Genesis 31

Genesis 31:1

ይህን

ይህ ቃል የታሪኩን ትረካ መሥመር ለማቋረጥ ተጠቅሞአል በዚህ ጸሐፊው አዲስ ታሪክ ይጀምራል

ያዕቆብ የላባን ወንዶች ልጆች ያሉትን ነገር ሰማ

ያዕቆብ የላባን ወንዳች ልጆች የሚሉትነ ሰማ

ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ሁሉ ወስዶታል

የላባን ወንዶች ልጆች ከመቆጣታቸው የተነሣ አጋንነው ይናገራሉ አት ያዕቆብ የወሰደው ነገር ሁሉ የአባታችን ነበር:: (ማጋነንና ገሃዳዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

ያዕቆብም የላባን ፊት አየ አመለካከቱም እንደተለወጠበት ተገናዘበ

አነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች በመሠረት አንድ ናቸው:: ሁለተኛው ያዕቆብ በላባን ፊት ያየውን ይገልጻል:: አት: “ያዕቆብም ላባን እንዳለተደሰተበት ተረዳ” (ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)

አባቶችህ

አባትህ ይስሐቅና አያትህ አብርሃም

Genesis 31:4

ያዕቆብም ልኮ ራሔልንና ልያን ወደ በጎቹ ሥፍራ ወደ ሜዳ ጠራቸው

ያዕቆብ መንጎቹ ወደተሠማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው

ለመንጋው እናም እንዲህ አላቸው

እነዚህ ሁለት አጫጭር ዐረፍተ ነገሮች ናቸው:: አት “ለመንጋው:: እንዲህም አላቸው” (የዐረፍተ ነገር ውቅር ይመልከቱ)

አባታችሁ ስለእኔ ያለው አመለካከት እንደቀድሞው አለመሆኑን ተረድቻለሁ

አባታችሁ በእኔ ደስተኛ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ

ባለኝ ጉልቤቴ ሁሉ አባታችሁን እንዳገለገልሁ እናንተ ታውቃላችሁ

እናንተ የሚለው ቃል ራሔልንና ልያን ያመለክታል እንዲሁም ደግሞ ትኩረትን ይጨምራል፡፡ አት፡ “አባታችሁን ባለኝ ጉልበት ሁሉ እንዳገለገልሁ እናንተው ራሳችሁ ታውቃላችሁ” (ሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

Genesis 31:7

አታልሎኛል

ዋሽቶኛል ወይም በፍትሃዊነት አላስተናገደኝም

ደመወዜ

ሊከፍለኝ የተናገረውን

ሊጐዳኝ

ተገቢ ትርጉሞች 1 አካላዊ ጥቃት በማንኛውም መንገድ ለያዕቆብ መከራ መንስሄ በመሆን

ነቁጣ እንስሳት

ነጭ ምልክት ያላቸው እንስሳት

መንጎቹ ወለዱ

በጎቹ ወለዱ

ዝንጉርጉር

ዝንጉርጉር ቀለም ያላቸው እንስሳት

በዚህ መንገድ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ

ይህም እንዴት እግዚአብሔር የአባታችሁን እንስሳት ለእኔ እንደሰጠኝ ነው

Genesis 31:10

አጠቃላይ መረጃ

ያዕቆብ ታሪኩን ለሚስቶቹ ለልያና ለራሔል መናገሩን ይቀጥላል

የሚጠቁበት ወራት በሚሆንበት ጊዜ

በሚጠቁበት ወራት

መንጋው በሚጠቃበት

እዚህ “መንጋው” ሴት ፍዬሎችን ያመለክታል:: አት: “ሴት ፍዬሎች በሚጠቁበት” (ክፍልን ለሙሉና ሙሉውን ለክፍል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ሽመልመሌ ዝንጉርጉርና ነቁጣ

ዝንጉርጉር ትንሽ ነቁጣና ትልቅነቁጣ ያላቸው

የእግዚአብሔር መልአክ

ተገቢ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር በሰው መልክ ሲገለጥ 2) ከእግዚአብሔር መልእክተኞች አንዱሲገለጥ ሀረጉ በተክክል እስካልተገለጸ ለ”መልአክ” የሚንጠቀመውን መደበኛ ቃል በመጠቀም በቀላሉ እንደ “እግዚአብሔር መልእክተኛ” መተረጐም ተገቢ ነው::

እኔም አልሁ

እኔም መለስሁ

እነሆኝ

አዎን እየሰማሁ ነኝ ወይም አዎን ምንድነው? በዘፍጥረት 22: 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡

Genesis 31:12

አጠቃላይ መረጃ

የእግዚአብሔርም መልአክ ያዕቆብን መናገር ቀጠለ:: (ዘፍጥረት 31:1ዐ ይመልከቱ)

ዐይኖችህን ቀና አድርግ

ይህ ቀና ብለህ ተመልከት ማለት ነው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

መንጎቹን የሚያጠቋቸውን

እዚህ “መንጋ” እንስት ፍዬሎች ብቻ ያመለክታል:: አት “የመንጋው እንስት ፍዬሎችን የሚያጠቋቸውን” (ክፍል ለሁሉና ሁሉን ለክፍል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ሽመልመሌ ዝንጉርጉርና ነቁጣ

ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸው

ዘይት የቀባሄው ሐውልት

ያዕቆብም ሐውልቱን ዘይፍ በመቀባት ለእግዚአብሔር የቀደሰው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

የትውልድህ ምድር

የተወለድህበት ምድር

Genesis 31:14

ራሔልና ልያም እንዲህ ብለው መለሱ

ይህ በተመሣሣይ ጊዜ ተናግረዋል ማለት አይደለም እንተስማሙ ያጸናል

ከአባታችን ሀብት የሚናገኘው ምን ድርሻ ወይም ውርስ አለን?

ራሔልና ልያ በጥያቄ መልክ አባታቸው ሊሰጣቸው ምንም እንዳልቀረ አጥብቀው ይናገራሉ፡፡ አት፡ “ከአባታችን ልንወርሰው በፍጹም የቀረ ምንም ነገር የለም!” (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

እኛን የሚያየን እንደባዕድ አይደለምን?

አባታቸው እንዴት እንደሚያዩአቸው ያላቸውን ቁጣ በጥያቄ ይገልጸሉ:: አት: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ገቢራዊ ዓረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል አት አባታችን እንደ ሴት ልጆቹ ሳይሆን እንደባዕድ ሴቶች ያየናል:: (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችና ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮች ይመልከቱ)

ሽጦናል

ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: ለራሱ ጥቅም ሽጦናል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ደግሞም ዋጋችንን በፍጹም በልቶታልና

ላባን ለሴት ልጆቹ መስጠት የነበረበትን ገንዘብ በፍጹም ለራሱ መጠቀሙ የዱር አራዊት እንደ ምግብ ገንዘቡን እንደበሉት ተደርጐ ተነግሮአል:: አት: “በፍጹም ገንዘባችንን ተጠቅሞአል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ)

ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው

ለእኛና ለልጆቻችን ይገባል

አሁንም

እዚህ አሁን የአሁን ጊዜ አይደለም ነገር ግን ለሚከተለውን አስፈላጊ ነጥብ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡

እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ አድርግ

እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ

Genesis 31:17

ወንዶች ልጆቹ

ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ ወሰደ:: ወራሾች ስለሆኑ ወንዶች ልጆቹን ብቻ የጠቀሳል:: አት: “ልጆቹን” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ከብቶቹን ሁሉ ነዳ

ሁሉን ከብቶች ነዳ:: እዚህ “ከብቶች” ሁሉን የቤት እንስሳትን ይወክላል፡፡

በጳዳን አራም ካፈራው ሀብት ሁሉ ጋር

በጳዳን አራም እያለ ያፈራቸውን ሌሎች ከብቶችንም

ከዚያም ወደ አባቱም አገር ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ጉዞውን ቀጠለ

አባቱ ይስሐቅ ወደሚኖርበት አገር ወደ ከነዓን ሄዴ

Genesis 31:19

ላባን በጐቹን ሊሸልት ሄዶ ሳለ

ላባን የበጐቹን ጸጉር ሊያስቆርጥ በሄደበት ጊዜ

ወንዙን

የኤፍራጥሰ ወንዝ ያመለክታል

አመራ

ተጓዘ

ወደ ኮረብታማው አገር ወደ ገለአድ

ወደ ገለአድ ተራራዎች ወይም ወደ ገለአድ ተራራ

Genesis 31:22

በሶስተኛው ቀን

የወጡበትን ቀን እንደ አንድ ቀን መቁጠር የአይሁድ ለማድ ነው:: አት: “ከወጡበት ሁለት ቀናት በኋላ”

ለላባን ተነገረው

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት አንድ ሰው ለላባን ነገረው ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮች ይመልከቱ

ያዕቆብም ኮበለለ

የቤተሰቡ መሪ ስለሆነ ያዕቆብ ብቻ ተጠቅሶአል ቤተሰቡ ከእርሱ ጋር እንደተጓዙ ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ያዕቆብ ከሚስቶቹና የልጆቹ ጋር ኮበለለ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ይዞ ተነሣ

ላባን ይዞ ተነሣ

ተከታተለው

አሳደደው

ለሰባት ቀናት ጉዞ

ያዕቆብን ደርሶ ለመያዝ ላባን ሰባት ቀናት ተጓዘ

ደረሰበት

ያዘው

Genesis 31:24

ከዚያም እግዚአብሔር ለሶሪያዊው ለላባን በሕልም ተገልጦ

“ከዚያም” የሚለው ቃል የተጠቀመው ታሪኩን ወደ ላባን የሕይወት ዳራ መረጃ ለመቀየር ነው አት: “በዚያ ሌሊት እግዚአብሔር ለላባን ተገልጦ” (የዳራ መረጃዎች ይመልከቱ)

ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ አለው

“ክፉ ሆነ ደግ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመው “ምንም” ለማለት ነው፡፡ አት፡ ያዕቆብን ከመሄድ ለማቋረጥ ለመሞከር ምንም ነገር እንዳትናገር (See: Merism)

ከዚያም ያዕቆብ ገለዓድ በተባለው ኰረብታማ አገር ድንኳን ተክሎ ሳለ ላባ ደረሰበት ላባና ዘመዶቹ በዚያው ሠፈሩ::

“ከዚያም” የሚለው ቃል የተጠቀመው ታሪኩን ወደ ያዕቆብናላባን የሕይወት ዳራ መረጃ ለመቀየር ነው:: አት: “ላባን ያዕቆብን በደረሰበት ጊዜ ያዕቆብ በኰረብታማው አገር ድንኳን ተክሎ ነበር: ከዚያም ላባንና ዘመዶቹ ደግሞ በኰረብታማው ገለዓድ አገር ድንኳን ተከሉ” (የዳራ መረጃዎች ይመልከቱ)

Genesis 31:26

ልጆቼን የጦር ምርኮኛ ይመስል አካልበህ ወሰድናቸው

ያዕቆብ ቤተሰቡን ከራሱ ጋር ወደ ከነዓን ምድር መውሰዱ ልክ ያዕቆብ እንደ የጦር ምርኮኞችን እናም አሰገድዶአቸው እየወሰደ እንዳለ ላባን ይናገራል ላባን ስለተቆጣና ያዕቆብ ስላደረገው ነገር ጸጸት እንዲሰማው አግንኖ ይናገራል:: (ተመሣሣይ ንጽጽር የማጋነንና ገሃዳዊ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ተደብቀህ ሄድህ

በድብቅ ሸሸህ

ፍስሐ በማድረግ

በደስታ

በከበሮ/ ታምቡርና በበገና

እነዚህ መሣሪያዎች ሙዝቃን የሚገልጹ ናቸው፡፡ አት፡ “እናም በሙዝቃ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ታምቡር

የከበሮ ዓይነት ለምት የሚሆን አናት ያለው ዙሪያሙ ከብረት የተሠራና መሣሪያው በሚመታበት ጊዜ የሚርገበገብ የሙዝቃ መሣሪያ ነው ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ

ወንዶች የልጅ ልጆቼን እንዲስማቸው

እዚህ ወንዶች የልጅ ልጆች ወንድ ሆነ ሴት ሁሉን የልጅ ልጆችን ይወክላሉ:: አት: “የልጅ ልጆቼን እንዲስማቸው” (በወንዴ ጾታ የተጠቀሱ ሴት ጾታንም የመግለጽ አባባል ይመልከቱ)

አሁን የሠራሄው የጅል ሥራ ነው

በጅልነት አድርገሄዋል

አሁንም

ይህ የዚያን ጊዜ ማለተ አይደለም ነገር ግን ለሚከተለውን ጠቃሚ ነገር ትኩረት እንደሰጥበት ነው

Genesis 31:29

እናንተን ልጐዳችሁ ነበር

እዚህ “እናንተ” ብዙና ከያዕቆብ ጋር ያሉትን ሁሉ ያመለክታል:: አት: “ሊጐዳችሁ የሚያስችለኝ ከእኔ ጋር ብዙ ሰዎች ነበሩ” (የሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ አለኝ

“ክፉ ሆነ ደግ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመው “ምንም” ለማለት ነው፡፡ በዘፍጥረት 31:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት፡ “ያዕቆብን ከመሄድ ለማቋረጥ ለመሞከር ምንም ነገር እንዳትናገር” (See: Merism)

አንተም ሄደሃል

አንተ የሚለው ነጠላና ያዕቆብን ያመለክታል:: (የሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

ወደ አባትህም ቤት

እዚህ ቤት ቤተሰብን ይወክላል:: አት: “ወደ አባትህና ሌሎች ቤተሰብህ ቤት ለመመለስ” (ክፍልን ሙሉና ሙሉውን ክፍል አድርጐ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

አምላኮቼን

ጣዖቶቼን

Genesis 31:31

ልጆችህን ከእኔ የምትቀማ ስለመሰለኝና ስለፈራሁ በድብቅ ወጣሁ፡፡

በድብቅ የወጣሁት ልጆችህን ከእኔ ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ ብዬ ስለፈራሁ ነው፡፡

ከእኛ መካከል የአንተን የጣዖታት ምስል ደብቆ የተገኘ ሰው ካለ ይሙት

ይህ በአዎንታዊ መንገድ መገለጽ ይችላል አት ጣዖቶችህን የሰረቀ ማንም ቢገኝ እንገድላለን (ምጸት ይመልከቱ)

ዘመዶቻችን/የእኛ ዘመዶች ባሉበት

የእኛ የሚለው ቃል የያዕቆብ ዘመዶችንና የላባን ዘመዶች ያመለክታል:: ሁሉም ዘመዶች ፍትሃዊና ግልጽ መሆኑን ለማረጋገጥ ያዩታል (ሁሉ አቀፍ አንደኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)

ያንተ የሆነ አንዳች ነገር ከኔ ዘንድ ቢገኝ ውሰድ

በእኛ ዘንድ ካለው ያንተ የሆነውን ፈልግና ውሰድ

ያዕቆብ ራሔል እነዚያን/ጣዖታቱን መስረቋን አያውቅም ነበር

ይህም ታሪኩን ወደ ያዕቆብ ሕይወት ዳራ መረጃ ይቀይራል (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 31:33

ሁለቱ ደንገጡሮቿ

ዘለፋንና ባላን ያመለክታል

አላገኛቸውም

ጣዖታቱን አላገኘም

Genesis 31:34

ከዚያም ራሔል በላያቸው ተቀምጣ ነበር

ከዚያም የሚለው ቃል ታሪኩን ወደ ራሔል ሕይወት ዳራ መረጃ የቀይራል (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)

ኮርቻ

ሰው እንዲቀመጥበት በጋማ እንስሳት ጀርባ የሚደረግ መቀመጫ ነው

ጌታዬ

አንድን ሰው “ጌታዬ” ብሎ መጥራት የማክበር መንገድ ነው

በፊትህ ተነስቼ መቆም ስላልቻልሁ

ይህ ከማሕጸንዋ ወራዊ ደም የሚፈስበት ጊዜ ውስጥ እንዳለች ያለመክታል:: (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ በተዘዋዋሪ አንድን ነገር ስለመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 31:36

እርሱም እንዲህ አለው

ያዕቆብ ላባንን እንዲህ አለ

ወንጄሌ ምንድነው? ይህን ያህል የምታሳድደኝ ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው?

ወንጄሌ ምንድነው እና ኃጢአቴ ምን ሆን የሚሉ ሀረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ያዕቆብ ላባንን ምን ስህተት እንደሠራ ይጠይቀዋል አት ይህን ያህል በጽኑ የምታሳድደኝ ምን ስህተት ቢፈጽም ነው? (ተጓዳኝ ተነጻጻሪ አባባል ይመልከቱ)

በጽኑ

እዚህ “ጽኑ” የሚለው ቃል ላባን በማጣደፍ ያዕቆብን ለመያዝ ባለው ተነሣሽነት እንዳሳደደው ይገልጻል (ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ)

ከቤትህስ ዕቃ ሁሉ ምን አገኘህ?

ያንተ ሆኖ ያገኘሄው ዕቃ የትኛው ነው?

በእኛ ዘመዶች ፊት አቅርብ

እዚህ እኛ የሚለውቃል የያዕቆብ ዘመዶችና የላባንን ዘመዶች ያመለክታል:: አት: ያገኘሄውን ማንኛውንም ነገር በዘመዶቻችን ፊተ አቅርብ (አካታች አንደኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)

እነርሱ ሁለታችንን ይፍረዱ ወይም እነርሱ ይፍረዱን

እዚህ “ሁለታችን” ያዕቆብንና ላባን ያመለክታል:: “ይፍረዱን” የሚለው አባባል ከክርክሩ የትኛው ትክክል እንደሆነ ይወስኑ ማለት ነው፡፡

Genesis 31:38

አጠቃላይ መረጃ

ያዕቆብ ለላባን መናገሩን ቀጠለ

ሃያ ዓመታት

2ዐ ዓመታት (ቁጥሮች ይመልከቱ)

ሴት በግ

እንስት የበግ ጠቦት

አልጨነገፉም

በእርግዝና ወቅት የተቀጨ ወይም ሞቶ የተወለደ ጠቦት አልነበረም ማለት ነው

በአውሬ የተሰበረውን አምጥቼ አላውቅም

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል አት አውሬ ከእንሰሳትህ አንዱን በገደለ ጊዜ በድኑን ለአንተ አምጥቼ አላውቅም (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ያጣሄውን እተካ ነበር

ያዕቆብ ከመንጋው የላባንን ሙት እንስሳት ምትክ መቁጠር በጫንቃው እንደተሸከመው ሽክም እንደነበር ተደርጐ ተገልጾአል:: አት: “ከመንጋህ እንደጠፋ ከመቁጠር ከመንጋዬ እንደጠፋ ቆጥረዋለሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

በቀን በሐሩር ሌሊት በቁር ይበላኝ ነበር

በሞቃትና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ መሠቃየት የአየር ሁኔታዎች ያዕቆብ እንደ አውሬዎች እንደበሉ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት በቀን ሐሩርና በሌሊት ቁር ከመንጋዎችህ ጋር ነበርሁ (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 31:41

አጠቃላይ መረጃ

ያዕቆብ ለላባን መናገሩን ቀጠለ

እነዚህ ሃያ ዓመታት

እነዚህ 2ዐ ዓመታት (ቁጥሮች ይመልከቱ)

አሥራ አራት ዓመታት

14 ዓመታት (ቁጥሮች ይመልከቱ)

ደመወዘን አሥር ጊዜ ለዋውጠህብኛል

መክፈል ያለበትን አሥር ጊዜ ለዋውጦብኛል:: በዘፍጥረት 31:7 ደመወዜን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

የአባቴ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሃት ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ

የአብርሃምና የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ

የአባቴ አምላክ

እዚህ “አባቴ” የሚለው ቃል አባቱን ይሰሐቅን ያመለክታል::

ይስሐቅ የሚፈራው

እዚህ “ፍርሃት” ለእግዚአብሔር ያለውን ፍርሃት ያመለክታል፡፡

ባዶ እጄን

ይህ ምንም አለመኖር ማለት ነው:: አት: “ፍጹም ባዶ” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

እግዚአብሔር መከራዬን አይቶ ልፋቴን ተመልክቶ

መከራ የሚለው ረቂቅ ስም መከራ አየ በሚቶል ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር ልፋቴን አይቶ እንዴት መከራ እንዳሳየሄኝ ተመልክቶ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

Genesis 31:43

ነገር ግን በእነዚህ ሴቶች ልጆቼና በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ?

ላባን ምንም ማድረግ እንደማይችል አግንኖ ለመቅለጽ ጥያቄ ይጠቀማል ይህ አጋናኝ ጥያቄ በዐረፍተነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ነገር ግን ከእኔ ጋር ወደ ኋላ ለመመለስ በልጆቼና በልጅ ልጆቼ ምንም ላደርግ አልችልም” (አግናኝ ጥቃቄዎች ይመልከቱ)

ምስክር ይሁን

እዚህ “ምስክር” የሚለው ቃል ሰውን አያመለክትም ነገር ግን ያዕቆብና ላባ የሚገቡትን ቃልኪዳን የሚያመለክትና በምሳለያዊነት የተጠቀመ ነው:: ምስክሩ ሁለቱ በሰላማዊ መንገድ ስስማሙ እንደተገኘ ሰው ተደርጐ ተነግሮአል (ሰውኛ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 31:45

ሐውልት

ይህ በክስተቱ ማብቂያ ያቆመው ትልቅ ድንጋይ ሲሆን አስፈላጊ ክስተት እንደተከናወነ ለማመለከት ነው

ድንጋይ ከመሩ

ድንጋዩን አንዱን በአንዱ ላይ በማድረግ ከመሩ

ከዚያም በድንጋዩ ክምር አጠገብ በሉ

አብሮ ምግብን መመገብ ቃል ኪዳን መፈጸሚያ አካል አንዱ ነው የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ይጋርሠሀዱታ

ተርጓሚዎች የማከተውን እንደግርጌ ማስናታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ይጋርሠሀዱታ” የሚለው ስም በላባን ቋንቋ “ክምር ምስክርነት” ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ገለዓድ

ተርጓሚዎች የማከተውን እንደግርጌ ማስናታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ገለዓድ” የሚለው ስም በላባን ቋንቋ “ክምር ምስክርነት” ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 31:48

ይህ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ምስክር ነው

ድንጋዮች በእርግጥ እንደሰው ምስክር ሊሆኑ አይችሉም:: አት: “ይህ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ማስታወሻ ይሆናል” (በሰውኛ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ገለዓድ

ተርጓሚዎች የማከተውን እንደግርጌ ማስናታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ገለዓድ” የሚለው ስም በላባን ቋንቋ “ክምር ምስክርነት” ማለት ነው:: በዘፍጥረት 31:47 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ምጽጳ

ተርጓሚዎች የማከተውን እንደግርጌ ማስናታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ምጽጳ” የሚለው “የመጠበቂያ ማማ” ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

እኛ በማንተያይበት ጊዜ

እዚህ “አለመተያየት” በተለያየን ይወክላል:: አት “በተለያየን ጊዜ” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት ስለመጠቀም ይመልከቱ)

ማንም ከእኛ ጋር ባይኖር

እዚህ “እኛ” ያዕቆብንና ላባን ያመለክታል:: አት: “ማንም የሚያየን ባይኖር”

እይ

“ተመልከት” “አስተውል” “ለሚናገረው ነገር ትኩረት ስጥ”

Genesis 31:51

ይህ ክምር መሥክር ነው… ይህም ሐውልት ምሥክር ነው

የሰላም ስምምነታቸውን በሚመለከት እነዚህ የድንጋይ ክምሮች ለላባና ለያዕቆብ የማስታወሻና ድንበር ምልክቶች ናቸው:: እነዚህ እንደሰው ምሰክሮች እንደሆኑ ተደርጐ ተነግሮአል (በሰውኛ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

የአባቱ የይስሐቅ ፍርሃት

እዚህ “ፍርሃት” ይስሐቅ ለእግዚአብሔር ያለውን አክብሮትና ያንንም በመታዘዝ መግለጹን ያመለክታል፡፡

Genesis 31:54

ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው

አብሮ ምግብ መብላት አብሮ ቃል ኪዳን የመግባት አካል ነው የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

በማግስቱም ማለዳ…ወደ አገሩ ተመለሰ

ቁጥር 55 በመጀመሪያው የዕብራይስጡ መጽሐፍ የምዕራፍ 32 የመጀመሪያ ቁጥር ነው ነገር ግን በአብዛኛዎቹ ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሶች የምዕራፍ 31 የመጨረሻ ቁጥር ነው በዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሶች የተጠቀመውን የቁጥር አቀማመጥ በቋንቋዎ እንዲጠቀሙ ይመከራል

የተባረከ

አዎንታዊና ጠቃሚ ነገሮች ለአንድ ሰው እንዲደረጉ መሻትን የሚገልጽ ማለት ነው