26

1 በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ረሀብ ሌላ ዳግመኛ ረሀብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማዋን ንጉሥ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤ 2 በዚህም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፣ "ወደ ግብፅ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበትም በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤ 3 እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ይህም ምድር ለአንተና ለዝርይዎችህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈፅማለሁ፤ 4 ዘርህን አንደ ሰማይ ክዋክብት አበዛዋልለሁ፤ ይህንንም ሁሉ ምድር አወርሳቸዋለሁ፤ ይህንንም ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ። 5 አንተን የምባርክበትንም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁት ሕግና ሥርዓት ሁሉ ስለ ጠበወ ነው። 6 ስለዚህ ይስሐቅ መኖሪያውን በገራር አደረገ፤ 7 በዚያ አገር ስሰዎችም ስለ ርብቃ "ምንህናት" ብለው በጠየቁት ጊዜ "እኅቴ ናት" አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቆንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው። 8 ይስሐቅ እዚያ አገር ብዙ ጊዜ ከቆያ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት ይስሐቅና ርብቃ እንደባልና ሚስት በመዳራት ሲጫወቱ አየ። 9 ስለዚህ አቢሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ "ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ "እኅቴ ናት' ያልከው ለምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው። እርሱም "ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኝል ብዬ አስፈራሁ ነው" ብሎ መለሰ። 10 አቢሜሌክ "ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ሰዎች አንዱ በቀላሉ ሚስትህን ለመድፈር በቻለ ነበር፤" 11 ቀጥሎም አቢሜሌክ "ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የሚነካ ሰው በሞቱ ይቀጣል"የሚል ማስጠንቀቂያ ለሕዝቡ ሰጠ። 12 ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ እግዚአብሔር ስለባረከውም በዚያኑ ዓመት መቶ እጥፍ አመረተ፤ 13 ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው። 14 ብዙ የበግና የከብት መንጋ፤ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት። 15 ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእሱን አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን ውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው። 16 በዚያን ጊዜ አቢሜሌክ ይስሐቅን "ኅይልህ ከእኛ ይልቅ እየበረታ ስለሄደ፤ አገራችንን ለቀህ ውጣ" አለው። 17 በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ያንን ቦታ ለቆ በገራር ሸለቆ ውስጥ ሰፈረ፤ እዚያም ተቀመጠ። 18 አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቆፍሮአቸው የነበሩትን አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጉድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቆፍሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸ ስሞችም ጠራቸው። 19 የይስሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሩና ጥሩ የምንጭ ውሃ አገኙ፤ 20 የገራር እረኞች ግን "ይህ ውሃ የእኛ ነው" በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ።በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጉድጓዱን "ዔሤቅ" ብሎ ሰየመው። 21 የይስሐቅ አገልጋዮች ሌላ የውሃ ጉድጓድ ቁፈሩ፤ በዚህኛውም ጉድጓድ ምክንያት ሌላ ጠብ ተነሣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ ይህን ጉድጓድ "ስጥና" ብሎ ሰየመው። 22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተናሳ "እነሆ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል ያንን ቦታ 'ረሖቦት" ብሎ ሰየመው። 23 ከዚያ በኋላ ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ፤ 24 በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና "እኔ የአባትህ አምላክ ነኝ፤እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ! ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ" አለው። 25 ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጉድጓድ ቆፈሩ። 26 አቢሜሌክ ከአማካሪው ከአሑዘትና ከሠራዊቱ ኣዥ ኮፊኮል ጋር ይስሐቅን ለመጎብኘት ከገራር ወት፤ 27 ስለዚህ ይስሐቅ "ከዚህ በፊት ጠልታችሁን አገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጎበኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?" አላቸው። 28 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፣ "እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈፀም አስበናል፤ በዚህም መጀረት ቃል ኮዳን እንድትገባልን የሚንፈለገው፣ 29 በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ምክንያቱም እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ አልሠራንም፤ ዘውትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።" 30 ከዚህ በኋላ፣ ይስሐቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡ። 31 በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ። 32 ከዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቁፈሩት ጉድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ "ውሃ አገኘን" ብለውም አበሠሩት። 33 እርሱም የውሃን ጉድጓድ "ሳቤህ"ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ "ቤርሳቤህ" እየተባለ ይጠራል። 34 ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆንው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ። 35 ይህም ጋብቻ ይስሐቅንና ርብቃን ሲያዝናቸው ይኖር ነበር።