23

1 ሣራ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ኖረች። እነዚህን ዓመታት ነበር ሳራ የኖረችው። 2 በከነዓን ምድር ባለችው ቂርያት አርባ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ ሃዘነ አለቀሰም። 3 ከዚያም አብርሃም ከተቀመጠበት ከሚስቱ ሬሳ አጠገብ ተነሳ፣ ኬጢያውያንን እንዲህ አላቸው፤ 4 «እኔ በመካከላችሁ በእንግድነት የምኖር ነኝ። እባካችሁ የመቃብር ቦታ ስጡኝ፤ የሚስቴንም ሬሳ ልቅበርበት።» 5 የኬጢ ልጆችም ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ 6 «ጌታ ሆይ ስማን፣ አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ። ከመቃብር ቦታችን በመረጥከው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፣ ማናችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የምቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።» 7 አብርሃም ተነሣ በኬጢያውያን ልጆች ፊት እጅ ነስቶ እንዲህ አለ። 8 የሚስቴን አስከሬን እዚህ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ የጾሐር ልጅ ዔፍሮምን ስለ እኔ ሆናችሁ ልምኑልኝ፤ 9 በእርሻው ዳር ያለችውን መክፈል የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፣ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንት ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።» 10 ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ የኬጢም ሰው ኤፍሮንም የኪጥ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሲስሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 11 «አይደለም ጌታዬ፣ ስማኝ። እርሻውን፣ በርሱም ዳር ያለውን ዋሻ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼአለሁ። ሬሳህን ቅበር።» 12 አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ። 13 የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፤ «እባክህ ፈቃደኛ ብትሆን አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ። አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ 14 ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 15 «ጌታዬ ሆይ እኔን ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋ እራት መቶ ሰቅል ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይሄ በእኔና በአንተ መካከል ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር» 16 አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬት ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው፤ ብሩንም በወቅቱ የንግድ መለኪያ መሰረት መዘነለት። 17 በዚህም ሁኔታ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለውን የኤፍሮንን እርሻ ቦታ ከነዋሻው በከልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤ 18 እርሻው በእርሱ ያለውን ዋሻው በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ። 19 ከዚያም በኋላ ኬብሮን በምትባል በምምሬ ፊት በከነአን ፊት ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍሌ በሆነው ዋሻ ውስጥ ሚስቱን ሳራን ቀበረ። 20 እርሻውና በርሱ ያለው ዋሻው በኪጥ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።