Genesis 49

Genesis 49:1

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ያዕቆብ ልጆቹን የሚባርከውን መጨረሻውን በረከት የጀምራል:: ይህም እስከ ዘፍጥረት 49:27 ይቀጥላል የያዕቆብ ምርቃቶች በግጥም መልክ ተጽፈዋል (ሥነ ግጥሞችን ይመልከቱ)

እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ ተሰብሰቡና ስሙ፤ አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ

ሁለቱ ዐረፍተ ነገሮች ትኩረት ለመስጠት ተመሣሣይ ሃሳብ ይናገራሉ አት ወደ አባታችሁ ኑና በጥንቃቄ አድምጡ (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)

እናንተ የያዕቆብ ልጆች አባታችሁን እስራኤልን አድምጡ

ያዕቆብ ራሱን እንደሶስተኛ ወገን ሰው ያቀርባል እንደአንደኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል አት ልጆች ሆይ እኔን አባታችሁን ስሙ (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አጠቃቀም ይመልከቱ)

Genesis 49:3

የበኩር ልጄ ኃይሌና የጉብዝናዬ መጀመሪያ

የበኩር ልጄ ኃይሌ የጉብዝናዬ መጀመሪያ የሚሉ ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ኃይል እና ጉብዝና የሚሉ ቃሎች የያዕቆብ ልጅ የመውለድ አቅሙን ያመለክታሉ በኩር እና መጀመሪያ የሚሉ ቃላት ሮቤል በኩር ልጁ እንደሆነ ይገልጻሉ (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)

በክብር ትልቃለህ በኃይልም ትበልጣለህ

ይህ እንደ አድስ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል አት በክብርና በኃይል የመጀመሪያ ትሆናለህ ወይም በክብርና በኃይል ማንኛውንም ሰው ትበልጣለህ

እንደ ውሃ የምትዋልል ነህ

ያዕቆብ ሮቤል ቁጣውን እንደማይችል ለማተኮር በከባድ ማዕበል እንደሚዋልል ውሃ አድርጐ ያቀርበዋልና እርሱ የተረጋጋ አይደለም (ተመሣሣይ አባባል ይመልከቱ)

እልቅና አይኖርህም

በወንድሞችህ መካከል የመጀመሪያ ወይም አለቃ አትሆንም

ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና ከዚያም አርክሰሄዋል ወደ አልጋዬም ወጥተሃል

እዚህ መኝታና አልጋ የያዕቆብን ቁባት ባላን ያመለክታሉ ያዕቆብ ሮቤል ከባላ ጋር የተኛበትን ያመለክታል (ዘፍጥረት 35:22 ይመልከቱ) አት “ወደ አልጋዬ ስለወጣህና በቁባቴ ከባላ ጋር ስለተኛህ አዋርደህኛልና” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

ወደ አባትህ አልጋ ወጥተሃል ወደ አልጋዬም ወጥተሃል

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)

Genesis 49:5

ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው

ይህ በትውልድ ወንድሞች መሆናቸውን አይገልጽም ያዕቆብ የሴኬም ሰዎችን ለመግደል አብረው መሥራታቸውን ለማተኮር ነው፡፡

ሰይፎቻቸው የዐመጽ መሣሪያ ናቸው

ሰዎችን ለመጉዳትና ለመግደል ሰይፎቻቸውን ይጠቀማሉ

ነፍሴ …. ልቤ

ያዕቆብ ራሱን ለመግለጽ ነፍሴ እና ልቤ የሚሉ ቃሎችን ይጠቀማልና ክፋን ለማድረግ ከሚያቅዱት ጋር ባለመተባበሩ ሌሎች ሰዎችና እግዚአብሔርም ደግሞ እጅግ እንዳከበሩት ይናገራል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ወደ ሸንጐአቸው አልግባ

ጉባዔያቸው ውስጥ አልገኝ እነዚህ ሁለቱ ሀረጐች በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ያዕቆብ ሁለቱን በማገናኘት በክፉ እቅዳቸው እንደማይሳተፍ አበክሮ ይገልጻል አት ማንኛውንም እቅድ ለማዘጋጀት ከእነርሱ ጋር አልተባበርም (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)

የቤሬዎችን ቋንጃ ቈራርጠዋል

ስምዖንና ለዊ ለዕይታ ብለው ቤሬዎችን አስነክሰዋል

ቋንጃ መቈረጥ ወይም ማስነከስ

ይህ የእንስሳትን ቋንጃ በመቁረጥ እንዳይራመዱ ማድረግ ነው

Genesis 49:7

ቁጣቸው ርጉም ይሁን ጽኑ ነበርና ንዴታቸው ጭከና የተሞላ ነበርና

እግዚአብሔር ስምዖንና ሌዊን የሚረግመው እግዚአብሔር ቁጣቸውንና ንዴታቸውን እንደሚረግም ተደርጐ የገልጾአል:: (ዘይቤያዊ አነጋገርና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ቁጣቸው የተረገመ ይሁን

አብዛኛውን ጊዜ ነብይ ትንቢትን ሲናገር የሚናገረው ቃል እግዚአብሔር እንደሚናገር ይቆጠራል:: ይህም የሚናገረው ነበዩና እግዚአብሔር እንዴት እንደተቆራኙ ነው::

ንዴታቸው ጭከና የተሞላ ስለነበር

እረግማለሁ የሚለው ቃል የታወቀ ነው አት ንዴታቸው ጭከናን የተሞላ ስለሆነ እረግማለሁ (የተደበቁትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

እኔም በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ በእስራእልም እበትናቸዋለሁ

“እኔ” እግዚአብሔርን ያመለክታል:: “እነርሱ” ስምዖንንና ለዊን ቢሆንም ምትክ ቃል ስለሆነ ለትውልዳቸውም ይሆናል:: “ያዕቆብ”ና “እስራኤል” ተወራራሽ ስሞችና የእስራእል ሕዝብ የሚተኩ ናቸው:: አት ትውልዳቸውን እበትናለሁ በእስራኤልም ሰዎች መካከል አሠራጫለሁ (ምትክ ቃላትና ተመሣሣይ ተነጻጻሪ አባባል ይመልከቱ)

Genesis 49:8

ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)

ያመሰግኑሃል፤ እጅህ

ሁለተኛው ዐረፍተ ነገር ለአንደኛው ምክንያት ነው ይህ “ስለ” ወይም “ምክንያቱም/የተነሣ” አገናኝ ቃላትን በመጠቀም ግልጽ ሊሆን ይችላል:: አት “ስለ እጅህ ያመሰግኑሃል” ወይም “ከእጅህ የተነሣ ያመሠግኑሃል” (አገናኝ ቃላት ይመልከቱ)

እጅህ በጠላቶችህ አንገት ላይ ነው

“ጠላቶችህን ታሸንፋለህ” የሚል አባባል ነው:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ይሰግዳሉ

ለአንድ ሰው እጅ መንሣት ወይም አክብሮት በትህትና ለመግለጽ ጐንበስ ማለትን ይገልጻል (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

Genesis 49:9

ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው

የአንበባ ደቦል እንደሆነ ስለ ይሁዳ ያዕቆብ ይናገራል:: ያዕቆብ የይሁዳን ጥንካሬ በአትኩሮት ይገልጻል:: አት “ይሁዳ እንደ አንበሳ ደቦል ነው” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ልጄ ሆይ ከአደንህ ወጣህ

“አንተ ልጄ ከአደንህ ተመለስህ”

እንደ እንስት አንበሳ

ያዕቆብ ይሁዳን ከእንስት አንበሳ ጋር ያነጻጽራል አት እንስት አንበሳ በአደን ቀዳማይና ቡድንዋን የሚትከላከል ነች (ተመሣሣይ አባባል ይመልከቱ)

ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?

ያዕቆብ ይሁዳ ለሌሎች ሰዎች ምንኛ አስፈሪ እንደሆነ ትኩረት ለመሰጠቅ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት “ማንም ሊቀሰቅሰው አይችልም” (አግናኝ ጥያቄ ይመልከቱ)

Genesis 49:10

በትሬ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል

በትርና ዘንግ ንጉሥ የሚይዛቸው ያገጡ ረጃጅም በትሮች ናቸው የሥልጣን አገዛዝ የሚተኩ ምልክቶች ናቸው እናም ይሁዳ የእርሱን ዘር ይወክላል:: አት “የአገዛዝ ሥልጣን ሁልጊዜም ለይሁዳ ዘር ይሆናል” (ምትክ ቃላትና ተመሣሣይ ተነጻጻሪ አባባል ይመልከቱ)

ገዥነት የሚገባው ወይም ሰሎ እስኪመጣ ድረስ

ተገቢ ትርጉሞች 1 ሰሎ ማለት ክብር ወይም አድናቆት ማለት ነው አት ሕዝቦች እስኪታዘዙለትና እስክያከብሩት ድረስ ወይም 2 ሰሎ የሴሎ ከተማን ይወክላል አት ገዥ ወደ ሰሎ እስኪመጣና ሕዝቦች እስኪታዘዙለት ድረስ ብዙ ሰዎች እንደሚናገሩት ይህ ትንቢት ከዳዊት ዘር ስለሚመጣው መስህ ነው ዳዊት ከይሁዳ ዘር ነውና

ሕዝቦች ይታዘዙለታል

ሕዝቦች ሰዎችን ያመለክታሉ አት ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙለታል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

Genesis 49:11

አህያውን ያስራል… በወይን ግንድ

ሁለቱም አረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው የወይኑ ፍሬ ብዙ ሰለሆነ አህያው ፍሬዎችን ቢበላ ጌታው እንደማይገደው ተደረጐ ተገልጾአል:: (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

የእርሱ … እርሱ

የእርሱ ወይም እርሱ በተጠቀሱባቸው ሁሉ ተገቢ ትርጉማቸው 1 የይሁዳን ዘር ያመለክታሉ:: “የእነርሱ” “እነርሱ” ወይም 2) እነርሱ በዘፍጥረት 49:1ዐ ምናልባት ሚናሴን የሚያመለክተውን ገዥ ያመለክታሉ::

ልበሱን ያጥባል… በወይን ጭማቂ

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ይህም በጭማቂዎቻቸው ልብሶቻቸውን ማጠብ እንኳ የሚያስችል ብዙ ወይን ፍሬዎች ይኖራሉ ማለት ነው (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አጠበ

አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት የሚፈጸሙ ትንብቶች እንደተፈጸመ ተደርጐ ይገለጻል ይህ በአትኩሮት የሚናገረው ክስተቱ በእርግጥ እንደሚፈጸም ነው አት እነርሱ ያጥባሉ ወይም እርሱ ያጥባል (ወደፊት አመላካች ኃላፊ ክስተት ይመልከቱ)

የወይን ደም ወይም ጭማቂ

የወይን ጭማቂን እንደ ወይን ደም ያቀርባል ይህም ጭማቂው ምንኛ ቀይ ቀለም እንዳለው ይገልጻል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ዐይኖቹ እንደ ወይን የቀሉ

ይህ እንደ ቀይ ቀለም ወይን የሰውን ዐይን ቀለም ቅላት ያመለክታል:: ተገቡ አማራጭ ትርጉሞች እነሆ አት 1)ጥቁር ቀለም ያላቸው ዐይኖች ጤናማ ዐይኖች ናቸው ወይም 2) ብዙ የወይን ጠጅ ከመጠጣት የተነሣ የሰዎች ዐይኖች ይቀላሉ (ተመሣሣይ አባባል እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ጥርሶቹ ከወተት ይልቅ የነጡ

ይህ የሰውን ነጭ ጥርስ ከወተት ንጣት ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህም ወተትን የሚጠጡበት ብዙ የሚታለቡ ላሞች እንደሚኖሩ ነው (ተመሣሣይ አባባል እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 49:13

ዛብሎን በበሕር ዳር ይኖራል

ይህ የዛብሎንን ነገድ ያመለክታል:: የዛብሎት ነገድ ወይም ትውልድ በበሕር ዳር ይኖራል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

እርሱም ወደብ ይሆናል

እዚህ እርሱ የዛብሎን ሰዎች የሚወርሱት ወይም የሚገነቡት የባሕር ዳር ከተሞችን ይወክላል እነዚህ የወደብ ከተሞች ለመረከበኞች መጠለያ ይሆናሉ (ምትክ ቃል አጠቃቀም ይመልከቱ)

ወደብ

በባህር ዳር ያለ መሬትና ለመርከቦች መቆሚያ ደኀንነት ያለው ቦታ ማለት ነው

Genesis 49:14

ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው

ያዕቆብ ስለይሳኮርና ነገድ ወይም ትውልድ ሲናገር እንደ አህያ ይቆጥራቸዋል ይህም እጅግ የሚሠሩ እንደሚሆኑ በአትኩሮት ይገልጻል የይሳኮር ትውልድ አንደ አጥንተ ብርቱ አህያ ነው (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ይሳኮርም

አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት የሚፈጸሙ ትንቢቶች እንደተፈጸመ ተደርጐ ይገለጻል ይህ በአትኩሮት የሚናገረው ክስተቱ በእርግጥ እንደሚፈጸም ነው ይህም በወደፊት ጊዜ ሊገለጽ ይችላል አት “ይሳኮር… ይሆናል” ወይም “የይሳኮር ትውልድ… ይሆናል” (ወደፊት አመላካች ኃላፊ ክስተት ይመልከቱ)

ይሳኮር …ያያል… ይሆናል

እዚህ ይሳኮር ለነገዱ ምትክ ሆኖ የሚቆም ስም ነው አት “የይሳኮር ትውልዶች… ያያሉ …ይሆናሉ” (ምትክ ቃላት ይጠቀሙ)

በበጐች ጉሬኖ መካከል ያርፋል

ተገቢ ትርጉሞች 1 በጭነት መካከል ይተኛል ወይም 2 በሁለት በጐች አጥር መካከል ይተኛል ደግሞም በሌላ መንገድ ያዕቆብ ስለይሳኮር ልጆች እጅግ እንደሚሠሩና ከዚያም ለእረፍት እንደሚተኙ ይናገራል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

መልካም የእረፍት ቦታና የለማች ምድር

መልካም እረፍት የሚያገኙበት ቦታና የለማች ምድር

ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል

ትከሻውን ለሽክም ያመቻቻል ማለት ሸክምን በመሸከም እጅግ ይሠራል ማለት ነው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ለሥራ ባሪያ ይሆናል

ለሌሎች እንደባሪያ ያገለግላል

Genesis 49:16

ዳን በወገኑ ይፈርዳል

እዚህ ዳን ነገዱን ይወክላል የዳን ልጆች በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ

የራሱ ሕዝብ

ተገቢ ትርጉሞች የራሱ ሕዝብ፤ 1) በዳን ሕዝብ 2) በእስራኤል ሕዝብ

ዳን የመንገድ ዳር እባብ ይሆናል

ያዕቆብ ስለዳንና የእርሱ ትውልድ እንደ እባብ አድርጐ ይናገራቸዋል እባብ ምንም ትንሽ ቢሆን መንገደኛውን ከፈረስ ላይ ማውረድ ይችላል እንዲሁ ዳን ትንሽ ነገድ ሲሆን በጠላቶቹ ላይ አደገኛ ነው አት የዳን ልጆች በመንገድ ዳር እንዳለ እባብ ናቸው (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ሆይ ማዳንህን እጠባበቃለሁ

ረቂቅ ስም “ማዳን” እንደ “መዳን” ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት “እግዚአብሔር ሆይ እንዲታድነኝ እጠባብቃለሁ”

እኔ እጠባበቃለሁ

“እኔ” ያዕቆብን ያመለክታል

Genesis 49:19

ጋድ …ይዘምቱበታል እርሱ ግን

ጋድ ትውልዱን ይወክላል:: አት “የጋድ ልጆች ..ይጠቃሉ ነገር ግን እነርሱ” (ምትክ ቃል ይጠቀሙ)

አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል …እርሱም

አሴር የአሴር ልጆችን ይወክላል:: እት “የአሴር ልጆች ማእደ ሰፊ… እናም እነርሱ” ምትክ ቃል ይጠቀሙ

ንፍታሌም …እርሱም

ንፍታሌም የንፍታሌምን ትውልድ ይወክላል:: አት “የንፍታሌም ልጆች.. እነርሱ… ይሆናሉ”

በተራሮች

ከዳን ልጆች በመሸሽ በተራራማው የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል

ምግቡ የተረከተ

እዚህ የበረከተ የሚለው ምግቡ ጣፋጭ ማለት ነው ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ

ንፍታለም ነጻ እንደተለቀቀች ሚዳቋ ነው

ያዕቆብ ስለንፍታሌም ልጆች ለመሮጥ እንደተለቀቀች እንደ እንስት ሚዳቋ እንደሆነ ይናገራል:: ይህም እነርሱ ፈጣን መልእክተኞች እንደሆኑ ነው:: አት “የንፍታሌም ዘሮች እንደተለቀቀች ሚዳቋ ይሆናሉ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

የሚያማምሩ ግልገሎች

ግልገሎች ትናንሽ የሚዳቋ ግልገሎች ናቸው የዕብራይስጡ ቃል ትርጉም ግልጽ አይደለም አንዳንድ ትርጉሞች መልካም ቃል ይሰጣል ወይም መልካም ነገር ይናገራል የሚለውን ተጠቅመዋል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 49:22

ዮሴፍ ፍሬያማ ዛፍ ነው

ዮሴፍ ትውልዱን/ዘሩን ይወክላል ያዕቆብ እነርሱን ብዙ ፍሬ እንደሚያፈራ የዛፍ ቅርንጫፍ አድርጐ ይናገራል:: አት “የዮሴፍ ዘር ፍሬያማ የዛፍ ቅርንጫፍ ነው”

የዛፍ ቅርንጫፍ

የዛፍ ዋና ቅርንጫፍ

ሐረጐቹ ቅጥርን ያለብሳሉ

ቅርንጫፎች አድገው ቅጥርን ማልበሳቸው እነዚያ በቅጥር ላይ እንደሚወጡ ተደርጐ ተገልጾአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 49:24

አጠቃላይ መረጃ

ያዕቆብ ዮሴፍንና ዘሩን መባረክ ይቀጥላል

ቀስቱ ጸና

ቀስቱን የያዘው ሰው መጽናቱ ቀስቱ ራሱ እንደጸና ተደርጐ ተግልጾአል ወደ ጠላቱ በሚያልምበት ጊዜ ቀስቱ እንደሚጸና ይገልጻል አት ወደ ጠላቱ በሚያልምበት ጊዜ ቀስቱን አጽንቶ ይይዛል (ምትክ ቃላት አጠቃቀም እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ቀስቱ….እጆቹ

እዚህ “እርሱ” ዘሩን የሚወክለውን ዮሴፍን ነው አት “ቀስቶቻቸውና እጆቻቸው” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

እጆቹ ቀልጣፋ ይሆናሉ

ቀስትን መያዘ የለመዱ እጆች ስለሆኑ ሙሉ ሰው እንደ እጆች ተገልጾአል:: (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ኃያል አምላክ እጆች

እጆች የእግዚአብሔርን ኃይል ይገልጻሉ:: አት “የሁሉን ቻይ አምላክ ኃይል” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

ከእረኛው ስም የተነሣ

እዚህ ስም ሙሉ ሰው ይወክላል አት ከእረኛው የተነሣ (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

እረኛው

ያዕቆብ እግዚአብሔር እረኛ እንደሆነ ይናገራል አት ይህም እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚመራና እንደሚጠብቅ ይናገራል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ዐለት

ያዕቆብ እግዚአብሔር ሰዎች የሚወጡበትና ከጠላቶቻቸው የምድኑበት አለት እንደሆነ ይናገራል ይህ የሚያጐላው እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚጠብቅ ነው (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 49:25

አጠቃላይ መረጃ

ያዕቆብ ዮሴፍንና ዘሩን መባረክ ይቀጥላል (ዘፍጥረት 49:22-23 ይመልከቱ)

አንተን በሚረዳህ …በሚባርክህ

እዚህ “አንተ” ዘሩን የሚወክለውን ዮሴፍን ያመለክታል አት “የአንተን ዘር በሚረዳ ….በሚባርክህ” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

በሰማይ በረከቶች

ሰማይ ተክልን ወይም ሰብልን የሚያሳድገው ዝናብን ይወክላል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

ከምድር ጥልቅ ከሚገኝ በረከት

ጥልቅ ለወንዞችና ለኩሬዎች የሚሆን ውሃ የሚወጣበትን ይወክላል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

በጡትና በማህጸን በረከት

እዚህ ጡቶችና ማህጸን እናቶች የመውለድና ጡት የማጥባት አቅም ያመለክታል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

Genesis 49:26

አጠቃላይ መረጃ

ያዕቆብ ዮሴፍንና ልጆቹን መባረክ ይቀጥላል፡፡

ከጥንት ተራሮች

የመሠረታዊው ቋንቋ ትርጉም ግልጽ አይደለም:: አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በጥንት ተራሮች ፈንታ ጥንት አባቶች ይጠቀማሉ::

እነርሱ በዮሴፍ ራስ ላይ ይሁኑ

እዚህ “እነርሱ” የአባቱ በረከቶች ናቸው::

በወንድሞች መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ

ያዕቆብ እነዚህ በረከቶች ልጆቹ እጅግ በበለጡት ላይ እንዲሆን ይሻል:: አት “እጅግ በበለጡ በዮሴፍ ልጆች ራስ አናት ላይ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው

ከወንድሞቹ ዋና በሆነው

Genesis 49:27

ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው

ብንያም ዘሩን የሚወክል ምትክ ስም ነው:: ያዕቆብ የብያም ልጆችን እንደ ተራበ ተኩላ ይናገራል:: ይህም አጉልቶ የሚናገረው አጥቂ ተዋጊዎች እንደሆኑ ነው:: የብንያም ነገድ ሰዎች እንደተራቡ ተኩላ ናቸው:: (ምትክ ቃልና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 49:28

እነዚህ አሥራ ሁሉቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው

እነዚህም በዘፍጥረት 49: 1- 27 የተዘረዘሩትን ይመለከታል እያንዳንዱ ልጅ የነገድ አባት ሆኖአል፡፡

በባረካቸው ጊዜ

እዚህ “ባረካቸው” የሚለው መደበኛ በረከቶችን እንደተናገረ ነው

እያንዳንዱን በተገቢ መንገድ ባረካቸው

ለእያንዳንዱ የሚገባውን በረከት ባረከ

መመሪያ ሰጣቸው

አዘዛቸው

ወደ ወገኖቼ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል

ይህ ለመሞት መድረሱን በትህትና የሚገለጸበት መንገድ ነው፡፡ አት “ለመሞት ቀርበአለሁ ወይም ልሞት ነኝ” (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽንና ፈሊጣዊ አነጋገርን ይመልከቱ)

ወደ ወገኖቼ የምሄድበት

ያዕቆብ በሚሞትበት ጊዜ የራሱ ውስጠኛው ሰው/ ነፍሱ ወደየት እንደሚሄድ ያመለክታል:: ከሞት በኋላ አብርሃምንና ይስሐቅን አንደሚገናኝ ይጠብቃል (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽንና ፈሊጣዊ አነጋገርን ይመልከቱ)

ኬጢያዊው ኤፍሮን

ይህ ወንድ ሰው ስም ነው፡፡ “ኬጢያዊ” የኬጥ ዘር ነው:: በዘፍጥረት 23:8 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ማክፌላ

የአንድ ቦታ ወይም ግዛት ስም ነው፡፡ በዘፍጥረት 23፡9 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

መምሬ

ይህ የሔብሮን ከተማ ሌላ ስምዋ ነው:: ምናልባት መምሬ የተባለው የአብርሃም ወዳጅ ስም የተሰየመ ሳይሆን አይቀርም:: በዘፍጥረት 13:18 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ(ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 49:31

አጠቃላይ መረጃ

ያዕቆብ ለልጆቹ መናገሩን ይቀጥላል

በዚያ የተገዛው

ግዥው ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “በዚያ አብርሃም የገዛውን” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ከኬጥ ሰዎች

ከኬጢያዊያን

እነዚህን መመሪያዎች ለልጆች ተናግሮ እንዳበቃ

“ለልጆቹ መመሪያ መሰጠቱን እንዳበቃ” ወይም “ልጆቹን አዝዞ እንዳበቃ”

እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ

ያዕቆብ በአልጋው ላይ ተቀምጦ ነበር አሁን ግን ሊሞት መልሶ እግሮቹን በአልጋ ላይ የሰበስባል

የመጨረሻ አስትንፋሱን ተነፈሰ/ሰጠ

ይህ አንድ ሰው መሞቱን ለዛ ባለ ቋንቋ የሚገለጽበት መንገድ ነው (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽን ይመልከቱ)

ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ

ያዕቆብ በሞተ ጊዜ ውስጠኛው ሰው ወይም ነፍሱ ከእርሱ በፊት የሞቱ ወገኖች ወደሄዱበት ቦታ ተሰብስቦአል (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽንና ፈሊጣዊ አነጋገርን ይመልከቱ)