Genesis 47

Genesis 47:1

ዮሴፍ ሄዶ ለፈርዖን ነገረው ….ከወንድምቹም አምስት ሰዎችን ወስዶ በፈርዖን ፊት አቀረባቸው

UDB ክስተቶች በቅደም ተከተል ሲያስቀምጥ ULB ጸሐፊው እንዳስቀመጠ ይዘረዝራል (የክስተቶች ቅደም ተከተል ይመልከቱ)

Genesis 47:3

እኛ ባሪያዎችህ የበግ አርቢዎች ነን

ባሪያዎችህ በጎችን እናረባለን

ባሪያዎችህ

የዮሴፍ ወንድምች ራሳቸውን እንደ “ባሪያዎችህ” ያቀርቡታል:: ይህ ብዙ ኃላፊነት ላለው ሰው የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: ይህም እንደ አንደኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኛ ባሪያዎችህ ወይም እኛ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

እንደ አባቶቻችን

“እኛና ቅድመ አባቶቻችን ሁላችን” ወይም “እኛና አባቶቻችን ሁሉ”

በዚህ ምድር ለጊዜው ለመኖር መጥተናል

በግብጽ ለጊዜው ለመኖር መጥተናል

በጎች የሚሠማሩበት ሥፍራ የለምና

በጎች የሚሠሩበት ሣር የለምና

አሁንም

ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነገር ትኩረት ለመስጠት ነው::

Genesis 47:5

የግብጽ ምድር በፊትህ ናት

“የግብጽ ምድር ለአንተ ክፍት ነው” ወይም “መላው የግብጽ ምድር በአንተ እጅ ነው”

በመልካም ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው በጌሤም ምድር

አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው በጌሤም ምድር አኑራቸው

ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ

ይህ የሚገለጸው ከብት የማርባት ችሎታ እንዳላቸው ነው:: አት “ከመካከላቸው ከብት በማርባት ትልቅ ችሎታ ያላቸውን የሚቃውቅ ከሆነ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 47:7

ያዕቆብ ፈርዖንን ባረከው

እዚህ “ባረከው” የሚለው ለዚያ ሰው አዎንታዊና ጠቃሚ ነገሮች እንዲሆኑለት መሻቱን ገለጸ ማለት ነው

እድሜህ ምን ያህል ነው?

እድሜህ ስንት ዓመት ነው?

የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሣ ዓመት ነው

የእንግድነቴ ዘመን የሚለው ሀረግ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመዘዋወር በምድር ላይ ምን ያህል እንደኖረ ያመለክታል:: አት “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍኩት ዘመን 13ዐ ዓመት ነው” (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

የሕይወቴ ዘመኖች አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋር ሲነጻጸር ጥቂት ናቸው

ከአብርሃምና ከይስሐቅ የሕይወት ዘመን ጋር ስነጻጸር ዮሴፍ የሕይወቱ ዘመን አጭር እንደሆነ ይናገራል

ችግር የበዛበት

ያዕቆብ በሕይወቱ ብዙ ሥቃይና ችግር ተለማምዶአል

Genesis 47:11

ዮሴፍም አባቱንና ወንደሞቹን አኖረ

ከዚያም ዮሴፍ አባቱንና ወንድሙን ተንከባከባቸው በሚኖሩበት ሥፍራ እንዲመሠረቱ አደረገ

ራሚሴ ምድር

ይህ የጐሼም ምድር ሌላው ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

በየልጆቻቸው ቁጥር

እዚህ “ልጆች” በቤተሰብ ጥገኝነት ያሉ ትናንሽ ልጆች ማለት ነው:: አት “በየቤተሰቡ በሚገኙ ትናንሽ ልጆች ቁጥር”

Genesis 47:13

አሁንም

ይህ ቃል ዋናው ታሪክ በመሃል የሚቋረጥበትን ለማመልከት ተጠቅሞአል:: በዚህ ጸሐፊው የታሪኩን አድስ ክፍለ መናገር ይጀምራል::

የግብጽ ምድርና የከነዓን ምድር

ይህ በእነዚህ አገሮች የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል አት የግብጽ ሰዎችና የከነዓን ሰዎች (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

ተጐዳ

ተቀጨ ወይም ደከመ

ዮሴፍም በግብጽ ምድርና በከነዓን ምድር በእህል ሸመት የተገኘውን ገንዘብ ሰበሰበ

ዮሴፍም የግብጽና የከነዓን ሰዎች ገንዘባቸውን ሁሉ ከዮሴፍ እህል ለመሸመት አውለዋል

ዮሴፍም ሰበሰበ… ዮሴፍም አመጣ

ገንዘቡን እንዲሰበስቡና እንዲያመጡ ዮሴፍ አገልጋዮቹን እንዳዘዘ ይገመታል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

Genesis 47:15

የግብጽና የከነዓን ምድር ገንዘብ ባለቀ ጊዜ

እዚህ ምድር በዚያ ምድር የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “የግብጽና የከነዓን ሕዝቦችም ገንዘባቸው ባለቀ ጊዜ” (ምትከ ቃላት አጠቃቀምና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

የግብጽና የከነዓን ምድሮች

ከግብጽ ምድር እና ከከነዓን ምድር

ብሩ አልቆብናልና በፊትህ ስለምን እንሞታለን?

ሰዎች እህል ለመሸመት እንዴት እንደጓጉ ትኩረት ለመሰጠት ጥቃቄ ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል፡ አት “ገንዘባችን ስላለቀብን እባካችሁ እንድንሞት አታድርጉ!” (ሽንገላ አዘል አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

እህልን መገባቸው

እህል ምግብን በአጠቃላይ ይወክላል:: አት “እህልን ሰጣቸው” ወይም “እህልን አደላቸው” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 47:18

እነርሱም ወደ እርሱ መጡ

ሰዎች ወደ ዮሴፍ መጡ

እኛ ከጌታችን አንሰውርም

ሰዎችን ዮሴፍን እንደ” ጌታችን” ያመለክታሉ ይህ ትልቅ ሥልጣን ላሌው ሰው የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: ይህ እንደ ሁለተኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል:: አት” ከጌታችን የምንሰውረው የለም” ወይም “ከአንተ የምንሰውረው የለም” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

በጌታችን ፊት አንዳች የቀረ የለም

እዚህ ፊት ዮሴፍን ያመለክታል:: አት “ለጌታችን የምንሰጠው የቀረ የለንም” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

እኛ በዐይኖችህ ፊት ስለምን እንሞታለን? ምድራችንስ ስለምን ትጠፋለች?

እዚህ ዐይኖች የዮሴፍን እይታ ያመለክታሉ ሰዎች እህልን ለመግዛት ምንኛ እንደጓጉ ለማተኮር ጥያቄ ይጠቀማሉ ይህ ጥያቄ እንደ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት “እኛ ስንሞት ምድራችም ስትጐዳ እባክህን እንዲሁ ዝም ብለህ አትመለከተን” (ምትክ ቃላት አጠቃቀምና ሽንገላ አዘል አግናኝ ጥያቄዎችን ይጠቀሙ)

እኛ ለምን እንሞታለን እኛና ምድራችን

የተዘራበት ዘር ስለሌለባት ምድሪቱ የተጐዳችና ጥቅም የሌላት መሆንዋ ምድሪቱ እንደሚትሞት ተደርጐ ተነግሮአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 47:20

በዚህ መንገድ የግብጽ ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛለት

ስለዚህ ምድሪቱ የፈርዖን ሆነች

ዮሴፍ ያልገዛው የካህናቱን መሬት ብቻ ነበር

ነገር ግን የካህናቱን መሬት አልገዛም

ካህናቱ ድርጐ ያግኙ ነበር

ድርጐ በቋሚነት አንድ ሰው ለሌላ ሰው የሚሰጠው የገንዘብ ወይም የመግብ መጠን ነው:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ፈርዖን በየዕለቱ ለካህናት የተወሰነ ምግብ ይሰጥ ነበር” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

እነርሱም ፈርዖን ከመደበላቸው ይመገቡ ነበር

ፈርዖን ከሰጣቸው ይመገቡ ነበር

Genesis 47:23

በመሬት ላይ ዝሩ

ሊትዘሩ ትችላላችሁ

በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስቱ እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ ይሆናል

አምስት እጅ የሚለው ቃል ክፍልፋይ ነው፡፡ አት “በመከር ጊዜ እህላችሁን በአምስት መደብ ትከፍላላችሁ አንዱን መደብ እንደክፍያ ለፈርዖን ትሰጡታላችሁ እናም አራቱ መደቦች ለእናንተ ይሆናሉ” (ክፍልፋዮችን ይመልከቱ) ለቤተሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ (የተደበቁትን ስለመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 47:25

በዐይኖችህ ፊት ሞገስ ካገኘን

ሞገስ ማግኘት የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ማግኘት የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: ደግሞም ዐይኖች ማየትንና ማየት ሃሳብንና በየናን ይወክላል:: አት “በእኛ ከተደሰትክ” (ፈሊጣዊና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

በግብጽ ምድር

“በግብጸ ምድር ላይ” ወይም “በመላው የግብጽ ምድር”

እስክ ዛሬ ድረስ

ጸሐፊው እስከጻፈበት ጊዜ ድረስ

አንድ አምስተኛ

በዘፍጥረት 47:24 አንድ እምስተኛ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

Genesis 47:27

ንብረትንም አፈሩ እጅግም በዙ

በዙ የሚለው ቃል እንዴት እንደአፈሩ ይገልጻል እነርሱም ብዙ ልጆች ነበሩአቸው (ድርብ ቃላት ይመልከቱ)

ፍሬያማ ነበሩ

እዚህ ፍሬያማ መበልጸግ ወይም ብዙ ልጆች መኖር ማለት ነው

አሥራ ሰባት ዓመታት

17 ዓመታት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

የያዕቆብም የሕይወቱ ዘመን አንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነበር

ያዕቆብ የኖረው 147 ዓመት ነው (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

Genesis 47:29

እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን

ይህ ጊዜ እንደሚጓዝና አንድ ቦታ እንደሚመጣ ይናገራል:: አት “እስራኤል የሚሞትበት ጊዜ እንደደረሰ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

በዓይኖችህ ፊተ ሞገስን ካገኘሁ

እዚህ ዓይኖች የማየት ምትክ ቃል ነው እናም ማየት ሃሳብን ወይም አመለካከትን ይወክላል:: አት “በአንተ ፊት ሞገስ ካገኘሁ ወይም ካስደሰትኩህ” (ምትክ ቃላትና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

አሁን

ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ለሚቀጥለው ጠቃሚ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው

ሞገስ ማግኘት

አንድ ሰው በአንድ ሰው ተቀባይነቱን ማረጋገጥ ማለት ነው ፈሊጣሊ አነጋገር ይመልከቱ

እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ

ለጠንቃቃ ቃል መግባት የሚደረግ ምልክት ነው በዘፍጥረት 24:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

በጐነትንና ታማኝነትን ሊታደርግልኝ

በጐነት እና ታማኝነት የተባሉ ረቂቅ ስሞች እንደ ቅጽል ስሞች ሊተረጐሙ ይችላሉ አት በበጐነትና በታማኝነት አድርግልኝ ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ

እባክህን በግብጽ አትቅበረኝ

እባክህን የሚለው ለዚህ ጥያቄ እጽንዖት ይሰጣል

ከአባቶቼ ጋር ሳንቀላፋ

ማንቀላፋት መሞትን ለዘብ ባለ ቃል የሚገልጽ ነውፀፀ አት “በሚሞትበትና ከዚህ ቀደም የሞቱ ቤተሰቦቼን በሚገናኝበት ጊዜ” (ንኀብነት ወይም ለዘብ ባለና በተዘዋዋሪ መንገድ አንድን ነገር የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ቃል ግባልኝ

“ተስፋ ስጠኝ” ወይም “ማልልኝ”

ማለለት

“ተስፋ ሰጠው” ወይም “ቃል ገባለት”