29

1 ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በስተ ምሥራቅ ወዳለው አገር ደረሰ፤ 2 እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጉድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጉድጓድ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጉድጓድ ነበር፤ ጉድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤ 3 መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጉድጓዱ ውሃ ያጠቱአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩንም መልሰው በጉድጓዱ አፍ ላይ ይከዱኑታል። 4 ያዕቆብም እረኞቹን "ወዳጆቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "እኛ የመጣነው ከካራን ነው" አሉት። 5 እርሱም "የናኮርን የልጅ ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "አዎ እናውቀዋለን" አሉት። 6 እርሱም "ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?" አላቸው። እነርሱም "አዎ፣ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያችውልህ! በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች" አሉት። 7 ያዕቆብም "ጊዜው ገና ቀን ነው፤ መንጋዎቻቸውንም ወደ ቤት የምታስገቡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ታዲያ ለምን ውሃ አጠጥታችሁ አታሰማሩአቸውም? ፤ አለ። 8 እነርሱም "እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን" አሉት። 9 ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ ምክንያቱም እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች። 10 ያዕቆብ ያጉቱን የላባን በጎች እየነዳች ስትመጣ ራሔልን አይቶ ወደ ጉድጓድ ሄደ፤ ጉድጓዱ የተከደነበትንም ድንጋይ አንከባሎ በጎቹን አጠጣቸው። 11 ከዚያ በኋላ ራሔልን ሳማት። ከደስታውም ብዛት የተነሣ አለቀሰ፤ 12 "እኔ የአባትሽ እኅት የሆነችው የርብቃ ልጅ ሄደች። 13 ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ አቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤ 14 ላባም "በእርግጥ አንተ ቅርብ የሥጋ ዘመዴ ነህ" አለው፤ ያዕቆብም አንድ ወር ያህል ከአጎቱ ጋር ተቀመጠ። 15 ላባ ያዕቆብን "ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነፃ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያህል ደመወዝ ላስብልህ? አለው። 16 ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ታላቂቱ ልያ፤ ታናሽቱ ራሔል ይባሉ ነበር። 17 ልያ ዐይነ ልም ስትሆን፣ ራሔል ግን ቁመናዋ የሚያምር የደስ ደስ ያላት ነበረች። 18 ያዕቆብ ራሔልን እጅግ ስለወደዳት "ራሔልን ብትድርልኝ ሰባት ዓመት አገለግልሃለሁ" አለ። 19 ላባም "ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ እሺ ተስማምቼአለሁ፤ እዚሁ ከእኔ ጋር ኑር" አለው። 20 ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለነበር የቆየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው። 21 ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ላባን "እነሆ የአገልግሎት ዘመኔ ተፈፅሞአል፤ ሚስት እንድትሆነኝ ልጅህን ስጠኝ" አለው። 22 ላባም የሠርግ ድግስ አዘጋጅቶ በአቅራቢያው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ጠራ። 23 ነገር ግን ላባ በራሔል ምትክ ልያን ለያዕቆብ ሰጠው፤ ያዕቆብም ከልያ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ። 24 ላባ ሴት አገልጋዩን ዚልፋን አገልጋያዋን እንድትሆን ለልጁ ለልያ ሰጣት። 25 በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ "ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልሁህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ"አለው። 26 ላባም "ታላቂቱ ሳትዳር፤ ታናሺቱን መዳር የአገራችን ልማድ አይደለም፤ 27 የልያ ሠርግ ሰባት ቀን እስኪሞላው ድረስ ጠብቅ፤ ከእንግዲህ ወዲይ ሰባት ዓመት የምታገለግለኝ ከሆነ ራሔልን እሰጥሃለሁ" አለው። 28 ያዕቆብም ነገሩ ተስማማ፤ ከልያ ጋር ሰባት ቀን ተሞሽሮ ከቆየ በኋላ፤ ላባ ልጁን ራሔልን ለያዕቆብ ሳረለት። 29 ላባ ሴት አገልጋዩን ባላን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት። 30 ያዕቆብ ከራሔልም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ከልያም አብልጦ ወደዳት፤ ከዚያ በኋላ ላባን ሰባት ዓመት አገለገለው። 31 ልያ የራሔልን ያህል እንዳልተወደደች እግዚአብሔር ባየ ጊዜ መውለድ እንድትችል ማሕፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መኻን ሆነች፤ 32 ልያ ርርግዛ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እግዚአብሔር መከራዬን ተመለከተ፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ባሌ ይወደኛል" ስትል ስሙን ሮቤል አለችው። 33 እንደገና አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወደች፤ "እግዚአብሔር እንዳልተወደድሁ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ' ስትል ስሙን ስምዖን አለችው። 34 እንደገና 'አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል" ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤ 35 እንደገና አረገዘችና ውንድ ልጅ ወለደች፤ "አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ" ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች።