክሬም ነነዌ ሀብታምና ተፈላጊ ከተማ እንድትሆን ታላቅ የአሦር ንጉሥ ነበር

  • ንጉሥ ሰናክሬም ከባቢሎንና ከይሁዳ መንግሥት ባደረጋቸው ጦርነቶች ይታወቃል
  • በጣም እብሪተኛና በያህዌ የተሳለቀ ንጉሥ ነበር
  • በንጉሥ ሕዝቅያስና በነቢዩ ኢሳይያስ ዘመን ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን አጠቃ
  • ያህዌ የሰነክሬም ሰራዊት እንዲደመሰስ አደረገ
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉት መጽሐፈ ነገሥትና መጽሐፈ ዜና መዋዕል በአገዛዝ ዘመኑ ስላደረጋቸው አንዳንድ ነገሮች ያመለክታሉ

ሰናዖር

ሰናዖር፣ “የሁለት ወንዞች አገር” ማለት ሲሆን በደቡባዊ ሜሶፖታሚያ ላለው ሜዳ ወይም አካባቢ የተሰጠ ስም ነበር

  • በኋላ ላይ ሰናዖር ከላድ ከዚያም ባቢሎን ተብሏል
  • ሰናዖር ውስጥ በጣም የታወቀው የባቤል ከተማ ሊሆን ይችላል፤ ረጅም ግንብ የሠሩ እዚያ የነበሩ ጥንታዊ ሕዝብ ነበሩ
  • አብርሃም በዚያ ዘመን ከለድያ ተብሎ ይጠራ ወደነበረው ወደዚህ አካባቢ የመጣው ከዑር ነበር

ሰዶም

ሰዶም የአብርሃም ወንድም ልጅ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ይኖርበት የነበረ ከከነዓን በስተ ደቡብ አካባቢ ያለ ከተማ ነበር

  • ሰዶም አካባቢ ያለው ምድር ውሃ የሞላበት ለም መሬት ነበር፤ መጀመሪያ ከነዓን በሰፈረ ጊዜ ሎጥ ለመኖር የመረጠው እዚያ ነበር
  • ሰዶምና በአካባቢው የነበረው በጎሞራ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ለፈጸሙት ክፉ ሥራ ቅጣት እንዲሆን ሙሉ በሙሉ በመደምሰሳቸው የዚህ ከተማ ትክክለኛ ቦታ አይታወቅም
  • የሰዶምና የገሞራ ሰዎች በጣም የሚታወቁበት ኅጢአት ወንድ ከወንድ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ነበር

ሰፎንያስ

ካህንና ነቢይን ጨምሮ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሶፎንያስ ተብለው የተጠሩ ብዙ ሰዎች ነበር። የሶፎንያስ ትንቢት የሚገኘው ትንቢተ ሶፎንያስ ውስጥነው።

  • ነቢዩ ሶፎንያስ የነበረው በኢየሩሳሌም ሲሆን፣ ትንቢት የተናገረው በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ዘመን ነበር።
  • ሶፎንያስ ሐሰተኛ አማልክት በማምለካቸው ሕዝቡን ገሐፀ።

ሱኮት

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሱኮት ተብለው የተጠሩ ሁለት ከተሞች አሉ። ሱኮት “መጠለያ” ወይም፣ “መጠጊያ” ማለት ነው

  • ሱኮት ተብላ የተጠራችው የመጀመሪያዋ ከተማ ከዮርዳኖስ ወንዝ ምሥራቅ ትገኝ ነበር
  • ያዕቆብ ከቤተ ሰቡ እና ከነበሩት የቤት እንስሳት ጋር በሱኮት ቆዩ፤ በዚያም መጠጊያ መጠለያ ሠራላቸው
  • ከመቶ ዓመታት በኋላ ጌዴዎንና ተዳክመው የነበሩት አብረውት ያሉ ሰዎች ምድያማውያንን እያሳደዱ በነበረ ጊዜ በሱኮት ቆይታ አድርገው ነበር፤ እዚያ የነበሩ ሰዎች ግን ምግብ እንኳ ሊሰጧቸው አልፈለጉም
  • ሁለተኛዋ ሱኮት የምትገኘው በሰሜናዊ የግብፅ ድንበር ሲሆን ከግብፅ ባርነት አምልጠው ቀይ ባሕርን ከተሻገሩ በኋላ ካረፉባቸው ቦታዎች አንዷ ነበረች

ሲላስ፣ ስልዋኖስ

ሲላስ በኢየሩሳሌም በነበሩ አማኞች መካከል መሪ ነበር

  • በኢየሩሳሌም የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ እንዲሄድ ሲላስን መረጠች
  • በኋላ ላይ ለሰዎች ስለ ኢየሱስ ለማስተማር ሲላስ ከጳውሎስ ጋር ወደ ሌሎች ከተሞች ተጉዟል
  • ጳውሎስና ሲላስ በፊልጵስዩስ ከተማ ታስረው ነበር። እዚያ በነበሩ ጊዜ ሁሉ በእግዚአብሔር በመታመን እርሱን በመዝሙር ያመሰግኑ ነበር። እግዚአብሔር ከእስር ቤት አወጣቸው፤ የወህኒውንም ጠባቂ ለማዳን ተጠቀመባቸው

ሲና፣ የሲና ተራራ

ሲና በአሁኑ ዘመን የሲና ፔኔንሱላ ተብሎ በሚጠራው ደቡባዊ ክፍል የሚገኝ ተራራ ስም ነው

  • ከግብፅ ወደ ተስፋው ምድር ሲጓዙ እስራኤላውያን ወደ ሲና ተራራ መጥተው ነበር
  • የሲና ተራራ በጣም ሰፉ ዐለታማ በረሐ ነው
  • እግዚአብሔር ለሙሴ አሥሩን ትእዛዞች የሰጠው በሲና ተራራ ነበር

ሲዶን፣ ሲዶናውያን

ሲዶን የከነዓን የመጀመሪያ ልጅ ነበር፤ ሲዶን የምትባል የከነዓናውያን ከተማም አለች

  • የሲዶን ከተማ ትገኝ የነበረው ሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ፣ በአሁኑ ዘመን ሊባኖስ የምትባለው አገር ያለችበት አካባቢ ነበር
  • “ሲዶናውያን” በጥንቷ ሲዶንና ዙሪያውን በነበረው አካባቢ በነበረችው በጥንቷ ሲዶን ይኖሩ የነበሩ ሕዝብ ናቸው። እንዚህ ሰዎች አረማውያን ነበሩ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲዶን ከጢሮስ ጋር በጥብቅ ተያይዛለች፤ ሁለቱም ከተሞች በሀብታምነታቸውና በመጥፎ ምግባራቸው ይታወቁ ነበር

ሳሙኤል

ሳሙኤል የመጨረሻው የእስራኤል መስፍን እና ነቢይ ነበር፤ የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆኑ ሳኦልንና ዳዊትን የቀባው እርሱ ነበር

  • ሳሙኤል አርማቴም በሚባል አገር ይኖሩ የነበሩ የሕልቃና እና የሐና ልጅ ነበር
  • ሐና መካን ነበረች፤ ሳሙኤልን የወለደችው ወንድ ልጅ እንዲሰጣት ለእግዚአብሔር ባቀረበችው ጸሎት መልስ ነበር
  • ሐና ባቀረበችው ጸሎት ልጇን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር።
  • ሳሙኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ካሕኑ ዔሊን በቤተ መቅደስ እንዲረዳ በገባችው ቃል መሠረት ወደዚያ ወሰደችው

ሳምሶን

ሳምሶን ከእስራኤል መሳፍንት ወይም ታዳጊ አንዱ ነበር። ሳምሶን ከዳን ነገድ ነበር።

  • እግዚአብሔር ለሳምሶን የእስራኤልን ጠላቶች ማለት ፍልስጥኤማውያንን የሚያጠቃበት አስደናቂ ልዕለ ሰብ ብርታት ሰጥቶት ነበር
  • ሳምሶን ጠጉሩን ላለመቆረጥና አልኮል ወይም ሌላ የሚያሰክር ነገር ላለመጠጣት ስለት ነበረበት
  • አታላይ ሚስቱ ደሊላ ላቀረበችለት ልመና በመታለል የብርታቱን ምስጢር በመናገሩ ብርታቱን እንዲያጣ ጠጉሩን ቆረጠችው
  • ሳምሶን እስር ላይ እያለ እግዚአብሔር ብርታቱን መልሶ እንዲገኝና ከብዙ ፍልስጥኤማውያን ጋር የሐሰተኛው አምላክ የዳጎንን ቤተመቅደስ ማፍረስ እንዲችል አደረገ

ሳሮን፣ የሳሮን ሜዳ

ሳሮን ከቀርሜሎስ ተራራ በስተ ደቡብ ሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ጠፍጣፋና ለም ምድር ነው። “የሳሮን ሜዳ” በመባልም ይታወቃል

  • ኢዮጴን፣ ልድያንና ቂሳርያን ጨምሮ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ጥቂት ከተሞች የሚገኙት የሳሮን ሜዳ ላይ ነበር
  • “ሳሮን የሚባለው ሜዳ” ወይም፣ “የሳሮን መስክ” ተብሎ ሊተረጎምም ይችላል

ሳባ

በጥንት ዘመን ሳባ ደቡብ አረቢያ አንድ ቦታ የሚገኝ ሥልጣኔ ወይም አካባቢ ነበር

  • ሳባ ከ1200 ዓቅክ እስከ 275 ዓም ድረስ በአሁኑ ዘመን የመን ወይም ኢትዮጵያ አጠገብ የሚገኝ ቦታ ነበር
  • ሳባ ውስጥ ይኖሩ የነበሩት ምናልባት የካም ዘሮች ሊሆኑ ይችላሉ
  • የሀብቱንና የጥበቡን ዝና በመስማቷ ንግሥተ ሳባ ሰሎሞንን ለመጎብኘት መጥታ ነበር
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “ሳባ” ተብለው የተጠሩ ጥቂት ሰዎች ነበሩ

ሳኦል (ብሉይ ኪዳን)

ሳኦል የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን እግዚአብሔር የመረጠው እስራኤላዊ ነበር

  • ሳኦል ረጅምና ቆንጆ እንዲሁም ብርቱ ወታደር ነበር። እስራኤላውያን ንጉሣቸው እንዲሆን የሚፈልጉት አይነት ሰው ነበር
  • መጀመሪያ ላይ እግዚአብሔርን ቢያገለግልም፣ በኋላ ትዕቢተኛ በመሆን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም። ከዚህም የተነሣ የንጉሥ ሳኦልን ቦታ እንዲወስድ እግዚአብሔር ዳዊትን ሾመ

ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ሳኦል የሚሉት ሌላ እስራኤላዊ ነበር፤ በኢየሱስ ካመነ በኋላ እግዚአብሔር ስሙን ጳውሎስ ወደሚል ለወጠው


ሳዶቅ

ሳዶቅ በንጉሥ ዳዊት ዘመን በእስራኤል የነበረ ሁነኛ ሊቀ ካህን ነበር።

  • አቤሴሎም ባመፀበት ጊዜ ሳዶቅ ዳዊትን ደግፎ ነበር፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያመጣ ዳዊትን የረዳው እርሱ ነበር።
  • ከዓመታት በኋላ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ እንዲሆን ሲቀባ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝቶ ነበር።
  • በነህምያ ዘመን የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲሠራ ሳዶቅ የተባሉ ሁለት ሰዎች ረድተው ነበር።
  • የንጉሥ ኢዮአታም አያት ስም ሳዶቅ ይባል ነበር።

ሴሎ

ሴሎ በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን አሸንፈው የያዟት በግንብ የተከበበች የከነዓናውያን ከተማ ነበረች

  • የሴሎ ከተማ የሚገኘው ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምዕራብና ከቤቴል ከተማ ሰሜን ምሥራቅ ነበር
  • ኢያሱ እስራኤልን እየመራ በነበረ ዘመን የሴሎ ከተማ የእስራኤላውያን መሰብሰቢያ ነበረች
  • ከምድረ ከነዓን ለእያንዳንዳቸው የሚሰጠውን ርስት ድርሻ ከኢያሱ ለመስማት አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች በሴሎ ተሰብስበው ነበር
  • በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ከመሠራቱ በፊት እስራኤላውይን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ ወደሴሎ ይመጡ ነበር
  • ሳሙኤል ሕፃን እያለ እርሱን ለጌታ ለመስጠት እናቱ ሐና ወደሴሎ ወስዳው ነበር። እግዚአብሔርን ስለማገልገል እየተማረ እዚያ ከካህኑ ከዔሊ ጋር ቆየ

ሴም

ሴም ከሦስቱ የኖኅ ወንዶች ልጆች አንዱ ሲሆን፣ ኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ የተለጸው የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜ ከአባቱ ጋር መርከቡ ውስጥ ገብቶ ነበር

  • ሴም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ የሆኑት የሴማውያን ነገድ አባት ነበር
  • የሴም ዕድሜ 600 ዓመት እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቧል

ሴት

ሴት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ ሦስተኛው የአዳምና የሔዋን ልጅ ነበር

  • ሴት በወንድሙ በቃየን በተገደለው በአቤል ምትክ የተሰጣት ልጅ መሆኑን ሔዋን ተናግራ ነበር
  • ሴት የኖኅና ከዚያ ወዲህ ላለው ማንኛውም ሰው ቀዳሚ አባት ነው
  • የሴት ዘሮች፣ “የእግዚአብሔርን ስም ለመጥራት” የመጀመሪያዎቹ ተብለዋል

ሴኬም

ሴኬም ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን 40 ማይል ርቀት ላይ የሚገኝ ከነዓን ውስጥ የነበረ ከተማ ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሴኬም ተብሎ የተጠራ ሰው ነበር።

  • ሴኬም ከወንድሙ ከኤሳው ጋር ከታረቀ በኋላ ያዕቆብ የሰፈረበት ቦታ ነበር
  • ያዕቆብ ከዔሞር ልጆች በሴኬም ርስት ገዛ፤ በኋላም የቤተሰቡ መቃብር ቦታ ሆነ፤ ያዕቆብን ልጆቹ የቀበሩት እዚያ ነበር

ሴዴቅያስ

ሴዴቅያስ የመጨረሻው የይሁዳ ንጉሥ ነው (597-587 ዓቅክ)።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሴዴቅያስ ተብለው የተጠሩ ብዙ ሰዎች ነበሩ።
  • ናቡከደነፆር አብዛኞቹን ንጉሣውያን ቤተ ሰቦች ወደ ባቢሎን ከወሰደ በኋላ ንጉሥ ሴደቅያስ ሥልጣን ሲይዝ ያሃ አንድ ዓመቱ ነበር።
  • ሴዴቅያስ ከኤርምያስና ከሕዝቅኤል ምክር ጠይቆ ነበር፤ ግን ጥሩ መሪ አልነበረም።
  • ኢየሩሳሌም ከተከበበች በኋላ ተይዞ የባቢሎንንጉሥ ፊት ቀረበ፤ ሁለት ልጆቹ እፊቱ ተገደሉ፤ የእርሱም ዓይኖች ታወሩ።

ስምዖን

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስምዖን የተባሉ ጥቂት ሰዎች ነበሩ

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ የያዕቆብ (እስራኤል) እና የልያ ሁለተኛ ልጅ ስምዖን ይባል ነበር። የእርሱ ዘሮች ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ሆኗል።
  • የስምዖን ነገድ የከነዓንን ደቡባዊ ጫፍ፣ ማለትም የይሁዳ ርስት ክፍል የነበረውን አካባቢ ይዞ ነበር
  • ማርያምና ዮሴፍ ሕፃን ኢየሱስን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ወደዚያ ባመጡት ጊዜ ስምዖን የሚባል ፃድቅ ሰው በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ነበር ስምዖን ኢየሱስን ባረከ፤ የሰዎች ሁሉ አዳኝ የሚሆነውን መሲሕ በመስጠቱም እግዚአብሔርን አመሰገነ

ሶርያ

ሶርያ ከእስራኤል ሰሜን ምሥራቅ የሚገኝ አገር ነው። አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን በሮም መንግሥት የሚተዳደር አገር ነው

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን ሶርያውያን ወታደራዊ ዐቅም የነበራቸ የእስራኤላውያን ጠላት ነበሩ
  • ሶርያውያን ንዕማን ነቢዩ ኤልሳዕ ከለምጹ የፈወሰው የሶርያ ወታደሮች አዛዥ ነበር
  • አብዛኞቹ የሶርያ ነዋሪዎች ከኖኅ ልጅ ከሴም የተወለደው የአራም ዘሮች ናቸው
  • የሶርያ ዋና ከተማ ደማስቆ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሳለች
  • ሳውል እዚያ የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ለመሄድ መንገድ ላይ ነበር፤ ኢየሱስ ያን ከማድረግ አስቆመው

ቀሬና

ቀሬና ከአፍሪካ ሰሜናዊ ባሕር ዳርቻ ሜዲትራንያን ባሕር ላይ ከቀርጤስ ደሴት ደቡብ ትገኝ የነበረች የግሪክ ከተማ ናት።

  • በአዲስ ኪዳን ዘመን አይሁዶችም ሁ ክርስቲያኖች በቀሬና ይኖሩ ነበር።
  • ቀሬና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይበልጥ የምትታወቀው ኢየሱስ መስቀሉን እንዲሸከም የረዳው ስምዖን የተባለው ሰው አገር በመሆንዋ ነው።

ቀርሜሎስ፣ የቀርሜሎስ ተራራ

“የቀርሜሎስ ተራራ” በሜዲትራንያን ባሕር አካባቢ ከሳሮን ሜዳማ ቦታ በስተ ሰሜን የነበረውን የተራራ ተረተር ያመለክታል። በጣም ትልቁ ጫፍ 546 ሜትር ከፍታ አለው።

  • ከጨው ባሕር ደቡብ በይሁዳ ምድር የሚገኝ “ቀርሜሎስ” የሚባል ከተማ ወይም መንደርም አለ።
  • ናባል የሚባለው ሀብታም ባለ ርስትና ሚስቱ አቢግያ ዳዊትና አብረውት የነበሩ የናባል በጎችን ይሸልቱ ለነበሩ ሰዎች ጠባቂ በነበሩበት ቀርሜሎስ በሚባለው መንደር ውስጥ ይኖሩ ነበር።
  • እውነተኛው አምላክ ያህዌ ብቻ መሆኑን ለማሳየት ኤልያስ ከባኣል ነቢያት ጋር ፉክክር የገጠመው ቀርሜሎስ ተራራ ላይ ነበር።
  • ይህ አንድ ተራራ ብቻ እንዳልነበረ ግልጽ ለማድረግ፣ “የቀርሜሎስ ተራራ” የሚለውን፣ “በቀርሜሎስ ተራሮች ተረተር ላይ የነበረ ተራራ” ወይም፣ “የቀርሜሎስ ተራራ ተረተር” በማለት መተርጎም ይቻላል።

ቀርጤስ፣ የቀርጤስ ሰው

ቀርጤስ ግሪክ ደቡባዊ ባሕር ዳርቻ ማዶ ትገኝ የነበረች ደሴት ናት። የቀርጤስ ሰው በቀርጤስ የሚኖር ሰው ነው።

  • በሐዋርያዊ ጕዞዎቹ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ቀርጤስ ደሴት ተጕዞ ነበር።
  • ክርስቲያኖችን እንዲያስተምርና እዚያ ለነበረችው ቤተ ክርስቲያን መሪዎችን በመሾም እንዲረዳ ጳውሎስ የሥራ ጓደኛው ቲቶን በቀርጤስ ትቶት ሄዶ ነበር።

ቀናተኛው ስምዖን

ቀናተኛው ስምዖን ከአሥራ ሁለት የኢየሱስ የቅርብ ደቀመዛሙርት አንዱ ነበር

  • ስለ ቀናተኛው ስምዖን የሚታወቀው በጣም ጥቂት ነው። በኢየሱስ ደቀመዛሙርት ዝርዝር ውስጥ ሦስቴ ተጠቅሷል
  • ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ በአንድነት ከተሰበሰቡት አሥራ አንድ ደቀመዛሙርት አንዱ ስምዖን ነበር
  • አንዳንድ ሰዎች፣ “ቀናተኛው” የሚለው የሚያመለክተው ስምዖን የሙሴን ሕግ በመጠበቅ ረገድ በጣም ቀናተኛ የነበሩና የሮም መንግሥትን አጥብቀው የሚቃወሙ፣ “ቀናተኞች” የሚባለው የአይሁድ ሃይማኖት ቡድን አባል ነበር በማለት ያስባሉ
  • ሌሎች ደግሞ፣ “ቀናተኛ” የሚለው የስምዖንን ሃይማኖታዊ ቅንዓት ለማመልከት ብቻ ነው ይላሉ

ቀያፋ

ቀያፋ መጥምቁ ዮሐንስና ኢየሱስ ባገለገሉበት ዘመን የእስራኤል ሊቀ ካህን ነበር።

  • ኢየሱስን በመመርመርና በኋላም እንዲገደል ፍርድ በማስተላለፍ ረገድ ቀያፋ ትልቅ ድርሻ ነበረው።
  • ሽባውን ሰው ከፈወሱት በኋላ በታሰሩ ጊዜ ሊቀ ካህናቶቹ ሐና እና ቀያፋ የጴጥሮስና የዮሐንስ ምርመራ ላይ ተገኝተው ነበር።
  • ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ለሕዝቡ ሁሉ ቢሞት ይሻላል በማለት የተናገረ ቀያፋ ነበር። ኢየሱስ ለሕዝቡ በእንዴት አይነት ሁኔታ እንዲሞት በትንቢት መልክ ይህን እንዲናገር ያደረገው እግዚአብሔር ነበር።

ቂሮስ

ቂቶስ በወታደራው ድል በ550 ዓ.ቅ.ክ. ገደማ የፋርስ መንግሥትን የመሠረተ ነበር። በዓለም ትሪክ ታላቁ ቂሮስ በመባልም ይታወቃል።

  • ንጉሥ ቂሮስ ባቢሎንን ድል አደረገ፤ ይህም በምርኮ እዚያ የነበሩ እስራኤላውያን ነጻ እንዲሆኑ አስቻለ።
  • ቂሮስ በጦርነት ድል አድርጎ ለያዛቸው ሕዝቦች ደግ በመሆንም ይታወቃል። ለአይሁድ ሕዝብ ደግ መሆኑ ከምርኮ በኋላ የኢየሩሳሌምን ቤተ መቅደስ እንደ ገና መሥራት ቻሉ።
  • ቂሮስ ሥልጣን ላይ የነበረው ዳንኤል፣ ዕዝራና ነህምያ በነበሩበት ዘመን ነበር።

ቃና

ቃና ናዝሬት በስተ ሰሜን ዘጠኝ ማይሎች ያህል ርቃ የምትገኝ ገሊላ አውራጃ ውስጥ ያለች መንደር ወይም ከተማ ነበረች።

  • ቃና ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት የነበረው የናትናኤል ትውልድ ቦታ ነበረች።
  • ኢየሱስ በቃና ሰርግ ላይ ተገኝቷል፤ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ በመለወጥ የመጀመሪያ ተአምሩን ያደረገው እዚያ ነበር።
  • ከዛ በኋላ አንድ ጊዜ ላይ ኢየሱስ ወደ ቃና ተመልሶ ሰመጣ ልጁን እንዲፈውስለት የጠየቀውን ከቅፍርናሆም የመጣ አንድ ሹም ጋር ተገናኘ።

ቃየን

ቃየንና ታናሽ ወንድሙ አቤል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የመጀመሪያ የአዳምና የሔዋን ልጆች ናቸው።

  • ቃየን የምግብ እህሎች የሚያመርት ገበሬ ሲሆን፣ አቤል ግን በጎች የሚጠብቅ እረኛ ነበር።
  • እግዚአብሔር የአቤልን መሥዋዕት ቢቀበልም፣ የቃየልን መሥዋዕት ግን ባለመቀበሉ በቅናት ተነሳሥቶ ቃየን ወንድሙ አቤልን ገደለው።
  • እርሱን ለመቅጣት እግዚአብሔር ቃየንን ከኤደን አባረረው ምድር በቂ እህል እንደማትሰጠውም ተናገረ።
  • እርሱ በምድር ላይ በሚንከራተትበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች እንዳይገድሉት እግዚአብሔር እንደሚጠብቀው ምልክት የሚሆን ግንባሩ ላይ አደረገ።

ቃዴስ

ቃዴስ ወይም ቀዴስ በርኔ በአሁኑ ጊዜ ሶርያ በሚባለው ውስጥ የምትገኝ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ጠቃሚ የሆነች ከተማ ነበረች።

  • ቃዴስ ዲን ምድረ በዳ መካከል ያለች ለም ቦታ ነበረች።
  • አብርሃም በጉዞው በቃዴስ በኩል አልፎ ነበር።
  • እስራኤል በምድረ በዳ ይጓዙ በነበረ ጊዜ በቃዴስ ሰፍረው ነበር።
  • ከዐለት ውሃ ማውጣትን በተመለከተ ባለመታዘዝ ሙሴ ወደ ተስፋው ምድር እንደማይገባ የተነገረው በቃዴስ እያለ ነበር።

ቃዴስ

ቃዴስ ወደ ምድር ከነዓን በገቡ ጊዜ እስራኤላውያን የወሰዷት ከነዓናዊ ከተማ ነበረች።

  • ቃዴስ ትገኝ የነበረው ከእስራኤል ክፍል ሰሜናዊ ክፍል ሲሆን. ለንፍታሌም ነገድ ተሰጥታ ነበር።
  • ቃዴስ መጠጊያ ከተማ የተለየች ነበረች፣ ሌዋውያን ካህናት ይኖሩበት ከነበሩ ከተሞችም አንዷ ነበረች።

ቄሳር

“ቄሳር” የተሰኘው ቃል ብዙዎቹ የሮም ገዦች የሚጠቀሙበት ስም ወይም መጠሪያ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ መጠሪያ ሦስት ገዦችን ያመለክታል።

  • ቄሳር ተብሎ የተጠራ የመጀመሪያ ሮማዊ መሪ ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን ሲገዛ የነበረው፣ “አውጉስጦስ ቄሳር” ነው።
  • ከሰላሳ ዓመት በኋላ ዮሐንስ እየሰበከ በነበረበት ዘመን የሮም መንግሥትን ይገዛ የነበረው ጤባርዮስ ቄሳር ነበር።
  • የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መስጠት እንደሚገባ ኢየሱስ ለሕዝቡ በተናገረ ጊዜ ጤባርዮስ ቄሳር ሮምን እየገዛ ነበር።
  • ጳውሎስ ቄሳር ፊት ቀርቦ እንደ ነበር ሲናገር የሚያመለክተው ኔሮ የተባለውን ሮማዊ ንጉሥ ሲሆን፣ እርሱም፣ “ቄሳር” በተሰኘው መጠሪያ ነበር የሚታወቀው።
  • “ቄሳር” የተሰኘው ቃል እንደ መጠሪያ ብቻውን ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “ንጉሥ” ወይም፣ “ሮማዊ ገዢ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • አውጉስጦስ ቄሳር ወይም ጤባርዮስ ቄሳር በተሰኙት ስሞች “ቄሳር” የሚለው ቃል ለአገሬው ሕዝብ ቋንቋ በሚቀራረብ ቋንቋ መነገር ይችላል።

ቄሳርያ፣ ፊልጶስ ቂሳርያ

ቂሳርያ ሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ፣ ከቀርሜሎስ ተራራ 39 ኪ.ሜ. ርቃ ትገኝ የነበረች በጣም ጠቃሚ ከተማ ነበረች። ፊልጶስ ቂሳርያ ከእስራኤል ሰሜን ምሥራቃዊ ክፍል አርሞንዔም ተራራ አጠገብ ያለች ከተማ ነበረች።

  • እነዚህ ከተሞች የሮም መንግሥትን ይገዙ ለነበሩ ቄሳሮች የተሰየሙት።
  • ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን አካባቢ ባሕር ዳርቻ የነበረው ቂሳርያ የይሁዳ የሮም አውራጃ ከተማ ሆነች።
  • ሐዋርያው ጴጥሮስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአሕዛብ የሰበከው በቂሳርያ ነበር።
  • ጳውሎስ ከቂሳርያ በመርከብ ወደ ጤርሴስ ሄደ፤ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ተልዕኮው በዚህች ከተማ ሁለት ጊዜ አልፏል።
  • ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በፊልጶስ ቂሳርያ ዙሪያ ወደ ነበሩ ከተሞች ተጉዘው ነበር።

ቄዳር

ቄዳር የእስማኤል ሁለተኛ ልጅ ሲሆን፣ ከእርሱ ዘሮች ብዙ ሕዝብ ያለው ነበር። ቄዳር የምትባል ታውቂ ከተማም አለች።

  • የቄዳር ከተማ የምትገኘው በአረቢያ ሰሜናዊ ክፍል ከፓለስቲና ደቡባዊ ድንበር በኩል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በትልቅነቷና በውበቷ ትታወቅ ነበር።
  • “ጥቋቁሮቹ የቄዳር ድንኳኖች” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የቄዳር ሕዝብ ይኖሩበት የነበረውን ከጥቋቁር የፍየል ቆዳ የተሠራውን ድንኳናቸውን ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “የቄዳር ክብር” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የዚያችን ከተማ ሕዝብ ታላቅነት ነው።

ቅፍርናሆም

ቅፍርናሆም ከገሊላ ባሕር ዳርቻ ሰሜን ምዕራብ የምትገኝ ዓሣ የሚጠመድባት ቦታ ናት።

  • ገሊላ ውስጥበሚያስተምርበት ጊዜ ኢየሱስ ይኖር የነበረው በቅፍርናሆም ነበር።
  • ከደቀ መዛሙርቱ ጥቂቶቹ ከቅፍርናሆም የመጡ ነበር።
  • የሞተችውን ልጅ ማስነሣትን ጨምሮ ኢየሱስ በዚህች ከተማ ብዙ ተአምራት አድርጎ ነበር።
  • ሕዝቦቿ እርሱን ችላ በማለታቸውና መልእክቱንም ባለማመናቸው ኢየሱስ ከገሰጻቸው ሦስት ከተሞች አንኳ ቅፍርናሆም ናት። ባለ ማመናቸው ምክንያት እግዚአብሔር እንደሚቀጣቸው አስጠንቅቋቸው ነበር።

ቆላስይስ፣ የቆላስይስ ሰዎች

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ቆላስይስ ፍርግያ በምትባለው የሮማውያን ግዛት ውስጥ የነበረች ከተማ ስትሆን በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው ከቱርክ ደቡብ ምዕራብ ባለው አካባቢ ነው። የቆላስይስ ሰዎች ቆላስይስ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

  • ከሜዲትራንያን ባሕር 100 ማይሎች ርቃ ትገኝ የነበረችው ቆላስይስ በኤፌሶን ከተማና በኤፍራጥስ ወንዝ መካከል ጠቃሚ የንግድ መላለፊያ ነበረች።
  • በሮም እስር ቤት በነበረ ጊዜ በመካከላቸው የነበረውን የሐሰት ትምህርት እንዲያስተካክሉ ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች መልእክት ጽፎላቸው ነበር።
  • ይህን መልእክት በጻፈበት ጊዜ ጳውሎስ በቆላስይስ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን አልጎበኘም ነበር፣ እዚያ ስለ ነበሩት አማኞች የሰማው የሥራ ባልደረባው ከነበረው ከኤጳፍራ ነበር።
  • ኤጳፍራ የቆላስይስን ቤተ ክርስቲያን የመሠረተ ክርስቲያን አገልጋይ ሳይሆን አይቀርም።
  • የፊልሞን መልእክት ጳውሎስ ለቆላስይስ ለነበረ ባሪያ አሳዳሪ የጻፈው ነበር።

ቆሬ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ቆሬ በትንሹ የሁለት ሰዎች ስም ነው።

  • ከኤሳው ልጆች አንዱ ቆሬ ይባል ነበር። እርሱም ይኖርበት ለነበረው ማኅበረ ሰብ መሪ ይሆናል።
  • ሌላው ቆሬ የሌዊ ዘር ሲሆን፣ ካህን ሆኖ መገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሏል። እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን በሰጠው ስፍራና ሥልጣን ቅናት አድሮበት ነበር።
  • የእስራኤላን ሕዝብ እግዚአብሔር በሰጣቸው መሪዎች ላይ ለማሳመፅ ከድታንና ከአቤሮን ጋር ሲያሤር ነበር።

ቆርኔሌዎስ

ቆርኔሌዎስ በትውልድ አይሁድ ያልሆነ የሮም ወታደሮች ባለ ሥልጣን ነበር።

  • ዘወትር ለእግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፤ ለድኾች ምጽዋት የሚሰጥ ደግ ሰው ነበር።
  • ቆርኔሎዎስና ቤተ ሰቡ ሐዋርያው ጴጥሮስ የሚያስተምረውን ወንጌል ሰምተው በኢየሱስ አመኑ።
  • የቆርኔሌዎስ ቤተ ሰቦች አይሁድ ያልነበሩ የመጀመሪያዎቹ አማኞች ነበሩ።
  • ይህም ኢየሱስ እርሱ የመጣው አረማውያንን ጨምሮ ሰዎችን ሁሉ ለማዳን መሆኑን ለኢየሱስ ተከታዮች ግልጽ አደረገላቸው።

ቆሮንቶስ፣ የቆሮንቶስ ሰዎች

ቆሮንቶስ ከአቴና በስተ ምዕራብ 50 ማይል ርቃ የምትገኝ የግሪክ ከተማ ነበረች። የቆሮንቶስ ሰዎች በቆሮንቶስ የሚኖሩ ሕዝብ ናቸው።

  • ቆሮንቶስ ከጥንት ቤተ ክርስቲያኖች አንዱ የነበረት ቦታ ነው።
  • 1ቆሮንቶስና 2ቆርንቶስ ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ ይኖሩ ለነበሩ ክርስቲያኖች የጻፋቸው መልክቶች ናቸው
  • በመጀመሪያው ሐዋርያዊ ጉዞው ጳውሎስ 18 ወሮች ያህል በቆሮንቶስ ኖሮ ነበር።
  • ጳውሎስ አቂላና ጵርስቅላ የተባሉትን አማኞች ያገኛቸው በቆሮንቶስ ነበር።
  • ከቆሮንቶስ ጋር የተያያዙ ሌሎች የጥንት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጥቂቶቹ ጢሞቴዎስ፣ ቲቶ፣ አጵሎስና ሲላስ ናቸው።

ቆጵሮስ

ቆጵሮስ ከዘመኑ ቱርክ በስተ ደቡብ 64 ኪሎ ሜትር ላይ ትገኝ የነበረች ሜዲትራንያን ባሕር ላይ ያለች ደሴት ናት።

  • በርናባስ የቆጵሮስ ሰው ነበር፤ የእኅቱ ልጅ ዮሐንስ ማርቆስም ከዚያው የመጣ ሊሆን ይችላል።
  • በመጀመሪያው ሐዋርያው ጉዞአቸው ጅማሬ ላይ ጳውሎስና በርናባስ በቆጵሮስ ደሴት ሰብከው ነበር። በዚያ ጉዞ እነርሱን ለመርዳት ዮሐንስ ማርቆስ ወደ እነርሱ መጣ።
  • በኋላ ላይ በርናባስና ማርቆስ እንደ ገና ወደ ቆጵሮስ መጥተው ነበር።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ቆጵሮስ የቆጵሮስ ዛፍ በብዛት ይገኝበት የነበረ ቦታ መሆኑ ተጠቅሷል።

በለዓም

በለዓም ወደ ከነዓን ምድር ለመግባት በሰሜናዊ ሞዓብ ሰፍረው በነበረ ጊዜ እስራኤልን እንዲረግም ንጉሥ ባላቅ ቀጥሮት የነበር አረማዊ ነብይ ነበር።

  • በለዓም የመጣው ከፋቱራ ከተማ ሲሆን የሚገኘው በኤፍራጥስ ወንዝ ዙሪያ ባልው አካባቢ ነበር፤ ከሞዓብ ምድር 400 ማይሎች ርቀት ላይ ይገኝ ነበር
  • ሜዶናዊው ንጉሥ ባላቅ ከእስራኤል ሕዝብ ብዛትና ጥንካሬ የተነሣ ፍርሃት አድሮበት ነበር፤ ስለዚህም እነርሱን እንዲረግምለት በለዓምን ቀጠረው
  • በለዓም እስራኤልን ወደነበሩበት አካባቢ በመሄድ ላይ እያለ፥ መንገዱ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ቆሞ ስለነበር አህያው ወደፊት መሄድ አልቻለችም። እግዚአብሔር ለአህያዋ ለበለዓም የመናገር ችሎታ ሰጣት
  • በለዓም እስራኤልን እንዲረግም እግዚአብሔር አልፈቀደም፤ ይልቁንም እርሱን እንዲባርክ አዘዘው
  • ይሁን እንጂ፥ በኋላ ላይ በኣል ፌጎርን እንዲያመልኩ በማድረግ እስራኤል ላይ ክፉ ነገር አምጥቷል

በርባን

በርባን ኢየሱስ በተያዘ ጊዜ ኢየሩሳሌም ውስጥ የነበር እስረኛ ነበር

  • በርባን ግድያንና በሮም መንግሥት ላይ የማመፅን ወንጀል የፈጸመ ሰው ነበር
  • ጴንጤናዊው ጲላጦስ በርባንን ወይም ኢየሱስን እንዲፈታላቸው ይፈልጉ እንደሆን ለሕዝቡ ምርጫ ሲያቀርብ ሕዝቡ በርባንን እንዲፈታላቸው ጠየቁ
  • ስለዚህ ጲላጦስ በርባንን እንዲፈታ፥ ኢየሱስ ግን እንዲገደል አዘዘ

በርቶሎሜዎስ

በርተሎሜዎስ ከአስራ ሁለት የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር

  • ከሌሎቹ ሐዋርያት ጋር በአንድነት በርተሎሜዎስ ወንጌልን እንዲሰብክና በኢየሱስ ስም ተአምራት እንዲያደርግ ተልኮ ነበር
  • ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲመለስ ከተመለከቱ አንዱ እርሱ ነበር
  • ከዚህ ጥቂት ሳምንቶች በኋላ በበዓለ ሃምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ እነርሱ ላይ በወረደ ጊዜ በኢየሩሳሌም ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ነበር

በርናባስ

በርናባስ በሐዋርያት ዘመን የነበረ ከጥንት ክርስቲያኖች አንዱ ነበር

  • በርናባስ ከሌዊ ነገድ የተገኘ እስራኤላዊ ሲሆን፥ የመጣው ከቆጵሮስ ደሴት ነበር
  • ሳውል(ጳውሎስ) ክርስቲያን በሆን ጊዜ እንደአንድ አማኝ እንዲቀበሉት ሌሎች አማኞችን ያግባባ በርናባስ ነበር
  • በርናባስና ሳውል በተለያዩ ከተማዎች የኢየሱስን ወንጌል ለመስበክ አብረው ተጉዘው ነበር
  • ስሙ፥ ዮሴፍ ነበር በኋላ ግን፥ “በርናባስ” ተብሎአል፤ “በርናባስ”፥ “የመፅናናት ልጅ” ማለት ነው

በናያስ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ መናያስ በሚል ስም የሚታወቁ ጥቂት ሰዎች ነበሩ

  • በናያስ የዮዳሄ ልጅ ሲሆን፥ ከዳዊት ኅያላን ሰዎች አንዱ ነበር። በጦር ችሎታው የታወቀ ስለነበረ የዳዊት ክብር ዘብ ወይም ዘብ ጠባቂ ሆኖ ነበር
  • ሰሎሞን በነገሠ ጊዜ በናያስ ጠላቶቹን በማጥፋት ረድቶት ነበር። በኋላ ላይ የእስራኤል ሰራዊት አዛዥ ሆኖ ነበር
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ በናያስ ተብለው የተጠሩ ሦስት ሌዋውያን፥ አንድ ካህን፥ ሙዚቀኛና የአሳፍ ልጅ አሉ

በኣል

“በኣል” ፦ “ጌታ” ወይም፥ “አለቃ” ማለት ሲሆን፥ ከነዓናውያን ከሚያመልኳቸው ዋነኞቹ ጣዖቶች የአንዱ ስም ነበር።

  • ከስማቸው ጋር፥ “በኣል” የሚል ስም የተያያዘ ሌሎች የአካባቢው ጣዖቶችም ነበሩ፤ ለምሳሌ “በኣል ጲኦር” አንዳንዴ እነዚህ ጣዖቶች ሁሉ በአንድነት፥ “በኣሎች” ተብለው ይጠሩ ነበር።
  • አንዳንድ ሰዎች፥ “በኣል” የሚል ቃል የተጨመረበት ስም ነበራቸው
  • የበኣል አምልኮ ሕፃናትን መሥዋዕት ማቅረብንና በአመንዝራዎች መጠቀምን የመሳሰሉ መጥፎ ተግባሮችን ይጨምራል
  • በታሪካቸው ውስጥ በአንዳንድ ወቅቶች በዙሪያቸው የነበሩ አረማውያን ሕዝቦችን ምሳሌ በመከተል እስራኤላውያንም በከፍተኛ ደረጃ በኣልን አምልከው ነበር
  • በንጉሥ አክዓብ ዘመን በኣል ሐሰት እንደሆነና እውነተኛው አምላክ ያህዌ ብቻ መሆኑን ለሕዝቡ ለማሳየት የእግዚአብሔር ነብዩ ኤልያስ አንድ ፈተና አቅርቦ ነበር፥ ከዚህም የተነሣ የበኣል ነብያት በሞት ተቀጡ፤ ሕዝቡም እንደገና ያህዌን ማምለክ ጀመሩ።

ቢታንያ

ቢታንያ ከኢየሩሳሌም ምሥራቅ 2ማይል ርቀት ላይ ከደብረ ዘይት ተራራ ምሥራቅ ባለው ተዳፋት ግርጌ የምትገኝ ከተማ ነበረች

  • ቢታንያ በኢየሩሳሌምና በኢያሪኮ መካከል በሚያልፈው መንገድ አጠገብ ነበረች
  • ኢየሱስ ወዳጆቹ አልዓዛር፥ ማርታና ማርያም ወደነበሩበት ቢታንያ ብዙ ጊዜ ይመጣ ነበር
  • ቢታንያ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት ያስነሣበት ከተማ በመሆን ትታወቃለች

ባሕሩ፣ ታላቁ ባሕር፣ የምዕራብ ባሕር

መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ታላቁ ባሕር” ወይም፣ “የምዕራብ ባሕር” የሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከሚያውቁት ባሕር ትልቁ የነበረው፣ ሜዲትራንያን ባሕርን ነው።

  • ታላቁ ባሕር (ሜዲትራንያን) ከእስራኤል፣ በሰሜንና በምዕራብ ከአውሮፓ፣ እና በሰሜን ከአፍሪካ ጋር ይዋሰናል።
  • ብዙ አገሮችን የሚያካልል በመሆኑ በጥንት ዘመን ይህ ባሕር ለንግድና ለጉዞ በጣም ጠቃሚ ነበር። ከሌሎች አገሮች ጋር በመርከብ በቀላሉ የንግድ ልውውጥ ማድረግ በመቻላቸው በዚህ ባሕር ዳርቻ የነበሩ ከተሞችና ሰዎች በጣም ሀብታም ነበር።
  • ታላቁ ባሕር የሚገኘው ከእስራኤል በስተ ምዕራብ በመሆኑ፣ “የምዕራብ ባሕር” ተብሏል።

ባሮክ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ባሮክ በመባል የሚታወቁ የተለያዩ ሰዎች አሉ

  • አንደኛው ባሮክ የኢየሩሳሌምን ቅጥር በመጠገን ከነህምያ ጋር አብሮ ይሠራ የነበረው የዘባይ ልጅ ባሮክ ነው
  • ከዚህም በላይ በነህምያ ዘመን ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ በኢየሩሳሌም መኖር ከጀመሩ መሪዎች አንዱ የነበረው የከልሐዜ ልጅ ባሮክ ነበር
  • ለየት ያለው የኔር ልጅ በሮክ የነብዩ ኤርምያስ ረዳት የነበረው ባሮክ ሲሆን፥ እግዚአብሔር ለነብዩ ኤርምያስ የሰጠውን መልዕክት በመጻፍና ያንን ለሕዝቡ ማንበብ በመሳሰሉ የተለያዩ ሥራዎች ኤርምያስን ረድቶታል

ባሳን

ባሳን ከገሊላ ባሕር በስተምስራቅ አካባቢ ያለ ቦታ ነው። በአሁኑ ዘመን የሶርያ አካል የሆነውን አካባቢና የጎላን ኮረብታን ይሸፍናል

  • በብሉይ ኪዳን የነበረው፥ “ጎላን” የሚባለው መጠለያ(መማፀኛ) ከተማ የሚገኘው በባሳን አካባቢ ነበር
  • ባሳን በዋርካ ዛፎችና በግጦሽ ሜዳዎቹ የሚታወቅ በጣም ለም አካባቢ ነበር
  • ባሳን በአንዳንድ ነገሥታትና በሕዝቦቻቸው መካከል ውጊያ ተደርጎ የነበረበት ቦታ እንደነበር ዘፍጥረት 14 ላይ ተጠቅሷል
  • ከግብፅ ከወጡ በኋላ እስራኤል በበረሃ ይንከራተቱ በነበረ ጊዜ እስራኤላውያን የተወሰነውን የባሳን አካባቢ ይዘው ነበር
  • ከዓመታት በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ከዚያ አካባቢ የሚያስፈልገውን ነገር ያገኝ ነበር

ባቢሎን፥ ባቢሎናዊ

የባቢሎን ከተማ የጥንት ባቢሎንያ አካባቢ ዋና ከተማ ሲሆን፥ የባቢሎን መንግሥት ግዛት አካልም ነበር

  • ባቢሎን ትገኝ የነበረው ኤፍራጥስ ወንዝ አካባቢ ነበር፤ ከመቶ ዓመታት በፊት የባቢሎን ግንብ ተሠርቶ የነበረውም በዚሁ አካባቢ ነበር
  • አንዳንዴ፥ “ባቢሎን” የተሰኘው ቃል የባብሎንን መንግሥት በሙሉ ያመለክታል። ለምሳሌ፥ “ የባቢሎን ንጉሥ” ያቺን ከተማ ብቻ ሳይሆን፥ በዚያ የነበረውን አካባቢ ሁሉ ይገዛ ነበር
  • ባቢሎናውያን ኅያል ሕዝብ በመሆናቸው የይሁዳን መንግሥት አጥቅተው ነበር። ለ70 ዓመት ያህል ሕዝቡን በምርኮ ወደባቢሎን ወስደው ነበር
  • የዚህ አካባቢ የተወሰነው ክፍል፥ “ከለድ” ሲባል፥ እዚያ የነበሩ ሕዝቦች “ከለዳውያን” ይባሉ ነበር። በዚህም ምክንያት፥ “ከለድ” የሚለው ቃል ባቢሎንን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ፥ “ባቢሎን” የተሰኘው ቃል ከጣዖት አምልኮና ኃጢአተኛ ተግባሮች ጋር የሚያያዙ ቦታዎችን፥ ሕዝቦችንና የአስተሳሰብ ዘይቤዎችን ለማመልከት ተለዋጭ ዘይቤ በመሆን ጥቅም ላይ ውሏል
  • “ታላቂቱ ባቢሎን” ወይም፥ “ታላቂቱ የባቢሎን ከተማ” የተሰኘው ሐረግ፥ ምሳሌያዊ ሲሆን መልኩ ልክ ጥንታዊቷ ባቢሎን እንደነበረችው በጣም ሰፊ ሀብታምና ኃጢአተኛ የሆን ከተማ ወይም ሕዝብን ያመለክታል።

ባቤል

ባቤል ከመሰጵጦምያ በስተደቡብ በነበረችው ሰናዖር በምትባል አካባቢ ዋነኛ ከተማ ነበረች በኋላ ላይ ሰናዖር ባቢሎን ተብላለች

  • የባቢሎን ከተማ የተመሠረተችው የሰናዖር አካባቢን ከገዛው የካም የልጅ ልጅ በነበረው በናምሩድ ነበር
  • የሰናዖር ሕዝብ በጣም ትዕቢተኞች ከመሆናቸው የተነሳ ወደሰማይ የሚደርስ ግንብ መሥራት ሞከሩ። በኋላ ላይ ይህ፥ “የባቢሎን ግንብ” በመባል የሚታወቅ ሆነ
  • ግንቡን እየሰሩ የነበሩ ሰዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ባለመበተናቸው እርስ በርስ መግባባት እንዳይችሉ ቋንቋቸውን ደበላለቀው። ይህም ከዚያ ተነስተው በተለያዩ የምድር አካባቢዎች እንዲኖሩ አደረጋቸው።
  • “ባቤል” የተሰኘው ቃል ትርጉም ሥረ-መሠረት፥ “ግራ መጋባት” ማለት ሲሆን እንዲህ የተባለው እግዚአብሔር የሕዝቡን ቋንቋ ስለደበላለቀው ነው።

ባቱኤል

ባቱኤል የአብርሃም ወንድም የናኮር ልጅ ነበር

  • ባቱኤል የርብቃና የወንድሟ የላባ አባት ነበር
  • ባቱኤል የሚባል ከተማም አለ፤ ምናልባትም ከቤርሳቤህ ብዙ ሳይርቅ ደቡባዊ ይሁዳ ውስጥ ሳይሆን አይቀርም።

ባኦስ

ባኦስ እስራኤል ሐሰተኛ አማልክትን እንዲያመልኩ ካደረጉ የእስራኤል ነገሥታት አንዱ ነበር

  • ባኦስ ሦስተኛው የእስራኤል ንጉሥ ሲሆን፥ አሳ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን ሃያ አራት ዓመት ገዝቷል
  • ባኦስ ከእርሱ በፊት ንጉሥ የነበረውን ናዳብን በማግለል የነገሠ የጦር መሪ ነበር
  • በባኦስ ንግሥና ዘመን በእስራኤልና በይሁዳ መንግሥት መካከል በተለይም ከይሁዳ ንጉሥ ከአሳ ጋር ብዙ ጦርነቶች ተደርገዋል
  • ባኦስ ከፈጸማቸው ብዙ ኃጢአቶች የተነሣ የኋላ ኋላ እግዚአብሔር በሞት ከሥልጣኑ አስወገደው

ቤርሳቤህ

ቤርሳቤህ በዳዊት ሰራዊት ውስጥ ወታደር የነበርው የኦርዮን ሚስት ነበረች። ኦርዮን ከተገደለ በኋላ የዳዊት ሚስትና የሰሎሞን እናት ሆናለች

  • የኦርዮን ሚስት እያለች ዳዊት ከእርስዋ ጋር አመንዝሮ ነበር
  • ቤርሳቤህ ከዳዊት በፀነሰች ጊዜ ዳዊት ኦርዮን በጦርነት እንዲገደል አደረገ
  • ከዚያም ዳዊት ቤርሳቤህን አገባትና ልጃቸውን ወለደች
  • ከተወለደ ጥቂት ቀናት በኋላ ልጁ እንዲሞት በማድረግ እግዚአብሔር ዳዊትን በኃጢአቱ ቀጣው
  • እንደገና ቤርሳቤህ ሰሎሞን የተባለ ልጅ ወለደች፥ እርሱም አድጎ ከዳዊት በኋላ ንጉስ ሆነ

ቤርሳቤህ (ቤርሼባ)

ብሉይ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ቤርሳቤህ አሁን ኔጌቭ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለው በረሐ ውስጥ ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ 45 ማይሎች ላይ የምትገኝ ከተማ ነበረች

  • በቤርሳቤህ ዙሪያ ያለው በረሐ አብርሃም ከድንኳኑ ከሸኛቸው በኋላ አጋርና እስማኤል ይተንከራተቱበት ጠፍ ቦታ ነበር
  • የዚህች ከተማ ስም፥ “የመሐላ ጉድጓድ” ማለት ነው። ይህን ስም የሰጣት የአቤሜሌክ ሰዎች ከአብርሃም ጉድጓዶች አንዱን በመቆጣጠራቸው እነርሱን እንደማይቀጣ አብርሃም መሐላ አድርጎ ስለነበር ነው

ቤርያ

አዲስ ኪዳን ውስጥ ቤርያ ከመቄዶንያ ደቡብ ምስራቅ ከተሰሎንቄ በስተደቡብ 80 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ በጣም ሀብታም የግሪክ ከተማ ነበርች።

  • በተሰሎንቄ ከአይሁድ ከደረሰባቸው ችግር እንዲያመልጡ አንዳንድ ክርስቲያን ወገኖች ከረዱአቸው በኋላ ጳውሎስና ሲላስ የሄዱት ወደ ቤርያ ነበር
  • በቤርይ የነበሩ ሰዎች ጳውሎስን ወንጌል ሲሰብክ ሲሰሙ እርሱ ይናገር የነበረው እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ቅዱሳት መጻሕፍትን መረመሩ

ቤተልሔም ኤፍራታ

ቤተልሔም ኢየሩሳሌም ከተማ አጠገብ የምትገኝ አንዲት ትንሽ የእስራኤል ከተማ ነበረች። “ኤፍራታ” በመባልም ትታወቃለች፤ ምናልባት የመጀመሪያ ስሟ ይህ ሳይሆን አይቀርም

  • ንጉሥ ዳዊት የተወለደው እዚያ ስለነበር፥ ቤተልሔም፥ “የዳዊት ከተማ” ተብላለች
  • መሲሁ ከ “ቤተልሔም ኤፍራታ” እንደሚመጣ ነብዩ ሚክያስ ተናግሮ ነበር
  • በዚያ ትንቢት ፍጻሜ ከብዙ ዓመቶች በኋላ ኢየሱስ በቤተልሔም ተወለደ
  • ቤተልሔም፥ “የእንጀራ ቤት” ወይም፥ “የምግብ ቤት” ማለት ነው

ቤቴል

ቤቴል ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን ከነዓን ምድር ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነበረች። የቀድሞ ስሟ “ሎዛ” ነበር

  • የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ከተቀበለ በኋላ አብራም (አብርሃም) ቤቴል አጠገብ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ። በዚያ ጊዜ የከተማዋ ትክክለኛ መጠሪያ ስም ገና ቤቴል አልተባለም ነበር፤ ይሁን እንጂ፥ ብዙ ጊዜ በጣም በምትታወቅበት፥ “ቤቴል” በሚል ስም ትጠራለች
  • ከወንድሙ ከኤሳው በሸሸ ጊዜ ያዕቆብ በዚህች ከተማ አጠገብ አንድ ሌሊት ከቤት ውጭ መሬት ላይ ተኝቶ አሳልፏል። ተኝቶ እያለ መላእክት የሚወጡበትና የሚወርዱበት ወደሰማይ የሚደርስ መሰላል በሕልሙ አየ
  • ያዕቆብ በዚያ ስም እስከጠራት ጊዜ ድረስ ይህች ከተማ፥ “ቤቴል” የሚባል ስም አልነበራትም። ስለአብርሃም የሚናገሩ ምንባቦች ውስጥ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ ያዕቆብ እዚያ የደረሰበትን ጊዜ(ስሙ ከመለወጡ በፊት) ግልጽ ለማድረግ አንዳንድ ትርጉሞች “ሎዛ በኋላ ቤቴል የተባለችው)” በማለት ተርጉመውታል

ቤትሳሚስ

ቤትሳሚስ ከኢየሩሳሌም በስተምዕራብ በግምት 30ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከነዓናዊት ከተማ ስም ነው

  • እስራኤላውያን ቤትሳሚስን የያዙት በኢያሱ መሪነት ዘመን ነበር
  • ቤትሳሚስ ሌዋውያን ካህናት እንዲኖሩባት የተሰጠች ከተማ ነበርች
  • ፍልስጥኤማውያን የማረኩትን የቃል ኪዳን ታቦት እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም በወሰዱ ጊዜ ቤትሳሚስ ታቦቱን ያሳረፉበት የመጀመሪያ ከተማ ነበረች

ብንያም

ብንያም ከያዕቆብና ከሚስቱ ከራሔል የተወለደ የመጨረሻው ልጅ ነው። የስሙ ትርጉም ፥ “የቀኝ እጄ ልጅ” ማለት ነው።

  • ከራሔል የተወለዱ እርሱና ታላቅ ወንድሙ ዮሴፍ ብቻ ናቸው። ራሔል ብንያምን ከወለደች በኋላ ሞታለች
  • የብንያም ዘሮች ከአስራሁለት የእስራኤል ነገዶች አንዱ ሆነዋል
  • ንጉሥ ሳኦል ከእስራኤላዊው የብንያም ነገድ የተገኘ ነበር
  • ሐዋርያው ጳውሎስም ከብንያም ነገድ ነበር

ብዔልዜቡል

ብዔልዜቡል የአጋንንት አለቃ ሲሆን፥ የሰይጣን ወይም የድያብሎስ ሌላ ስም ነው

  • አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ብዔልዜቡልን ቡዓልዜቡብ ይሉታል
  • ቃል በቃል “የዝንቦች አምላክ” ማለት ሲሆን፥ “የአጋንንት አለቃ” የሚል ትርጉም አለው
  • ይህ ቃል ስም እንደመሆኑ መጠን፥ እንደስም መተርጎም አለበት
  • ስለማን እየተናገር እንደሆነ ግልጽ ለማድረግ፥ “ብዔልዜቡል ድያብሎስ” በማለት መተርጎም ይቻላል

ቦዔዝ

በዔዝ የሩት ባል፣ የንጉሥ ዳዊት አያትና ኢየሱስ የተገኘበት ዘር ዋና ግንድ የነበረ እስራኤላዊ ነበር።

  • ቦዔዝ የነበረው መሳፍንት እስራኤልን ይገዙ በነበረበት ዘመን ነው።
  • ባልዋና ልጆቿ በሞዓብ ከሞቱ በኋላ ወደ እስራኤል የተመለሰቸው ኑኃሚን የተባለች እስራኤላዊት ሴት የሥጋ ዘመድ ነበር።
  • ቦዔዝ እርሷን በማግባትና ከእርሷ ልጆች በመውለድ ሩት የተባለችውን የኑኃሚን አማት “ዋጀ”።
  • ክርስቶስ እኛን ከኃጢአት የመዋጀትኑና የማዳኑ ምሳሌ ተደርጎ ይወሰዳል።

ተርሴስ

ተርሴስ የኖኅ ልጅ የያፌት ልጅ ልጅ ስም ነው

  • ነቢዩ ዮናስ ወደ ተርሴስ እየተጓዘ በነበረ መርከብ በመሳፈር እግዚአብሔር ካዘዘው ተግባር ማምለጥ ሞከረ
  • ተርሴስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ የወደብ ከተማ ነበር፤ ትክክለኛ ቦታው የት እንደሆነ ግን አይታወቅም። አንዳንዶች ካርቴጅን ወይም ከእስራኤል ርቀው ያል የፊንቃውያን ከተማን እንደሚያመለክት ያስባሉ
  • ንጉሥ ሰሎሞን በጣም ሀብታም ከነበረችው ተርሴስ ጋር የንግድ ልውውጥ ያደርግ ነበር
  • ወደ ነነዌ እንዲሄድ እግዚአብሔር ዮናስን ሲያዝዘው እርሱ ወደ ተርሴስ እያመራች የነበረች መርከብ ተሳፍሮ ወደ ኢዮጴ ሄደ

ተሰሎንቄ፣ የተሰሎንቄ ሰዎች

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ተሰሎንቄ በጥንቱ የሮም ግዛት ውስጥ የነበረችው የመቄዶንያ ዋና ከተማ ነበረች። በዚያ ከተማ የነበሩ፣ “የተሰሎንቄ ሰዎች” ይባላሉ።

  • የተሰሎንቄ ከተማ በጣም ጠቃሚ ወደብ ነበረች፤ ሮምን ከተቀረው የሮም መንግሥት ጋር በሚያያዘው አውራ መንገድ ላይ ትገኝ ነበር።
  • በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ጳውሎስ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ ጋር ወደ ተሰሎንቄ መጥተው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ በዚያ በጣም እየሰፋች የነበረች ቤተ ክርስቲያን ተመሥርታ ነበር። በኋላም በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ጳውሎስ ይህችን ከተማ ጎብኝቷል።
  • ጳውሎስ በተሰሎንቄ ለነበሩ ክርስቲያኖች መልእክቶች ጽፏል። የ1ኛና የ2ኛ ተሰሎንቄ መልእክቶች አዲስ ኪዳን ውስጥ ተካትተዋል።

ቲርዛ

ቲርዛ በጣም ጠቃሚ የከነዓናውያን ከተማ ነበረች፤ በኋላም የሰሜናዊው የእስራእል መንግሥት ጊዜያዊ ዋና ከተሞች አንዷ ሆና ነበር።

  • የቲርዛ ከተማ የምናሴ ነገድ በያዘው ክልል ውስጥ ነበር የምትገኘው። ከሴኬም ከተማ 10 ማይሎች ርቀት ላይ እንደ ነበረች ይታሰባል።
  • ቲርዛ ርስት እንዲሰጣችአው ከጠየቁ የምናሴ ሴቶች ልጆች አንዷ ነበረች፤ እንዲህ ያደረጉት በዘመኑ በነበረው ባሕል ርስት የሚካፈሉ ወንድሞች ስላልነበራቸው ነበር።

ቲቶ

ቲቶ ሐዋርያው ጳውሎስ ያስተማረው የጥንት ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር።

  • ቲቶ በቀርጤስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን የመሾም ኀላፊነት ተሰጥቶት ነበር።
  • ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አንዱ ጳውሎስ ለቲቶ የጻፈው መልእክት ነው።
  • ከአሕዛብ ወገን የነበረ መሪ በመሆኑ ቲቶ እንዲገረዝ አልተጠየቀም።

ቲኪቆስ

ቲኪቆስ ከጳውሎስ ጋር የወንጌል አገልጋዮች ከነበሩት አንዱ ነው።

  • ቲኪቆስ ጳውሎስ ወደ እስያ ባደረገው ጉዞ ቢያንስ በአንዱ አብሮት ነበር።
  • ጳውሎስ፣ “የተወደደው” እና፣ “ታማኙ” በማለት ጠርቶታል።
  • የጳውሎስን መልእክቶች ወደ ኤፌሶንና ወደ ቆላስይስ ያደረሰው ቲኪቆስ ነበር።

ታላቁ ሄሮድስ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሄሮድስ የሚባሉ ጥቂት ገዦች ነበር። ኢየሱስ በተወለደ ዘመን ሄሮድስ አይሁድ ያልሆነ የይሁዳ ንጉሥ ነበር።

  • ኢየሩሳሌም የነበረው የአይሁድ ቤተ መቅደስ እንዲደረግ ባዘዘው ሥራ በጣም ይታውቃል።
  • ጨካኝና ብዙ ሰዎች የገደለ ነበር ሌላ የአይሁድ ንጉሥ በቤተልሔም መወለዱን ሲሰማ፣ እዚያ የነበሩ ሕፃናትን ሁሉ አስገደለ።
  • ሄሮድስ አንቲጳስና ሄሮድስ ፊልጶስ የተሰኙት የእርሱ ልጆችና በኋላም የልጅ ልጁ ሄሮድስ አርግጳ የይሁዳ ገዦች ሆነዋል። የልጅ ልጅ ልጁ የሆነው ሄሮድስ አግሪጳ ዳግማዊ (ንጉሥ አግሪጳ ተብሎም ይጠራል) መላው የይሁዳን አካባቢ ገዝቶአል።

ታራ

ታራ የኖኅ ልጅ የሴም ዘር ነው። የአብርሃም፣ የናኮርና የካራን አባት ነበር።

  • ታራ ከልጁ ከአብርሃም፣ ከወንድሙ ልጅ ከሎጥና ከአብራም ሚስት ሦራ ጋር ወደ ምድረ ከነዓን ለመሄድ ዑር የነበረውን ቤቱን ትቶ ወጥቶ ነበር።
  • ወደ ከነዓን እየህዱ እያለ በሜስፖታሚያ ባለችው ካራን አጭር ቆይታ አድርገው ነበር፤ ታራ በ205 ዓመቱ በካራን ሞተ።

ትዕማር

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ትዕማር ተብለው የተጠሩ በርካታ ሴቶች ነበሩ። ትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ ትዕማር የተባለ ቦታ ተጠቅሷል

  • ትዕማር የይሁዳ ልጅ ማስት ነበርች። የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንታዊ አባት የሆነው ፋሬስ የተወለደው ከእርሷ ነበር
  • ከንጉሥ ዳዊት ልጆች አንዷ ትዕማር ትባል ነበር፤ ከፊል መንድሟ አሆነው አምኖን አስገድዶ በመድፈር ሕይወቷን አበላሸ

ቶማስ

ቶማስ ደቀ መዛሙርቱ እንዲሆኑ ኢየሱስ ከመረጣቸው ሰዎች አንዱ ነበር (ሐዋርያት ተብለዋል)።

  • የቶማስ ሌላው ስም ዳዲሞስ ሲሆን፣ ትርጕሙ፣ “መንታ” ማለት ነው።
  • ቶማስ የኢየሱስን ቁስል በዓይኑ ካላየና በእጁም ካልዳሰሰ ከሞት መነሣቱን እንደማያምን በመናገሩ ይታወቃል።
  • ወደ አብ የሚያደርሰውን መንገድ እንዴት ማወቅ እንደሚቻል እንዲነግረው ኢየሱስን የጠየቀ ቶማስ ነበር።

ቶቤል

ቶቤል የኖኅ ልጅ የያፌት ልጅ ነው።

  • ቶቤል ትንቢተ ኢሳይያስና ሕዝቅኤል ውስጥ የተጠቀሱ ሕዝብ ናቸው።
  • ይህ ሰው የላሜሕ ልጅ ከሆነው ቱባልቃየን የተለየ ነው።

ነህምያ

ነህምያ የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ በባቢሎናውያን በምርኮኝነት በተወሰዱ ጊዜ ባቢሎን መንግሥት ውስጥ ይኖር የነበረ እስራኤላዊ ነው።

  • የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ወይን ጠጅ አሳላፊ በነበረ ጊዜ ነህምያ ወደ ባቢሎን ለመመለስ ከንጉሡ ፈቃድ ጠየቀ።
  • ባቢሎናውያን የደመሰሱትን የኢየሩሳሌም ቅጥር እንደ ገና እንዲሠራ እስራኤላውያንን የመራ ነህምያ ነበር።
  • ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ከመመለሱ በፊት ለአሥራ ሁለት ዓመት የኢየሩሳሌም አስታዳሪ ነበር።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ የምናገኘው መጽሐፈ ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ለመሥራትና ሕዝቡን ለማስተዳደር ነህምያ ያደረገውን ውጣ ውረድ ያቀርባል።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ነህምያ የሚባሉ ሌሎች ሰዎችም ነበር። ማንነታቸውን መለየት እንዲቻል በእነዚህ የተለያዩ ሰዎች ስም ጋር የአባታቸው ስም ተያይዞአል፤ ለምሳሌ፣ “የሐካልያ ልጅ ነህምያ” እንደሚለው።

ነነዌ፣ የነነዌ ሰዎች

ነነዌ የአሦር ዋና ከተማ ነበረች። የነነዌ ሰዎች ነነዌ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።

  • ከክፉ መንገዳቸው እንዲመለሱ አጠንክሮ እንዲናገር እግዚአብሔር ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሰዎች ላከ። ከክፉ መንገዳቸው በመመለሳቸው እግዚአብሔር ሳያጠፋቸው ቀረ።
  • በኋላ ላይ አሦራውያን እግዚአብሔርን ማገልገል ተዉ። የእስራኤልን መንግሥት ድል በማድረግ ሕዝቡን ወደ ነነዌ ወሰዱ።

ናሆም

ናሆም ክፉው ንጉሥ ምናሴ እየገዛ በነበረበት ዘመን ያገለገለ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር።

  • ናሆም ከኤልቆሺ ከተማ ሲሆን፣ ይህች ቦታ ከኢየሩሳሌም በግምት 20 ማይሎች ትርቃለች።
  • ትንቢተ ናሆም የአሦር ከተማ የነንዌን መደምሰስ በተመለከተ የተነገሩ ትንቢቶች ይዞአል።

ናቡከደነፆር

ናቡከደነፆር የባቢሎን መንግሥት ንጉሥ ነበር። የእስራኤልና የይሁዳ መንግሥታት በነበሩበት ዘመን ባቢሎን ገናና መንግጥ ነበረች።

  • ናቡከደነፆር ብዙ ሕዝቦችን ድል ያደረገ በጣም ብርቱ ሰራዊት ነበረው።
  • በናቡከደነፆር አመራር ዘመን የባቢሎን ሰራዊት የይሁዳን መንግሥት ድል በማድረግ አብዛኛውን ሕዝብ በምርኮኝነት ወደ ባቢሎን ወስዶ ነበር። ይህ “የባቢሎን ምርኮ” ዘመን ለ70 ዓመት ዘልቋል።

ናታን

ናትን ዳዊት የእስራኤል ንጉሥ በሆነበት ዘመን የኖረ ታማኝ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው።

  • ዳዊት ኦርዮን ላይ ታላቅ ኀጢአት በፈጸመ ጊዜ ዳዊትን ፊት ለፊት እንዲገናኘው እግዚአብሔር ናታንን ላከው።
  • ምንም እንኳ ዳዊት ንጉሥ ቢሆንም፣ ናታን ፊት ለፊት ዳዊትን ገሠጸው።
  • ናታን ካናገረው በኋላ ዳዊት ተጸፍቶ ንስሐ ገባ።

ናኮር

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ናኮር ተብለው ከተጠሩ ሁለት ሰዎች አንደኛው የአብርሃም አያት ሲሆን፣ ሁለተኛው የአብርሃም ወንድም ነበር።

  • የይስሐቅ ሚስት ርብቃ የአብርሃም ወንድም የናኮር ትልቋ የልጅ ልጅ ነበረች።
  • “የናኮር ከተማ” የምትባል ከተማም ነበረች፤ ምናልባትም የአብርሃምን አያት ለማመልከት ይሆናል። ይህ ሐረግ፣ “ናኮር የምትባል ከተማ” ወይም፣ “ናኮር የነበረበት ከተማ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ናዝሬት፣ ናዝራዊ

ናዝሬት በሰሜናዊ እስራኤል ገሊላ አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች።

  • ማርያምና ዮሴፍ ከናዝሬት ነበር፤ ኢየሱስ ያደገውም እዚያ ነበር።
  • በእነርሱ መካከል በማደጉ ብዙዎቹ የናዝሬት ሰዎች ለኢየሱስ ትምህርት ክብር አልሰጡትም፤ እርሱ እንደ ማንኛውም ተራ ሰው እንደ ሆነ ነበር ያሰቡት።
  • እርሱ መሲሕ መሆኑን በተናገረ ጊዜ የናዝሬት ሰዎች ኢየሱስን ለመግደል ሞክረው ነበር።

ኔጌብ

ኔጌብ በደቡባዊ እስራኤል የሚገኝ በረሃማ አካባቢ ነው።

  • የመጀመሪያው ቃል፣ “ደቡብ” ማለት ሲሆን፣ አንዳንድ ትርጕሞች በዚሁ መልኩ ተጠቅመዋል።
  • ምናልባትም ይህ ደቡባዊ አካቢ በዚህ ዘመን የኔጌብ በረሠ ካለበት ቦታ ጋር አንድ ላይሆን ይችላል።
  • አብርሃም በቃዴስ ከተማ በነበረ ጊዜ፣ በኔጌብ ወይም በደቡባዊው አካባቢ ነበር።
  • የይሁዳና የስምዖን ነገዶች በዚህ ደቡባዊ አካባቢ ነበር የሚኖሩት።
  • ኔጌብ ውስጥ ትልቁ ከተማ ቤርሳቤህ ነው።

ንዕማን

ንዕማን የእስራኤል ጠላቶች አንዱ የነበረው የሶርያ ጦር አዛዥ ነበር።

  • ንዕማን ከባድ የቆዳ ሕመም ነበረበት፤ ማንም እርሱን መፈወስ አልቻለም ነበር።
  • ኤልሳዕ በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲታጠብ ለንዕማን ነገረው። ንዕማን በመታዘዙ እግዚአብሔር ከደዌው ፈወሰው።
  • ከዚህ ሕመም ስለ ፈወሰው ንዕማን በእግዚአብሔር አመነ።

ንፍታሌም

ንፍታሌም ስድስተኛው የያዕቆብ ልጅ ነው። የእርሱ ዘሮች ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ የሆነውን የንፍታሌም ነገድ አስገኝተዋል።

  • ንፍታሌም ከእስራኤል ሰሜናዊ ጫፍ አካባቢ የሚኖር ነገድ ነው።
  • ይህ ነገድ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ተጠቅሷል።
  • ንፍታሌም የሚለው ስም ይህ ነገድ የሚኖርበትን አካባቢም ያመለክታል። ይህም፣ “የንፍታሌም ነገድ የሚኖርበት ምድር” ወይም፣ “የንፍታሌም ዘሮች የሚኖሩበት አገር” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • ንፍታሌም “ትግል” ማለት ነው።

ኖኅ

ኖኅ በዓለም የነበሩ ክፉ ሰዎችን ለማጥፋት እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ የሚያዳርስ ጎርፍ በላከበት ጊዜ ከ4000 ዓመት በፊት ይኖር የነበረ ሰው ነው። ጎርፉ ምድርን በሚሸፍንበት ጊዜ እርሱና ቤተ ሰቡ የሚኖሩበት ግዙፍ መርከብ እንዲሠራ እግዚአብሔር ለኖኅ ነገረው።

  • ኖኅ በማንኛውም ነገር ለእግዚአብሔር የታዘዘ ጻድቅ ሰው ነበር።
  • ግዙፉን መርከብ እንዴት እንደሚሠራ እግዚአብሔር ሲነግረው ኖኅ በትክክል እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ሠራው።
  • መርከቡ ውስጥ ኖኅና ቤተ ሰቡ በመልካም ሁኔታ ነበር፤ በኋላም ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ምድርን እንደ ገና በሰዎች ሞሉ።
  • ከጥፋት ውሃ በኋላ የተወለደ ሁሉ የኖኅ ቤተ ሰብ ነው።

አልዓዛር

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልዓዛር የበርካታ ስሞች ስም ነበር።

  • አልዓዛር የአሮን ወንድም የሙሴ ሦስተኛ ልጅ ነበር። አሮን ከሞተ በኋላ አልዓዛር የእስራኤል ሊቀ ካህን ሆኖአል።
  • ከዳዊት፣ “ኀያላን ሰዎች” አንዱ አልዓዛር ይባል ነበር።
  • ከኢየሱስ ጥንተ አባቶች አንዱ አልዓዛር ይባል ነበር።

አልዓዛር

አልዓዛር ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው ወዳጁ ነበር።

  • አልዓዛር ማርያምና ማርታ የሚባሉ ሁለት እኅቶች ነበሩት፤ ሁለቱም በኢየሱስ ያምኑ ነበሩ።
  • ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት ካስነሣው በኋላ የአይሁድ መሪዎች በጣም ተቆጥተው ስለ ነበር ሁለቱንም የሚያጠፉበትን መንገድ እየፈለጉ ነበር።

አማሌቅ፣ አማሌቃዊ

አማሌቃዊ ከኔጌብ ምድረ በዳ አንሥቶ እስከ አረብ አገር ድረስ ባለው የከነዓን ደቡባዊ ክፍል በሙሉ የሚኖሩ ዘላን ሕዝብ ነበሩ።እነዚህ ሰዎች የኤሳው ልጅ ልጅ የአማሌቅ ዘሮች ናቸው።

  • አማሌቃውያን እስራኤላውያን በከንዓን ለመኖር መጀመሪያ ከመጡ ጀምሮ ጽኑ የእስሬል ጠላት ነበሩ።
  • አንዳንዴ “አማልቅ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ መልኩ አማሌቃውያንን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።
  • ከአማሌቃውያን ጋር ተደርጎ በነበረ አንድ ውጊያ ሙሴ እጆቹን ከፍ ሲያደርግ እስራኤላውያን ያሸንፉ ነበር።ደክሞት እጆቹ ወደ ታች ሲወርዱ ይሸነፉ ነብር።ስለዚህም የእስራኤል ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አማሌቃውያንን እስኪያሸንፉ ድረስ አሮንና ሐር ሙሴ እጆቹን ከፍ እንዳደረገ እንዲቆይ ረዱት።
  • ንጉሥ ሳኦልና ንጉሥ ዳዊት አማሌቅን ለመዋጋት ዘመቻ አድርገው ነበር።
  • አማሌቅን ባሸነፈበት አንዱ ውጊያ ከዘረፋ የተገኙ ነገሮችን ለራሷ በመውሰድ እግዚአብሔር እንዳዘዘው የአማሌቃውያንን ንጉሥ ባለ መግደል ሳኦል ለእግዚአብሔር ሳይታዘዝ ቀረ።

አሜስያስ

አባቱ ንጉሥ አዩአስ ከተገደለ በኋላ አሜስያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ።

  • ንጉሥ አሜስያስ ከ796-767 ዓቅክ ለሃያ ዘጠኝ ዓመት ይሁዳን ገዛ።
  • መልካም ንጉሥ ቢሆንም ጣዖቶች ይመለክበት የነበረውን ከፍታ ቦታዎች ግን አላጠፋም
  • የኃላ ኃላ አሜስያስ የአባቱ ገዳዮችን ሁሉ ገደለ
  • ዐምፀኞች ኤደማውያንን ድል በማድረግ እንደገና በይሁዳ መንግሥት ቁጥጥር ሥር እንዲሆኑ አደረገ።
  • ከእስራኤል ንጉሥ ከኢዮአስ ጋር ውጊያ ቢያደርግም ተሸነፈ የተወሰነው የኢያሩሳሌም ቅጥር ፈርሶ ሳለ ነብር። ከቤተ መቅደሱ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ተዘረፉ።
  • ከዓመታት በኋላ ንጉሥ አሜሶያስ ፊቱን ከያህዌ አዞረ በኢያሩሳሌም እርሱ ላይ ያሤሩ ሰዎች ገደሉት።

አምኖን

ከአኪናሆም የተወለደ የዳዊት ታላቅ ልጅ ነው፤፤

  • አምኖን ከፊል እህቱ የነበረችውን ትዕማርን ደፈረ፤እርስዋ የአቤሴሎምም እናት ነበረች፤፤
  • ከዚህ የተነሳ አቤሴሎም አምኖን ላይ አሴር፤በኋላም ገደለው።

አሞራዊ

አሞራውያን ከኖህ የልጅ ልጅ ከከነዕን የተገኘ ሃያል ህዝብ ነበሩ፤

  • የስማቸው ትርጉም ከፍ ያለ እንደ ማለት ሲሆን፡የሚኖሩበትን ተራራም አካባቢ ወይም ደግሞ ረጃጅሞች መሆናቸውን ለማመልከት ሊሆን ይችላል።
  • አሞራዊያን በሁለቱም የዮርዳኖስ ወንዝ አካባቢ ነበር የሚኖሩት፤ጋይ የተባለችው ከተማ የአሞራውያን መኖሪያ ነበረች።
  • የአሞራውያን ሃጢያት ሃሰተኛ አማልት ማምልካቸውንና በዚያ ውስጥ የሚካተት ሃጢያትንም እንደሚጨምር እግዚእበሄር አመልክቷል።
  • እግዚአብሄር ባዘዘው መሰረት እሞራውያንን ለመደምስስ እያሱ እስራኤልን መርቷል።

አሞን፣አሞናውያን፣አሞናዊት

“የአሞን ሕዝብ” ወይም ፣ “አሞናውያን” ከነዓን ውስጥ ከነበሩት ሕዝቦች አንዱ ናቸው።ሎጥ ከትናሿ ልጁ የወለደው የቤን አሚ ዘር ናቸው።

  • “አሞናዊት” የሚለው በተለይ ሴት አሞናዊትን ያመለክታል፤ይህ “አሞናዊት ሴት” ተብሎ መተርጎምም ይችላል፤፤
  • አሞናምን ከዮርዳኖስ ወንዝ ምስራቅ ይኖሩ ነበር፤የእስራኤል ጠላቶችም ነበሩ፤፤
  • አንድ ጊዜ አሞናዊን እስራኤልን እንዲረግምላቸው፤ለለዓም የሚባል ነቢይ ቀጥርው ነበር፤እግዚአብሄር ግን ያንን አልፈቀደም።

አሞጽ

አሞጽ በይሁዳ ንጉስ በዕዝያን ዘመን የነበረ እስራኤላዊ ነብይ ነበር፤

  • የነቢይነት ከመጠራቱ በፊት አሞጽ በይሁዳ መንግሥት ውስጥ ይኖር የነበረ እረኛና በለስ የሚያመርት ገበሬ ነበር።
  • አሞጽ ሰዎች ላይ በሚፈጽሙት ግፍ ባለድጎቹ የሰሜናዊ እስራኤል መንግሥት ሰዎች ላይ ስለሚመጣው ቅጣት ትንቢት ተናግሮ ነበር፤

አሞጽ

የነቢዩ ኢሳይያስ አባት አሞጽ ይባል ነበር።

  • መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው ኢሳይያስ የአሞጽ ልጅ መሆኑን ለማመልከት ብቻ ነበር።

አሦር፥ አሦራዊ፥ የአሦር መንግሥት

አሦር እስራኤል በከነዓን ምድር ይኖሩ በነበሩበት ዘመን በጣም ኅያል መንግሥት ነበር። የአሦር መንግሥት በአሦር ንጉሥ ይተዳደሩ የነበሩ አገሮች ናቸው።

  • የአሦር ሕዝብ ከአሁኗ ኢራቅ በስተሰሜን አካባቢ ይኖር ነበር
  • አሦራውያን በታሪካቸው በተለያየ ጊዜ ከእስራኤል ጋር ተዋግተዋል
  • በ722 ዓቅክ አሦራውያን ሙሉ በሙሉ የእስራኤልን መንግሥት ድል አደረጉ። ብዙዎቹ እስራኤላውያን ወደ አሦር እንዲሄዱ አስገደዱ
  • እዚያው የቀሩት እስራኤላውያን አሦራውያን ከሰማሪያ ካመጧቸው ባዕድ ሰዎች ጋር እርስ በርስ ተጋቡ። የእነዚህ እርስ በርስ የተጋቡ ሰዎች ዘሮች በኋላ ላይ ሳምራውያን ተባሉ

አረቢያ፤ አረባዊ

አረቢያ፥3000000 ስኩዬር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የዓለማችን ትልቁ ባሕር ገቡ፤አካባቢ ነው ከእስኤል ደቡብ ምስራቅ ያለ ቦታ ሲሆን ከቀይ ባሕር ከአረቢያ ባሕርና ከፋርስ ባሕር ሰላጤ ጋር ይዋስናል።

  • አረባዊ የሚለው ቃል በአርቢያ የሚኖር ሰዎን ወይም ከአረቢያ ጋር የተያያዘ ነገርን ለማመላከት ጥቅም ላይ ይውላል።
  • የመጀመሪያዎቹ የአረቢያ ነዋሪዎች የሴም ልጅ ልጆች ነበሩ።ሌሎች ጥንታዊ የአርቢያ ነዋሪዎች እንደ ኤሳው ዘሮች ሁሉ የአብራሃም ልጅ እስማኤልንና ዘሮቹንም ይጨምራል።
  • እስራኤላዊያን ለ40 ዓመት ይተንከራቱቱበት በረሐ የሚገኘው በአርቢያ ነው።
  • በእይሱስ ካመነ በሖላ ሐዋሪያው ጻውሎስ ጢቂት ዓመት በአረቢያ በረሐ አሳልፎአል፤
  • ገላትያ ለነበሩ ከርስቲያኖች በጻፈው መልእክት የሲና ተራራ የሚኘው በአረቢያ መሆኑን ጳውሎስ ጠቅሷል።

አራም፤አራማዊ ፤አራማይክ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ አርም የሁለት ሰዎች ስም ነው፤የአሁኑ ሲሪያ ያለችበት ከከነዓን ሰሜን ምስራቅ ያለው አካባቢ ስም ነው፤

  • አራም ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ሰዎች አራማውያን ተብሎ የሚናገሩት ቋንቋ አረማይክ ነበር፤እይሱስና በዝሙት የነበሩ ሌሎች አይሁዳም፤አራማይክ ይኖሩ ነበር፤
  • ከሴም ልጆች አንዱ አራም ያባል ነበር፤አራም ተብሎ የሚጠራው ሌላው ሰው የርብቃ ወንድም ልጅ ነበር፤የአራም አካባቢ ከእነዚህ ሁለት ሰዎች በአንዱ ሳይጠራ እንዳልቀረ ይታሰባል።
  • በኋላ ላይ አራም፥ በግሪክ ስሙ ፥ “ሶርያ” ተጠርቷል
  • “ፔዳን አራም” የተሰኘው ገለጻ፥ “የኣራም ሜዳ” ማለት ሲሆን የሚገኘው ከአራም ሰሜናዊ ክፍል ነበር።
  • ከአብርሃም ዘመዶች ጥቂቶቹ “ፔዳን አራም” ውስጥ በሚገኘው ካራን ከተማ ይኖሩ ነበር
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ እንዳንዴ፥ “አራም” እና “ፔዳን አራም” የሚለው አገላለጽ አብዛኛውን ጊዜ አንዱን አካባቢ ነበር የሚያመለክተው
  • “አራም ነኻሪም” የሚለው፥ “ባለሁለት ወንዞች አራም” ማለት ሲሆን ይህ አካበቢ የሚገኘው መሰዽጦሚያ በስተሰሜን እና፥ ከ”ፔዳን አራም” በስተምሥራቅ ነበር።

አራራት

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “አራራት” ለአንድ አካባቢ፥ ለአንድ መንግሥትና የተራራ ሰንሰለት የተሰጠ ስም ነው።

  • “የአራራት ምድር” ምናልባት በአሁኑ ዘመን ቱርክ በሚባለው አገር ሰሜናዊ ምሥራቅ ክፍል የነበረ ቦታ ሊሆን ይችላል።
  • አራራት ይበልጥ የሚታወቀው የጥፋት ውሃ መቀነስ ከጀመረ በኋላ የኖህ መርከብ ያረፈችበት ተራራ ስም በመሆኑ ነው።
  • በዚህ ዘመን አንድ ተራራ፥ “የአራራት ተራራ” ተብሎ ከተጠራ ብዙውን ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱሱ “አራራት ተራራ” ቦታ እንደሆነ ይታሰባል።

አርሞንዔም ተራራ

አርሞንዔም ተራራ እስራኤል ውስጥ ካሉ ተራሮች በጣም ረጁም ነው።

  • የሚገኘው ከገሊላ ባሕር በስተ ምሥራቅ፣ በእስራኤልና በሶርያ ድንበር በስተ ሰሜን ነበር።
  • የአርሞንዔም ተራራ ሌሎች ስሞች፣ “የሰርዮን ተራራ” እና፣ “ሳኔር ተራራ” የተባሉት ናቸው።
  • የአርሞንዔም ተራራ ሦስት ዋና ዋና ጫፎች አሉት።

አርጤክስስ

አርጤክስስ ሃያ ዓመት የጥንቱን ፋርስ/ኢራቅ የገዛ ንጉሥ ነበር።

  • ይህ የሆነው በምርኮ የወሰዱ አይሁድ የነበሩበት ባቢሎን በፋርስ አገዛዝ ሥር በሆነበት ዘመን ነበር።
  • የዚህ ንጉሥ ሌላው ስም አትሸዊሮስ ሊሆን ይችላል።
  • በቁጣ ተነሣሥቶ የእርሱን ልዕልት(ሚስቱን) ካባረረ በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ አዲሷ ሚስቱንና ልዕልቱ እንድትሆን አስቴር የተባለች አይሁዳዊት ሴት መርጦ ነበር።

አርጤክስስ

አርጤክስስ ከ 464-424 ዓቅክ የፋርስን መንግሥት ሲገዛ የነበረ ንጉሥ ነው

  • በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከይሁዳ የተወሰዱት እስራኤላውያን በዚያ ጊዜ በፋርስ ቁጥጥር ሥር በነበረችው በባቢሎን ምርኮ ውስጥ ነበሩ
  • ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ለእስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲያስተምሩ አርጤክስስ ለካህኑ ዕዝራና አብረውት ለነበሩ አይሁድ መሪዎች አርጤክስስ ፈቃድ ሰጠ
  • በዚሁ ጊዜ ጥቂት ቆየት ብሎ ከተማዋን የሚከብበውን ቅጥር የሚሠሩ አይሁድን እየመሩ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ አርጤክስስ ለወይን ጠጅ አሳላፊው ለነህምያ ፈቃድ ሰጥቷል
  • በዚያን ጊዜ ባቢሎን በፋርስ አገዛዝ ሥር ስለነበርች አንዳንዴ አርጤክስስ “የባቢሎን ንጉሥ” ተብሎ ይጠራል
  • አርጤክስስ አሐሻዊሮስ ከሚባለው ሰው ጋር አንድ እንዳይደለ ልብ በሉ

አሮን

አሮን የሙሴ ታላቅ ወንድም ነበር። የእስራኤል ሕዝብ የመጀመሪያ ሊቀ ካህን እንዲሆን እግዚአብሔር አሮንን መረጠ።

  • እስራኤልን እንዲለቅ ለፈርዖን እንደገና ሙሴን የረዳው አሮን ነው።
  • እስራኤል በምድረበዳ በሚጓዙበት ጊዜ የሚያመልኩት ጣዖት ለሕዝቡ በመሥራት አሮን ኀጢአት አደረገ።
  • ለእስራኤል ሕዝብ ካህናት እንዲሆኑ እግዚአብሔር አሮንና ልጆቹን ሾመ።

አሳ

አሳ ክ913-873 አቅክ ድረስ ለአርባ ዓመት የይሁዳን መንግሥት የገዛ ንጉሥ ነበር

  • ንጉሥ አሳ መልካም ንጉሥ ነበር፤ የሐሰተኛ አማልክት ምስሎችን አስወግዷል፤ እስራኤላውያን እንደገና ያህዌን ወደማምለክ እንዲመለሱ አድርጓል
  • ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ባደረገው ውጊያ እንዲያሸንፉ ያህዌ ለንጉሥ አሳ ድል ሰጠው
  • ይሁን እንጂ በአገዛዙ ዘመን በኋላ ላይ አሳ በያህዌ መተማመኑን ትቶአል፤ የኋላ ኋላ ለሞት በበቃው ጽኑ ሕመም ታምሞአል

አሳፍ

አሳፍ ሌዋዊ ካህን ሲሆን፥ ለንጉሥ ዳዊት መዝሙሮች ሙዚቃ ያዘጋጀ ጥሩ ስጦታ ያለው ሙዚቀኛ ነበር። አሳፍ የራሱን መዝሙሮችም ጽፎአል

  • በቤተ መቅደሱ አምልኮ ዝማሬ ከሚያቀርቡ ሦስት ሙዚቀኞች አንዱ እንዲሆን አሳፍ በንጉሥ ዳዊት ተሹሞ ነበር። ከእነዚህም መዝሙሮች አንዳንዶቹ ትንቢት ነበሩ
  • አሳፍ ልጆቹን-------------- ነበር፤ ይህንኑ ኅላፊነት በመፈጸም ቤተመቅደሱ ውስጥ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ይጫወቱና ትንቢት ይናገሩ ነበር
  • ከሙዚቃ መሣሪያዎቹ ጥቂቱ ዋሽንት፥ በገና፥ መለከትና ጽናጽል ነበሩ።
  • መዝሙር 50 እና እንዲሁም 73-85 ያሉት መዝሙሮች የአሳፍ እንደሆኑ ይነገራል። ምናልባትም ከእነዚህ መዝሙሮች አንዳንዶቹ በእርሱ ቤተሰቦች ተጽፈው ይሆናል

አሴር

አሴር የያዕቆብ ስምንተኛ ልጅ ነው። የእርሱ ዘሮች ከአሥራ ሁሉቱ የእስራኤል ነገድ አንዱ ሆኑ፤ ዘሮቹም “አሴር” ተብለው ይጠራሉ።

  • የአሴር እናት የልያ አገልጋይ የነበርችው ዘለፋ ናት
  • የስሙ ትርጉም “ደስተኛ” ወይም “የተባረከ” ማለት ነው
  • እስራኤላውያን ወደ ተስፋው ምድር ከገቡ በኋላ ለአሴር ነገድ የተሰጠው ክልል ስም አሴር ነው የሚባለው

አስቀሎና

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን አስቀሎና ሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ የምትገኝ ዋና የፍልስጥኤማውያን ከተማ ነበርች። ዛሬም እስራኤል ውስጥ ትገኛለች።

  • ከአሽዶድ፥ ከአቃሮን፥ ከጋት እና ጋዛ ጋር አስቀሎና ከአምስቱ ጠቃሚ የፍልስጥኤማውያን ከተሞች አንዷ ነበረች
  • ምንም እንኳ የይሁድ መንግሥት ተራራማውን አገሩን መያዝ ቢችልም፥ እስራኤላውያን ሙሉ በሙሉ የአስቀሎናን ሰዎች ድል አላደረጉም
  • አስቀሎና በመቶ ለሚቆጠሩ ዓመታቶች በፍልስጥኤማውያን እንደተያዘች ቆየች።

አስቆሮቱ ይሁዳ

የአስቆሮቱ ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር። ለአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠ እርሱ ነበር።

  • “አስቆሮቱ” የሚለው ፣ ይሁዳ ያደገበትን ከተማ ለማመልከት “ከቂርያት የመጣ” ማለት ሊሆን ይችላል።
  • ይሁዳ ሌባ ነበር፤ የሐዋርያቱ ገንዘብ ያዥ በነበረ ጊዜ ከገንዘቡ ጥቂቱን ለራሱ ጥቅም ይሰርቅ ነበር።
  • ኢየሱስ የሚገኝበትን ቦታ ለሃይማኖት መሪዎቹ በመንገር ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ሰጠ።
  • የሃይማኖት መሪዎቹ ኢየሱስ ላይ ሞት በፈረዱ ጊዜ፣ ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ በመስጠቱ ተጸጸተ፤ ስለዚህም ራሱን ገደለ።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የኢየሱስን ወንድምና ከደቀመዛሙርቱ አንዱን የመሳሰሉ ይሁዳ የሚባሉ ሰዎች ነበሩ።

አስቴር

አይሁድ በባቢሎን በምርኮ በነበሩበት ዘመን የፋርስ መንግሥት ልዕልት የሆነች አይሁዳዊት ሴት ናት።

  • አስቴር የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ልዕልት መሆን እንዴት እንደቻለችና ሕዝቧን ለማዳን እግዚአብሔር እንደተጠቀመባት መጽሐፈ አስቴር ይናገራል።
  • አስቴር አባትና እናት ያልነበራት ስትሆን፣ ያሳደጋት እግዚአብሔርን የሚፈራው ሽማግሌው አጎቷ መርዶክዮስ ነበር።
  • ለአሳዳጊ አባቷ ታዛዥ መሆንዋ፣ ለእግዚአብሔርም ታዛዥ እንድትሆን ረዳት።
  • ሕዝቧ አይሁድን ለማዳን ስትል ሕይወቷን ለአደጋ በማጋለጥ አስቴር ለእግዚአብሔር ታዝዛለች።
  • መጽሐፈ አስቴር በታሪክ ውስጥ የሚፈጸሙ ነገሮችን ለመቆጣጠር የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነትና በተለይም እንዴት ሕዝቡን እንደሚጠብቅና ለእርሱ በሚታዘዙ ሰዎች በኩል እንዴት እንደሚሠራ ይገልጻል።

አስጢን

ከመጽሐፈ አስቴር እንደምንመለከተው አስጢን የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ሚስት ነበረች።

  • ወደ ግብዣው መጥታ ለሰካራም ጓደኞቹ እንድታሳይ ንጉሡ ያዘዘውን ባለማድረጓ አስጢን ከልዕልትነት ተሻረች።
  • ከዚህም የተነሣ አዲስ ልዕልት ለማግኘት ፍለጋ ተጀመረና አስቴር አዲሷ የንጉሡ ሚስት እንድትሆን ተመረጠች።

አሼራ፥ የአሼራ ምስል፥ አስታሮት

አሼራ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነዓናውያን ያመልኳት የነበሩ ጣዖት ነበረች። “አስታሮት” ሌላው የአሼራ ስም ነው፥ ወይም ደግሞ ተመሳሳይ የሆነች ሌላ ጣዖት ስም ሊሆን ይችላል።

  • “የአሼራ ምስል” የሚለው ገለጻ፥ ይህችኑ ጣዖት እንዲወክሉ እንጨት መቅረጽን ወይም ዛፎችን ማበጀትን ያመለክታል
  • ብዙውን ጊዜ የአሼራ ምስል የአሼራ ባል ነው ተብሎ በሚታሰበው በዓል የተሰኘው ጣዖት መሠዊያ አጠገብ ነበር የሚቆመው። አንዳንድ ሕዝቦች በዓልን እንደፀሐይ አምላክ፥ አሼራን ወይም አስታሮትን እንደጨረቃ አምላክ ያመልኩ ነበር
  • የተቀረጹ የአሼራ ምስሎችን ሁሉ እንዲያጠፉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ
  • ጌዴዎንን፥ ንጉሥ አሳን፥ ንጉሥ ኢዮስያስን የመሳሰሉ እስራኤላውያን መሪዎች ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ሕዝቡ እነዚህን ጣዖቶች እንዲያጠፉ አደረጉ
  • ይሁን እንጂ፥ ንጉሥ ሰሎሞንን፥ ንጉሥ ምናሴንና ንጉሥ አክዓብን የመሳሰሉ ሌሎች እስራኤላውያን መሪዎች የአሼራን ምስሎች ባለማስወገዳቸው ሕዝቡ እነዚህን ጣዖቶች ማምለክ ቀጠለ

አሽዶድ አዛጦን

አሽዶድ ከአምስቱ በጣም ጠቃሚ የፍልስጥኤም ከተሞች አንዷ ነበረች። ሜድትራኒያን ባሕር አጠገብ ከከነዓን ደቡብ ምዕራብ፥ በጋዛና በኢዮጴ መካከል ግማሽ ርቀት ላይ ነበር የምትገኘው

  • የፍልስጥኤማውያን ጣዖት የዳጎን ቤተመቅደስ የነበረው በአሽዶድ ነበር።
  • የቃል ዲዳኑን ታቦት በመውሰዳቸውና አሽዶድ በነበረው የአረማውያን ቤተመቅደስ ውስጥ በማኖራቸው እግዚአብሔር የአሽዶድ ሰዎችን ክፉኛ ቀጣቸው
  • የዚህች ከተማ የግሪክ ስም አዛጦን ነው። ወንጌላዊው ፊሊጶስ ወንጌል ከሰበከባቸው ከተሞች አንዷ ነበረች

አቂላ

አቂላ ከጥኩር በቀር ደቡባዊ ባሕር ዳርቻ ከነበረው ጻንጦስ አውራጃ የነበረ አየሁዳዊ ነበር፤

  • አቂላና ጽርስቅላ ለተወሰነ ጊዜ በሮም ጣልያን ኖሩ፤ በሖላ ግን ሮማዊው ንጉስ ቀላውዲውስ አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ አስገደደ።
  • አቂላና ጽርስቅላ ወደ ቆሮንቶስ ከመጡ በሖላ ከሐዋርያው ጻውሎስ ጋር ተገናኙ።
  • እንደ ጻውሎስ ሁሉ እነርሱም ድንዅን ይሰፉ ነበር።በሐዋሪያዊ ተልኮውም ይረዱት ነበር፤
  • አቂላና ጽርስቅላ እየሱስን በተመለከተ እውነቱን ለአማኞች አስተማሩ፤ከእነዚህ አማኞች አንዱ አጽሎስ የሚሉት ስጦታ ያለው መምህር ነበር፤

አቃሮን

አቃሮን የፍልስጥኤማውያን ዋነኛ ከተማ ሲሆን የሚገኘው ከሜድትራንያን ባሕር ዘጠኝ ማይል ገባ ብሎ ያለ ቦታ ላይ ነበር።

  • ቤል ዜቡል የተባለ ጣዖት ቤተ መቅደስ የሚገኘው አቃሮን ነበር።
  • አንድ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ማርከው ወደ አቅሮን ወስደውት ነበር።
  • በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር በአቃሮን የነበሩ ብዙ ሰዎች በበሽታ ሞቱ፣ ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ታቦቱን ወደ እስራኤል መለሱት።

አቢሜሌክ

አብርሃምና ይስሐቅ በከነዓን ምድር በሚኖሩበት ዘመን አቢሜሌክ በጌራራ አካባቢ የነገሠ ንጉስ ነበር ።

  • ሣራ እኅቴ እንጂ ሚስቴ አይደለችም በማለት አብርሃም ንጉሥ ኢቢሜሌክን አታልሎት ነበር።
  • በቤርሳህ የነበሩ የውሃ ጉድጓዶች ባለቤትነትን በተመለከተ አብርሃምና አቢሜሌክ ስምምነት አድረጉ።
  • ርብቃ እኅቴ እንጂ ሚስቴ አይደለችም በማለት ከብዙ ዓመታት በኋላ ይስሐቅም አቤሜሌክንና ሌሎች በጌራራ የነበሩ ሰዎችን አትልሎአል።
  • በእርሱ በመዋሸታቸው ንጉሥ አቢሜሌክ አብርሃምን በኋላም ይስሐቅን ገሥጾአቸዋል።
  • አቤሜሌክ የተሰኘ ስም የነበረው ሌላው ሰው የጌዴዎን ልጅና የኢዮአታም ወንድም ነበር።እርሱ ከንጉሥ አቢሜሌክ የተለየ ሰው መሆኑን ግልጽ ለማድረግ አንዳንድ ትርጉሞች ስሙ ላይ ጥቂት ለውጥ ያደርጉ ይሆናል።

አቢያ

ከ 915- 913 ዓቅክ ነግሦ የነበር የይሁዳ ንጉሥ ስም ነው እርሱ የንጉሥ ሮብዓም ልጅ ነበር። ብሉይ ኪዳን ውስጥ አቢያ የሚል ስም የሚታወቁ ሌሎች ጥቂት ሰዎችም ነበሩ።

  • አቢያና ኢዩኤል የተበሉት የሳሙኤል ወንዶች ልጆችና ራስ ወዳዶች ስለ ነበሩ በእርሱ ፈንታ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ሕዝቡ ሳሙኤልን ጠየቁ።
  • ሌላው አቢያ በንጉሥ ዳዊት ዘመን የቤተ መቅደሱ ካህናት ከነበሩ ሰዎች አንዱ ነበር።
  • አቢያ ከንጉሥ ሮብዓም ልጆች አንዱ ነበር።
  • ከባቢሎን ምርኮ ከዘሩባቤል ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሰ ሊቀካህን ስም አቢያ ይባል ነበር።

አቤል

አቤል የአዳምና የሔዋን ሁለተኛ ልጅ ነበር። እርሱ የቃየል ታናሽ ወንድም ነበር።

  • አቤል እረኛ ነበር።
  • መሥዋዕት እንዲሆኑ አቤል ከእንስሳቱ ጥቂቶቹን ለእግዚአብሔር ሠዋ።
  • በአቤልና በመሥዋዕቱ እግዚአንሔር ደስ አሰኘ።
  • የአዳምና የሔዋን የመጀመሪያ ልጅ ቃየል አቤልን ገደለ።

አቤሴሎም

አቤሴሎም የዳዊት ሦስተኛ ወንድ ልጅ ነበር። በቁንጅናውና በቁመናው እንዲሁም በጣም ቅብጥብጥ በመሆኑ ይታወቃል።

  • የአቤሴሎም እህት ትዕማር ከፊል ወንድሟ በመሆኑ በአምኖን በተደፈረች ጊዜ አቤሴሎም አምኖንን ለመግደል ዕቅድ አወጣ።
  • አምኖንን ከገደለ በኋላ አቤሴሎም የእናቱ የመዓካ አገር ወደ ሆነው ወደ ጌሹር አካባቢ በመኮብለል በዚያ ሦስት ዓመት ቆየ።ከዚያም ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጣ ንጉሥ ዳዊት መልዕክተኞች ላከ ። ይሁን እንጂ ለሁለት ዓመት ያህል አቤሴሎም እፊቱ እንዲቀርብ አልፈቀደም ነበር።
  • አቤሴሎም አንዳንድ ሰዎችን ዳዊት ላይ አነሣሣ፤እርሱ ላይ ዐመፅ አስነሣ።
  • የዳዊት ሰራዊት ከአቤሴሎም ጋር ተዋግቶ ገደለው። እንዲህ በመሆኑ ዳዊት በጣም አዘነ።

አቤኔር

አቤኔር የንጉሥ ሳኦል አጎት ልጅ ነበር።

  • አበኔር የሳኦል ሰራዊት ዋና አዣዥ ነበር፤ ግዙፉን ሰው ጎልያድን ዳዊት ከገደለ በኋላ ወጣቱ ዳዊትን ካሳኦል ጋር ያስተዋወቀ እርሱ ነበር።
  • ከንጉሥ ሳኦል ሞት በኋላ ዳዊት የይሁዳ ንጉሥ ሲሆን አበኔር የሳኦልን ልጅ አያቡስቴን የእስሬል ንጉሥ አደረገው።
  • በኋላ ላይ አበኔር በዳዊት ሰራዊት ዋና አዛዥ በአዩአብ በክህደት ተገደለ።

አብርሃም፣ አብራም

አብራም የእስራኤላውያን አባት እንዲሆን እግዚአብሔር የመረጠው ከዑር ከተማ የመጣ ከለዳዊ ነበር። በኋላ ላይ እግዚአብሔር “አብርሃም” በማለት ስሙን ለውጦታል።

  • “አብራም” ማለት “ከፍ ያለው አባት ማለት ነው።”
  • “አብርሃም” ማለት “የብዙዎች አባት ማለት ነው”
  • ብዙ ልጆች እንደሚኖሩትና እነርሱም ታላቅ ሕዝብ እንደሚሆኑ እግዚአብሔር ለአብርሃም ቃል ገባለት።
  • አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ ለእርሱም ታዘዘ። አብርሃምን ከከላዳውያን አገር ወደ ከነዓን ምድር እንዲሄድ እግዚአብሔር አብርሃምን መራው።
  • በከነዓን ምድር እየኖሩ እያለ በጣም አርጅተው እያለ አብርሃምና ሣራ ይስሐቅ የሚባል ወንድ ልጅ ወለዱ።

አብያታር

በንጉሥ ዳዊት ዘመን አብያታር የእስራኤል ሕዝብ ሊቀ ካህን ነበር።

  • ንጉሥ ሳኦል ካህናትን በገደለ ጊዜ አብያተር በማምለጥ ምድረ በዳ ውስጥ ወደ ነበረው ዳዊት ሄደ።
  • አብያተርና ሌላ ሰዶቅ የሚሉት ሊቀ ካህን በንግሥና ዘመኑ ሁሉ ዳዊትን በታማኝነት አገልግለዋል።
  • ከዳዊት ሞት በኋላ በሰሎሞን ቦታ ንጉሥ አብያተር አዶንያስን ረድቶት ነበር ።
  • ከዚያም የተነሣ ንጉሥሰሎሞን አብያተርን ከክህነት ሻረው። (እንዲሁም. . . . ይመ)
  • አቢያ

አብድዩ

አብድዩ በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ከነበሩ የእስራኤል ነቢያት አንዱ ነበር።

  • በዚያ ዘመን የነበሩ ነቢያት ሕዝቅኤልና ዳንኤል ናቸው።
  • አብድዩ ትንቢት የተናገረው የዔሳው ዘር በሆኑት የኤዶም ሕዝብ ላይ ነበር።

አናንያ

ከትንቢተ ዳንኤል እንደምንመለከተው አናንያ በምርኮ ዘመን ወደ ባቢሎን ተወስደው ስለነበሩ አስተዋይ አይሁዳውያን ወጣቶች አንዱ ነበር። ይበልጥ የሚታወቀው ሲድራቅ በተሰኘው ስሙ ነው።

  • ባሳየው የፀባይ ብልጫና እግዚአብሔር ከሰጠው ችሎታ የተነሣ ባቢሎናውያን ለአናንያ ከፍተኛ ሥልጣን ሰጥተውት ነበር።
  • የባቢሎን ንጉሥ ለአናንያ ሲድራቅ የሚል ስም ሰጠው።
  • ለንጉሡ መስገድ ባለ መፈለጋቸው ከሌሎች አይሁዳውያን ጓደኞቹ ጋር ሲድራቅ እሳት ውስጥ ተጥሎ ነበር። እነርሱ ላይ ምንም ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ እግዚአብሔር ኀይሉን አሳየ።
  • በተለያዩ የብሉይ ኪዳን ክፍሎች እናንያ (ሐናንያ) የሚባሉ ይህን ያህል ታዋቂነት ያልነበራቸው ሰዎች ነበሩ።
  • አንደኛው አናንያ (ሐናንያ) በነቢዩ ኤርምያስ ዘመን የነበረው ሐሰተኛ ነቢይ ነው።

አንጾኪያ

አዲስ ኪዳን ውስጥ አንጾኪያ የሁለት ከተሞች ስም ነበር፤አንደኛው ሜድትርያን ባሕር ዳርቻ አጠገብ በሶሪያ ነበር፤ሌላው ግን ቆላስያስ ከተማ አጠገበ በነረው ጺስዲያ ነበር።

  • በሶሪያ አንጾኪያ የነበረው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ክርስቲያን ተበለው የተጠሩበት የመጀመርያው ቦታ ነበር፤እዚያ የነበረው ቤተ ክርስቲያን ለአሕዛበ ወንጌል እንዲሰብኩ መልክተኛ ይልክ ነበር፤
  • ጻውሎስ በርናባስና ዩሐንስ፤ማርቆስ ወንጌል ለመስበክ ወደ ጽስዲያ ተጉዘው ነበር፤ሁከት ለማስነሳት ጥቂት አይሁድ ከሌሎች ከተሞች ወደዚያ መጡ፤ጻውሎስን ለመግደልም ሞከሩ፤አይሁድንና አሕዛብን ጨምሮ ሌሎች ብዙዎች ትምህርቱን በመስማት በእየሱስ አመኑ።

አኪያ

አኪያ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተለያዩ ሰዎች ስም ነው። የሚከተሉት ከእነዚህ ሰዎች ጥቂቶቹ ናቸው፣

  • አኪያ በሳኦል ዘመን የነበረ ካህን ስም ነበር።
  • በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን አኪያ የሚባል ጸሐፊ ነበር።
  • አኪያ ከሴሎ የመጣውና የእስራኤል መንግሥት ለሁለት እንደምከፈል ትንቢት የተናገረው ነብይ ስም ነበር።
  • የእስራኤል ንጉሥ ሳኦል አባት ስም አኪያ ይባል ነበር።

አካዝ

አካዝ ከ732 ዓቅከ - 716 ዓክከ የይሁዳን መንግሥት የገዛ በጣም ክፉ ንጉሥ ነበር። ይህ ይሆነው በእስራኤልና በይሁዳ የነበሩ ብዙ ሰዎች በምርኮ ወደ ባቢሎን ከመወሰዳቸው 140 ዓመት በፊት ነበር።

  • ይሁዳን እየገዛ በነበረበት ዘመን አካዝ የአሦራውያንን ሐሰተኛ አማልክት ለማምለክ መሠዊያ ሠርቶ ነበር፤ይህም ሕዝቡ ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ከያህዌ እንዲመለሱ አደረገ።
  • ንጉሥ አካዝ ይሁዳን መግዛት በጀመረ ጊዜ 20 ዓመቱ ነበር፤16 ዓመት በሥልጣን ቆየ።

አካዝያስ

አካዝያስ የሁለት ንጉሦች ስም ነው፤አንደኛው የእስራኤል መንግሥት ስገዛ ሌላው የይሁዳን መንግሥት ገዛ።

  • የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ የንጉሥ አዩራም ልጅ ነበር። ለአንድ ዓመት 841 ዓቅክ ሥልጣን ላይ ከቆየ በኃላ ኢዩ ገደለው። በኋላ ላይ የአካዝያስ ታናሽ ልጁ ኢዮአስ የንጉሥነቱን ቦታ ያዘ።
  • የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ የንጉሥ አክዓብ ልጅ ነበር። ለሁለት ዓመት ሥልጣን ላይ ቆየ (850-49 ዓቅክ)። ከቤተ መንግሥቱ ሰገነት ሲወድቅ በደረሰበት ጉዳት የተነሣ ሞተ በእርሱ ቦታ ወንድሙ አዮራም ነገሠ።

አክዓብ

አክዓብ ከ 875-854 ዓቅክ ስሜናዊ የእስራኤል መንግሥት ላይ ነግሦ የነበረ በጣም ክፉ ንጉሥ ነው።

  • ንጉሥ አክዓብ ሐሰተኛ አማልክት እንዲያመለኩ የእስራኤል ሕዝብ ላይ ተፅዕኖ አደረገ።
  • ነብዩ ኤልያስ ከአክአብ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ እስራኤል እንዲፈጽሙ ስላደረገው ኅጢያት ቅጣት እንዲሆን ለሦስት ዓመት ተኩል ከባድ ድርቅ እንደሚሆን ነገረው።
  • አክአብና ሚስቱ ኤልዛቤል ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ንጹሕ ሰዎችን መግደልን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ክፉ ነገሮችን አድርጓል።

አዛርያስ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ አዛርያስ በሚባል ስም የታወቁ ሰዎች ነበሩ

  • አንደኛው አዛርያስ አብድናጎ በተሰኘው ባቢሎናዊ ስሙ ነበር ይበልጥ የሚታወቀው። በናቡከደነፆር ሰራዊት ከይሁዳ ወደ ባቢሎን ከተወሰዱ ብዙ እስራኤላውያን አንዱ ነበር። አዛርያስ ሐናንያና ሚሳኤል የሚባሉ እስራኤላውያን ጓደኞቹ ለባቢሎን ንጉሥ መስገድ አልፈለጉም፤ ስለዚህም ወደሚንቀለቀለው እሳት በመጣል ተቀጡ። ይሁን እንጂ፥ እግዚአብሔር ስለጠበቃቸው በፍጹም አልተጎዱም።
  • የይሁዳ ንጉሥ ዖዝያንም፥ “አዛርያስ” በሚባል ስም ይታወቃል
  • ሌላው አዛርያስ የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህን ነበር
  • በነብዩ ኤርምያስ ዘመን አዛርያስ የሚባል አንድ ሰው፥ ከትውልድ አገራቸው እንዳይሄዱ በመንገር እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ላይ እንዲያምጹ አድርጓል።

አዳም

አዳም እግዚአብሔር የፈጠረው የመጀመሪያ ሰው ነው።እርሱና ሚስቱ ሔዋን በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥረዋል።

  • እግዚአብሔር አዳምን ከአፈር አበጀው፤ አውስጡም ሕይወት እፍ አለበት
  • የአዳም ስም “ቀይ አፈር”ወይም “መሬት” ከሚለው ቃል ጋር ይመሳሰላል።
  • አዳም የተሰኘው ስም “ የሰው ልጅ”ወይም፣ “ሰብዓዊ ፍጡር” የተሰኘው የብሉይ ኪዳን ጋር አንድ ነው።
  • ሰዎች ሁሉ የአዳምና የሔዋን ልጆች ናቸው።
  • አዳምና ሔዋን እግዚአብሔር ላይ ኅጢያት አደረጉ። ይህም ከእግዚአብሔር ለያያቸው ፤ኅጢአትና ሞትም ወደ ዓለም እንዲመጡ አደረገ።

አዶንያስ

አዶንያስ የንጉሥ ዳዎት አራተኛ ልጅ ነው።

  • ከወንድሞቹ ከአቤሴሎምና ከአምናን መሞት በኋላ አዶንያስ የእስራኤል ንጉሥ ለመሆን ሞክሮ ነበር።
  • ይሁን እንጂ፣ዙፋኑ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን እንደሚሆን እግዚአብሔር ተናግሮ ነበር፤ስለዚህ የአዶንያስ ሤራ ከሽፎ ዙፋኑ ለሰሎሞን ተሰጠ።
  • አዶንያስ ራሱን ለማድረግ ለሁለተኛ ግዜ በመሞከር እርሱ እንዲገደል ሰሎሞን አዘዘ።

አጋር

አጋር የሦራ አገልጋይ ነበረች።

  • በኋላ ላይ ሣራ የተባለችው ሣራ ከእርሷ ጋር እንዲተኛ አገልጋይዋን አጋርን ለአብርሃም ሰጠችው።
  • አጋር ለእርሷና ለአብርሃም ልጅ እንድትወልድ ሦራ ፈልጋ ነበር።
  • አጋር እስማኤል የሚባል ልጅ ለአብርሃም ወለደችለት።

አጽሎስ

አጽሎስ ግሪክ ዉስጥ ከነበረው እስክንድሪያ የመጣ ስለ እየሱስ ለሰወች ለማስተማር ልዩ ችሎታ የነበረው አይሁዳዊ ነበር።

  • አጽሎስ የአይሁድ ቅዱሳት መጽሕፍትን በሚገባ የተማረና የንግግር ችሎታ ያለው ሰው ነበር፤
  • አቂላና ጽርስቅላ የተባሉት ሁለት ክርስቲያኖች በኤፌሶን በሚገባ ተማረ
  • እንደ ሌሎች ወንጌላዊያንና መምህራን ሁሉ እርሱና አጽሎስም ሰዎች በክርስቶስ እንዲያምኑ ለመርዳት አሰሩ እንደ ነበር ጻውሎስ አጠንክሮ ተናግሮአል።

አፍራታ፥ የኤፍራታ ሰው

አፍራታ በሰሜኑ የእሥራኤል ክፍል የሚገኝ የአንድ ከተማ ስም ነበር።


ኢሳይያስ

ኢሳይያስ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር።

  • ኢሳይያስ እርሱ በሕይወት እያለ የተፈጸሙ እስራኤልን የሚመለከቱ ብዙ ትንቢቶች ተናግሮአል።
  • በተለይ ደግም ኢሳይያስ ከ700 ዓመት በኋላ ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ በተፈጸሙት መሲሑን አስመልክቶ በተናገራቸው ትንቢቶቹ ይታወቃል።
  • መሲሑን በተመለከተ ለሰዎች ለማስተማር ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የኢሳይያስን ትንቢቶች ጠቅሰዋል።
  • ትንቢተ ኢሳይያስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛ መጻሕፍት አንዱ ነው።

ኢቆንዮን

ኤቄንዮን ደቡብ ማዕከላዊ እስያ ውስጥ (አሁን ቱርክ ያለችበት) የምትገኝ ከተማ ነበረች።

  • አቆንዮን የነበረችው የዘመኑ ኮንያ ከተማ አሁን ያለችበት ቦታ ላይ ነበር።
  • በመጀመሪያው ሐዋርያው ጉዞአቸው በአንጾኪያ ለነበሩ አሕዛብ የተዋጣለት አገልግሎት ከሰጡ በኋላ ጳውሎስና በርናባስ በአይሁድ ከአንጾኪያ አካባቢ ሲባረሩ የሄዱት ወደ ኢቆንዮን ነበር።
  • በኢቆንዮን የነበሩ አይሁድና አሕዛብ ጳውሎስንና አብረውት ያሉትን በድንጋይ ለመውገር ባሰቡ ጊዜ በአቅራቢያው ወዳለችው ልስጥራ ከተማ ሸሹ። ከዚያም የኢቆንዮንና የአንጾኪያ ሰዎች ወደ ልስጥራ መጥተው ጳውሎስን በድንጋይ እንዲወግሩ እዚያ የነበሩ ሰዎችን አንሣሡ።

ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊ

ኢትዮጵያ ከግብፅ በስተደቡብ ያለች አፍሪካዊት አገር ስትሆን፣ በስተምዕራብ የአባይ ወንዝ፣ በስተምሥራቅ ደግሞ ከቀይ ባሕር ጋር ትዋሰናለች። ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘ ሰው ኢትዮጵያዊ ይባላል።

  • የጥንቷ ኢትዮጵያ ከግብፅ በስተደቡብ ያለች ሱዳንን፣ የአሁኗ ኢትዮጵያን፣ ሶማልያን፣ ኬንያን፣ ዩጋንዳን፣ ማዕከላዊ ሪፖብሊክንና ቻድን የመሳሰሉ በርካታ የዘመኑ አፍሪካ አገሮችን የምታካትት ነበረች።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢትዮጵያ አንዳንዴ “ኩሽ” ወይም፣ “ኑቢያ” ትባላለች።
  • የኢትዮጵያ አገሮች (“ኩሽ”) እና ግብፅ ብዙ ጊዜ በአንድነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል፤ እንዲህ የሆነው ጎረቤታሞች ስለሆኑና ሕዝቦቻቸው ተመሳሳይ ጥንተአባቶች ስለነበሯቸው ሊሆን ይችላል።
  • እግዚአብሔር ፊልጶስን ወደምድረ በዳ ላከው፣ እርሱም የኢየሱስ ክርስቶስን ምሥራች ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ተናገረ።

ኢየሩሳሌም

ኢየሩሳሌም በኋላ እጅግ ተፈላጊ የሆነች በመጀመሪያ የከነዓናውያን የነበረች ጥንታዊት ከተማ ነበረች። አሁንም ኢየሩሳሌም የዘመናዊት ኢየሩሳሌም ዋና ከተማ ነች።

  • የብሉይ ኪዳንዋ የሳሌም ከተማ ምናልባት የአሁኗ ኢየሩሳሌም ከተማ ሳትሆን እንዳልቀረች ይታሰባል። ሁለቱም ስሞች፣ “ሰላም” የሚል ትርጉም ያለው ሥርወ ቃል አላቸው።
  • አብርሃም የኢየሩሳሌም ከተማ አካል በሆነው በሞሪያ ተራራ ልጁ ይስሐቅን መሥዋዕት አቀረበ።
  • ንጉሥ ዳዊት ከኢያቡሳውያን ነጥቆ ኢየሩሳሌምን ያዘ፤ ዋና ከተማዋም አደረጋት።
  • የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ያለ ሞሪያ ተራራ ላይ የመጀመሪያውን ቤተመቅደስ ሠራ።
  • ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ደመሰሱ፤ ከ70 ዓመት በኋላ ግን ተመልሰው ከተማዋን እንዲሠሩ እግዚአብሔር ፈቀደላቸው።
  • ቤተመቅደሱ የነበረው እዚያ በመሆኑ፣ ዋና ዋናዎቹ የአይሁድ በዓሎች የሚከበሩበት ማዕከል ኢየሩሳሌም ነበረች።
  • ኢየሱስ በሕፃንነቱ ለእግዚአብሔር የተሰጠው ኢየሩሳሌም በነበረው ቤተመቅደስ ነበር። ለፍርድ የቀረበውና መስቀል ላይ እንዲሞት የተፈረደበትም በኢየሩሳሌም ነበር።
  • ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት ከደቀመዛሙርቱ ጋር ጊዜ ካሳለፈባቸው ዋና ዋና ቦታዎች አንዷ ኢየሩሳሌም ነበረች።
  • ኢየሩሳሌም ያለችው በእስራኤል ተራሮች ላይ በመሆኑ ወደኢየሩሳሌም የሚሄዱ ሰዎች፣ “ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው” ይሉ ነበር።

ኢዩ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዩ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሰዎች አሉ።

  • አንደኛው ኢዩ በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመን የነበረ ነብይ ነው።
  • ንጉሥ ሆኖ ለሃያ ስምንት ዓመት ይሁዳን የገዛ ኢዩ የሚባል የጦር መሪ ነበር።
  • ኢዩ ክፉዋ ንግሥት ኤልዛቤልን ጨምሮ የቀድሞው ንጉሥ አክዓብ ዘመዶችን ሁሉ ገደለ።
  • ከአክዓብ ጋር ዝምድና የነበራቸው ሁለት ንጉሦችንም ገድሏል፤ የእስራኤል ኢዮራምና የይሁዳ አሃዝያ።

ኢያሪኮ

ኢያሪኮ በተስፋው ምድር በከነዓን የነበረች በጣም ኅያል ከተማ ነበረች።

  • እስራኤላውያን እንዲቆጣጠሯት እግዚአብሔር የነገራቸው ምድረ ከነዓን ውስጥ የመጀመሪያ ከተማ ነበረች።
  • እንደሁሉም ከነዓናውያን የኢያሪኮ ሰዎችም ጣዖት ያመልኩ ነበር።
  • ኢያሪኮን ለመያዝ ኢያሱ እስራኤላውያንን እየመራ ሲሄድ ከተማዋን ድል አድርጎ መያዝ እንዲችሉ እግዚአብሔር ታላቅ ተኣምር አደረገ።

ኢያሱ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢያሱ በመባል የሚታወቁ በርካታ ሰዎች አሉ። በጣም ታዋቂው የነዌ ልጅና የሙሴ ረዳት የነበረው በኋላም የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁነኛ መሪ የሆነው ኢያሱ ነበር።

  • የተስፋውን ምድር እንዲሰልሉ ሙሴ ከላካቸው አሥራ ሁለት ሰላዮች አንዱ ኢያሱ ነበር።
  • ወደተስፋው ምድር ገብተው ከነዓናውያንን እንዲያሸንፉ እግዝአብሔር ለሰጠው ትእዛዝ እንዲታዘዙ እስራኤላውያንን በማበረታታቱ ከካሌብ ጋር ሆኖ ጉብዝናውንና በእግዚአብሔር መተማመኑን አሳይቷል።
  • ከብዙ አመት በኋላ ሙሴ ሲሞት የእስራኤልን ሕዝብ እየመራ ወደተስፋው ምድር እንዲገባ እግዚአብሔር ኢያሱን ሾመው።
  • ከከነዓናውያን ጋር በተደረገው የመጀመሪያውና ዝነኛው ጦርነት እግዚአብሔር እንደነገረው ኢያሱ እስራኤላውያን ኢያሪኮን እንዲይዙ መርቷል።
  • የተስፋውን ምድር መያዝና ምድሪቱን ለእስራኤል ነገዶች ማከፋፈልን ጨምሮ በኢያሱ አመራር ዘመን የሆነው ሁሉ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ባለው መጽሐፍ ኢያሱ ተጽፎ ይገኛል።
  • በነቢዩ ሐጌ እና በነቢዩ ዘካርያስ መጻሕፍት ኢያሱ የሚባል ሌላ ሰው ተጠቅሷል። ይኸኛው ኢያሱ የኢየሩሳሌም ቅጥሮች ሲሠሩ እገዛ ያደረገ ሊቀ ካህን ነበር። እርሱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ነበር።

ኢያቡሳዊ

ኢያቡሳውያን፤ ያቡስ ከሚባል ሰው የተወለዱ በከነዓን የነበሩ ነገድ ናቸው።

  • ያቡስ የጥንቷ ኢየሩሳሌም ከተማን አሸንፎ በመያዝ በስሙ እንድትጠራ አደረገ፤ ለተወሰነ ጊዜ ያቡስ ተብላ ብትጠራም፤ በኋላ የቀድሞ መጠሪያ ስሟ ተመለሰ።
  • ብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳን ውስጥ ታዋቂ የሆነው ሊቀ ካህኑ መልከጼዴቅ ከኢያቡሳውያን የተገኘ ነበር።

ኢይዝራኤል

ኢይዝራኤል ከጨው ባሕር ደቡብ ምዕራብ ነገድ ክልል ውስጥ የነበረች በጣም ጠቃሚ የእስራኤል ከተማ ስም ነው። ጥቂት የእስራኤል ንጉሦች ቤተመንግሥታቸውን የሠሩት እዚያ ነበር።

  • የኢይዝራኤል ከተማ የመጊዶ ሜዳማ ቦታ ምዕራባዊ ጫፎች ከሆኑት አንዷ ስትሆን የኢይዝራኤል ሸለቆ ተብሎም ይጠራል።
  • የናቡቴ ወይን እርሻ የነበረው በኢይዝራኤል አክዓብ ቤተመንግሥት አጠገብ ነበር። ነብዩ ኤልያስ እዚያ በነበረው አክዓብ ላይ ትንቢት ተናገረ።
  • ክፉዋ የአክዓብ ሚስት ኤልዛቤል የተገደለችው በኢይዝራኤል ነበር።
  • ጥቂት ጦርነቶችን ጨምሮ በዚህ ከተማ ሌሎችም ሁነኛ ጉዳዮች ተፈጽመዋል።

ኢዮራም

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮራም ተብለው የሚጠሩ ሁለት ንጉሦች ነበሩ።

  • አንዱ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው የኢዮሳፍጥ ልጅ ነው።
  • ሌላው ኢዮራም የእስራኤል ንጉሥ የሆነው የአክዓብ ልጅ ነበር። ይህ ንጉሥ፣ “ዮራም” በመባል ይታወቃል።

ኢዮራም

ኢዮራም የእስራኤል ንጉሥና የአክዓብና የኤልዛቤል ልጅ ነበር።

  • ኢዮራም የነገሠው ሌላው ኢዮራም የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ተመሳሳይ ጊዜ ነበር።
  • ኢዮራም ጣዖቶችን ያመልክ የነበረና እስራኤልን ወደ ኀጢአት የመራ ክፉ ንጉሥ ነበር።

ኢዮርብዓም

የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ከ900-910 ዓቅክ ገደማ የሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት የመጀመሪያው ንጉሥ ነበር። ኢዮርብዓም የሚባል ሌላው ንጉሥ የኢዮአስ ልጅ ሲሆን ከ120 ዓመት በኋላ እስራኤልን ገዝቷል። አንዳንዴ፣ “ቀዳማዊ ኢዮርብዓም” እና “ዳግማዊ ኢዮርብዓም” ይባላሉ።

  • ከኢዮርብዓም በኋላ እስራኤልን የገዙ ንጉሦችም የእርሱን ክፉ ምሳሌ ተከትለዋል።
  • ከ120 ዓመት በኋላ ኢዮርብዓም የሚባል ሌላ ንጉሥ የሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት ገዢ ሆነ። ይኸኛው ኢዮርብዓም የንጉሥ ኢዮአስ ልጅ ሲሆን የበፊቶቹ የእስራኤል ንጉሦች እንደነበሩት ሁሉ እርሱም በጣም ክፉ ነበር።
  • ይህ ሁሉ ለእስራኤል ምሕረት በማድረጉ ምድሪቱን እንዲቆጣጠሩና ድንበራቸውን እንዲያሰፉ እግዚአብሔር ይኸኛውን ንጉሥ ኢዮርብዓም ረዳው።

ኢዮሳፍጥ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮሳፍጥ ቢያንስ የሁለት ሰዎች ስም ነበር።

  • በዚህ ስም በጣም የታወቀው አራተኛው የይሁዳ መንግሥት ገዥ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ነበር።
  • በይሁዳና በእስራኤል መካከል ሰላም እንዲኖር አደረገ፤ የሃሰት አማልክት መሠዊያዎች ደመሰሰ።
  • ኢዮሳፍጥ ተብሎ የሚጠራ ሌላው ሰው በንጉሥ ዳዊትና በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን አስተዳደር ውስጥ ይሠራ የነበረ ነው።

ኢዮስያስ

ኢዮስያስ ለሰላሳ እንደ ዓመት የይሁዳን መግሥት የገዛ እግዚአብሔርን የሚፈራ ንጉሥ ነበር። ሕዝቡ በንስሐ እንዲመለሱና ያህዌን እንዲያመልኩ ለማበረታታት ብዙ ነገሮች አድርጓል።

  • አባቱ ንጉሥ አሞን ከተገደለ በኋላ ኢዮስያስ በስምንት ዓመቱ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ።
  • በአሥራ ስምንተኛው የአገዛዝ ዘመኑ ንጉሥ ኢዮስያስ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ እንደገና እንዲሠራ ሊቀካህኑ ኬልቅያስን አዘዘ። ይህ እየተደረገ እያለ የሕጉ መጻሕፍት ተገኙ።
  • የሕጉ መጻሕፍት ሲነበቡለት ሕዝቡ ምን ያህል በእግዚአብሔር ላይ እያመፁ መሆናቸውን በማሰብ ኢዮስያስ በጣም አዘነ። የጣዖት አመልኮ ቦታዎች ሁሉ እንዲፈርሱና የጣዖቶች ካህናትም እንዲገደሉ አዘዘ።
  • እንደገና የፋሲካ በዓል ማክበር እንዲጀምሩ ሕዝቡን አዘዘ።

ኢዮብ

ኢዮብ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅና በደል የሌለበት እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገርለት ሰው ነው። የበለጠ የሚታወቀው ታላቅ ስቃይና ሐዘን ቢደርስበትም በእግዚአብሔር በነበረው እምነት በመጽናቱ ነበር።

  • ኢዮብ በዚህ ምድር የነበረው ዓለምን ሁሉ ካደረሰው የኖኅ ዘመን ጎርፍ በኋላና አብርሃም ከነበረበት ዘመን በፊት እንደነበር ይታሰባል።
  • ኢዮብ በሞተበት ጊዜ ዕድሜው ምናልባት ሁለት መቶ ዓመት ሳይሆን አይቀርም።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው መጽሐፈ ኢዮብ በሕይወቱ ከደረሱት አያሌ አውዳሚ ሁኔታዎች የተነሣ ኢዮብ ላይ ስለ ደረሰው መከራ ይናገራል። የአጽናፍ ዓለሙ ሉዓላዊ ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን ነገሮችን ከእግዚአብሔር ዕይታ አንጻር ከማቅረብም በላይ ያንን መከራ በተመለከት ኢዮብና ሌሎች ሰዎች ስለሰጡት ምላሽም ይናገራል።
  • ከዚያ ሁሉ ውድመት በኋላ መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር ሁሉንም እንደገና ለኢዮብ መለሰለት፤ እርሱንና ቤተሰቡን በሀብት በጣም ባረካቸው።

ኢዮአስ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮአስ ተብለው የሚጠሩ ጥቂት ሰዎች ነበሩ።

  • አንደኛው ኢዮአስ የእስራኤላዊው ጦረኛ የጌዴዎን አባት ነበር።
  • ኢዮአስ ተብሎ የሚጠራው ሌላው ሰው የያዕቆብ ታናሽ ልጅ የብንያም ዘር ነበር።
  • በጣም ታዋቂው ኢዮአስ በሰባት ዓመቱ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው ነው። በግድያ ሕይወቱን ያጣው የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ ልጅ ነበር።
  • በጣም ትንሽ ልጅ ስለነበር ንጉሥ ለመባል ብቁ እስኪሆን ድረስ የኢዮአስ አክስት ደብቃ ከመገደል አዳነችው።
  • በአገዛዝ ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ንጉሥ ኢዮአስ ለእግዚአብሔር እየታዘዘ ነበር። በኋላ ግን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፤ እስራኤላውያንም እንደገና ጣዖቶችን መምልክ ጀምሩ።
  • በጦርነት ከቆሰለ በኋላ ንጉሥ ኢዮአስ በሁለት የገዛ ራሱ ባለ ሥልጣኖች ተገደለ።
  • ማስታወሻ፣ ይህ ንጉሥ በዚሁ ዘመን እስራኤልን ከግዛው ንጉሥ ኢዮአስ የተለየ ነው።

ኢዮአቄም

ኢዮአቄም የይሁዳን መንግሥት ከገዙ ንጉሦች አንዱ ነበር።

  • 18 ዓመት ሲሆነው ኢዮአቄም ንጉሥ ሆነ። የገዛው ሦስት ወር ብቻ ሲሆን በኋላ በባቢሎናውያን ሰራዊት ተይዞ ወደ ባቢሎን ተወሰደ።
  • በአጭሩ የአገዛዝ ጊዜው አያቱ ንጉሥ ምናሴና አባቱ እንዳደረገው ክፉ ነገር አደረገ።

ኢዮአቄም

ኢዮአቄም ከ60 ዓቅክ ጀምሮ በይሁዳ መንግሥት ላይ የነገሠ በጣም ክፉ ነጉሥ ነበር። እርሱ የንጉሥ ልጅ ነበር። መጀመሪያ ላይ ኤልያቄም ይባል ነበር።

  • የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ፥ የኤልያቄምን ስም ኢዮአቄም ወደሚል ለውጦ የይሁዳ ንጉሥ አደረገው።
  • ፈርዖን ኒካዑ ለግብፅ ግብር እንዲከፈል ኢዮአቄምን አስገደደ።
  • በኋላ ላይ ይሁዳ በንጉሥ ናቡከደነፆር ስትወረር ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ሰዎች አንዱ ኢዮአቄም ነበር።
  • ኢዮአቄም ለእግዚአብሔር የማይታዘዝና እንዲያውም የይሁዳ ሕዝብ ያህዌን እንዳያመልክ ያደረገ ንጉሥ ነበር። ነብዩ ኤርምያስ በእርሱ ላይ ትንቢት ተናግሮ ነበር።

ኢዮአብ

ኢዮአብ በአገዛዝ ዘመኑ ሁሉ የንጉሥ ዳዊት ሁነኛ የጦር መሪ ነበር።

  • ዳዊት ንጉሥ ከመሆኑ በፊት እንኳ ኢዮአብ ታማኝ የዳዊት ተከታይ ነበር።
  • ዳዊት ንጉሥ ሆኖ እስራኤልን በሚገዛበት ዘመን ኢዮአብ የንጉሥ ዳዊት ጦር አዛዥ ሆኖአል።
  • የኢዮአብ እናት ከንጉሥ ዳዊት እኅቶች አንዷ የነበረችው ጽሩያ ነበረች። ስለዚህ ኢዮአብ የዳዊት እኅት ልጅ ነበር ማለት ነው።
  • ንጉሥነቱን ለመውሰድ በመሞከር የዳዊት ልጅ አቤሴሎም በከዳው ጊዜ፣ ንጉሡን ለመታደግ ኢዮአብ አቤሴሎምን ገደለ። ኢዮአብ በጣም ጨካኝ ጦረኛ ስለነበር ብዙ የእስራኤል ጠላት የነበሩ ሰዎችን ገድሏል።

ኢዮአታም

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮአታም ተብለው የሚጠሩ ሦስት ሰዎች አሉ።

  • ኢዮአታም የሚባለው አንዱ የጌዴዎን ታናሽ ልጅ ነበር። ሌሎች ወንድሞቻቸውን ሁሉ የገደለው ታላቅ ወንድሙ አቤሜሌክን ድል ለማድረግ ኢዮአታም ተባብሮአል።
  • ሌላው ኢዮአታም የሚባል ሰው ከአባቱ ከዖዝያን ሞት በኋላ ለአስራ ስድስት ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የነበረ ነው።
  • እንደአባቱ ሁሉ ኢዮአታም ለእግዚአብሔር የታዘዘ መልካም ንጉሥ ነበር።
  • ይሁን እንጂ እንደአባቱ ሁሉ ንጉሥ ኢዮአታም ጣዖት የሚመለክባቸው ቦታዎችን አላጠፋም፤ ይህም በኋላ ላይ ሕዝቡ እንደገና ጣዖት ወደማምለክ እንዲመለሱ አድርጓል። የጣዖት አምልኮ ሌላው ውጤት የኢዮአታም ልጅ አካዝ ክፉ ንጉሥ መሆኑ ነበር።
  • ኢዮአታም የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ባለው የኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ሐረግ ከተዘርዘሩት ጥንተ አባቶች አንዱ ነበር።

ኢዮኤል

ኢዮኤል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለውን ትንቢተ ኢዮኤል የጻፈ ነብይ ነበር፤ ትንቢተ ኢዮኤል የመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ክፍል ከሆኑት አሥራ ሁለት አጫጭር ትንቢቶች አንዱ ነው።

  • የነቢዩ ኢዮኤልን ግላዊ ታሪክ በተመለከተ ያለን መረጃ የአባቱ ስም ባቱኤል ይባል እንደነበረ ብቻ ነው።
  • ከመጽሐፉ ይዘት መረዳት እንደሚቻለው ኢዮኤል የኖረውና ትንቢት የተናገረው የደቡባዊው የእስራኤል መንግሥት በነበረው በይሁዳ ነበር።
  • ኢዮኤል የኖረውና ትንቢት የተናገረው መቼ እንደነበረ ግልጽ አይደለም፤ ሆኖም፣ የመጽሐፉን ይዘት መሠረት በማድረግ በንጉሥ ኢዮአስ ዘመን ሊሆን እንደሚችል አንዳንዶች ያስባሉ።
  • በበዓለ ሃምሳ ቀን በሰበከው ስብከት ሐዋርያው ጴጥሮስ ከትንቢተ ኢዮኤል ጠቅሶ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢዮኤል የሚባሉ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ።

ኢዮጴ

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ኢዮጴ ከተማ ከኢየሩሳሌም ሰሜናዊ ምዕራብ 30 ማይሎች ርቃ ሜድትራንያን ባሕር ላይ የምትገኝ በጣም ጠቃሚ የንግድ ባሕር ወደብ ነበረች።

  • ጥንት ኢዮጴ የነበረችበት ቦታ በዚህ ዘመን ጃፋ ከተማ ያለችበት ሲሆን፣ ጃፋ ቤቴል አቪብ ከተማ አካል ነት።
  • ብሉይ ኪዳን እንደሚነግረን ዮናስ ወደተርሴስ የሚሄድ መርከብ የተሳፈረው ከኢዮጴ ነበር።
  • አዲስ ኪዳን እንደሚነግረን ጴጥሮስ ጣቢታ የምትባለውን ክርስቲያን ልጅ ከሞት ያስነሣው ኢዮጴ ነበር።

ኤላም

ኤላም የሴም ልጅ፣ የኖኅ የልጅ ልጅ ነው።

  • የኤላም ዘሮች ኤላማውያን ይባሉ ነበር፤ የሚኖሩትም “አላም” በሚባል አካባቢ ነበር።
  • ኤላም የነበረበት አካባቢ በአሁኑ ጊዜ ምዕራብ ኢራን በሆነው ከጤግሮስ ወንዝ ደቡብ ምሥራቅ ነበር።

ኤልሳቤጥ

ኤልሳቤጥ የመጥምቁ ዮሐንስ እናት ናት። የባልዋ ስም ዘካርያስ ነበር።

  • ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ አልነበራቸውም፤ በስተርጅናቸው ግን ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ እግዚአብሔር ቃል ገባላቸው።
  • እግዚአብሔር ቃሉን ጠበቀ፤ ብዙም ሳይቆይ ኤልሳቤጥ ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ሕፃኑንም ዮሐንስ አሉት።
  • ኤልሳቤጥ የኢየሱስ እናት የማርያምም ዘመድ ነበረች።

ኤልሳዕ

ኤልያስ አክዓብን፣ አካዝያን፣ ኢዮራምን፣ ያሑን፣ ኢዮአስንና ዮአስን በመሳሰሉ በርካታ የእስራኤል ነገሥታት ዘመን ነበር ያገለገለው።

  • ለነቢይነት ኤልሳዕን እንደ ቀባው እግዚአብሔር ሌልያስ ነገረው።
  • ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ወደ ሰማይ ከተወሰደ በኋላ ኤልሳዕ ለእስራኤል ነገሥታት የእግዚአብሔር ነቢይ ሆነ።
  • ከሶሪያ የመጣውን ለምፃም ሰው መፈወስንና ከሱናም የመጣችውን ሴት ልጅ ከሞት ማስነሣትን ጨምሮ ኤልሳዕ ብዙ ተአምራት አድርጎአል።

ኤልዛቤል

ኤልዛቤል ዐመፀኛዋ የእስራኤል ንጉሥ የአክአብ ሚስት ነበረች።

  • አክዓብና የተቀረው እስራኤል ጣዖቶች እንዲያመልኩ ተፅዕኖ ያሳደረችባቸው ኤልዛቤል ነበረች።
  • ብዙ የእግዚአብሔር ነብያትንም ገድላልች።
  • ባልዋ አክዓብ የወይን እርሻውን እንዲወርስ ለማድረግ ኤልዛቤል ናቡቴ የሚሉትን ድሐ ሰው አስገድላልች።
  • ካደረገችው ብዙ መጥፎ ተግባሮች የተነሣ መጨረሻ ላይ ኤልዛቤል ተገደለች። ስለምትሞትበት ሁኔታ ኤልያስ ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ ልክ እንደተናገረው ሆነባት።

ኤልያስ

ኤልያስ በጣም ታዋቅ ከሆኑት የያህዌ ነቢያት አንዱ ነበር። ንጉሥ አክዓብን ጨምሮ ኤልያስ በተለያዩ የእስራኤል ወይም የይሁዳ ነገሥታት ዘመን ነበር ያገለገለው።

  • የሞተውን ልጅ ማስነሣትን ጨምር እግዚአብሔር በኤልያስ በኩል ብዙ ተአምራት አድርጓል።
  • በአል የተሰኘውን ጣዖት በማምለኩ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን ገሥጾታል።
  • እውነተኛው አምላክ ያህዌ ብቻ መሆኑን ለማሳየት ባቀረበው ፈተና ያህዌ የበአል ነቢያትን ተገዳደረ።
  • የኤልያስ ሕይወት ማብቂያ ላይ ገና በሕይወት እያለ በተአምር እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወሰደው።
  • ከመቶ ዓመታት በኋላ ኤልያስ ከሙሴ ጋር፣ ተራራው ላይ ከኢየሱስ ጋር ታየ፤ ወደ ፊት ስለሚሆነው የኢየሱስ መከራና በኢየሩሳሌም ስለ መሞቱ እየተነጋገሩ ነበር።

ኤልያቄም

ኤልያቄም የሁለት የብሉይ ኪዳን ሰዎች ስም ነው።

  • የመጀመሪያው የንጉሥ ሕዝቅያስ ቤተ መንግሥት አስተዳዳሪ ነበር።
  • ሁለተኛው የንጉሥ ኢዮስያስ ልጅ ነበር። ግብፃዊው ፈርዖን ኒካዑ በይሁዳ ላይ አንግሦት ነበር።
  • የኤልያቄምን ስም፣ ኢዮአቄም ወደሚል የለወጠው ፈርዖን ኒካዑ ነበር።

ኤሞር

ኤሞር አይሁዳዊ ያልነበረ የያዕቆብ ጎረቤት የነበረ ሰው ነው።

  • ሚስቶቹንና ልጆቹን ይዞ ያዕቆብ ወደ ትውልድ አገሩ ከተመለሰ በኋላ ለቤተ ሰቡ መቃብር የሚሆን መሬት ከኤሞር ልጆች ገዛ።
  • የኤሞር ልጅ ሴኬም የያዕቆብን ልጅ ዲናን ደፈራት፤ ወንድሞቿም ኤሞርንና ቤተ ሰቡን ተበቀሉ።

ኤርምያስ

ኤርምያስ በይሁዳ መንግሥት የእግዚአብሔር ነብይ ነበር።

  • እንደ አብዛኞቹ ነብያት ሁሉ ኤርምያስ እግዚአብሔር በኀጢአታቸው ሕዝቡን እንደሚቀጣ ዘወትር ሕዝቡን ማስጠንቀቅ ነበረበት።
  • ባቢሎን ኢየሩሳሌምን እንደምትይዝ ኤርምያስ ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ ይህ ግን የይሁዳን ሕዝብ አስቆጣ። ስለዚህም እዚያው እንዲሞት ደረቅ ጉድጓድ ውስጥ ከተቱት። ይሁን እንጂ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኤርምያስን ከጉድጓድ እንዲያወጡት አዘዘ።

ኤሳው

ኤሳው ይስሐቅ ከርብቃ ከወለደቻቸው መንታ ልጆች ታላቁ ነበር፣ መንታ ወንድሙ ያዕቆብ ነበር።

  • ኤሳው በምስር ወጥ ብኩርናውን ለወንድሙ ለያዕቆብ ሸጠ።
  • ኤሳው የመጀመሪያ ልጅ በመሆኑ፣ አባቱ የተለየ በረከት ይሰጠው ነበር። ይሁን እንጂ፣ ያዕቆብ አባቱን በማታለል ያንን በረከት ወሰደ። መጀመሪያ ላይ ኤሳው በጣም ተቆጥቶ ያዕቆብን መግደል ፈልጎ ነበር፤ በኋላ ግን ይቅርታ አደረገለት።
  • ኤሳው ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩት። የእርሱ ዘሮች በምድረ ከነዓን የሚኖሩ በጣም ብዛት ያለው ሕዝብ ሆነዋል።

ኤዊያውያን

ምድሪቱን እንዲወርሱ ኢያሱ እስራኤላውያንን እየመራ በወሰደ ጊዜ ኤዊያውያን በከነዓን ምድር ከነበሩ ሰባት ዋና ዋና ሕዝቦች አንዱ ነበሩ።

  • ኤዊያውያን ከኖኅ ልጅ ከካም የተገኙ ናቸው።
  • እነርሱን ድል አድርጎ ከመያዝ ይልቅ እስራኤላውያን በስሕተት ከኤዊያውያን ጋር ኪዳን አደረጉ።
  • ኤዊያዊው ሴኬም የያዕቆብ ልጅ ዲናን ደፈረ፤ ይህን ለመበቀል ወንድሞቹ ብዙ ኤዊያውያንን ገደሉ።

ኤደን፣ ኤደን ገነት

በጥንት ዘመን ኤደን እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ወንድና ሴት ያኖረበት የአትክልት ቦታ ያለው አካባቢ ነበር።

  • አዳምና ሔዋን የነበሩበት አትክልት ቦታ ከኤደን ጥቂት ክፍሉ ብቻ ነበር።
  • ኤደን የነበረበትን ትክክለኛ አካባቢ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፤ የኤፍራጥስና የጤግሮስ ወንዝ ያጠጡት እንደ ነበር ግን ተገልጿል።
  • ኤደን የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን፣ “በጣም ደስ መሰኘት” የሚል ትርጕም አለው።

ኤዶም፣ ኤዶማዊ፣ ኤዶሚያ፣ ሴይር፣ ቴማን

ኤዶም፣ የኤሳው ሌላው ስም ሲሆን፣ ኤዶማውያን የእርሱ ዘሮች ናቸው። የኤዶም አገር ኤዶምያ ወይም ሴይር በመባልም ይታወቃል።

  • ኤዶም ተራራማና ከእስራኤል በስተ ደቡብና በስተ ምሥራቅ የሚገኝ ቦታ ነበር።
  • ኤዶም፣ “ቀይ” ማለት ሲሆን፣ ኤሳው ሲወለድ በቀይ ጠጉር ተሸፍኖ እንደ ነበር ለማመልከት ሊሆን ይችላል። ወይም ደግም የበኵርና መብቱን የለወጠበትን ቀይ የምስር ወጥ ለማመልከት ሊሆን ይችላል።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብዙውን ጊዜ የኤዶም ምድር የተጠቀሰው የእስራኤል ጠላይ ከመሆኑ አንጻር ነበር።
  • በኤዶም ላይ የሚመጣውን ጥፋት አስመልክቶ እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ብዙ ትንቢቶች ሰጥቷል። ትንቢተ አብድዩ በሙሉ የሚናገረው ኤዶም ላይ ስለማመጣው ፍርድ ነው።

ኤፌሶን

ኤፌሶን በአሁኑ ዘመን ቱርክ በምትባለው አገር ምዕራባዊ ባሕር ዳርቻ የነበረች ጥንታዊ የግሪክ ከተማ ነበረች።

  • በጥንት ክርስቲያኖች ዘመን ኤፌሶን በዚያ ጊዜ ትንሿ የሮም አውራጃ የነበረችው እስያ ዋና ከተማ ነበረች።
  • ከነበረችበት ቦታ አምቺነት የተነሣ ይቺ ከተማ የንግድና የጉዞ ማዕከል ነበረች።
  • የአርጤምስ (ዳያና) ጣዖትን ለማምለክ የተሠራው ታዋቂ የአረማውያን ቤተ መቅደስ ይገኝ የነበረው በአፌሶን ነበር።
  • ጳውሎስ ከሁለት ዓመት የበለጠ በአፌሶን እየኖረ አገለገለ፤ በኋላም እዚያ የነበሩ አማኞችን እንዲያገለግል ጢሞቴዎስን ሾመ።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው የአፌሶን መልእክት ጳውሎስ በአፌሶን ለነበሩ አማኞች የጻፈው ነው።

ኤፍራጥስ

ኤፍራጥስ በኤደን የአትክልት ቦታ ውስጥ ያልፉ ከነበሩ አራት ወንዞች አንዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተደጋጋሚ የተጠቀሰ ወንዝ ነው፣ አንዳንዴ፣ “ወንዙ” በመባል በአጭር ቃል ተጠርቷል።

  • በዚህ ዘመን ኤፍራጥስ ተብሎ የሚጠራው ወንዝ የሚገኘው መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ሲሆን፣ በእስያ ካሉት ወንዞች ረጅሙና በጣም ጠቃሚው ወንዝ ነው።
  • ከጤግሮስ ወንዝ ጋር በአንድነት ኤፍራጥስ ሜስፖታሚያ በመባል ከሚታወቀው ምድር ጋር ይዋሰናል።
  • አብርሃም የተገኘባት የጥንቷ ዑር ከተማ የምትገኘው የኤፍራጥስ ወንዝ ልሳን ላይ ነበር።
  • ይህ ወንዝ ለአብርሃም እንደሚሰጠው እግዚአብሔር ቃል የገባለት ምድር ድንበሮች አንዱ ነው። (ዘፍጥረት 15፣18)

ኤፍሬም

ኤፍሬም የዮሴፍ ሁለተኛ ልጅ ነው። የእርሱ ዘር የሆኑት ኤፍሬማውያን አስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ከተሰባሰቡባቸው አንዱ ሆኗል።

  • የኤፍሬም ነገድ ከእስራኤል በስተሰሜን ክፍል ከነበሩ አሥሩ ነገዶች አንዱ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንዴ ኤፍሬም ሰሜናዊውን የእስራኤል መንግሥት በሙሉ ያመለክታል።
  • ኤፍሬም፣ “ከተራራማው የኤፍሬም አገር” ወይም፣ “የኤፍሬም ተራሮች” የሚለውን ማጣቀሻ መሠረት በማድረግ ኤፍሬም ተራራማ ወይም ኮረብታማ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ይቻላል።

እሴይ

እሴይ የቦዔዝ የልጅ ልጅና የንጉሥ ዳዊት አባት ነው።

  • እሴይ ከይሁዳ ነገድና ከቤተልሔም ከተማ የተገኘ ነበር።
  • ከእሴይ ዘሮች አንዱን አስመልክቶ ኢሳይያስ ሰፋ ያለ ትንቢት ተናግሮአል።
  • ያንን ትንቢት የፈጸመ የእሴይ ዘር ኢየሱስ ነው።

እስማኤል

እስማኤል የአብርሃምና የሥራ አገልጋይ የነበረችው የአጋር ልጅ ነው።

  • “እስማኤል” እግዚአብሔር ይሰማል ማለት ነው።
  • እስማኤል ስለ እርሱና ስለ የወደ ፊት ሕይወቱ እግዚአብሔር ለአጋር የገባላትን መለኮትዊ ተስፋ ጥቅም ተቀብሏል።
  • ይሁን እንጂ፣ በእርሱ በኩል ዘሮቹን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛ ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ የሚፈጸምበት ልጅ እስማኤል አይደለም።

እስያ

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን፥ “እስያ” የሮም መንግሥት አውራጃ ስም ነበር። በአሁኑ ጊዜ ቱርክ ከሚባለው አገር ምዕራባዊ ክፍል ነበር የሚገኘው።

  • ጳውሎስ ወደእስያ ተጉዞ እዚያ ለነበሩ ጥቂት ከተሞች ወንጌልን ሰብኳል። ከእነዚህ ከተሞች መካከል ኤፌሶንና ቆላስይስ ይገኙበታል
  • በዚህ ዘመን ካለው እስያ ጋር እንዳይምታታ፥ ይህን “እስያ የሚባለውን የጥንቱ የሮም አውራጃ” ወይም “የእስያ አውራጃ” በማለት መተርጎም ያስፈልጋል።
  • በዮሐንስ ራእይ ውስጥ የተጠቀሱ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የእስያ የሮም አውራጃ ውስጥ ነበሩ

እስጢፋኖስ

እስጢፋኖስ የመጀመሪያው ክርስቲያን ሰማዕት ማለትም በኢየሱስ በማመኑ የተገደለ የመጀመሪያ ሰው በመሆኑ ይበልጥ ይታወቃል። ሕይወቱንና አሟሟቱን የሚያመለክት ዝርዝር ሐዋርያት ሥራ የተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል

  • እስጢፋኖስ ለመበለቶች ምግብና ለሌሎች ክርስቲያኖች የሚያስፈልገውን በማደል ክርስቲያኖችን እንዲያገለግል በጥንት ቤተ ክርስቲያን የተመረጠ ሰው ነበር
  • እግዚአብሔርንና የሙሴን ሕጎች ተሳድበሃል በማለት አይሁድ እስጢፋኖስን በሐሰት ከሰሱት
  • እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ከነበረው ግንኙነት ታሪክ በመጀመር እስጢፋኖስ በድፍረት ስለ ኢየሱስ እውነቱን ተናገረ
  • የአይሁድ መሪዎች በጣም ታቆጡ፤ እስጢፋኖስን ከከተማ ውጪ በድንጋይ ቀጥቅጠው ገደሉት
  • እርሱ ሲገደል በኋላ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ የተባለው የጠርሴሱ ሳውል ይመለከት ነበር
  • እስጢፋኖስ ከመሞቱ በፊት፣ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ኅጢአት አትቁጠርባቸው” በማለት በተነገረው የመጨረሻ ቃሉ በሚገባ ይታወቃል፤ ይህን ማለቱ ለሌሎች የነበረውን ፍቅር ያመለክታል

እንድርያስ

  • እንድርያስ ደቀ መዛሙርቱ እንደሆኑ እየሱስ ከመረጣቸው አሥራ ሁለት ሰዎች አንዱ ነበር(በኋላ ሐዋርያት የተባሉት)።
  • የእንድርያስ ወንድም ስምዖን ጴጥሮስ ይባል ነበር፤ሁለቱም ዓሣ አጥማጆች ነበሩ።
  • ደቀ መዛሙርቱ እንደሆኑ እየሱስ በጠራቸው ጊዜ ጴጥሮስና እንድርያስ በገሊላ ባሕር ዓሣ እያጥጠመዱ ነበር፤
  • ጴጥሮስና እንድርያስ ከእየሱስ ጋር ከመገንኛተቸው በፊት ያአጥማቂው የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ነበሩ።

ኦርዮን

ኦርዮን ጻድቅ ሰውና ከንጉሥ ዳዊት ምርጥ ወታደሮች አንዱ ነበር።

  • ኦርዮን ቤርሳቤህ የምትባል በጣም ቆንጆ ሚስት ነበረችው።
  • ዳዊት ከኦርዮን ሚስት ጋር አመነዘረ፤ እርሷም ከዳዊት ፀነሰች።
  • ኀጢአቱን ለመሰወር ዳዊት ኦርዮንን አስገደለ፤ ከዚያም ዳዊት ቤርሳቤህን አገባ።

ከለድ፣ ከለዳዊ

ከለድ የመስጶጤምያ ወይም የባቢሎን ደቡባዊ ክፍል የነበረ ቦታ ነበር። በዚህ ቦታ የነበሩ ስዎች ከለዳውያን ይባሉ ነበር።

  • የአብርሃም አገር የነበረው ዑር ከተማ የሚገኘው ከለድ ውስጥ ነበር። ብዙውን ጊዜ፣ “የከለዳውያን ዑር” ተብሎም ይጠራል።
  • ንጉሥ ናቡከደነፆር የባቢሎን ንጉሥ ከሆኑት ጥቂት ከለዳውያን አንዱ ነበር።
  • ከብዙ ዓመታት በኋላ በ600 ዓቅክ አካባቢ፣ “ከለዳዊ” የሚለው ቃል፣ “ባቢሎናዊ” ማለት ሆነ።
  • ትንቢተ ዳንኤልም ውስጥ፣ “ከለዳዊ” የተሰኘው ቃል የተማሩና ስል ከዋክብት ያጠኑ የተለዩ ሰዎችንም ያመለክታል።

ከሊታውያን

ከሊታውያን ምናልባት የፍልስጥኤም አካል የነበሩ ሕዝብ ነበሩ።

  • “ከሊታውያንና ፈሊታውያን” በንጉሥዳዊት ሰራዊት ውስጥ ልዩ ወታደሮች ሲሆኑ፣ ዋናው ተግባራቸው የእርሱ ክብር ዘብ (ጠባቂ) መሆን ነበር።
  • የዳዊት አስተዳደር ክፍል አባል የነበረው ዮዳሔ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና ፈሊታውያን መሪ ነበር።
  • ኤሴሎም ባመፀ ጊዜ ዳዊት ከኢየሩሳሌም ሲሸሽ ከሊታውያን ከእርሱ አልተልዩም ነበር።

ከነዓን፣ ከነዓናዊ

ከነዓን የኖኅ ወንዶች ልጆች አንዱ የነበረው የካም ልጅ ነበር። ከነዓናውያን የከነዓን ዘሮች ናቸው።

  • “ከነዓን” ወይም “የከነዓን ምድር” የሚለው ቃል በዮርዳኖስ ወንዝና በሜዲትራንያን ባሕር መካከል የነበረውንም ቦታ ወይም አካባቢ ያመልክታል። በስተ ደቡብ በኩል እስክ ግብፅ ዳርቻና በስተ ሰሜን እስከ ሶርያ ዳርቻ ይደርሳል።
  • በዚያ ምድር ከንዓናውያንና ሌሎችም በርካታ ሕዝቦች ይኖሩ ነበር።
  • የከነዓንን ምድር ለአብርሃምና የእርሱ ዘሮች ለሆኑት እስራኤላውያን እንደሚሰጥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶአል።

ኩሽ

ኩሽ የኖኅ ልጅ ካም ትልቁ ልጅ ነበር። የናምሩድ ጥንተ አባትም ነበር። ሁለቱ ወንድሞቹ ግብፅና ከነዓን ነበር።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ “ኩሽ” ከእስራኤል በስተ ደቡብ የሚገኝ በጣም ሰፊ አካባቢ ነበር። ቦታው ስያሜውን ያገኘው ከካም ልጅ ከኩሽ እንደ ሆነ ይታሰባል።
  • በጥንት ዘመን የኩሽ ምድር በተለያዩ ዘመን ውስጥ ሱዳንን፣ ግብፅን፣ ኢትዮጵያንና ምናልባትም ሳዑዲ አረቢያን ያጠቃልል ነበር።
  • መዝሙር መጽሐፍ ውስጥ ኩሽ የሚባል አንድ ሌላ ሰው ተጠቅሷል። ይህ ሰው ክብንያም ነገድ ነበር።

ኪልቅያ

ኪልቅያ አሁን የዘመኑ ቱርክ ካለችበት ደቡብ ምሥራቃዊ ክፍል የነበረች አነስተኛ የሮማውያን አውራጃ ነበረች። ከኤጂያን ባሕር ጋር ይዋሰናል።

  • ሐዋርያው ጳውሎስ ኪልቅያ ውስጥ የነበረችው የጠርሴስ ሰው ነበር።
  • በደማስቆ መንገድ ከኢየሱስ ጋር ከተገናኘ በኋላ ጳውሎስ በኪልቅያ ጥቂት ዓመቶች አሳልፎ ነበር።
  • ከኪልቅያ ከመጡ አይሁድ መካከል አንዳንዶቹ እስጢፋኖስን ተቀውመው ነበር፤ በድንጋይ ቀጥቅጠው እንዲገድሉትም ሕዝቡን አንሳሥተዋል።

ካሌብ

ካሌብ የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ሙሴ ከላካቸው አሥራ ሁለት እስራኤላውያን አንዱ ነበር።

  • ከእነርሱ ትውልድ ወደ ከነዓን ምድር እንዲገቡ እግዚአብሔር የፈቀደላቸው ሰዎች ኢያሱና ካሌብ ብቻ ነበር።
  • የኬብሮን ምድር ለእርሱና ለቤተ ሰቡ እንድትሰጥ ካሌብ ጠየቀ። እዚያ የነበሩ ሰዎችን እንዲያሸንፍ እግዚአብሔር እንደሚረዳው አውቆ ነበር።

ካም

ካም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተጠቀሱት ሦስቱ የኖኅ ልጆች ሁለተኛው ነው።

  • ምድርን ሁሉ አዳርሶ በነበረው ታላቅ ጎርፍ ጊዜ፣ ካምና ወንድሞቹ ከሚስቶቻቸው ጋር ከኖኅ ጋር መርከቡ ውስጥ ነበሩ።
  • ከጎርፉ በኋላ ካም አባቱ ኖኅን እንደሚገባ ያላከበረበት ጊዜ ነበር። ከዚህም የተነሣ ኖኅ የካምን ልጅ ከነዓንንና ዘሮቹን ሁሉ ረገመ፤ እነዚህ የከነዓን ዘሮች የኋላ ኋላ ከነዓናውያን በመባል የታወቁት ናቸው።

ኬልቅያስ

ኬልቅያስ በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን የነበረ ሊቀ ካህን ስም ነው።

  • ቤተ መቅደስ በሚታደስበት ጊዜ ሊቀ ካህኑ ኬልቅያስ የሕጉን መጽሐፍ አገኘ፤ መጽሐፉ ወደ ንጉሥ ኢዮስያስ እንዲወስድም አዘዘ።
  • የሕጉ መጽሐፍ በተነበበ ጊዜ ኢዮስያስ በጣም ተነካ፤ ሕዝቡ እንደ ገና ያህዌን እንዲያመልኩና ለሕጎቹም እንዲታዘዙ አደረገ።
  • ኬልቅያስ የተባለው ሌላው ሰው የአልያቂም ልጅ ሲሆን፣ በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ቤተ መንግሥት ውስጥ ይሠራ ነበር።

ኬብሮን

ኬብሮን ከኢየሩሳሌም ደቡብ 20 ማይሎች ርቀት ላይ ያለች ከፍታ ያለው ዐለታማ ኮረብታላይ የምትገኝ ከተማ ናት።

  • ከተማዋ የተመሠረተችው በ2000 ዓቅክ ገደማ በአብራም ዘመን ነበር የብሉይ ኪዳን ታሪክ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሳለች።
  • ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ውስጥ ኬብሮን በጣም አስፈላጊ ድርሻ አላት። አቤሴሎምን ጨምሮ፣ ከልጆቹ ጥቂቱ የተወለዱት እዚያ ነበር።
  • 70 ዓ.ም. ላይ ከተማዋ በሮማውያን ተደምስሳለች።

ኬጢያዊ

ኬጢያውያን በልጁ በከነዓን በኩል የካም ዘሮች ነበር። በአሁኑ ዘመን ቱርክ በሚባለውና ከፐስቲና በስተ ሰሜን ባለው አካባቢ ታላቅ መንግሥት ሆነው ነበር።

  • በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ደረጃ ኬጢያውያን ሁሌም ለእስራኤል ስጋት ነበሩ።
  • የሞተችው ሚስቱ ሣራን እዚያ በነበረ ዋሻ ውስጥ መቅበር እንዲችል አብርሃም ከኬቲያዊው ኤፍሮን ርስት ገዛ። የኋላ ኋላ አብርሃምና ከዘሮቹ ብዙዎቹ የተቀበሩት በዚያ ዋሻ ነበር።
  • ሁለት ኬቲያውያን ሴቶች ባገባ ጊዜ የኤሳው ወላጆች አዝነው ነበር።
  • ከዳዊት ኀያላን ሰዎች አንዱ ኬጢያዊው ኦርዮን ነበር።
  • ከሰሎሞን ባዕዳን ሚስቶች አንዳንዶቹ ኬጢያውያን ነበር። እነርሱ ያመልኳቸው ከነበሩ ሐሰተኛ አማልክት የተነሣ እነዚህ ሴቶች የሰሎሞንን ልብ እግዚአብሔርን ከማምለክ መለሱት።

ኮሬብ

የኮሬብ ተራራ አሥሩ ትእዛዞች የተጻፈባቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠበት የሲና ተራራ ሌላ ስም ነው።

  • በጎቹን እየጠበቀ ሳለ ሙሴ የሚቃጠለውን ቁጥቋጦች ያየው በኮሬብ ነበር።
  • ዐለቱን በበትሩ በመታው ውሃ ለጠማቸው እስራኤላውያን ውሃ እንደሚያወጣ እግዚአብሔር ለሙሴ የነገረው በኮሬብ ነበር።
  • የዚህ ተራራ ትክክለኛ ቦታ የት እንደ ሆነ አይታወቅም፤ ይሁን እንጂ፣ የሲና ባሕረ ገብ ደቡባዊ ክፍል ላይ ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል።
  • አንዳንድ ምሁራን፣ “ኮሬብ” ትክክለኛ የተራራ ስም ሲሆን፣ “የሲና ተራራ” የሚለው ግን ሲና በረሐ ውስጥ የነበረውን ተራራው የነበረበትን ቦታ ያመለክታል በማለት ያስባሉ።

ዐባይ ወንዝ፣ የግብፅ ወንዝ

ዐባይ ወንዝ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ በጣም ረጅምና ሰፊ ወንዝ ነው።

  • ዐባይ ወንዝ በግብፅ ውስጥ ወደ ሰሜን ይፈስሳል፤ ከዚያም ሜዲትራንያን ባሕር ውስጥ ይገባል።
  • ለም በሆነ፣ ሸለቆው ውስጥ እህል በጥሩ ሁኔታ ያድጋል።
  • የሚጠጡት ውሃ እና የሚመገቡት ምግብ ዋና ምንጭ በመሆኑ አብዛኞቹ ግብፃውያን ዐባይ ወንዝ አጠገብ ይኖራሉ።
  • ሙሴ ሕፃን እያለ ቅርጫት ውስጥ ሆኖ ዐባይ ወንዝ ዳር ያሉ ቄጤማዎች መሐል እንዲሆን ተደርጎ ነበር።

ዑር

ዑር በጥንቱ ከለድያ አካባቢ ኤፍራጥስ ወንዝ ዳር የነበረ ጠቃሚ ከተማ ሲሆን የሚገኘው በዚህ ዘመን ኢራቅ በሚባለው አገር ውስጥ ነው።

  • አብርሃም የመጣው ከዑር ነበር፤ ወደ ምድረ ከነዓን እንዲሄድ እግዚአብሔር የጠራው ከዚያ ነበር።
  • የአብርሃም ወንድምና የሎጥ አባት ሐራን የሞተው በዑር ነበር። ምናልባትም ዑርን ለቅቆ በወጣ ጊዜ ሎጥ ከአብርሃም ጋር እንዲሄድ ምክንያት የሆነው ይህ ሊሆን ይችላል።

ዓረባ

በብሉይ ኪዳን ዘመን ዓረባ የሚለው አገልላለጽ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ በስትደቡብ ወደ ሰሜናዊ የቀይ ባህር ጫፍ የሚዘረጋ የነበረውን ሸለቆ ጨምሮ በጣም ስራ በረሐ ለጥ ያለ ሜዳ ያመለክታል።

  • ከግብጽ ወደ ከነዓን ሲጎዙ እስራኤላዊያን በዚህ በረሐ አካባቢ ውስጥ አልፈው ነበር።
  • የዓረብ ባሕር- ዓረብ ባሕር አካባቢ ያለ ባሕር ተብሎ መተርጎም ይቻላል፤ይህ ባሕር አብዛኛውን ጊዜ የጨው ባሕር ወይም ሙት ባሕር በመባል ይታወቃል፤
  • ዓረባ የሚለው አገላለጽ በአጠቃላይ ማንኛውንም በረሐማ አካባቢ መግለጫ ሊሆን ይችላል።

ዓይንጋዲ

ዓይንጋዲ ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምሥራቅ ይሁዳ ምድረ በዳ ላይ የምትገኝ ከተማ ስማ ነው።

  • ዓይንጋዲ የሚገኘው ከጨው ባሕር ምዕራባዊ ዳርቻ ላይ ነበር።
  • የስሙ ከፊል፣ “ምንጭ” ማለት ሲሆን ከከተማው ወደ ባሕሩ የሚያልፈውን የውሃ ምንጭ ለማመልከት ይሆናል።
  • ዓይጋንዲ በሚያማምሩ የወይን እርሻዎቹና ምናልባትም ያለሟቋረጥ ከሚፈሰው ምንጭ የተነሣ ሌሎች ለም ቦታዎቹ ይታወቃል።
  • በዓይጋንዲ ንጉሥ ሳኦል ባሳደደው ጊዜ ዳዊት ሸሽቶ የተደበቀበት ዋሻ (ምሽግ) ነበር።

ዕንባቆም

ዕንባቆም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የነበረ የብሉይ ኪዳን ነቢይ ነው።

  • ነቢዩ ትንቢተ ዕንባቆምን የጻፈው በ600 ዓቅክ ኢየሩሳሌም በባቢሎናውያን ከመያዝዋ በፊት ነበር።
  • ዕንባቆም በአብዛኛው ትንቢት የተናገረው ከለዳውያንን (ባቢሎናውያንን) አስመልክቶ ሲሆኑ፣ ከነቢዩ ኤርምያስ ቀደ ባሉት ዓመታት ጋር በአንድ ዘመን የነበረ ሰው ነው።
  • በጣም ታዋቂ ከሆነው የዕንባቆም ቃሎች አንዱ፣ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” የሚለው ነው።

ዕዝራ

ዕዝራ እስራኤላዊ ካህንና የአይሁድ ሕግ ሊቅ ነበር፤ ለ70 ዓመት በባቢሎን ምርኮ ከኖሩ በኋላ ወደኢየሩሳሌም የተመለሱ እስራኤላውያንን ታሪክ በጽሁፍ ያሰፈረ እርሱ ነበር።

  • ዕዝራ ይህን የእስራኤል ታሪክ አንድ ክፍል በጽሁፍ ያሰፈረው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኘው መጽሐፈ ዕዝራ ነው። መጀመሪያ ላይ ሁለቱም እንደአንድ መጽሐፍ ይታወቁ ስለነበር መጽሐፈ ነህምያንም የጻፈው እርሱ ሊሆን ይችላል።
  • ዕዝራ ወደኢየሩሳሌም ከተመለሰ በኋላ፣የሙሴን ህግ መጽሐፍ እንደገና ለሕዝቡ አስተዋወቀ፤ በዚያ ጊዜ እስራኤላውያን የሰንበትን ሕግ ማክበር ትተው ነበር፤ የአረማውያን ሃይማኖትን የሚከተሉ ባዕድ ሴቶች አግብተው ነበር።
  • ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ሲቆጣጠሩ የደመሰሱትን ቤተመቅደስ እንደገና የሠራ ዕዝራ ነበር።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዕዝራ በመባል የሚታወቁ ሰዎች ነበሩ።

ዖምሪ

ዖምሪ በኋላ ስድስተኛው የእስራኤል ንጉሥ የሆነ የጦር አዛዥ ነበር።

  • ዖምሪ ቴርሳ ከተማ ተቀምጦ 12 ዓመት ገዝቷል።
  • ከእርሱ በፊት እንደነበሩት የእስራኤል ንጉሦች ሁሉ ዓምሪ የእስራኤልን ሕዝብ የበለጠ ወደ ጣዓት አምልኮ የመራ ክፉ ንጉሥ ነበር።
  • ዓምሪ በክፋት የሚታወቀው የአክዓብ አባት ነበር።

ዖዝያ፣ አዛርያስ

በ800 ዓቅክ ዖዝያ በ16 ዓመቱ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፤ ለ52 ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ ይህ በጣም ረጅም ዘመን ነበር። ዖዝያ “አዛርያስ” ተብሎም ይጠራል።

  • ንጉሥ ዖዝያ በአደረጃጀቱና በወታደራዊ ችሎታው በጣም የታወቀ ነበር። ከተማውን ለመጠበቅና እዚያ ላይ ሆኖ ፍላጻዎችንና ትልልቅ ድንጋዮችን መወንጨፍ እንዲያስችለው ትልልቅ ግንቦች አስገንብቶ ነበር።
  • ጌታን እያገለገለ እስከ ነበረ ድረስ ዖዝያ በልጽጎ ነበር። ሕይወቱ ማብቂያ አካባቢ ግን ትዕቢት አደረባት፣ ካህናት ብቻ ማድረግ የነበረባቸውን ዕጣን ቤተ መቅደስ ውስጥ በማመን እግዚአብሔር ላይ ዐመፀ።
  • ከዚህ ኀጢአቱ የተነሣ በለምጽ ተመታ፤ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ከሌሎች ተገልሎ መኖር ነበረበት።

ዘሩባቤል

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዘሩባቤል ተብለው የተጠሩ ሁለት ሰዎች ነበር።

  • ከእነዚህ አንዱ የኢዮአቄምና የሴዴቅያስ ዘር ነበር።
  • የሰላይታል ልጅ ተብሎ የሚጠራው ሌላው ዘሩባቤል የባቢሎን ምርኮኞች እየተመለሱ በነበረበት አንዱ ጉዞ የይሁዳ ነገድ አለቃ ሆኖ የነበረው ነው።
  • ይኸኛው ዘሩባብል የነበረው የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እስራኤላውያን ከባቢሎን ምርኮ ነጻ እንዲወጡ ባደረገበት ዘመን ነበር።
  • ዘሩባቤልና ሊቀ ካህኑ ኢያሱ ቤተ መቅደስና የእግዚአብሔር መሠዊያ ሲሠራ ከረዱት መካከል ነበር።
  • ዘሩባቤል የነበረው ዕዝራና ነህምያ በነበሩበት ዘመን ነበር።

ዘብዴዎስ

ዘብድዎስ ዓሣ አጥማጅ የገሊላ ሰው ነበር። ያዕቆብና ዮሐንስ የተባሉ ሁለት ልጆቹ አብረውት ይሠሩ ነበር። በኋላ ግን ሥራቸውን ትተው ሁለቱም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ።


ዘካርያስ - (አዲስ ኪዳን)

ዘካርያስ በኋላ መጥምቁ ዮሐንስን የወለደ የአይሁድ ካህን ነበር።

  • ዘካርያስ እግዚአብሔርን ይወድና ለእርሱም ይታዘዝ ነበር።
  • ዘካርያስና ሚስቱ ኤልሳቤጥ ልጅ እንዲወልዱ አጥብቀው ብዙ ዓመት ቢጸልዩም፣ መውለድ አልቻሉም ነበር። በጣም ባረጁ ጊዜ ግን እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ ልጅ ሰጣቸው።
  • የእርሱ ልጅ ዮሐንስ የመሲሑን መንገድ የሚያዘጋጅ ነቢይ እንደሚሆን ዘካርያስ ትንቢት ተናገረ።

ዘካርያስ (ብሉይ ኪዳን)

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዘካርያስ ተብለው የተጠሩ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ከእነርሱም ዋና ዋናዎቹ፣

  • በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረው ታዋቂ የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂ (1ዜና 26፡2፣14)።
  • ኢዮራም የተባለው ወንድሙ የገደለው የንጉሥ ኢዮሳፍጥ ልጅ (2ዜና 21፡2)።
  • ጣዖት በማምለካቸው ስለ ገሠፃቸው ሕዝቡ በድንጋይ ቀጥቅጠው የገደሉት ካህን (2ዜና 24፡20)።
  • ለስድስት ወር ብቻ ሥልጣን ላይ ከቀየ በኋላ የተገደለው የእስራኤል ንጉሥ (2ነገሥት 14፡29)።
  • በንጉሥ ዳርዮስ ቀዳማዊ ዘመን ትንቢት የተናገረ ነቢይ። የእርሱ ትንቢት የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት እየተመለሱ የነበሩ ምርኮኞችን ያበረታታ ነበር። እርሱ የነበረው ዕዝራ፣ ነህምያ፣ ዘሩባቤልና ነቢዩ ሐጌ በነበሩበት ዘመን ነበር።

ዘኬዎስ

ዘኬዎስ የኢያሪኮ ሰው ሲሆን፣ በጣም የሚታወቀው ኢየሱስን ለማየት ዛፍ ላይ በመውጣቱ ነው።

  • ዘኬዎስ በኢየሱስ ሲያምን ሕይወቱ ሙሉ ብሙሉ ተለወጠ።
  • የሀብቱን ግማሽ ለድኾች ለመስጠት ቃል ገባ።
  • ያለ አግባብ ቀረጥ ላስከፈላቸው ሰዎች አራት እጥፍ አድርጎ ለመመለስ ቃል ገባ።

ዘዓር

ዘዓር እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን ሲያጠፋ ሎጥ ሮጦ ያመለጠባት ትንሽ ከተማ ነበረች።

  • የዘዓር የጥንት ትርጕም ትንሽ ማለት ነው።
  • ዘዓር የሙት ባሕር ደቡብ መጨረሻ ላይ ትገኝ እንደ ነበር ይታሰባል።

ዛብሎን

ዛብሎን የያዕቆብና የልያ የመጨረሻ ልጅ ሲሆን፣ ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች የአንዱ ስም ነበር።

  • ለዛብሎን ነገድ የተሰጠው ርስት ከሙት ባሕር በስተ ምዕራብ ያለው አካባቢ ላይ ነበር።
  • አንዳንዴ ዛብሎን ይህ ነገድ የነበረበትን ቦታ ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • “ዛብሎን” – “የላቀ፣ ከፍ ያለ” ማለት ነው።

የእስራኤል መንግሥት

ንጉሥ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን በሁለት መንግሥታት ተከፈሉ። የእስራኤል መንግሥት አሥሩን ነገዶች የያዘው ሰሜናዊ መንግሥት ነበር።

  • የእስራኤል መንግሥት ንጉሦች ሁሉ ክፉዎች ነበር። ሕዝቡ በኢየሩሳሌም ባለው ቤተ መቅደስ ማምለኩን እንዲተዉና ከዚያ ጣዖቶችንና ሐሰተኛ አማልክትን እንዲያመልኩ አሳምነውት ነበር። የኋላ ኋላ እንዲያጠቓችውና ብዙውን ሕዝብ እንዲማርኩ እግዚአብሔር እሦራውያንን ላከ።
  • አሦራውያን በእስራኤል መንግሥት ከቀሩት ጥቂቶች ጋር አብረው እንዲኖሩ የሌላ አገር ሰዎችን ወደዚያ አመጡ። እነዚህ የሌላ አገር ሰዎች ከእስራኤላውያን ጋር ተጋብተው፣ ሳምራውያን የተባሉት ወገኖች ተገኙ።

የእግዚአብሔር ሰው

የእግዚአብሔር ሰው የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር የያህዌ ነቢይ በአክብሮት የሚጠራበት ቃል ነው።

  • ብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በዚህ የክብር መጠሪያ ተጠርተዋል።
  • ይህ ሐረግ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሰው” ወይም፣ “እግዚአብሔር የመረጠው ሰው” ወይም፣ “እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሰው” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

የዳዊት ቤት

“የዳዊት ቤት” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር የንጉሥ ዳዊትን ቤተ ሰብ ወይም ዘር ያመለክታል።

  • ይህም፣ “የዳዊት ዘሮች” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • ኢየሱስ የመጣው ከዳዊት ዘር ስለ ነበር እርሱ፣ “የዳዊት ቤት” አካል ነው።
  • አንዳንዴ፣ “የዳዊት ቤት” ወይም፣ “የዳዊት ቤተ ሰብ” ሲል የሚያመለክተው አሁንም በሕይወት ያሉ የዳዊት ቤተ ሰብ የሆኑ ሰዎችን ነው።
  • ሌላ ጊዜ ይህ ሐረግ በጣም ጠቅለል ያለ ሲሆን፣ የሞቱትን ጨምሮ የእርሱ ዘር የሆኑትን ሁሉ ያመለክታል።

የዳዊት ከተማ

“የዳዊት ከተማ” የኢየሩሳሌምና የቤተልሔም ሌላው ስም ነው።

  • ኢየሩሳሌም ዳዊት እስራኤልን ይገዛ በነበረ ጊዜ የኖረባት ከተማ ናት።

የገሊላ ባሕር

የገሊላ ባሕር ምሥራቃዊ እስራኤል ያለ ሐይቅ ነው። የገሊላ ባሕር በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ወደ ደቡብ ከዚያም ወደ ሙት ባሕር ይፈስሳል።

  • የቅፍርናሆምና የቤተሳይዳ ከተሞች ገሊላ ባሕር አጠገብ ነበሩ
  • የገሊላ ባሕር ሌሎች ስሞች፣ የጥብርያዶስ ባሕር፣ ጌንሳሬጥ ባሕርና የጌንሳሬጥ ሐይቅ የተሰኙ ናቸው

የጨው ባሕር፣ ሙት ባሕር

ሙት ባሕር ተብሎም የሚጠራው የጨው ባሕር የሚገኘው በምዕራብ በኩል ከእስራኤል በስተደቡብና በምሥራቅ በኩል ከሞአብ መካከል ነው

  • የዮርዳኖስ ወንዝ ወደ ደቡብ ወደ ጨው ባሕር ይፈስሳል
  • ከአብዛኞቹ ባሕሮች ያነሰ በመሆኑ፣ “የጨው ባሕር” ተብሎም ይጠራል
  • ይህ ባሕር ከፍ ያለ የማዕድኖች ክምችት አለው፤ እንዲህ በመሆኑም ውሃው ውስጥ ሕይወት ያለው ነገር አይኖርም። “ሙት ባሕር” የተባለው በዚህ ምክንያት ነው
  • በአራባና በኔጌብ አካባቢ የሚገኝ በመሆኑ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህ ባሕር “የአራባ ባሕር” እና፣ “የኔጌብ ባሕር” ተብሎ ይጠራል

ያዕቆብ (የኢየሱስ ወንድም)

ያዕቆብ የማርያምና የዮሴፍ ልጅ ሲሆን፣ ከኢየሱስ ግማሽ ወንድሞች አንዱ ነበር።

  • ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ እርሱ መሲሕ መሆኑን ያዕቆብና ወንድሞቹ አላመኑም ነበር።
  • ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ ግን ያዕቆብ በእርሱ አምኗል፤ በኢየሩሳሌም የነበረችው ቤተ ክርስቲያንም መሪ ሆኗል።
  • ያዕቆብ በሌሎች አገሮች ለነበሩ ክርስቲያኖች መልእክት ጽፎአል። መልእክቱም፣ “የያዕቆብ መልእክት” ተብሎ ይታወቃል።

ያዕቆብ (የእልፍዮስ ልጅ)

የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር።


ያዕቆብ (የዘብዴዎስ ልጅ)

የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብ ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር። ዮሐንስ የሚባል ታናሽ ወንድም የነበሩት ሲሆን፣ እርሱም ከኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር።

  • ያዕቆብና ዮሐንስ፣ “የነጎድጓድ ልጆች” የተሰኘ መጠሪያ ነበራቸው፤ እንዲህ የተባሉት ምናልባት ቶሎ ስለሚቆጡ ሊሆን ይችላል።
  • ይኸኛው ያዕቆብ፣ የያዕቆብ መልእክትን ከጻፈው የተለየ ነው። ሁለቱ የተለያዩ ሰዎች መሆናቸውን ለማመልከት አንዳንድ ቋንቋዎች ስሞቻቸውን በተለየ ሁኔታ መጻፍ የሚችሉበት መንገድ ይኖራቸዋል።

ያዕቆብ፣ እስራኤል

ያዕቆብ የይስሐቅና የርብቃ ታናሹ መንታ ልጅ ነው።

  • ያዕቆብ፣ “አታላይ” ወይም፣ “አሳሳች” ማለት ነው።
  • ያዕቆብ ብልጥና አታላይ ነበር። በአታላይነቱ የበኩር ልጅነትን ውርስ እና የታላቅ ወንድሙ የኤሳውን በረከት መውሰድ ችሏል።
  • ኤሳው በጣም ተቆጥቶ ያዕቆብን መግደል ፈለገ፤ ስለዚህ ያዕቆብ የትውልድ ቦታውን ለቅቆ ሸሸ። በኋላ ግን ተመልሶ ከወንድሙ ጋር በሰላም ኖሮአል።
  • የያዕቆብን ስም እግዚአብሔር እስራኤል ወደሚል ለወጠው፣ ያም፣ “ከእግዚአብሔር ጋር ታገለ” ማለት ነው።
  • የአብርሃም ልጆች በሆኑት በይስሐቅና በልጁ በያዕቆብ በኩል እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሮቹ የገባውን ኪዳን ፈጸመ።
  • ያዕቆብ አሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት። የእነርሱ ዘሮች አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ሆነዋል።

ያፌት

ያፌት ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተጠቀሱት ሦስቱ የዮኅ ልጆች አንዱ ነው።

  • ምድርን ሁሉ ያደረሰው ጎርፍ በመጣ ጊዜ ያፌትና ሁለት ወንድሞቹ ሚስቶቻቸውን ይዘው ከአባታቸው ጋር መርከብ ውስጥ ነበሩ።
  • ታላቅ ወይም ታናሽ ወንድም መሆኑ ግልጽ አይደለም።

ይሁዳ

ይሁዳ የያዕቆብ አራተኛ ልጅ ነው እናቱ ልያ ትባላለች።

  • የይሁዳ ነገድ የሆኑት የይሁዳ ዘሮች ናቸው።
  • “አይሁድ” የሚለው ቃል የመጣው፣ “ይሁዳ” ከሚለው ነው።
  • የሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ማብቂያ ላይ የእስራኤል ሕዝብ ሲከፋፈል፣ የይሁዳ መንግሥት ደቡባዊው ክፍል ሆኗል።

ይሁዳ

“ይሁዳ” የሚለው ቃል የመጣው ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ከነበረው ይሁዳ ከሚለው ስም ነው። ጠበብ ባለና ሰፋ ባለ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

  • አንዳንዴ ከሙት ባሕር በስተ ምዕራብ በጥንተ እስራኤል ደቡባዊ ክፍል ያለውን ክፍለ ሀገር ብቻ ለማመልከት፣ “ይሁዳ” ጠበብ ባለ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል። አንዳንድ ተርጓሚዎች ይህን ይሁዳ ይሉታል።
  • አንዳንዴ ደግሞ ገሊላን፣ ሰማርያን፣ ፔርያን፣ ኤዶምያስንና ይሁዳን ጨምሮ ያጥንት እስራኤል ክፍለ ሀገሮችን ሁሉ ለማመልከት፣ “ይሁዳ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።

ተርጓሚዎቹ ልዩነቱን በጣም ግልጽ ማድረግ ከፈለጉ፣ ሰፋ ባለ መልኩ የቀረበውን ይሁዳ (ለምሳሌ ሉቃስ 1፥5) “የይሁዳ አገር” በማለት መተርጎም ይችላሉ፤ ጠበብ ባለ መልኩ (ለምሳሌ ሉቃስ 1፥39) ጥቅም ላይ ከዋለ፣ ይህ ቦታ መጀመሪያ የይሁዳ ነገድ የነበረበት የጥንቱ የእስራኤል ምድር አካል ስለነበር፣ “የይሁዳ ክፍለ ሀገር” በማለት መተርጎም ይቻላል።


ይሁዳ፣ የያዕቆብ ልጅ

የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት አንዱ ነበር። ይኸኛው ከአስቆሮቱ ይሁዳ የተለየ መሆኑን ልብ በሉ።

  • ይሁዳ የሚባል ሌላው ሰው የኢየሱስ ወንድም የነበረው ይሁዳ ነው።
  • “የያዕቆብ ወንድም” በማለት ራሱን ስላስተዋወቀ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው የይሁዳ መልዕክት የኢየሱስ ወንድም በነበረው ይሁዳ የተጻፈ ሊሆን ይችላል።
  • የይሁዳ መልዕክት የያዕቆብ ልጅ በነበረው ይሁዳ የተጻፈ ሊሆንም ይችላል

ይሁዳ፣ የይሁዳ መንግሥት

የአይሁድ ሕዝብ የሚለማመደውን ሃይማኖት ማለትም የአይሁድ ሃይማኖትን ለማመልከት አዲስ ኪዳን ከተጻፈበት ዘመን አንስቶ እስከዚህ ዘመን ድረስ፣ “ይሁዲ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ “ይሁዲ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ አልዋለም ነበር። በዚያ ዘመን የእስራኤል ሃይማኖቶች፣ “ የአይሁድ ሃይማኖት” ነበር የሚባለው።
  • የአይሁድ ሃይማኖት(ይሁዲ) እንዲታዘዙት እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጠውን የብሉይ ኪዳን ሕጎችንና መመሪያዎች ሁሉ ያጠቃልላል። በዘመናት ውስጥ የአይሁድ ሃይማኖት ውስጥ የተጨመሩ ባህሎችና ወጎችንም ሁሉ ያካትታል። ከዚያ በፊት ቃሉ ጨርሶ ስላለነበር፣ “ይሁዲ” የሚለውን ቃል ጥቅም ላይ መዋል ያለበት አዲስ ኪዳን ውስጥ ብቻ ነው።

ይሳኮር

ይሳኮር የያዕቆብ ማለትም የእስራኤል ዘጠነኛ ልጅ ነው።

  • በኋላ የያዕቆብ ዕቁባት የሆነችው የልያ አገልጋይ የነበረች ሴት ልጅ ነው።
  • የይሳኮር ነገድ ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ነው።

ይስሐቅ

ምንም እንኳ በጣም ያረጁ ቢሆኑም ለእነርሱ እንደሚሰጣቸው እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለሣራ ቃል የገባላቸው ልጅ ነው።

  • ከአብርሃም ጋር ያደረገው ኪዳን ይስሐቅንና ዘሮችንም ለዘላለም የሚያካትት እንደ ሆነ እግዚአብሔር ቃል ገብቷል።
  • ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ ለእርሱ እንዲያቀርብለት በመንገር እግዚአብሔር የአብርሃምን እምነት ፈተነ።
  • የይስሐቅ ልጅ ያዕቆብ አሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት። በኋላ ላይ ዘሮቻቸው አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ሆኑ።
  • ይስሐቅ፣ “ሳቀ” ማለት ነው። እርሱና ሣራ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ እግዚአብሔር ለአብርሃም በነገረው ጊዜ ሁለቱም በጣም አርጅተው ስለ ነበር አብርሃም ሳቀ።

ዮሐንስ (ሐዋርያው)

ዮሐንስ ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት እንዱ ነበር፤ ከኢየሱስ የቅርብ ወዳጆችም አንዱ ነበር።

  • ዮሐንስና ወንድሙ ያዕቆብ የዘብዴዎስ ልጆች ነበሩ።
  • ይኸኛው ዮሐንስ ከመጥምቁ ዮሐንስ የተለየ ሰው ነው።
  • ኢየሱስ ወደሰማይ ከተመለሰ በኋላ ዮሐንስ (ሐዋርያው) ስለ ኢየሱስ ሰዎችን አስተምሯል።
  • ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ የሚናገሩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱ አንድ ወንጌልና ሦስት መልዕክቶች ጽፏል።

ዮሐንስ (መጥምቁ)

ዮሐንስ የዘካርያስና የኤልሳቤጥ ልጅ ነበር። ዮሐንስ የተሰኘው ስም በጣም የተለመደ ከመሆኑ የተነሳ ሐዋርያው ዮሐንስን ከመሳሰሉ ዮሐንስ ከተባሉ ሌሎች ሰዎች እርሱን ለመለየት፣ “መጥምቁ ዮሐንስ” ተብሏል።

  • ዮሐንስ በእርሱ እንደሚያምኑና መሲሑን እንዲከተሉ ሰዎችን ለማዘጋጀት እግዚአብሔር የላከው ነቢይ ነበር።
  • መሲሑን ለመቀበል ዝግጁ ለመሆን ኀጢአታቸውን እንዲናዘዙ፣ ወደእግዚአብሔር እንዲመለሱና ኀጢአትን እንዲተው ዮሐንስ ለሕዝቡ ነገረ።
  • በኀጢአታቸው ለመጸጸታቸውና ከኀጢአታቸው ፊታቸውን ለማዞራቸው ምልክት እንዲሆን ዮሐንስ ብዙ ሰዎችን በውሃ አጠመቀ።

ዮሐንስ (ማርቆስ)

ዮሐንስ ማርቆስ በሐዋርያዊ ተልዕኮው ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር ከተጓዙ ሰዎች አንዱ ሲሆን፣ ማርቆስ ተብሎ ይጠራል።

  • ዮሐንስ ማርቆስ በመጀመሪያው ሐዋርያዊ ተልዕኳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር አብሮ ተጉዞ ነበር።
  • ጴጥሮስ በኢየሩሳሌም በታሰረ ጊዜ አማኞች ለእርሱ እየጸለዩ የነበረው የዮሐንስ ማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ነበር።
  • ማርቆስ ከመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት አንዱ ባይሆንም ከሐዋርያው ጳውሎስና ጴጥሮስ ተምሯል፤ በአገልግሎትም ከእነርሱ ጋር ሠርቷል።

ዮርዳኖስ ወንዝ

ዮርዳኖስ ወንዝ ከሰሜን ወደደቡብ፣ ከነዓን ተብሎ ይጠራ ከነበረው ምድር ምሥራቃዊ ድንበር ይፈስ የነበረ ወንዝ ነው።

  • በዚህ ዘመን ዮርዳኖስ እስራኤልን በምዕራብ ዮርዳኖስን በምሥራቅ ይከፍላል።
  • ዮርዳኖስ ወንዝ በገሊላ ባሕር ውስጥ ያልፍና ሙት ባሕር ውስጥ ገብቶ ይዋጣል።
  • ኢያሱ እስራኤላውያንን ወደ ከነዓን እየመራ በነበረ ጊዜ ጎረ እያለ እና ጥልቀቱም በጣም ጨምሮ በነበረ ጊዜ ዮርዳኖስን መሻገር ነበረባቸው በውስጡ ለማለፍ ወንዙ በጣም ጥልቅ ስለነበረ እነርሱ መሻገር እንዲችሉ እግዚአብሔር በተዓምር ወንዙን አደረቀው።

ዮሴፍ (ብሉይ ኪዳን)

ዮሴፍ የያዕቆብ አሥራ አንደኛ ልጅ ሲሆን፣ ለራሔል ደግሞ የመጀመሪያ ልጇ ነበር።

  • ዮሴፍ በአባቱ ዘንድ በጣም የተወደደ ልጅ ስለነበር ወንድሞቹ ቀኑበት፤ ለባርነትም ሸጡት።
  • በግብፅ አገር ባርያና እስረኛ መሆንን ጨምሮ ዮሴፍ በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ አልፏል፤ ያም ሆኖ ግን ለእግዚአብሔር ታማኝነቱን ጠብቋል።
  • እግዚአብሔር ግብፅ ውስጥ ሁለተኛ ወደነበረው የሥልጣን ደረጃ አደረሰው፤ ግብፅንና የአባቱን ቤተሰቦች በራብ ከመሞት እንዲያድን ተጠቀመበት።

ዮሴፍ (አዲስ ኪዳን)

ዮሴፍ የማርያም እጮኛ የነበረ ሲሆን፣ እንደ አባት ኢየሱስን አሳድጓል።

  • ዮሴፍ የንጉሥ ዳዊት ዘር ነበር።
  • ዮሴፍ የመሲሑ ኢየሱስ እናት እንድትሆን እግዚአብሔር ከመረጣት ድንግል ጋር ተጫጭቶ ነበር።
  • ማርያም በተአምር እንድትፀንስ ያደረገ መንፈስ ቅዱስ መሆኑንና ከማርያም የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን መልአክ ለዮሴፍ ነገረው።
  • ዮሴፍ ምልአኩ የነገረውን አመነ፤ ማርያምን ወደቤቱ በመውሰድም ለእግዚአብሔር ታዘዘ።
  • ኢየሱስ እስኪወለድ ድረስ ዮሴፍ ማርያም በድንግልና እንድትቆይ አደረገ።

ዮቶር፣ ራጉኤል

ዮቶር እና ራጉኤል የተሰኙት ስሞች የሚያመለክቱት የሙሴን ሚስት የሴፎራን አባት ነው። ራጉኤል የጎሳው ስም ሊሆን ይችላል።

  • ሙሴ በምድያም ምድር እረኛ በነበረ ጊዜ ራጉኤል የሚሉት ምድያማዊ ልጅ አገባ። ይኸ ሰው ወደኋላ፣ “የምድያም ካህን ዮቶር” ተብሎ ተጠርቷል።
  • አንድ ቀን ሙሴ በጎች በመጠበቅ ላይ እያለ በሚነድ ቁጥቋጦ ውስጥ ሆኖ እግዚአብሔር ተናገረው።
  • እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ካወጣ ጥቂት ጊዜ በኋላ የሕዝቡን ጉዳይ መዳኘትን በተመለከተ ጠቃሚ ምክር ሊሰጠው ዮቶር ምድረበዳ ውስጥ ወደነበረው ሙሴ መጣ።
  • እግዚአብሔር በግብፅ ስላደረጋቸው ተአምራት ዮቶር ሲሰማ በእግዚአብሔር አመነ።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ራጉኤል በመባል የሚታወቁ ጥቂት ሰዎች አሉ፤ ከእነርሱ አንዱ ከኤሳው ልጆች አንዱ ነው።

ዮናስ

ዮናስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ እስራኤላዊ ነቢይ ነበር።

  • እግዚአብሔር ዮናስን ወደነነዌ የላከው መቼ እንደነበር ትንቢተ ዮናስ ይናገራል።
  • ወደነነዌ እንዲሄድና ሕዝቡ ከኀጢአት እንዲመለሱ እንዲናገር እግዚአብሔር ለዮናስ ነገረው።
  • ዮናስ ግን አልታዘዘም ወደሌላ አገር ለመሄድ መርከብ ተሳፈረ።
  • መርከቡ ላይ የነበሩ ሰዎች ዮናስን ወደባሕር ጣሉት፣ አንድ ትልቅ ዓሣ ዮናስን ዋጠው።
  • ዮናስ ሥስት ቀን በዓሣ ሆድ ውስጥ ነበር።
  • ዮናስ ወደነነዌ ሄደ ለሕዝቡ ሰበከ፤ እነርሱም ከኀጢአታቸው ተመለሱ።

ዮናታን

ዮናታን ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል። ትርጉሙ፣ “ያህዌ ሰጥቷል” ማለት ነው።

  • በጣም የታወቀው ዮናታን የንጉሥ ሳኦል ትልቁ ልጅ ነበር። የዳዊት ጥብቅ ጓደኛ ነበር።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱ ሌሎች ዮናታን የተባሉ ሰዎች የሚከተሉትንም የጨምራል፤ የሙሴ የልጅ ልጅ የነበረው፤ የንጉሥ ዳዊት እኅት ልጅ፣ የካህኑ የአብያታር ልጅ፣ ዳዊትን ሲያገለግል የነበረው፣ ኤርምያስ --------ታስሮ የነበረው ዮናታን የተባለውና ሌሎች ብዙዎችም አሉ።

ዮዳሔ

ዮዳሔ ንጉሥ ለመሆን እስከበቃበት ድረስ የንጉሥ አካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ደብቆ ያቆየውና የተከላከለለት ካህን ነበር።

  • ቤተመቅደሱ ውስጥ በነበሩ ሰዎች ንጉሥ እንዲሆን በታወጀ ጊዜ፥ ዮዳሔ ወጣቱ ኢዮአስን የሚጠብቁ በመቶ የሚቆጠሩ ጠባቂዎች አዘጋጀ።
  • የበኣል መሠዊያዎችን ሁሉ እንዲያጠፉ ሕዝቡን የመራ ዮዳሔ ነበር።
  • በተቀረው የህይወት ዘመኑ ካህኑ ዮዳሔ ለእግዚአብሔር እንደታዘዘና ሕዝቡን በመልካም መንገድ እንዲገዛ ንጉሥ ኢዮአስን ሲረዳው ነበር።
  • ዮዳሔ ተብሎ የሚጠራ ሌላ ሰው የበናያስ አባት ነበር።

ዮፍታሔ

ዮፍታሔ የእስራኤል መስፍን ወይም ገዢ በመሆን ያገለገለ ከገለአድ የመጣ ጦረኛ ነበር።

  • ዮፍታሔ ዋና የሕዝቡ ታዳጊ በመሆኑ ዕብራውያን 11፥32 ላይ ስሙ ተነሥቷል።
  • ሕዝቡን ከአሞናውያን እጅ የታደገና ኤፍሬማውያንን ለማሸነፍ ሕዝቡን የመራ እርሱ ነበር።
  • ያም ሆኖ፣ ዮፍታሔ ሞኝና ችኩል ስእለት ለእግዚአብሔር ተስሎ ስለነበር፣ ያደረገው ስሕተት ሴት ልጁን መሥዋዕት እንዲያቀርብ አድርጎታል።

ደሊላ

ደሊላ ሚስቱ ባትሆንም ሳምሶን ወዶአት የበረች ፍልስጥኤማዊት ናት።

  • ደሊላ ከሳምሶን ይበልጥ ገንዘብ ትወድ ነበር።
  • እርሱን ደካማ መሆን የሚችልበትን መንገድ እንዲነግራት እንድታግባባ ፍልስጥኤማውያን ለደሊላ ገንዘብ ሰጥተዋት ነበር። የነበረው ኃይል ከእርሱ በመወሰዱ ፍልስጥኤማውያን በቀላሉ ያዙት።

ደማስቆ

ደማስቆ ሶርያ የሚባለው አገር ዋና ከተማ ነው። ዛሬም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የነበረበት ቦታ ላይ ነው ያለው።

  • ደማስቆ ሰዎች ያለ ማቋረጥ ሲኖሩባቸው ከነበሩ ጥንታዊ የዓለም አገሮች አንድ ነው።
  • አብርሃም በነበረበት ዘመን ደማስቆ የአራም መንግሥት ዋና ከተማ ነበር (የነበረው አሁን ሶርያ ያለችበት ቦታ ላይ ነበር)።
  • በመላው ብሉይ ኪዳን በደማስቆ ነዋሪዎችና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ስለ ነበረው ግንኙነት የሚያወሱ ብዙ ጥቅሶች አሉ።
  • በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ደማስቆ እንደምትጠፋ ያመልክታሉ። በብሉይ ኪዳን ዘመን አሦር ከተማዋን ያጠፋ ጊዜ እነዚህ ትንቢቶች ተፈጽመው ይሆናል፤ ወይም ደግሞ ይህች ከተማ ሙሉ በሙሉ መውደም ገና ወደ ፊት የሚፈጸም ሊሆን ይችላል።
  • ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለከተው ኢየሱስ ፊት ለፊት ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ በእርሱ የሚያምን ሰው ባደረገው ጊዜ በኋላ ጳውሎስ የተባለው ፈሪሳዊው ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ለማሰር ወደ ደማስቆ እየሄደ ነበር።

ደብረ ዘይት ተራራ

ደብረ ዘይት ተራራ ከኢየሩሳሌም ከተማ በስተ ምሥራቅ በኩል ያለ ተራራ ወይም ረጅም ኮረብታ ነው። ይህን ስሙን ያገኘው በብዛት እዚያ ከሚገኙት የወይራ ዛፎች ሊሆን ይችላል።

  • ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ለመጸለይና ዕረፍት ለማድረግ በተለያየ ጊዜ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ይሄዱ ነበር።
  • ኢየሱስ የተያዘው በጌቴሴማኒ አትክልት ቦታ ሲሆን፣ ይህ ቦታ የሚገኘው ደብረ ዘይት ተራራ ላይ ነበር።
  • “የወይራ ዛፎች ተራራ” ተብሎም ይጠራል።

ደንገል፣ ቄጤማ

“ደንገል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ውሃ ውስጥ፣ ብዙውን ጊዜም ወንዝ ወይም ምንጭ ዳር የሚበቅል ረጅም አገዳ ያለው ተክል ነው።

  • ሙሴ በሕጻንነቱ ዐባይ ወንዝ ዳር ባሉ ደንገሎች ወይም ቀጤማዎች መካከል ተጥሎ ነበር።
  • በጥንት ግብፅ ይህ ተክል ወረቀት፣ ቅርጫትና ጀልባ ለመሥሪያ ያገለግል ነበር።
  • የደንገል አገዳ በቀላሉ ይተጣጠፋል፤ ነፋስ ሲኖር ጎንበስ ቀና ይላል።

ዳርዮስ

ዳርዮስ የበርካታ የፋርስ ነገሥታት ስም ነው። “ዳርዮስ” የማንነት መገለጫ እንጂ መጠሪያ ስም አይደለም።

  • ሜዶናዊው ዳርዮስ” ነቢዩ ዳንኤል እግዚአብሔርን በማምለኩ እንደ ቅጣት የአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ እንዲጣል በማድረጉ ተታልሎ ነበር።
  • “የፋርስ ንጉሥ ዳርዮስ” በዕዝራና በነህምያ ዘመን በኢየሩሳሌም የነበረው ቤተ መቅደስ እንደ ገና እንዲሠራ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ረድቶ ነበር።

ዳን

ዳን አምስተኛው የያዕቆብ ልጅ ሲሆን ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ነበር። የዳን ነገድ ይኖርበት የነበረው ሰሜናዊው የከነዓን ክፍል በዚህ ስም ይጠራል።

  • አብራም በነበረበት ዘመን ከኢየሩሳሌም በስተ ምዕራብ ዳን የሚባል ከተማ ነበር።
  • ከብዙ ዓመታት በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ተስፋው ምድር ሲገባ ከኢይሩሳሌም በስተ ሰሜን 60 ማይሎች ላይ ዳን የምትባል ሌላ ከተመ ተመሥርታ ነበር።
  • የዳን ነገድ የዳን ዘሮች ሲሆን፣ ነገዱ የሚጠራውም በዚሁ ስም ነበር።

ዳንኤል

ዳንኤል ገና ወጣት እያለ በ600 ዓቅክ በባቢሎን ነጉሥ ናቡከደነፆር በምርኮ የተወሰደ እስራኤላዊ ነቢይ ነበር።

  • ይህ የሆነው ከይሁዳ ምድር ብዙ እስራኤላውያን ለ70 ዓመት የባቢሎን ምርኮኞች በሆኑበት ዘመን ነበር።
  • ዳንኤል፣ ብልጣሶር የሚሰኝ ባቢሎናዊ ስም ተሰጥቶት ነበር።
  • ዳንኤል ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ የተከበረና ጻድቅ ሰው ነበር።
  • ዳንኤል የአንዳንድ ባቢሎናውያን ነገሥታትን ሕልም ወይም ራእይ የመፍታት ችሎታ እግዚአብሔር ሰጥቶት ነበር።
  • ከዚህ ችሎታውና ከተከበረው ፀባዩ የተነሣ ዳንኤል በባቢሎን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ አመራር ቦታ ያዘ።
  • ከብዙ ዓመታት በኋላ የዳንኤል ጠላቶች ከንጉሡ በቀር ሌላ ማንም እንዳይመለክ የመከለክል ሕግ እንዲያወጣ ባቢሎናዊው ንጉሥ ዳርዮስን አሳሳቱት። ዳንኤል ግን ወደ እግዚአብሔር መጸለይን አላቋረጠም፤ ስለዚህም ተይዞ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣለ። ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር ስለ ጠበቀው አንበሶቹ አልጎዱትም።

ዳዊት

ዳዊት እግዚአብሔርን በመውደዱና እርሱን በማገልገሉ የታወቀ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ ነው። የመዝሙራት መጽሐፍ ዋናው ጸሐፊም እርሱ ነው።

  • ዳዊት ገና ትንሽ ልጅ እያለ የቤተ ሰቡን በጎች ሲጠብቅ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠው።
  • ዳዊት ብርቱ ጦረኛ ሆነ፤ በጠላቶቻቸው ላይ እንዲዘምቱ የእስራኤልን ሰራዊት መርቷል። ፍልስጥኤማዊው ጎልያድን ማሸነፉ በጣም ታዋቂ እንዲሆን አድርጎታል።
  • ንጉሥ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ሞክሮ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እርስን ጠብቀው፤ ከሳኦል ሞት በኋላም ንጉሥ አደረገው።
  • ዳዊት በጣም ከባድ ኀጢአት ፈጽሞ ነበር፤ ይሁን እንጂ ንስሐ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ይቅር አለው።
  • የንጉሥ ዳዊት ዘር በመሆኑ መሲሑ ኢየሱስ፣ “የዳዊት ልጅ” ተብሏል።

ገለዓድ

ገለዓድ የጋድ፣ የሮቤልና የምናሴ ነገዶች የነበሩበት ከዮርዳኖስ ወንዝ ምሥራቅ የነበረ ተራራማ አካባቢ ስም ነው።

  • አካባቢው ከነበረው ኮረብታማ ተፈጥሮ የተነሣ “ኮረብታማው የገለዓድ አገር” ወይም፣ “የገለዓድ ተራራ” ተብሎ ይጠራ ነበር።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ገለዓድ ተብለው የተጠሩ ጥቂት ሰዎች አሉ። ከእነርሱም አንድ የምናሴ የልጅ ልጅ ነው።

ገሊላ፣ ገሊላዊ

ገሊላ ከሰማርያ እንኳ በጣም ርቆ ሰሜናዊ የእስራኤል ጫፍ አካባቢ ነበረች።

  • ገሊላ በምሥራቅ በኩል፣ “የገሊላ ባሕር” ከሚባለው ትልቅ ሐይቅ ጋር ትዋሰናለች።
  • ኢየሱስ ያደገውና የኖረው ገሊላ ውስጥ በነበረችው ናዝሬት ነበር።

ገላትያ

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ገላትያ በአሁኑ ዘመን ማዕከላዊ ቱርክ የሚባለው ቦታ ላይ ትገኝ የነበረች የሮም ከተማ ነበረች።

  • ሐዋርያው ጳውሎስ ገላትያ ከተማ ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ ክርስቲያኖች የገላትያን መልእክት ጽፎላቸው ነበር። ይህ መልእክት አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው የገላትያ መልእክት ነው።
  • ከአሕዛብ ወገን የነበሩት የገላትያ ክርስቲያኖች አንዳንድ የሙሴን ሕጎች መፈጸም እንደሚገባቸው ከአይሁድ ክርስቲያኖች ተጽዕኖ ደርሶባቸው ነበር።
  • ጳውሎስ መልእክቱን ለገላትያ ሰዎች ከጻፈበት ምክንያት አንዱ ድነት በጸጋ እንጂ በሥራ አለመሆኑን በድጋሚ ለማስረገጥ ነበር።

ገባኦን፣ ገባኦናውያን

ገባኦን፣ ገባኦናውያን የሚኖሩባት ምድረ ከነዓን ውስጥ የነበረች ከተማና አካባቢ ናት።

  • “ገባኦናዊ” ገባኦን በሚባለው አካባቢ የሚኖር ሰው ማለት ነው።
  • እስራኤላይውና ኢያሪኮን መደምሰሳቸውን ሲሰሙ ገባኦናውያን ፈሩ። ስለዚህም ወደ እስራኤላውያን መጥተው የሩቅ አገር ሰዎች መሆናቸውን ተናገሩ።
  • እስራኤላውያን ከገባኦናውያን ጋር ውል ስላደረጉ አላጠፏቸውም

ገብርኤል

ገብርኤል ከእግዚአብሔር መላእክት የአንዱ ስም ነው።

  • በጣም አስፈላጊ መልእክቶችን ለነቢዩ ዳንኤል፣ ለካህኑ ዘካርያስና ለድንግል ማርያም እንዲናገር እግዚአብሔር ገብርኤልን ላከ።
  • ብሉይ ኪዳን እንደ ሰው እና መብረት እንደሚችል ፍጡር ተገልጿል።

ጊብዓ

ጊብዓ ከኢየሩሳሌም በስተ ሰሜንና ከቤቴል በስተ ደቡብ የነበረ ከተማ ስም ነው።

  • ጊብዓ የብንያም ነገድ ክልል ውስጥ ነበረች።
  • በብንያማውያንና በእስራኤላውያን መካከል ከባድ ውጊያ የተደረገባት ቦታ ናት።

ጋዛ

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጋዛ የሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ አካባቢ፣ ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ 77 ኪሎ ሜትር፣ ከአሽዶድ በስተ ሰሜን 38 ኪሎ ሜትር ላይ ትገኝ የነበረች በጣም አስፈላጊ የፍልስጥኤማውያን ከተማ ነበረች።

  • በጥንት ዘመን ጋዛ በእስያና በግብፅ መሐል ያለች የወታደራዊና የንግድ መተላለፊያ በር ነበረች።
  • በዚህ ዘመንም ጋዛ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ወደብ ስትሆን፣ ሜዴትራንያን ባሕር ዳርቻ አካባቢ የምትገኝና በስተ ሰሜንና በስተ ምሥራቅ ከእስራኤል ጋር፣ በስተ ደቡብ ከግብፅ ጋር ትዋሰናለች።
  • ፍልስጥኤማውያን ሳምሶንን ከያዙት በኋላ የወሰዱት ወደ ጋዛ ነበር።
  • ወንጌላዊው ፊልጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ያገኘው ወደ ጋዛ በሚወስደው የበረሐ መንገድ ላይ ነበር።

ጋይ

በብሉይ ኪዳን ዘመን ጋይ ከቤቴል በስተ ደቡብ ከኢያሪኮ ሰሜን ምዕራብ 8 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኝ የከነዓናውያን ከተማ ስም ነበረች።

  • ኢያሪኮን ካሸነፈ በኋላ ጋይን እንዲያጠቁ ኢያሱ እስራኤላውያንን መራ። ይሁን እንጂ፣እግዚዘብሔር በእርሱ ደስ በለ መሰኘቱ በቀላሉ ተሸነፉ።
  • አካን የሚባል እስራኤላዊ ከኢያሪኮ የተገኘውን ምርኮ ሰርቆ ነበር፤እርሱና ቤተሰቦቹ እዲገደሉ እግዚአብሔር አዘዘ። ከዚያ በኃላ የጋይን ሕዝብ ድል እንዲያደርጉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ረዳቸው።

ጋድ

ጋድ ከያዕቆብ ማለትም ከእስራኤል ልጆች የአንዱ ስም ነው። የጋድ ቤተሰብ ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ሆነዋል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጋድ ተብሎ የተጠራ ሌላ ሰው የእስራኤልን ሕዝብ በመቁጠር ኃጢአት ባደረገ ጊዜ ንጉሥ ዳዊትን እንዲገሥጽ የተላከው ነቢይ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “የጋድ ሸለቆ” የሚባል ቦታ ተጠቅሷል።

ጌልጌላ

ጌልጌላ ከኢያሪኮ በስተ ሰሜን ያለች አገር ስትሆን፣ ወደ ከነዓን ለመግባት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ ከተሻገሩ በኋላ የሰፈሩባት የመጀመሪያ ቦታ ናት።

  • እነርሱ ከተሻገሩት የዮርዳኖስ ወንዝ ደረቅ ምድር የወሰዳቸውን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ኢያሱ የተከለው በጌልጌላ ነበር።
  • ኤልያስ ወደ ሰማይ በሚወሰድበት ጊዜ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ሲሄዱ ኤልያስና ኤልሳዕ ተነሣሥተው የሄዱት ከጌልጌላ ነበር።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “ጌልጌላ” ተብለው የተጠሩ ሌሎች ጥቂት ቦታዎች ነበር።
  • “ጌልጌላ” ማለት፣ “የድንግይ ክብ” ማለት ነው። እንዲህ የተባለው እዚያ ተሠርቶ በነበረው ክብ ቅርጽ በነበረው መሠዊያ የተነሣ ሊሆን ይችላል። ከሚሽከረከር ነገር የተያያዘ ነገርን የሚያመለክትም ቃል ነው።

ጌሣም

ጌሣም ከግብፅ ሰሜናዊ ክፍል አካባቢ የሚገኝ ቦታ ስም ነበር።

  • ዮሴፍ ግብፅ ውስጥ ባለ ሥልጣን በነበረ ጊዜ በከነዓን ከነበረው ራብ አምልጠው እባቱ ወንዶቹና ቤተ ሰቦቻቸው እዚያ ለምኖር ወደ ጌሤም መጥተው ነበር።
  • እነርሱና ዘሮቻቸው ለ400 ዓመት በጌሤም ከኖሩ በኋላ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን በባርነት እንዲያገለግሉ አስገደዳቸው።

ጌራራ

ጌራራ ምድረ ከነዓን ውስጥ የነበረ ከተማና አካባቢ ሲሆን፣ ከኬብሮን ደቡብ ምዕራብና ከቤርሳቤህ ሰሜን ምዕራብ ይገኝ ነበር።

  • አብርሃምና ሥራ እዚያ በነበሩ ጊዜ ንጉሥ አቢሜሌክ የጌራራ ንጉሥ ነበር።
  • እስራኤላውያን በከነዓን በነበሩ ዘመን ፍልስጥኤማውያን ጌራራ አካባቢ በብዛት ይኖሩ ነበር።

ጌርሳውያን

ጌርሳውያን የኖኅ ልጅ የካም ልጅ የሆነው የከነዓን ዘሮች ይኖሩበት በነበረው ምድረ ከነዓን የነበሩ ነገድ ናቸው።

  • ጌርሳውያን የኖኅ ሦስት ልጆች ዘሮች በሚዘረዘሩበት ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ስማቸው ተጠቅሷል።
  • ጌርሳውያን፣ “ከነዓናውያን” ተብለው ከሚጠሩ በርካታ ሕዝቦች አንዱ ናቸው።

ጌሹር

በንጉሥ ዳዊት ዘመን ጌሸር ከገሊላ ባሕር በስተ ምሥራቅ በኩል፣ በእስራኤልና በአራም አገሮች መካከል የነበረች ታናሽ መንግሥት ነበረች።

  • የንጉሡ ልጅ መዓካን በማግባት ዳዊት ከጌሹር ጋር ኅብረት አደረገ።
  • መዓካ ከዳዊት አቤሴሎምን ወለደች።
  • ከፊል ወንድሙ የነበረውን አምኖንን ከገደለ በኋላ አቤሴሎም ከኢየሩሳሌም ሰሜን ምሥራቅ 88 ማይሎች ርቀት ላይ ወደ ጌሹር ሸሸ።

ጌቴሴማኒ

ጌቴሴማኒ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከቄድሮን ሸለቆ ማዶ፣ ደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ያለ የወይራ ዛፎች የነበሩበት አትክልት ቦታ ነው።

  • የጌቴሴማኒ አትክልት ቦታ ኢየሱስና ተከታዮቹ ከሕዝቡ ርቀው ብቻቸውን ለመሆንና ለማረፍ የሚሄዱበት ቦታ ነበር።
  • በይሁዳ አማካይነት ተላልፎ ከመስጠቱና ከመያዙ በፊት ኢየሱስ በጸሎት የቃተተው እዚያ ነበር።

ጌት

ጌት ከአምስቱ የፍልስጥኤም ዋና ዋና ከተሞች አንዷ ነበረች። የምትገኘው ከአቃሮን በስተ ሰሜንና ከአሾዶድና ከአስቄሎና በስተ ምሥራቅ ነበር።

  • የፍልስጥኤማውያን ጀግና ጎልያድ አገር ጌት ነበር።
  • በሳሙኤል ዘመን ፍልስጥኤማውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከእስራኤል ዘርፈው አአሽደድ ወደ ነበረው የአረማውያን ቤተ መቅደስ ከዚያም ወደ ጌት ወስደውት ነበር። ሆኖም. እግዚአብሔር የነዚህ ከተሞችን ሰዎች በበሽታ በመቅጣቱ፣ ወደ እስራኤል መለሱት።
  • ዳዊት ከንጉሥ ሳኦል በሸሸ ጊዜ ወደ ጌት ሄዶ ከሁለት ሚስቶቹ ጋር ለአጭር ጊዜ እዚያ ኖረ።

ጌዴዎን

ጌዶዎን እስራኤልን ከጠላቶቻቸው እንዲያድን እግዚአብሔር ያስነሣው እስራኤላዊ ነው።

  • ዴሴዎን የነበረው እስራኤላውያን ከነዓን ከገቡ ብዙ ዓመታት በኋላ ሜዶናውያን የተባለ ሕዝብ እነርሱን እያጠቃ በነበረበት ዘምን ነበር።
  • ጌዴዎን ሜዶናውያንን በጣም ፈትሯቸው ነበር፣ እግዚአብሔር ግን ሜዶናውያንን እንዲወጉና እንዲያሸንፉ እስራኤልን እንዲመራ ተጠቀመበት።

ግሪክ

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ግሪክ የሮም መንግሥት ግዛት ውስጥ ያለች አገር ነበረች።

  • እንደ አሁኗ ዘመን ግሪክ ሁሉ ከሜዲትራንያን ባሕር፣ ከኤጅያንና ሎንያን ባሕር ጋር በሚዋሰን በአብዛኛው በውሃ በተከበበ መሬት ላይ ትገኝ ነበር።
  • በመጀመሪያው መቶኛ ዓመት ግሪክ ውስጥ ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች ተመሥርተው ነበር፤ ከእነዚህም መሐል ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ ከተሞች፣ በተሰሎንቄና በፊልጵስዩስ የመሠረታቸው ቤተ ክርስቲያኖች ይገኛሉ።
  • ከግሪክ አገር የተገኙ ሰዎች ግሪካውያን ይባላሉ። በሮም ግዛት ውስጥ ጥቂት ግዛት ውስጥ ጥቂት አይሁዶችን ጨምሮ ግሪክኛ የሚናገሩ ሌሎች ብዙ ሰዎች ነበሩ።

ግሪክ፣ ግሪካዊ፣ የግሪክ ባሕል

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ግሪክኛ በግሪክና በመላው የሮም መንግሥት ብዛት መግባቢያ ቋንቋ ነበር፤ የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት የተጻፉት በግሪክኛ ነበር።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንዴ አይሁድ ያልሆነ ሰውን በአጠቃላይ ለሚመለከት “ግሪክ” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ይውል ነበር። ይህም በዚያ ዘመን ሮም መንግሥት ግዛት ውስጥ የነበሩ አብዛኞቹ አይሁድ ያልሆኑ ሰዎች የተለያዩ አገር ሰዎች ቢሆኑ እንኳ ግሪክኛ ይናገሩ ስለ ነበር ነው። ለዚህ ምሳሌ የምትሆነን ማርቆስ 7 ላይ የተጠቀሰችው ሴርፊኒቃዊት ሴት ናት።
  • አይሁድ ያልሆነ ሰውን አስመልክቶ በዚህ መልኩ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “ግሪክ” የሚለውን፣ “አሕዛብ” አይሁድ በግሪክ ባሕል ውስጥ ተወልደው ያደጉና ግሪክኛ ይናገሩ የነበሩ አይሁድ ናቸው። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች “ግሪክ” የሚለውን የግሪክን ባሕል የተቀበለ በማለት ተርጉመዋል። ይህም ዕብራይስጥን ብቻ የሚናገሩ አይሁድ፣ “ዕብራውያን” ተብለው እንደሚጠሩት ማለት ነው።

ግብፅ፣ ግብፃዊ

ግብፅ ከአፍሪካ ሰሜን ምሥራቅ ክፍል፣ ከምድር ከነዓን ደቡብ ምዕራብ የምትገኝ አገር ነች።

  • ግብፃዊ በግብፅ የተወለደና ዘሮቹም ከዚያው ከግብፅ የሆነ ሰው ነው።
  • ጥንታዊቷ ግብፅ ላይኛውና ታችኛው ግብፅ በመባል ለሁለት ትከፈል ነበር። “ታችኛው ግብፅ” የሚባለው፣ የአባይ ወንዝ ወደ ሜዲትራንያን ባሕር የሚገባበት አካባቢ ነበር።
  • ማርያምና ዮሴፍ ከሄሮድስ ለመሸሽ ሕፃኑ ኢየሱስን ይዘው ወደ ግብፅ ሄደው ነበር።
  • ብዙ ጊዜ በከነዓን የምግብ እጥረት ሲያጋጥም፣ እስራኤላውያን ጥንተ አባቶች ለቤተ ሰቦቻቸው ምግብ ለመግዛት ወደ ግብፅ ይሄዱ ነበር።

ጎልያድ

ጎልያድ ዳዊት በወንጭፍ ድንጋይ የገደለው ግዙፍ ፍልስጥኤማዊ ወታደር ነበር።

  • ጎልያድ ከሁለት እስከ ሦስት ሜትር ይረዝም ነበር። በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሣ ብዙውን ጊዜ ጊዜ ግዙፍ ሰው እየተባለ ይጠራል።
  • ምንም እንኳ ጎልያድ የበለጠ መሣሪያ ቢኖረውም፣ ከዳዊት የበለጠ ግዙፍ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ለዳዊት ጎልያድን የሚያሸንፍበትን ብርታትና ችሎታ ሰጠው።
  • ዳዊት ጎልያድን ድል ከማድረጉ የተነሣ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ድል እንዳደረጉ ተቆጠረ።

ጎልጎታ

“ጎልጎታ” ኢየሱስ የተሰቀለበት ቦታ ስም ነው። ቃሉ የመጣው፣ “የራስ ቅል” ወይም፣ “የራስ ቅል ቦታ” ከተሰኙ የአረማይክ ቃል ነው።

  • ጎልጎታ ከኢየሩሳሌም ከተማ ቅጥር ውጭ ባለው የደብረ ዘይት ተራራ ክፍል በሆነ ቦታ ይገኝ ነበር።
  • አንዳንድ ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ጎልጎታን፣ “ቀራንዮ” በማለት ይተረጉሙታል፤ ይህም በላቲን የራስ ቅል ማለት ነው።

ጎሞራ

ጎሞራ ከባቢሎንያ አካባቢ በስተ ምሥራቅ ባለው በጣም ለም ሸለቆ ውስጥ አንድ ቦታ ላይ የነበረች ከተማ ነበረች።

  • ብዙውን ጊዜ ጎሞራ ከሰዶም ጋር ተያይዛ ትጠቀሳለች፤ የእነዚህ ከተማ ሰዎች በክፉ ሥራቸው የታወቁ ነበር።
  • ሰዶምና ጎሞራ በነበሩበት ቦታ ብዙ ነገሥታት እየተዋጉ ነበር።
  • በሰዶምና በሌሎችም ከተሞች መካከል በተደረገው ግጭት የሎጥ ቤተ ሰብ ተይዞ በተወሰደ ጊዜ ያስጣሏቸው አብርሃምና አብረውት የነበሩ ሰዎች ነበሩ።
  • ይህ ከሆነ በኋላ ብዙም ሳይቆም እዚያ ከነበሩ ሰዎች ኀጢአት የተነሣ እግዚአብሔር ሰዶምና ጎሞራን አጠፋ።

ጎቶልያ

ጎቶልያ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ሚስት ስትሆን፥ በጣም ክፉ ሴት ነበርች። በክፋቱ የታወቀው የእስራኤል ንጉሥ የዘምሪ የልጅ ልጅ ነበረች

  • የጎቶልያ ልጅ አካዝያስ ኢዮራም ከሞተ በኋላ ንጉሥ ሆነ።
  • ልጇ አካዝያስ ሲሞት ጎቶልያ የተቀረውን የንጉሡን ቤተሰብ በሙሉ ለመግደል አቀደች
  • ሆኖም፥ የጎቶልያ ትንሹ የልጅ ልጅ ኢዮአስን አክስቱ ደብቃው ስለነበር ከሞት ተረፈ፤ በኋላም የይሁዳ ንጉሥ ሆነ።

ጠርሴስ

ጠርሴስ በአሁኑ ዘመን ማዕከላዊ ደቡብ ቱርክ ባለበት የሮም ኪልቂያ አውራጃ ውስጥ የነበረች ጥንታዊ ሀብታም ከተማ ናት

  • ዋነኛ ወንዝና ሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ ላይ የነበረች መሆኗ በጣም ተፈላጊ የንግድ መተላለፊያ አድርጓታል
  • በታሪክ አንድ ወቅት ላይ የኪልቅያ ዋና ከተማ ሆና ነበር
  • ጠርሴስ የሐዋርያው ጳውሎስ ትውልድ ቦታ ናት

ጢሞቴዎስ

ጢሞቴዎስ እርሱ በነበረበት ልስጥራ ከተማ ጳውሎስ ባገለገለ ጊዜ በክርስቶስ ያመነ ወጣት ሰው ነበር። በኋላም ጳውሎስ ባደረገው በርካታ ሐዋርያዊ ጉዞ አብሮት ነበር፤ የአዲስ አማኞች ማኅበረ ሰብ መጋቢ በመሆንም አገልግሏል።

  • አያቱ ሎይድና እናቱ አውንቅ በክርስቶስ ያመኑ አይሁዳውያን ቢሆኑም፣ አባቱ ግሪካዊ ነበር።
  • ጢሞቴዎስ በግማሽ ጎኑ አይሁዳዊ ስለ ነበር እነርሱን ቅር ሲያሰኝ ከአይሁድ ጋር ተገናኝቶ እንዲያገልግላቸው ጳውሎስ ገረዘው።
  • ጳውሎስና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እጃቸውን በመጫንና በጸሎት ወግ ባለው ሁኔታ ጢሞቴዎስን ሾሙት።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥያሉትን አንደኛና ሁለተኛ የጢሞቴዎስ መልእክቶች ጳውሎስ የጻፈው የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ወጣት መሪ ለነበረው ጢሞቴዎስ መመሪያ ለመስጠት ነበር።

ጢሮስ

ጢሮስ በአሁኑ ዘመን ሊባኖስ በሚባለው ሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ ላይ የነበረች ጥንታዊ የከነዓናውያን ከተማ ናት። የከተማዋ አንድ ክፍል ከባሕሩ ዳርቻ አንድ ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ካለው ደሴት ጋር ይያያዛል።

  • የጢሮስ ከተማ እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ከመምጣታቸው በፊት ነበረች። ሁሌም የአረማውያን ከተማ ነበረች።
  • ከነበረችበት ቦታና ከተፈጥሮ ሀብቷ የተነሣ ጢሮስ ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ሀብታም ከተማ ነበረች።
  • የጢሮስ ሕዝብ በምግባረ ብልሹነታቸው ይታወቃሉ።
  • ብዙ ጊዜ ጢሮስ አጠገቧ ካለችው ጥንታዊት ከተማ ሲዶና ጋር ትያያዛለች።

ጢሮአዳ

የጢሮአዳ ከተማ በጥንቱ የሮም እስያ አውራጃ ሰሜን ምዕራብ ባሕር ዳርቻ ትገኝ የነበረች ወደብ ናት።

  • በሐዋርያዊ ጉዞው እግረ መንገዱን ጳውሎስ ቢያንስ ሦስት ጊዜ ወደ ጢሮአዳ መጥቶ ነበር።
  • አንድ ጊዜ እዚያ እያለ ጳውሎስ ስብከቱን እስከ ዕኩለ ሌሊት ድረስ በማርዘሙ አውጤኪስ የሚባል ወጣት አንቀላፋ። የተቀመጠው የተከፈተ መስኮት አጠገብ ስለ ነበር አውጤኪስ ወድቆ ሞተ። በእግዚአብሔር ኀይል ጳውሎስ ያንን ወጣት ከሞት አስነሣው።
  • ጳውሎስ ሮም በነበረ ጊዜ ጢሮአዳ ትቶት የመጣውን መጽሐፍና ካባ እንዲያመጣለት ለጢሞቴዎስ ተናገረ።

ጤባርዮስ ቄሳር

ጤባርዮስ ቄሳር ኢየሱ ባገለገለበት ዘመን ይሁዳን እየገዛ የነበረ ሮማዊ ነው። ምንም እንኳ በእርግጥ ንጉሥ ባይሆንም አንዳንዴ “ንጉሥ ሄሮድስ” እየተባለ ይጠራል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ሄሮድስ” በሚል መጠሪያ የሚታወቁ በርከት ያሉ ሰዎች አሉ። ታላቁ ንጉሥ ሄሮድስ፣ የአንቲጳስ ቄሳር አባት ነበር። እነዚህ ሁለት ሄሮድሶች የተለያዩ ሰዎች መሆናቸውን በትጕም ሥራው በግልጽ መቀመጡን እርግጠኛ ሁኑ።
  • ሄሮድስ አንቲጳስ ዮርም ግዛት አንድ አራተኛን ይገዛ ነበር፤ ስለዚህም “የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ” ተብሎም ይጠራል።
  • መጥምቁ ዮሐንስ አንተጉ ተቆርጦ እንዲገደል ያዘዘው ሄሮድስ አንቲጳስ ነበር።
  • ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት ጥያቄ ለኢየሱስ አንዳንድ ጥያቄዎች ያቀረበለት ይኸው ሄሮድስ ነበር።

ጲላጦስ

ጲላጦስ ኢየሱስ እንዲገደል የፈረደ ሮማዊ ባለ ሥልጣን ነበር።

  • አገረ ገዢ ስለ ነበር ጲላጦስ ወንጀለኞችን በሞት የመቅጣት ሥልጣን ነበረው።
  • ጲላጦስ ኢየሱስ ተሰቅሎ እንዲገደል እንዲፈረድበት አይሁድ ፈልገው ስለ ነበር ኢየሱስ ከባድ ወንጀለኛ እንደ ነበር በሐሰት ተናገሩ።
  • ኢየሱስ ንጹሕ ሰው እንደ ነበር ጲላጦስ ቢያውቅም፣ ሕዝቡን በመፍራቱ ወታደሮቹ ኢየሱስን እንዲሰቅሉት አዘዘ።

ጳርቴ፣ ጳንጦስ

ጳርቴ ወይም ጳንጦስ በሮም መንግሥትና በጥንት ቤተ ክርስቲያን ዘመን የሮም አውራጃ ነበረች። የምትገኘው በአሁኑ ዘመን ቱርክ በሚባለው ሰሜናዊ ክፍል ጥቁት ባሕር ዳርቻ ነበር።

  • በበአለ ሃምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ መጀመሪያ ሐዋርያቱ ላይ ሲወርድ ከጳርቴ አውራጃ የመጡ ሰዎች በኢየሩሳሌም ነበሩ።
  • ግሪካዊው አጵሎስ ከጳርቴ የመጣ ነበር።
  • ጴጥሮስ በተለያዩ የጳንጦስ አካባቢዎች ተበትነው ለነበሩ ክርስቲያኖች ሁሉ መልእክት ጽፎአል።

ጳውሎስ፣ ሳውል

ጳውሎስ ለሌሎች ብዙ ሕዝቦች የምሥራቹን ቃል እንዲያደርስ ኢየሱስ የላከው የጥንት ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር።

  • ጳውሎስ ጠርሴስ በምትባል የሮም ከተማ የተወለደ አይሁዳዊ ሲሆን፣ የሮም ዜግነትም ነበረው።
  • ጳውሎስ መጀመሪያ ይጠራ የነበረው ሳውል በተባለ አይሁዳዊ ስሙ ነበር።
  • ጳውሎስ የአይሁድ ሃይማኖት መሪ ሆነ፤ እርሱ በኢየሱስ የማያምን ሰው ስለ ነበር ክርስቲያን የሆኑትን አይሁዳውያን ያስር ነበር።
  • ኢየሱስ በታላቅ ብርሃን ወደ ሳውል መጥቶ ክርስቲያኖችን ማሳደዱን እንዲያቆም ነገረው። ከዚያም ኢየሱስ ሳውልን እንዲያስተምረው አንድ ክርስቲያን ሰው ላከ፤ ጳውሎስም በኢየሱስ አመነ።
  • መጀመሪያ ላይ ሳውል ለአይሁድ ስለ ኢየሱስ ማስተማር ጀመረ።
  • በኋላም በተለያዩ የሮም ከተሞች ለነበሩ ሰዎች ስለ ኢየሱስ እንዲያስተምር እግዚአብሔር ሳውልን ላከው። በዚያ ጊዜ ጳውሎስ በተሰኘ ሮማዊ ስም መጠራት ጀመረ።
  • ጳውሎስ በተለያዩ ከተሞች የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማበረታታትና ለማስተማር መልእክቶች ጻፈ። መልእክቶቹም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ።

ጴጥሮስ፣ ስምዖን ጴጥሮስ፣ ኬፋ

እነዚህ ስሞች ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ የነበረው የጴጥሮስ መጠሪያዎች ናቸው። በጥንት ቤተ ክርስቲያን ታዋቂ መሪ ነበር።

  • ኢየሱስ እርሱን ከመጥራቱ በፊት ይህ ሰው ስምዖን ይባል ነበር።
  • በኋላ ላይ ኢየሱስ፣ ኬፋ በማለትም ጠርቶታል፤ ይህም በአረማይክ ቋንቋ “ድንጋይ” ወይም፣ “ዐለት” ማለት ነው። ጴጥሮስ ተብሎም ተጠርቷል፤ ይህም በግሪክ ቋንቋ “ድንጋይ” ወይም፣ “ዐለት” ማለት ነው።
  • በጣም የሚታወቀው ጴጥሮስ ወይም ስምዖን ጴጥሮስ በተሰኘው ስሙ ነው።
  • ሰዎችን ለመፈወሰና የኢየሱስን የምሥራች ቃል ለመስበክ እግዚአብሔር በጴጥሮስ ተጠቅሟል።
  • አማኝ ወገኖችን ለማበረታታትና ለማስተማር ጴጥሮስ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉትን ሁለት መልእክቶች ጽፏል።

ጴጥፍራ

ያዕቆብና ሚስቶቹ እንዲሁም ልጆቹ በከነዓን ምድር በነበሩ ጊዜ ጴጥፍራ የግብፅ ፈርዖን ከፍተኛ ባለ ሥልጣን ነበር። ጴጥፍራ የዘቦች አለቃ ነበር።

  • ጴጥፍራ የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍን ባርያው እንዲሆን ገዛው፤ በቤቱ ሁሉ ላይ ኃላፊ አደረገው።
  • ዮሴፍ ባልፈጸመው በደል በሐሰት በተከሰሰ ጊዜ ጴጥፍራ ዮሴፍን አሳሰረው።

ኀይል፣ ኀይላት “ኀይል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አብዛኛውን ጊዜ በታላቅ ብርታት ነገሮችን ማድረግን ወይም ነገሮች እንዲሆኑ የማድረግ ችሎታን ነው። “ኀይላት” የሚያመለክተው ነገሮች እንዲሆኑ የማድረግ ታላቅ ችሎታ ያላቸው ሰዎችን ወይም መናፍስትን ነው።

  • “የእግዚአብሔር ኀይል” ማንኛውንም ነገር በተለይም ለሰዎች የማይቻሉ ነገሮችን ለማድረግ እግዚአብሔር ያለውን ችሎታ ያመለክታል።
  • እግዚአብሔር በፈጠረው ማንኛውም ነገር ላይ ፍጹም ኀይል አለው።
  • እርሱ የሚፈልገውን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለእሕዝቡ ኀይል ይሰጣል፤ ስለዚህ በሽተኞችን ሲፈውሱ ወይም ሌሎች ተአምራት ሲያደርጉ ያንን ያደረጉት በእግዚአብሔር ለይል ነው ማለት ነው።
  • ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር በመሆናቸው ይኸው ኀይል አላቸው።

ጵርስቅላ

ጵርስቅላ ከባልዋ ከአቂላ ጋር በሐዋርያዊ ተልዕኮው ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር አብራ ትሠራ የነበረች የመጀመሪያው መቶኛ ዓመት አይሁዳዊት ክርስቲያን ነበረች።

  • ጳውሎስ አቂላና ጵርስቅላን ያገኘው በቆሮንቶስ ነበር።
  • አቂላና ጵርስቅላ ለጊዜው በሮም ኖረዋል።
  • ባልና ሚስቱ ከጳውሎስ ጋር ድንኳን ይሰፉ ነበር፤ በሐዋርያዊ ሥራውም ይረዱት ነበር።
  • አቂላና ጵርስቅላ የጳውሎስ ረዳቶች መሆናቸው አዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል።
  • ጵርስቅላ በጥንት ቤተ ክርስቲያን የነበረች ሴት መምህር መሆንዋ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳል።

ፈርዖን፣ የግብፅ ንጉሥ

በጥንት ዘመን ግብፅን ይገዙ የነበሩ ንጉሦችን ፈርዖን ነበር።

  • በጠቅላላው በ2000 ዓመቶች ውስጥ ከ300 በላይ ፈርዖኖች ግብፅን ገዝተዋል።
  • እነዚህ የግብፅ ንጉሦች በጣም ኀያልና ሀብታም ነበሩ፥
  • ከእነዚህ ፈርዖኖች አንዳንዶቹ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰዋል።
  • ብዙውን ጊዜ ይህ የማንነት መለያ እንደ ስም ጥቅም ላይ ውሏል።

ፊልጵስዩስ

ፊልጵስዩስ በጥንቷ ግሪክ ሰሜናዊ ክፍል ትገኝ የነበረች ከተማ ናት።

  • ጳውሎስና ሲላስ እዚያ ለነበሩ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ለመስበክ ወደ ፊልጵስዩስ ሄደው ነበር።
  • ጳውሎስና ሲላስ የታሰሩት በፊልጵስዩስ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን በተአምር ከእስር ቤት አወጣቸው።
  • ጳውሎስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የፊልጵስዩስ መልእክት የጻፈው ፊልጵስዩስ ለነበሩ ክርስቲያኖች ነበር።

ፊልጶስ (ሐዋርያው)

ሐዋርያው ፊልጶስ ከመጀመሪያዎቹ አሥራ ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበር።

  • ፊልጶስ የመጣው ከቤተ ሳይዳ ሲሆን፣ ናትናኤልን ከኢየሱስ ጋር ያስተዋወቀውም እርሱ ነበር።
  • አንድ ቀን ከ5000 በላይ ለሆኑ ሰዎች የሚበቃ ምግብ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ኢየሱስ ፊልጶስን ጠይቆት ነበር።
  • ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት እየበላ በነበረ ጊዜ ስለ አባቱ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር። እግዚአብሔር አብን እንዲያሳያቸው ፊልጶስ ኢየሱስን ጠየቀው።
  • ይኸኛው ፊልጶስ ከወንጌላዊው ፊልጶስ ጋር እንዳይምታታ ለማድረግ አንዳንድ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት ዘዴ ይኖራቸው ይሆናል።

ፊልጶስ (ወንጌላዊው)

በኢየሩሳሌም በነበረችው የጥንት ቤተ ክርስቲያን ፊልጶስ ለድኾችና ችግረኛ ክርስቲያኖች በተለይም ለመበለቶች ጥንቃቄ እንዳይደርጉ ከተመረጡ ሰባት መሪዎች አንዱ ፊልጶስ ነበር።

  • ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ላገኘው ኢትዮጵያዊ ጨምሮ በይሁዳና በገሊላ አውራጃዎች ውስጥ ለነበሩ ብዙ ከተማ ሰዎች ወንጌልን እንዲያዳርስ እግዚአብሔር በፊልጶስ ተጠቅሟል።
  • ከዓመታት በኋላ ፊልጶስ በቂሣርያ እየኖረ ሳለ ጳውሎስና ጓደኞቹ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ያረፉት እርሱ ቤት ውስጥ ነበር።
  • ወንጌላዊው ፊልጶስ የኢየሱስ ሐዋርያ ከነበረው ፊልጶስ የተለየ ሰው እንደ ነበር አብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ይስማማሉ።

ፊንሐስ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ፊንሐስ ተብለው የተጠሩ ሁለት ሰዎች አሉ።

  • አንዱ ፊንሐስ የአሮን የልጅ ልጅና በእስራኤል ሐሰተኛ አማልክት መመለክን አጥብቆ ይቃወም የነበረው ካህን ነበር።
  • ምድያማውያን ሴቶች ጋር በመጋባታቸውና ሐሰተኛ አማልክቶቻቸውንም በማምለካቸው እነርሱን ለመቅጣት ያህዌ ከላከው መቅሠፍት እስራኤልን ያዳነ ፊንሐስ ነበር።
  • በተለያየ ጊዜ ፊንሐስ ምድያማውያንን ለማጥፋት ከእስራኤል ሰራዊት ጋር ሄዷል።
  • ፊንሐስ ተብሎ የተጠራው ሌላው ሰው በነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ከነበረው ካህኑ ዔሊ ክፉ ልጆች አንድ ነበር።
  • ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን በጠቁበትና የኪዳኑ ታቦትንም በወሰዱበት ጊዜ ፊንሐስና ወንድሙ ሐፍኒ ተገድለዋል።

ፊንቂያ

በጥንት ዘመን ፊንቂያ ሜዲትራንያን ባሕር ዳር የምትገኝ በጣም ሀብታም ከተማ ነበረች። የአሁኗ ሊባኖስ ካለችበት ምዕራብ አካባቢ ነበር የምትገኘው።

  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን የፊንቂያ ዋና ከተማ ጢሮስ ነበረች። ሌላዋ ሁነኛ የፊንቃውያን ከተማ ሲዶን ነበረች።
  • ፊንቂያ በጣም የምትታወቀው በዝግባ ዛፎችና ሐምራዊ ጨርቅ በማቅለም ሲሆን፣ ሕዝቧ በባሕር በመጓጓዝና በንግድ የታወቀ ነበር።

ፋራን

የፋራን በረሐ ከግብፅ በስተምሥራቅና ከምድረ ከንዓን በስተደቡብ የሚገኝ ምድረበዳ ነበር። ፋራን የሚባል ተራራም ነበር፤ ምናልባትም ይህ ስም የሲና ተራራ ሌላ ስም ሊሆን ይችላል።

  • እነርሱን እንዲያባርር ሣራ አብርሃምን ካዘዘችው በኋላ ባርያይቱ አጋርና ልጇ እስማኤል በፋራን በረሐ ለመኖር ሄደው ነበር።
  • ሙሴ እስራኤልን እየመራ ከግብፅ በወጡ ጊዜ በፋራን በረሐ ውስጥ አልፈው ነበር።
  • ምድረ ከንዓንን እንዲስልሉና መረጃ እንዲያመጡ ሙሴ አሥራ ሁለት ሰዎችን ወደዚያ የላከው ፋራን ምድረበዳ ውስጥ ካለው ቃዴስ በርኔ ነበር።
  • የጺን ምድረበዳ በጣም ሰፊ የሆነው የፋራን በረሐ ክፍል ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል።

ፋርስ፣ ፋርሳውያን

ፋርስ በ550 ዓቅክ ታላቁ ቂሮስ የመሠረተው መንግሥት ነው። ማዕከሉ የነበረው የአሁኗ ዘመን ኢራን ያለችበት ቦታ ላይ ነበር። የፋርስ ነዋሪዎች፣ “ፋርሳውያን” ይባላሉ።

  • የፋርስ መንግሥት በጣም ሰፊና ኀያል ነበሩ።
  • በንጉሥ ቂሮስ ትእዛዝ አይሁድ ከባቢሎን ምርኮ ነጻ ሆኑ፤ የፋርስ መንግሥት ባደረገው እገዛ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንደ ገና ተሠራ።
  • ዕዝራና ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደ ገና ለመሥራት ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ የፋርስ መንግሥትን እየገዛ የነበረው ንጉሥ አርጤክስስ ነበር።
  • ንጉሥ አርጤክስስን በማግባቷ አስቴር የፋርስ መንግሥት ልዕልት ሆነች።

ፌርዛውያን

ፌርዛውያን በፓለስቲና ከነበሩ እስራኤላውያን ጋር ብዙ ውጊያ ያደረጉ፣ “ብሔር” ነበሩ። ስለ ማንነታቸው ወይም የት ይኖሩ እንደ ነበር ምንም ገለጻ አልተሰጠም።

  • ፌርዛውያን ከእስራኤል ጋር እንደ ተጋቡና ሐሰተኛ አማልክቶቻቸውን እንዲያመልኩ ተፅዕኖ እንዳደረጉባቸው በመጽሐፈ መሳፍትን ተደጋግሞ ተጠቅሷል።
  • ፌርዛውያን፣ ከፋርሳውያን የተለዩ ናቸው፤ ስሞቹ እንዳይምታቱ መጠንቀቅ አለባችሁ።

ፌጎር፣ ፌጎር ተራራ፣ ፌጎር በአል

ፌፎር ከጨው ባሕር በስተ ምሥራቅ ሞዓብ ምድር ውስጥ የሚገኝ ተራራ ስም ነው። የሮቤል ነገድ የሚኖረው እዚህ ነበር።

  • “ቤት ፌፎር” የፌጎር ከተማ ሌላ ስም ነበር።
  • “ፌጎር በአል” ሞዓባውያን ፌጎር ተራራ ላይ የሚያመልኩት የሐሰት አምላክ ነው።

ፍልስጥኤማውያን

ፍልስጥኤማውያን ፍልስጥኤም በመባል በሚታወቀው የሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ አካባቢ የሚኖሩ ሕዝብ ናቸው። የስማቸው ትርጕም፣ “የባሕር ሰዎች” ማለት ነው።

  • የአሽዶድ ከተማ የፍልስጥኤም ሰሜናዊ ክፍል ስትሆን፣ የጋዛ ከተማ ደግሞ ደቡባዊ ክፍል ነበረች።
  • ፍልስጥኤማውያን ይበልጥ የሚታወቁት ከእስራኤል ጋር ለብዙ ዓመት ባደረጉት ጦርነት ነው።
  • አብዛኛውን ጊዜ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የሚደረገውን ጦርነት የመራ ንጉሥ ዳዊት ሲሆን፣ ገና ወጣት እያለ ፍልስጥኤማዊው ጦረኛ ጎልያድን አሸንፎ ነበር።

ፍልስጥኤም

ፍልስጥኤም ምድረ ከነዓን ውስጥ በጣም ሰፊ የነበረው አካባቢ ስም ሲሆን፣ የምትገኘው በሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ ነበር።

  • ያ አካባቢ የሚገኘው በስተ ሰሜን ከኢዮጴ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ጋዛ በሚደርስ በጣም ለም የባሕር ዳርቻ ነበር። 64 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 16 ኪሎ ሜትር ስፋት ነበረው።
  • ፍልስጥኤም ውስጥ የሚኖሩ የዝወትር የእስራኤል ጠላት የሆኑት “ፍልስጥኤማውያን” በሚባሉት ሕዝብ ነበር።

ፔዳን አራም (ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ)

ፔዳን አራም ወደ ምድረ ከንዓን ከመሄድ በፊት የአብርሃም ቤተሰብ የነበረበት ቦታ ነው።

  • የአብርሃም ወንድም የናኮር ቤተሰብ በፔዳን አራም ቀርቶ ነበር። እነርሱ፣ “አረማውያን” በመባል ሲታወቁ ቋንቋቸውም፣ “አራማይክ” ተብሏል።
  • የካራን ከተማ የምትገኘው በፔዳን አራም ሲሆን፣ የርብቃ ወንድም ላባን ይኖር የነበረውም እዚያ ነበር።
  • ፔዳን አራም የነበረችው የአሁኗ ሶርያ ባለችበት አካባቢ ወይም ደቡብ ምሥራቅ ቱርክ አካባቢ ሊሆን ይችላል።