ምዕራፍ 6

1 እንደዚሁም፥ አብሮ እንደሚሰራ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንዲሁ እንዳትቀበሉ እለምናችኋለሁ። 2 ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሏልና "በምቹ ጊዜ ሰማሁህ በድነትም ቀን ረዳሁህ።" ልብ በሉ፥ ምቹ ጊዜም ሆነ የድነት ቀን አሁን ነው። 3 አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ በማንም ፊት ማሰናከያ አናኖርም። 4 ከዚያ ይልቅ፥ በድርጊቶቻችን ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች መሆናችንን እናረጋግጣለን። ይህም በመፅናት፥በመከራ፥ በስቃይ፥በችግር 5 በመገረፍ፥ በእስራት፥ጥላቻ በተሞላ አመፅ፥ ፥በከባድ ስራ ፥እንቅልፍ በማጣት፥በርሃብ፥ 6 በንፅህና፥በእውቀት፥በትዕግስት፥በርህራሄ፥በመንፈስ ቅዱስ፥በእውነተኛ ፍቅር፥ 7 በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ሃይል ማለትም ለቀኝ እና ለግራ ለሚሆን ለፅድቅ የጦር ዕቃ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን። 8 በክብርም ሆነ በውርደት፥ በሃሜትም ሆነ በሙገሳ ውስጥ እንሰራለን። በሃሰት ብንከሰስም እውነተኞች ሆነን ተገኝተናል። 9 ያልታወቅን ሆነን ስንሰራ፥እንታወቃለን፤ የምንሞት ስንመስል ህያዋን ነን። በጥፋታችን እንደሚቅጣ ሰው ብንሆንም፥ሞት አልተፈረደብንም። 10 እንደ ሃዘንተኞች ስንሰራ ሁልጊዜም ግን ደስተኞች ነን፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለፀጎች እናደርጋለን፥ ምንም የሌለን ስንሆን፥ ሁሉም አለን። 11 የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ ሁሉን ነገር በግልፅ ነግረናችኋል፥ልባችንንም ለእናንተ ከፍተንላችኋል። 12 ልባችሁ በራሳችሁ መሻት እንጂ በእኛ ምክንያት አልተዘጋም። 13 ተገቢ በሆነ ሁኔታ እኔም እንደ ልጆች እናገራችኋለሁ፤ልባችሁን ክፈቱልን። 14 ከማያምኑ ጋር በማይሆን መንገድ በአንድ ላይ አትተሳሰሩ። ፅድቅ ከአመፀኝነት ጋር ምን መዛመድ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለው? 15 ክርስቶስስ ከቤልዖር ጋር ምን ስምምነት አለው? የሚያምንስ ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው? 16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስስ ከጣዖታት ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔር "ከእነርሱም ጋር አድራለሁ፥በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፥ እነርሱም ህዝብ ይሆኑኛል" ብሎ ስለተናገረ እኛ የህያው እግዚአብሔር መቅደሶች ነን። 17 ስለዚህም "ከመካከላቸው ውጡ፤የተለያችሁም ሁኑ" ይላል ጌታ፥ "እርኩሱን አትንኩ፥እኔም እቀበላችኋለሁ። 18 አባት እሆናችኋለሁ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ።" ብሏል ሁሉን የሚችል ጌታ።