Genesis 46

Genesis 46:1

ወደ ቤርሳቤህ ሄደ

ወደ ቤርባህ መጣ

እነሆ አለው

“አዎን እየሰማሁ ነኝ”

ወደ ግብጽ ለመውረድ

ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደ ታች መውረድ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው::

ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ

እዚህ አንተን የሚለው ነጠላ አገላለጽና ያዕቆብን የሚያመለክት ነው እዚህ ያዕቆብ ታላቅ የሚሆነውን የእርሱን ዘር ይወክላል አት ብዙ ትውልድ እሰጥሃለሁና እነርሱም ታላቅ ሕዝብ ይሆናሉ (አንተ የሚለውን ቃል አጠቃቀምና ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

ወደ ግብጽ ውስጥ

ወደ ግብጽ

ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ

ተሰፋ የተሰጠው ለያዕቆብ ነው ነገር ግን ተስፋው የሚፈጸመው ለእስራኤል ትውልድ ሁሉ ነው አት በእርግጥ ዘርህን ከግብጽ ምድር አወጣለሁ (አንተ የሚለውን ቃል አጠቃቀምና ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

ደግሞም ወደ ላይ አወጣሃለሁ

ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደላይ መውጣት” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው::

የዮሴፍ የራሱ እጆች ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል

የራሱ እጆች ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል የሚለው ሀረግ እስራኤል በሚሞትበት ጊዜ ዮሴፍ እንደሚገኝና በሞቱ ጊዜ የዮሴፍ እጆች የያዕቆብን የዐይን ሽፋሽፍቶች እንደሚዘጉ የሚናገርበት መንገድ ነው:: አት “ዮሴፍም ቢሆን በሞትህ ዕለት ይገኛል” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል

አንድ ሰው ዐይኑን ከፍቶ በሚሞበት ጊዜ የዐይኑን ሽፋሽፍቶች መበሳብ መዝጋት የተለመደ ባህል ነበር:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 46:5

ተነሣ

ከዚያ ወጣ

በሠረገሎች

“ሠረገሎች” ሁለት ወይም አራት እግር ያላቸው የጭነት ሠረገሎች ናቸው እንስሳት ተሳቢውን ይጐትቱታል:: በዘፍትረት 45:19 ሠረገሎች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

ያካበቱትን

“ያገኙትን” ወይም “ያፈሩትን”

ከራሱ ጋር ይዞ አመጣቸው

ያዕቆብ ከራሱ ጋር ይዞአቸው መጣ

የልጆቹን ወንድ ልጆች

ወንድ የልጅ ልጆች

የልጆቹን ሴት ልጆች

ሴት የልጅ ልጆች

Genesis 46:8

ስማቸው ይህ ነበር

ይህ ጸሐፊው የሚዘረዝራቸውን የሰዎች ስሞች ያመለክታል፡፡

የእስራኤል ልጆች

የእስራኤል ቤተሰብ አባላት ሄኖኀ ፌሉሶ አስሮንና ከርሚ…ይሙኤል ያሚን ኦሃድ ያኪን ጾሐርና ሳኡል …ጌድሶን ቀዓትና ሜራሪ፤ እነዚህ ሁሉ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 46:12

ዔር አውናን ሴሎም

እነዚህ ይሁዳ ከሚስቱ ከሰዋ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ነበሩ:: በዘፍጥረት 38:3-5 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

ፋሬስና ዛራ

እነዚህ ይሁዳ ከምራቱ ከታማር የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ነበሩ:: በዘፍጥረት 38:29-30 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

ኤስሮም ሐሙል … ቶላ ፋዋ ዮብ … ሺምሮን… ሴሬድ ኤሎን… ያሕልኤል

እነዚህ ሁሉ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ዲና

ይህ የልያ ሴት ልጅ ስም ነው በዘፍጥረት 30:21 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::(ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

የወንዶችና የሴቶች ልጆች ቁጥር ሠላሣ ሶስት ነበር

እዚህ ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆች የያዕቆብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እና የልያ የልጅ ልጆች ያመለክታል አት በአንድነት 33 ወንዶችና ሴቶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበረው (ቁጥሮች ይመልከቱ)

Genesis 46:16

ጽፎን… ሐጊ ሹኒ… ኤስቦን ዔሪ አሮዲና… አርኤሊ…ዩምና …የሱዋ የሱዊና… በሪዓ …ሐቤር… መልኪኤል

እነዚህ ሁሉ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ሤራሕ

ይህ የሴት ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ዘለፋ

የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ለያዕቆብ የወለደቻቸው እነዚህ ወንዶች ልጆች በአንድነት አሥራ ስድስት ናቸው

ይህ ከዘለፋ የተወለዱ አሥራ ስድስት ልጆች የልጅ ልጆችና የልጁ ልጅ ልጆች ናቸው (ቁጥሮች ይመልከቱ)

Genesis 46:19

አስናት

የሴት ስም ነው:: በዘፍጥረት 41:45 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ጶጥፌራ

የወንድ ስው ስም ነው:: በዘፍጥረት 41:45 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

የኦን ካህን

ኦን የጸሐይ አምላክ ረሐ አምልዕኮ ማዕከል ያለባትና የጸሐይ ከተማ ደግሞም ሄልዮቱ የተባለች ከተማ ነች:: በዘፍጥረት 41:45 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ቤላ ቤኬር አስቤል ጌራ ናዕማን አኪ ሮስ ማንፌን ሑፊምና አርድ

እነዚህ የወንድ ሰዎች ስሞች ናቸው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

በአጠቀለይ አሥራ አራት ናቸው

ራሔል የወለደቻቸው 14 ወንዶችና የልጅ ልጆች ናቸው

Genesis 46:23

ሑሺም ያሕጽኤል ጉኒ ዬጽርና ሺሌም

እነዚህ የወንድ ሰዎች ስሞች ናቸው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ባላ

የራሔል ሴት ባሪያ ወይም አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:29 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ

ይህ ባላ የወለደቻቸው 7 ልጆችና የልጅ ልጆች እንደሆኑ ያመለክታል (ቁጥሮች ይመልከቱ)

Genesis 46:26

ስድሳ ስድስት

66 (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

ሰባ

7ዐ (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

Genesis 46:28

በፊቱ የጌሤምን መንገድ እንዲያሳየው

የጌሜምን መንገድ እንዲያሳያቸው

ዮሴፍ ሰረገላውን አዘጋጀና … ወጣ

እዚህ “ዮሴፍ” አገልጋዮቹን ወይም ባሪያዎቹን ይወክላል:: አት “የዮሴፍ አገልጋዮች ሠረገላውን አዘጋጁለትና ዮሴፍም ….ወጣ” (ምትክ ቃላት ይጠቀሙ)

እስራኤልን ሊገናኘው …..ወጣ

“ወደ ላይ ወጣ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመው ዮሴፍ አባቱን ሊገናኘው ወደ ከፍታማ ሥፍራ ስለተጓዘ ነው:: አት “እስራኤልን ሊገናኘው ሄዴ”

አንገቱን አቀፈና ረጅም ጊዜ አለቀሰ

እንገቱ ላይ ተጠመጠመና ረጅም ጊዜ አለቀሰ

አሁን ቢሞት እይቆጨኝ

“አሁን ለሞት ተዘጋጅቻለሁ” ወይም “አሁን እንግዲ የሚሞተው በደስታ ነው”

አንተ ገና በሕይወት ሳለህ ፊትህን አይቻለሁና

እዚህ “ፊት” ሙሉ ሰው ይወክላል”” ያዕቆብ ዮሴፍን በማየቱ የተሰማውን ደስታ ይገልጻል:: አት “አንተን እንደገና በሕይወት ስላየሁህ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 46:31

የአባቱን ቤት

እዚህ ቤት ቤተሰቡን ይወክላል:: አት “የአባቱን ቤተሰብ” ወይም “የአባቱን ቤተሰዎች” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

ወደ ፈርዖን ወጥቼ እናገረዋለሁ

ወደ አንድ ትልቅ ባለሥልጣን ሄዶ መናገር ወደ ላይ ወጣ የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር አት ለፈርዖን ለመናገር እሄዳለሁ

ለፈርዖን እነግረዋለሁ: ወንድምቼ … ያላቸውን ሁሉ

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል ይህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ወንድሞቼ …ያላቸውን ሁሉ… ለፈርዖን እነግረዋለሁ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

Genesis 46:33

እንዲህም ሆነ

ይህ ሀረግ የተጠቀመው በታሪኩ ስለተከሰተው ዋና ክስተት ለማመልከት ነው፡፡ በቋንቋዎ ይህንን የሚገልጹበት መንገድ ካለ የጠቀሙ

ሥራችሁ ምንደነው ብሎ ቢጠይቃችሁ

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል:: ይህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ምን ሥራ ታከናውናላችሁ ብሎ ቢጠይቃችሁ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

እንዲህ በሉት እኛ ባሪያዎችህ…. እኛም አባቶቻችንም…

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል:: ይህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እንዲህ በሉት….እኛና አባቶቻችን ሁላችን…” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

የአንተ ባሪያዎች

የዮሴፍ ቤተሰቦች ለፈርዖን ሲናገሩ ራሳቸውን ባሪያዎችህ ብለው ማቅረብ አለባቸው:: ይህ ለአንድ ታላቅ ባለሥልጣን የሚነገርለት መንገድ ነው:: ይህም እንደ አንደኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኛ አገልጋዮችህ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጻዊያን ርኩስ/ ጸያፍ ነውና

“ጸያፍ” የሚለው ረቂቅ ስም “የሚያስጠላ” በሚለው ቅጽል ስም ሊተረጐም ይችላል:: አት “ግብጻዊያን የከብት ጠባቂዎችን እንደ ጸያፍ ይቆጥሩ ነበር” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)