36

1 ኤዶም የተባለው የዔሳው የትውልድ ታሪክ የሚከተለው ነው፤

2 ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤውያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣ 3 እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችውን የእስማኤል ልጅ ቤስሞት ነበሩ። 4 ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት። 5 እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆቹ ናቸው። 6 ዔሳው ሚስቶቹንና ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ። 7 ብዙ ሀብት ስለነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፣ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም። 8 ስለዚህ ዔዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።

9 በተራራማው አገር በሴይር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤

10 የዔሳው ልጆች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤

11 የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤

12 የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።

13 የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህም ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው።

14 የፅብዖን የልጅ ልጅ፤ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤

15 ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኩር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ቄኔዝ 16 ቆሬ፣ ጎቶምና አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።

17 የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሃማና፣ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ነበሩ።

18 የዔሳው ሚስት የአሕሊባማ ልጆች፦የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ ከዔሳው ሚስት አሕሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። 19 እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።

20 በኤዶም ምድር ነዋሪዎች የነበሩት የሴይር ልጆች የነበሩ የሖራውያን አለቆች፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣ 21 ዲሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ በሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።

22 የሎጣን ልጆች፦ ሖሪና ሔማም የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር።

23 የሦባል ልጆች፦ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባልና ስፎና አውናንም፤

24 የፅብዖን ልጆች፦ አያና፣ ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅባዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍልውሃ ምንጮችን በምድረበዳ ያገኘ ሰው ነው።

25 የዓና ልጆች፦ዲሶንና የዓና የሴት ልጅ አህሊባማ፤

26 የዲሶን ልጆች፦ ሔምዳን፣ ሴስባን፣ ይትራንና ክራን፤

27 የኤድር ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤

28 የዲሳን ልጆች፦ዑፅና አራን።

29 የሖራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ፅዖን፥ ዓና፣ 30 ዶሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።

31 ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦

32 የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነግሦ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።

33 ባላቅ ሲሞት፣ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።

34 የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ሲሞት የቴማኒው ሑሳም ነገሠ።

35 ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር።

36 ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።

37 ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ።

38 ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በልሐናን በምትኩ ነገሠ።

39 የዓክቦር ልጅ በልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብዔል ሲሆን፣ እርሷም መጥሬድ የወለደቻት የሜዛሃብ ልጅ ነበረች።

40 ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ፣ ዓለዋ፣ የቴት፣ 41 አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፌኖን፣ 42 ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 43 መግዲኤልና ዒራም፣ እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነበር።