Genesis 30

Genesis 30:1

ራሔል ለያዕቆብ ልጅን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ

ራሔል ማርገዝ እንዳልቻለች ባወቀች ጊዜ

እሞታለሁ

ራሔል ልጅ ባለመኖርዋ ምነኛ እንደተከፋች ማጋነንዋ ነው:: አት: ምንም እንደማልጠቅም ይሰማኛል:: (በማጋነንና በገሃድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ልጅ ስጠኝ

እንዳረግዝ አድርገኝ

ያዕቆብም ቁጣ በራሔል ላይ ነደደ

የያዕቆብ ቁጣ እንደ እሳት ተደርጐ ተገልጾአል፡፡ አት፡ “ያዕቆብ ራሔልን በጣም ተቆጣት” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እኔ እንዳትወልጂ ያደረግሽን እግዚአብሔርን መሰልኩሽን?

ይህ ያዕቆብ ራሔልን ለመቆጣት የተጠቀመው ቅኔያዊ ጥያቄ ነው:: ይህም እንደ ዐረፍተ ነገር ልተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “እኔ እግዚአብሔር አይደለሁም! ልጅ እንዳትወልጂ የሚከለክለው እኔ አይደለሁም” (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

Genesis 30:3

እርስዋም አለች

ራሔል አለች

እነሆ

“ተመልከት” ወይም “ስማ” ወይም “ሊናገር ስላለሁ ነገር ትኩረት ስጥ”

አገልጋዬ ባላ አለችልህ ……. ከእርስዋ ልጆች እንዳገኝ

በዚያን ጊዜ መካን ሴት በሕጋዊነት ልጅ የሚታገኝበት ተቀባይነት ያለው መንገድ ይህ ነው:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ባላ

የራሔል ሴት ባሪያ ስም ነው፡፡ በዘፍጥረት 29፡29 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡

በጉልበቶቼ ወይም በጭኖቼ

ይህ ባላ የሚትወልደው ልጅ ለራሔል እንደሚሆን የሚገልጽ አባባል ነው:: አት: “ለእኔ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

በእርሷ አማካኝነት ልጅ ይኖረኛል

በዚህ መንገድ ልጅ እንዲኖረኝ ታደርጋለች

Genesis 30:5

ባላ

የራሔል ሴት ባሪያ ስም ነው፡፡ በዘፍጥረት 29፡29 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡

ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደች

ለያዕቆብ ወንድ ልጅም ወለደችለት

ስሙንም አወጣችለት

ራሔል ስም አወጣችለት

ዳን ብላ ጠራችው

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ዳን የሚለው ስም ‘እርሱ ይፈርዳል’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 30:7

ባላ እንደገና ጸነሰች

ባላ እንደገና አረገዘች

ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደች

ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅን ወለደችለት

ከእኀቴ ጋር ብርቱ ትግልን ታገልሁ

ትግልን ታገልሁ የሚለው ሀረግ አጽንዖትን የሚሰጥ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው ራሔል እንደ እኀትዋ አንድን ልጅ ለማግኘት ያደረገችው ከልያጋር አካላዊ ትግል እንዳደረገች የሚገልጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው:: አት: “እንደ ታላቅ እኀቴ ልያ ልጅን ለማግኝት ትልቅ ተጋድሎ አድርጌያለሁ:: (ፈሊጣዊና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ቻልኩኝ

አሸነፍሁ ወይም ተሳክቶልኛል

ስሙንም ንፍታለም ብላ አወጣችለት

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ንፍታለም የሚለው ስም ‘ትግሌ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 30:9

ልያም ባየች ጊዜ

ልያም በተረዳች ጊዜ

አገልጋይዋን ዘለፋን ወሰደች ሚስት ትሆነውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው

አገልጋይዋን ዘለፋን ሚስት እንዲትሆነው ለያዕቆብ ሰጠችው

ዘለፋ

የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደች

ለያዕቆብ ወንድ ልጅን ወለደችለት

ምን ዓይነት መታደል ነው!

እንዴት ያለ መታደል ነው! ወይም ምን ዓይነት ዕድል ነው!

ስሙንም ጋድ ብላ አወጣችው

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ጋድ የሚለው ስም ‘እድለኛ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 30:12

ዘለፋ

የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደች

ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት

ምነኛ ደስተኛ ሆንሁ!

እንዴት የተባረኩ ነኝ! ወይም እንዴት ደስተኛ ነኝ !

ሴቶች ልጆች

ሴቶች ወይም ልጃገረዶች/ወጣት ሴቶች

ስሙንም አሴር ብላ አወጣችለት

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “አሴር የሚለው ስም ‘ደስታ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 30:14

ሮቤል ወደ ሜዳ ወጣ

ሮቤልም ወጣ

ስንዴ በሚታጨድበት ቀናት

ቀናት የሚለው አባባል በዓመት ውስጥ ያለ ወቅት ወይም ጊዜ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: አት “በዓመት ስንዴ በሚታጨድበት ጊዜ” ወይም “ስንዴ በሚታጨድበት ወቅት” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እንኮይ

ከፍቅረኛ ጋር ለመተኛት ስሜት የሚያነሣሣና ፍሬን የሚጨምር የአትክልት ፍሬ ነው:: አት: “የፍቅር ፍሬ” (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ባሌን….ጥቂት ነገር ነውን?

ባሌን …. አይሰማሽምን? ይህ ራሔልን ለመቆጣት የተጠቀመችው ቅኔያዊ ጥያቄ ነው ይህ ጥያቄ በስድ ዐረፍት ነገር ሊገለጽ ይችላል:: ባሌን የማያስከፋ ነው:: (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ) …ደግሞ ሊትወስጂ አማረሽ? ይህንም ቅኔ አዘል ጥያቄ የተጠቀመችው ራሔልን ለመቆጣት ነው ይህ ጥያቄ በስድ ዐረፍት ነገር ሊገለጽ ይችላል:: አት: አሁን ደግሞ… አማረሽ! (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ከዚያም ይተኛ

“ከዚያም ያዕቆብ ይተኛ” ወይም “ያዕቆብ እንዲተኛ እፈቅዳለሁ”

Genesis 30:16

በልጄ እንኮይ

ለልጄ “እንኮይ” ዋጋ በዘፍጥረት 3ዐ;14 እንኮይ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

ጸነሰች

አረገዘች

ለያዕቆብ አምስተኛ ወንድ ልጅ ወለደች

አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች

እግዚአብሔር ዋጋዬን ከፈለልኝ

እግዚአብሔር ልያን መካሡ ለሚሠራው ሠራተኛ አንድ አለቃ ድርጐውን እንደሚከፍል እንደከፈለላት ተደርጐ ተገልጾአል “እግዚአብሔር የድርሻዬን ሰጠኝ” ወይም “እግዚአብሔር ካሠኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ስሙንም ይሳኮር ብላ አወጣችለት

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ይሳኮር የሚለው ስም ‘ካሣ አለ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 30:19

ልያ አሁንም ደግሞ ጸነሰች

ልያ እንደገና አረገዘች

ለያዕቆብ ስድስተኛ ወንድ ልጅ ወለደች

ስድስተኛ ወንድ ልጅም ለያዕቆብ ወለደች

ስሙንም ዛብሎን አለችው

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ዛብሎን የሚለው ስም ‘ክብር’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ስምዋንም ዲና አለቻት

ይህ የልያ ሴት ልጅ ስምዋ ነው፡፡(ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 30:22

እግዚአብሔርም ራሔልን አሰባት ልመናዋንም ሰማ

አሰባት የሚለው አባባል አስተዋላት ማለት ነው:: ይህ እግዚአብሔር ራሔልን ረስቶአታል ማለት አይደለም:: ጥያቄዋን አሰበ ማለት ነው:: አት: “እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ የፈለገችውንም ሰጣት” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ኀፍረተን አስወገደልኝ

እግዚአብሔር ራሔል እንዳታፍር ያደረገው ሐፍረት አንድ ሰው ከአንድ ሰው ወስዶ እንደሚያስወግድ ዕቃ ተደርጐ ተነገሮአል:: ረቂቅ ስም ሐፍረት እንደ እፍረት ሊገለጽ ይችላል::

አት: እግዚአብሔር ከእንግዲህ ወዲህ እንዳላፍር አድርጐኛል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር ወይም ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ) ስሙንም ዮሴፍ አለችው

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ዮሴፍ” የሚለው ስም ‘እርሱ ይጨምር’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ሌላ ወንድ ልጅ ጨምሮ ይስጠኝ

የራሔል የመጀመሪያዎቹ ወንድ ልጆች ከሴት አገልጋይዋ ከባላ ነበር

Genesis 30:25

ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ

ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ

እናም እመለስ ዘንድ

እንዲመለስ

እንዳገለገልሁህ ታውቃለህ

ያዕቆብ ላባንን የተስማሙበትን ኮንትራት ያስታውሳል (ዘፍጥረት 29 :27) ረቂቅ ስም “አገልግሎት” እንደ “አገለገለ” ሊገለጽ ይችላል:: አት: ለረጅም ጊዜያት እንዳገለገልሁህ ታውቃለህ:: (ረቂቅ ስሞች ይጠቀሙ)

Genesis 30:27

ላባንም እንዲህ አለው

ላባንም ያዕቆብን እንዲህ አለው

በአይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ቢሆን

አይኖች ማየትን ይወክላሉ እናም ማየት ሃሳብን ወይም ውሳኔን ይወክላል:: አት: “በአንተ ፊት ሞገስ ካገኘሁ” ወይም “በእኔ የተደሰትህ ከሆንህ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ሞገስ ማግኘት

አንድ ሰው በሌላኛው ሰው ዘንድ ሞገስ ማግኘቱን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ቆይ ምክንያቱም

ተቀመጥ ምክንያቱም

በንግርት ተረድቸአለሁ

በመንፈሳዊና ማጅካዊ ልምምዶቼ ተረድቸአለሁና

በአንተ የተነሣ

በአንተ ምክንያት

ደመወዝህን ንገረኝ

ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት እዚሁ ላቆይህ ምን ያህል መክፈል እንዳለብኝ ንገረኝ፡፡ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 30:29

ያዕቆብም አለው

ያዕቆብ ላባንን አለው

ከብቶችህ በእኔ ጥበቃ ምን ያህል እንደተመቻቸው

ጥበቃ ከጀመርኩባቸው ጊዜ ከብቶች እንዴት እንደተመቻቸው

እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት ነበሩ

ለአንተ ሥራ ከመጀመረ በፊት መንጐችህ ጥቂት ነበሩ

እናም ይህ በመጨመር ተትረፍርፎአል

ነገር ግን አሁን ሀብትህ በጣም ጨምሮአል

አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የሚሆነውን የማቀርበው መቼ ነው?

አሁንም እኔ ደግም ለቤተሰቤ የምሠራው መቼ ነው? ያዕቆብ ለቤተሰቡ የሚሆነውን ማቅረብ እንዳለበት ለማጽናት ጥያቄ ይጠቀማል ይህም ጥያቄ በዐረፍተነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “አሁን ለቤተሰበ የሚሆነውን ማሰብ አለብኝ” (ቅኔ አዘል ጥያቄችን ይመልከቱ)

Genesis 30:31

ታዲያ ምን ልስጥህ?

“ታዲያ ምን መክፈል እችላለሁ?” ወይም “ታዲያ ምን መስጠት እችላለሁ?” ይህ የበለጠውኑ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት እንዲትቆይና እንዲትሠራልኝ ዘንድ ምን መክፈል እችላለሁ?(ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)

ይህንም ነገር ቢታደርግልኝ

ያዕቆብ ሊናገር ያለው እርሱ ከተናገረው ጋር እንደሚጻረር ለማሳየት አገናኝ ቃል “ነገር ግን” በመግቢያው ሊጠቀም ይቻላል:: አት: “ነገር ግን ይህንም ነገር ቢታደርግልኝ” (አገናኝ ቃላት ይመልከቱ)

ይህ ነገር

“ይህ ነገር” የሚለው ሀረግ ያዕቆብ በቁጥር 32 የሚያቀርበውን ያመለክታል::

መንጎችህን እመግባለሁ/አሠማራለሁ እጠብቃለሁ

መንጎችህን እመግባለሁ እጠብቃለሁ

ከበጐቹ መካከል ዝንጉርጉር የሆኑትን ነቁጣ ያለባቸውንና ጥቋቁሮቹን እንዲሁም ከፍዬሎች ነቁጣ ያለበቸውንና ዥንጉርጉሮቹን እለያለሁ

ማንኛውንም ዥንጉርጉርና ጥቁር የሆነውን በግና ዝንጉርጉር የሆነውን ፍዬል እለያለሁ

እነዚህ ደመወዜ ይሁኑ

እንዚህ እዚሁ ለሚቆየው ዋጋዬ ይሁኑ

Genesis 30:33

ታማኝነቴ ይታወቃል

ታማኝነት የሚለው ቃል አማንነት ማለት ነው ይህም ታማኝነት አንድ ሰው ሰለሌላኛው ሰው በመደገፍ ወይም በመቃወም የሚሰጠው ምሥክርነት እንደሆነ ይናገራል:: አት: “ለአንተ ታማኝ መሆነንና አለመሆነን በኋላ ታውቀዋለህ”:: (ሰውኛ አገላለጽ ይመልከቱ)

በመንጋቼ መካከል ዥንጉርጉር ወይም ነቁጣ የሌለበት ፍዬል ወይም ጥቁር ያልሆነ ቢገኝ ያ እንደተሰረቀ ይቆጠር

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ ገቢራዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል አት ማንኛውም ዥንጉርጉር ያለሆነ ፍዬልና ጥቁር ያልሆነ በግ ቢታገኘው እንደተሰረቀ መቁጠር ትችላለህ:: (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዙ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

እነሆ እንደቃልህ ይሁን

“እንደተናገርከው ይሁን” ወይም “አንተ እደተናገርከው እናደርጋለን”

Genesis 30:35

ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቁጣ ያለባቸውን

ሽመልመሌና ነቁጣ ያለባቸውን

ነቁጣ ያለባቸውንና ዥንጉርጉር የሆኑትን

ነቁጣ ያለባቸውን

ማንኛውንም ነጭ ያለበትን

ማንኛውም ነጭ ያለበት በግ

ከበጎች ሁሉ ጥቋቁር የሆኑትን

ጥቁር በጎችን ሁሉ

በእነርሱ እጅ ሰጣቸው

እዚህ “እጅ” “ቁጥጥር” ወይም “ጥበቃ” የሚተካ ነው:: አት: “ልጆቹ እንዲጠብቁ አደረጋቸው” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 30:37

እርጥብ የልብን የለውዝንና የኤርሞን

እነዚህ ሁሉ ነጭ ዛፎች ናቸው:: (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ቅርፊታቸውን ልጦ የበትሮቹ ውስጠኛው ነጩ አካል እንዲታይ አደረገ

የቅርፊታቸውን አንዳንድ ክፍሎችን በመላጥ የበትሮቹ ውስጠኛው ነጭ አካል እንዲታይ አደረገ

በማጠጫ ገንዳዎች

ከብቶችን ለማጠጣት ውሃን የሚይዙ ረጅምና ክፍት የሆኑ ገንዳዎች

Genesis 30:39

መንጋዎች ይሳረሩ ነበር

“የመንዎች እንስሳት ይጸልሱ ነበር” ወይም “ይጠቃቁ ነበር”

ሽመልመሌ ዝንጉርጉርና ነቁጣ የጣለባቸውን ግልገሎች ወለዱ

ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን ግልገሎት ወለዱ

ያዕቆብም ለያቸው

ይህ ለብዙ ዓመታት እንደተረገ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ለሚቀጥሉት ብዙ ዓመታት ያዕቆብ ለያቸው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ፊታቸውን መልሰው

ፊት ለፊት እያዩ

ከመንጋዎቹ ለራሰ ለያቸው

የራሱን መንጋ ለየ

Genesis 30:41

በመንጋዎች ዐይን ፊት

እዚህ የመንጋዎች ዐይን በጎችን ወይም መንጋዎችን የሚያመለክትና የሚያዩትን እንደሚያተኩር ነው:: አት: (መንጋው እንዲያየው ዘንድ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉውን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

በበትሮቹ መካከል

በበትሮቹ ፊትለፊት

በከሱ እንስሳት

በደካማዎች እንስሳት

ስለዚህ ደካማ ደካማዎቹ ለላባን ሲሆኑ ብርቱ ብርቱዎቹ ለያዕቆብ ሆኑ

ይህን ይበልጥኑ ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ደካማ ደካማዎቹ ዝንጉርጉርና ነቁጣ ስለሌላቸው ለላባን ሲሆኑ ብርቱ ብርቱዎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ ስላላቸው ለያዕቆብ ሆኑ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 30:43

ይህ ሰው

ያዕቆብ

እጅግ ባለጠጋ ሆነ

“እጅግ በለጸገ” ወይም “ሀብታም ሆነ”