ምዕራፍ 2

1 ከአስራ አራት ዓመት በኋላ ቲቶን ይዤ ከበርናባስ ጋር እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ። 2 የሄድኩበትም ምክንያት መሄድ እንዳለብኝ እግዚአብሔር ስላመለከተኝ ነበር። ሄጄም በአህዛብ መካከል እየሰበኩት ስላለው ወንጌል ነገርኳቸው፣ ነገር ግን በከንቱ እንዳልሮጥኩ ወይም እየሮጥኩ እንዳልሆን እርግጠኛ ለመሆን ይህን የተናገርኩት በሌሎቹ ዘንድ እንደ ዋና ለሚታሰቡት ብቻ ነበር። 3 ግሪካዊ የሆነው ሲላስ እንኳ እንዲገረዝ አልተገደደም። 4 ይህ ጉዳይ የተንሳው በክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነት ለመሰለል ሾልከው በገቡ ውሸተኞች ወንድሞች ምክንያት ነበር። 5 የህግ ባሪያዎች ሊያደርጉን ይመኙ ነበር። ነገር ግን ለእናንተ ወንጌሉ ሳይለወጥ ይቆይላችሁ ዘንድ ለአንድ ሰዓት እንኳ ለሀሳባቸው አልተገዛንም። 6 ነገር ግን ሌሎች መሪዎች ናቸው ያልዋቸው ምንም አስተዋፅኦ አላደርጉልኝም። ማንም ይሁኑ ለእኔ ትርጉም አልነበረውም። ሆኖም ግን ልክ ጴጥሮስ ለተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተሰጠው ሁሉ 7 እኔም ላልተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተቀበልኩ አዩ፥ 8 ምክንያቱም ለተገረዙት ሃዋሪያ ይሆን ዘንድ በጴጥሮስ የሰራ እግዚአብሔር ላልተገረዙት ሃዋሪያ እሆን ዘንድ በእኔም ስለሚስራ ነው። 9 እንደመሪዎች የሚታወቁት ያዕቆብ፥ኬፋና ዮሀንስ በእኔ ላይ ያለውን ፀጋ ባዩ ጊዜ እኛ ወደ አህዛብ እነርሱ ደግሞ ወደተገረዙት ይሄዱ ዘንድ የማህበራቸውም ተካፋዮች እንድንሆን ሙሉ መብት ሰጡን። 10 እኔ ለማድረግ የምናፍቀውን ድሆችን እንድናስብም አሳሰቡን። 11 ከዚያም ኬፋ ወደ አንፆኪያ በመጣ ጊዜ ሥራው ትክክል ስላልነበረ ፊት ለፊት ተቃወምኩት። 12 ምክንያቱም ከያዕቆብ ዘንድ ሰዎች ከመምጣታቸው በፊት ኬፋ ከአህዛብ ጋር ይበላ ነበር። ሰዎቹ በመጡ ጊዜ ግን እነኚህን የተገረዙ ሰዎች ፈርቶ ከአህዛብ ጋር መብላቱን አቆመ እንዲያውም ተለያቸው። 13 በርናባስ እንኳ በግብዝነታቸው እስኪሳብ ድረስ ሌሎቹም አይሁድ በኬፋ ግብዝነት ተካፋዮች ነበሩ። 14 ወንጌልን በሚፃረር መንገድ መሄዳቸውን ባየሁ ጊዜ ኬፋን በሁሉም ፊት «አንተ አይሁዳዊ ሆንህ በአህዛብ ስርአት የምትኖር ከሆነ አህዛብ በአይሁድ ስርአት እንዲኖሩ ለምን ታስገድዳቸዋልህ?» አልኩት። 15 እኛ«አህዛብ ኃጢአተኞች» ያልሆንን ነገር ግን በትውልድ አይሁዳዊ የሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ባለ እምነት እንጂ ማንም ህግን በመፈፀም እንደምይፀድቅ እናውቃለን። 16 በህግ ሥራ ማንም ሊፀድቅ ስለማይችል በህግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነት እንፀድቅ ዘንድ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ እምነት ተጠርተናል። 17 ነገር ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲያፀድቀን እየፈለግን ሳለ ራሳችንን ኃጢአተኞች ሆነን እናገኛለን፥ 18 ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ሆነ ማለት ነው? በፍፁም አይደለም። 19 ምክንያቱም አውልቄ የጣልኩትን ህግን የመፈፀም ትምክህት እንደገና ብገነባ ራሴን ህግ ተላላፊ ሆኜ አገኘዋለሁ። በህግ በኩል ለህግ ሞቼአለሁ። 20 ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። 21 የእግዚአብሔርን ፀጋ አላቃልልም፥ ህግን በመጠበቅ ፅድቅ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ መሞቱ ከንቱ በሆነ ነበር።