20

1 አብርሃም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ አካብቢ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም መኖር ጀመረ። ለጥቂት ጊዜ በጌራራ ተቀመጠ። 2 አብርሃም ሚስቱ ሥራራን፣ "እኅቴ ናት" ይል ነበር፤ ስለዚህ ይጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ሰዎች ልኮ ሣራን ወሰዳት። 3 እግዚአብሔር ግን በሕልም ወደ እቢሜሌክ መጥቶ፣ "እነሆ በወሰድካት ሴት ምክንያት አንተ ምውት ነህ፤ ምክንያቱም እርሷ ባለ ባል ናት" አለው። 4 አቢሜሌክ ገና አልሰረሰባትም ነበርና እንዲህ አለ፤ "ጌታ ሆይ፣ በደል ያልተገኘበትን ሕዝብ ልታጠፋ ነውን? 5 'እኅቴ ናት' ያለኝ እርሱ ራሱ አይደለምን? እርሷም ብትሆን 'ወንድሜ ነው' ብላኛለች። እኔ እንዲህ ያደረግሁት በቅን ልቦናና በንጹሕ እጅ ነው።" 6 በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም እንዲህ አለው፤ "አዎን፣ ይህን ያደረግኸው በልብ ቅንነት እንደ ነበር እኔም አውቃለሁ፤ እኔ ላይ ኀጢአት እንዳትፈጽም የጠበቅሁህና እንዳትነካትም ያደረግሁት በዚህ ምክንያት ነው፤ 7 ስለዚህ የሰውየውን ሚስት መልስለት፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ ይጸልይልሃል አንትም ትድናለህ። እርሷን ካልመለስህ፣ እንተና የአንተ የሆነው ሁሉ በእርግጥ እንደምትጠፉ ዐውቃለሁ።" 8 አቤሜሊክ ጧት በማለዳ ተነሥቶ ሹማምንቶቹን ሁሉ ጠራ። የሆነውን ሁሉ ሲነግራቸው በጣም ፈሩ። 9 ከዚያም አቤሜሌ አብርሃምን አስጠርቶ፣ "ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህብን ነው? በእኔና በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ትልቅ መዘዝ ያመጣህብኝ ምን ብበድልህ ነው? መደረግ ያልነበረትን አድርገህብኛል" አለው። 10 በመቀጠልም፣ አብርሃምን፣ "እንዲህ እንድታደርግ ያነሣሣህ ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው። 11 አብርሃምም፣ "በዚህ ቦታ እግዚአብሔርን መፍራት የለም፤ ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል በማለት ስላሰብሁ ነው። 12 በዚህ ላይ ደግሞ ከእናቴ ባትወለድም የአባቴ ልጅ እኅቴ ናት፤ በኋላም ሚስቴ ሆነች። 13 የአባቴን ቤት ትቼ በየአገሩ እንድዞር እግዚአብሔር ሲያዝዘኝ፣ "ለእኔ ለባልሽ ያለሽን ታማኝነት በዚህ አሳዪኝ፤ በምንሄድበት ቦታ ሁሉ 'ወንድሜ ነው' በዪ አልኳት።" 14 ከዚያ አቤሜሊክ በጎችና በሬዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ለአብርሃም ሰጠው። ሚስቱ ሣራንም ለአብርሃም መለሰለት። 15 አቤሜሌክ እንዲህ አለ፤ "አገሬ አገርህ ነው፤ ደስ በሚያሰኝህ ቦታ ተቀመጥ።" 16 ሣራንም፣ "ለወንድምሽ አንድ ሺህ ጥሬ ብር እሰጠዋለሁ። ይህም፣ በአንቺ ላይ ለተፈጸመው በደል ካሣ እንዲሆንና አብረውሽ ያሉ ሁሉ አንቺ ንጹሕ ሴት መሆንሽን እንዲያውቁ ነው።" 17 ከዚያም አብርሃም ለአቤሜሌክ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ ልጅ ለመውለድም በቁ። 18 ከአብርሃም ሚስት ከሣራ የተነሣ በአቢሜሌክ ቤት የሚገኙ ሴቶችን ሁሉ ያህዌ ማኅፀናቸውን ዘግቶ ነበር።