Genesis 45

Genesis 45:1

ራሱን ሊቆጣጠር አልቻለም

ስሜቱን ሊገታ አልቻለም ማለት ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ማልቀስ ጀምሮ ነበር”

ከጐኑ

አጠገቡ

የፈርዖን ቤት

እዚህ “ቤት” በፈርዖን ቤተመንሥት ያሉ ሰዎችን ይወክላል፡፡ አት “በፈርዖን በተመንግሥት ያለው ሁሉ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

በፊቱ ተደናግጠው

እርሱን ፈርተው

Genesis 45:4

ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ

ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አት “ወደ ግብጽ ላመጡኝ ነጋዴዎች እንደ ባሪያ የሸጣችሁኝ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አትዘኑ

“አትቈጩ” ወይመ “አትጨነቁ”

ወደዚህ ስለሸጣችሁኝ

ትርጉሙም በግልጽ ሊነገር ይችላል፡፡ አት “እንደ ባሪያ ሸጣችሁኝ እናም ወደ ግብጽ ምድር ላካችሁን”

ሕይወት ለማዳን

እዚህ “ሕይወት” ዮሴፍ በረሃቡ ጊዜ ያዳናቸውን ሰዎች ይወክላል:: አት “የብዙ ሰዎችን ሕይወት እንዳድን” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና አሉ

የማይታረስባቸው ወይም ሰብል የማይሰበሰባቸው አምስት ዓመታት አሉ እዚህ የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበስብባቸው ሰብሎች ከድርቁ የተነሣ እንደማይመረቱ የሚገልጹ ናቸው:: አት “ረሃቡ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ይቀጥላል” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

Genesis 45:7

በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ

“እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ከምድር ላይ ፈጽማችሁ እንዳትጠፉ” ወይም “ዘራች ከምድር ላይ እንዲኖር”

ሕይወታችሁን በታላቅ ማዳን ለመታደግ

ማዳን የተባለው ረቂቅ ስም ማትረፍ በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት “በታላቅ መንገድ በማትረፍ በሕይወት እንዲትኖሩ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

ፈርዖን አባት አድርጐኛል

ዮሴፍ ፍርዖንን ማማከሩና መርዳቱ ዮሴፍ እንደፈርዖን አባት ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “የፈርዖን መሪ ወይም አማካሪ አድርጐኛል” ወይም “የፈርዖን ዋና አማካሪ አድርጐኛል” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

በቤቱ ሁሉ ላይ

እዚህ “ቤት” በቤተመንግሥቱ የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል:: አት “በቤተሰዎቹ ሁሉ ላይ” ወይም “በቤተመግሥቱ ላይ” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ

እዚህ “ምድር” ሰዎችን ይወክላል:: አት “በግብጽ ምድር ሰዎች ሁሉ ላይ ገዥ” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

ገዥ

ዮሴፍ ከግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሁለተኛ ደረጃ ገዥ ነው ማለት ነው:: ይህ የተነገረው መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 45:9

ወደ አባቴ ውጡ

ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ ሲነገር ወደ ላይ መውጣት የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር:: አት “ወደ አባቴ ሂዱ”

እንዲህም በሉት ልጅህ ዮሴፍ እዲህ ይላል “እግዚአብሔር … ያለህን ሁሉ”

ይህ ሶስት ደረጃ ያለው ጥቅስ ነው በሁለት ደረጃዎች ቀለል ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኔ የምለውን ንገሩት እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

ወደ እኔ ና/ውረድ

ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ ሲነገር ወደ ታች መውረድ የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር:: አት “ወደዚህ ወደ እኔ ና”

ወደ ችግር ና

ችግርን እንደ መድረሻ አድርጐ ይናገራል:: አት “ማጣት” ወይም “ረሀብ” (ዘይቤያዊ አነገር ይመልከቱ)

Genesis 45:12

የእናንተ ዐይኖች አይተዋል እናም የወንድማችሁ የብንያምም ዐይኖች አይተዋል

እዚህ “ዐይኖች” ሙሉ ሰው ይወክላሉ:: አት “እናንተ ሁላችሁና ብንያም ታያላችሁ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ለእናንተ የተናገረቻችሁ የእኔ አፍ እንደሆነች

እዚህ አፍ ሙሉ ሰውን ይወክላል፡፡ አት “እኔ ዮሴፍ እነግራችኋለሁ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

በግብጽ ስላለኝ ክብር ሁሉ

የግብጽ ሰዎች በታላቅነት እንዴት እንደሚያከብሩኝ

አባቴን ወደ ታች ወደዚህ አምጡት

ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ ሲነገር ወደ ታች መውረድ የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር:: አት “አባቴን ወደዚህ አምጡት”

Genesis 45:14

የወንድሙን የብንያምንም አንገት አቀፎ አለቀሰ ብንያምም በአንገቱ ላይ አለቀሰ

ዮሴፍ ወንድሙን ብንያምን አቀፈውና ሁለቱም አለቀሱ

ወንድሞቹን ሁሉ ሳማቸው

በጥንታዊቷ ቅርብ ምሥራቅ ዘመድን በመሳም ሰላምታ መስጠት የተለመደ ነበር:: በቋንቋዎ እንዲህ የመሰለ ስሜት ገላጭ ሰላምታ አሰጣጥ ካለ ያን ይጠቀሙ:: ከሌለ ግን ተገቢ የሆነውነ ቃል ይጠቀሙ::

እየሳማቸው አለቀሰ

ይህም ዮሴፍ በሳማቸው ጊዜ እያለቀሰ ነበር ማለት ነው

ከዚያም በኋላ ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መነጋገር ጀመሩ

አስቀድመው ሊነጋገሩ ፈርተው ነበር:: አሁን ግን በነጻነት መነጋገር እንደሚችሉ ተሰማቸው:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉሙ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “ከዚያም በኋላ ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር በነጻነት መነጋገር ጀመሩ” (ግምታም እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 45:16

በፈርዖን ቤት የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: እንዲሁም ደግሞ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “የዮሴፍ ወንድሞች እንደመጡ በፈርዖን ቤተመንግሥት ያለው ማንኛውም ሰው ሰማ” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅስ እናም ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

የፈርዖን ቤት

የፈርዖንን ቤተመንሥት ይወክላል

ለወንድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ይህን አድርጉ አህዮቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከነዓን ምድር ሂዱ፤ አባታችሁንና ቤተሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብጽ ምድር እሰጣችኋለሁ፤ የምድርቱንም ስብ/በረከት ትበላላችሁ፡፡

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: አት “አህዮቻቸውን እንዲጭኑና ወደ አባታቸውና ቤተሰቦቻውው ወደ ከነዓን እንዲሄዱ ለወንድሞችህ ንገራቸው፤ ወደዚህ እንዲመጡና እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብጽ ምድር እንደሚጣቸወ፤ የምንሰጠውን በረከት እንደሚመገቡ ደግሞም ንገራቸው” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅስ ይመልከቱ)

እኔም መልካም ከሆነው የግብጽ ምድር እሰጣችኋለሁ፤

እኔም እጅግ ለም የሆነውን የግብጽ ምድር እሰጣችኋለሁ

የምድርቱንም ስብ ትበላላችሁ

ምድርቱ የሚትሰጠው መልካም እህል እንደ ምድሪቱ ስብ ተደርጐ ተቆጥሮአል:: አት “የምድሪቱንም እህል ትመገባላችሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 45:19

አጠቃላይ መረጃ

ዮሴፍ ለወንድሞቹ ምን መናገር እንዳለበት ፈርዖን መናገሩን ቀጠለ

አሁን

ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ጠቃሚ ነጥብ/ ቁም ነገር ትኩረት እንዲሰጥበት ተጠቅሞአል

እንዲህ ብለህ እዘዛቸው ይህን አድርጉ ከግብጽ ምድር ልጆቸችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጉዙበት ሠረገላዎች ውሰዱ አባታችሁንም ይዛችሁ ኑ ስለንብረታችሁ ምንም አታስቡ ከግብጽ ምድር እጅግ ለም የሆነው የእናንተ ነውና

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: አት “ደግሞም ከግብጽ ምድር ልጆቸችሁንና ሚስቶቻችሁን እናም አባታችሁንም ይዘው እንዲመጡ የሚያጓጉዙበትን ሠረገላዎች እንዲወስዱ ንገራቸው እኔም በግብጽ መልካም የሆነውን ስለሚሰጣቸው ንብረታችሁን ይዘው ለመምጣት ምንም አይጨነቁ (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅስ ይመልከቱ)

ታዝዘሃል

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት “ደግሞም እንትነግራቸው አዝሃለሁ ወይም ደግሞም ንገራቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ሠረገላዎችን ይውሰዱ

ሠረገላዎች ሁለት ወይም አራት ጐማ ያላቸው የጭነት ሠረገላዎች ናቸው እንስሳት ተሳቢውን ይገትቱታል

Genesis 45:21

ለመንገድ ስንቅ ሰጣቸው

ለጉዞአቸው የሚያስፈልጋቸውን ሰጣቸው

ለሁሉም ሁለት ሁለት መለወጫ ልብስ ሰጣቸው

አምስት መለወጫ ልብስ ከተሰጠው ከብንያምን በስተቀር ሌሎች አያንዳንዳቸው ሁለት መለወጫ ልብስ ተቀብለዋል (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ሶስት መቶ ጥሬ ብር

3ዐዐ ጥሬ ብር (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

አሥር እህዮች … አሥር እንስት አህዮች

አህዮቹ በሥጦታው ተካትተዋል (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 45:24

አትጣሉ

ተገቢ ትርጉሞች የሚያጠቃልሉት 1) አትከራከሩ 2) አትኮራረፉ

ከግብጽ ወጥተው ወደ ላይ ወጡ

ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደላይ” የሚለው ቃለ መጠቀም የተለመደ ነው

በግብጽ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኖአል

እዚህ “የግብጽ ምድር” የግብጽ ሰዎችን ይወክላል አት በግብጽ ሰዎች ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል:: (ምትከ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

ልቡ ደነገጠ

እነርሱ የተናገሩትን እንደ እውነት መቀበል አቃተው

Genesis 45:27

ነገሩት

ለያዕቆብ ነገሩት

ዮሴፍ የነገራቸውን ነገር ሁሉ

ዮሴፍ የነገራቸውን ማንኛውንም ነገር

የአባታቸው የያዕቆብ መንፈስ ታደሰ

እዚህ መንፈስ ሙሉ ሰው ይወክላል፡፡ አት “አባታቸው ያዕቆብ ከጭንቀቱ/ከሐዘኑ ተሻለው” ወይም “አባታቸው ያዕቆብ እጅግ ደስተኛ ሆነ” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም የመልከቱ)