19

1 ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ወደ ሰዶም መጡ፤ በሰዶም ከተማ መግቢያበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ሎጥ ሲያያቸው ሊቀበላቸው ተነሣ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ። 2 እርሱም፣ "እባካችሁ ጌቶቼ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ሌሊቱንም ከእኛ ጋር አሳልፉ፤ ከዚያ ጧት በማለዳ ተነሥታችሁ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም፣ "የለም፤ እዚሁ አደባባዩ ላይ እናድራለን" አሉት። 3 ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው እርሱ ቤት ለማደር አብረውት ገቡ። ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ። 4 ሆኖም፣ ገና ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት። 5 ሎጥን በመጣራት፣ "በዚህ ምሽት ወደ ቤትህ የመጡ ሰዎች የታሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን" አሉት። 6 ሎጥ ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ መዝጊያውን ከበስተ ኋላው ዘጋ። 7 እንዲህም አለ፤ "ወንድሞቼ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ እለምናችሏለሁ። 8 ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁና የወደዳችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን ምንም ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ተብተዋልና።" 9 እነርሱ ግን፣ "ዞር በል!" ይኸ ሰውዬ ስደተኛ ሆኖ እዚህ ለመኖር መጣ፤ ደግሞ ዳኛ ሆነብን! ይልቁ በእነርሱ ላይ ካሰብነው የከፋ እንዳይደርስብህ ዘወር በልልን" አሉት ሎጥንም እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተቃርበው ነበር። 10 ሰዎቹ እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ ቤት አስገቡትና በሩን ዘጉ። 11 ከቤቱ ውጪ የነበሩትን ውጣቶችንም ሆን ሽማግሌዎችን ግን የሎጥ እንግዶች ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ እነርሱም በሩን ለማግኘት ይደነባበሩ ጀመር። 12 ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፤ "በከተማዋ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን፣ የወንዶች ልጆችህን ሚስቶች፣ የሴቶች ልጆችህን ባሎችና ሌሎች ዘመዶችህን ሁሉ ከዚህ አውጣ። 13 ምክንያቱም ይህን ቦታ ልናጠፋ ነው፤ በያህዌ ፊት ከተማዋ ላይ የሚቀርቡ ክሶች በጣም እየጮኹ በመሆናቸው እንድናጠፋት እርሱ ልኮናል።" 14 ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹን ባሎች፣ የሴት ልጆቹን እጮኞች፣ "ቶሎ ከዚህ ቦታ ውጡ፤ ያህዌ ከተማዋን ሊያጠፋ ነው" አላቸው። የሴት ልጆቹ ባሎች ግን የሚቀልድ መሰላቸው። 15 ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥኝ፣ "ከተተማዋ ላይ በሚመጣው ቅጣት አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱ ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ" እያሉ አቻኮሉት። 16 ሎጥ አመነታ፤ ያህዌ ምሕረት ስላደረገላቸው ሰዎቹ የእርሱ፣ የሚስቱንና የሁለት ሴት ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አወጣቸው። 17 ከከተማው ካወጧቸው በኋላ ከሰዎቹ አንዱ፣ "ሕይወታችሁን ለማዳን ሩጡ! ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ወይም ረባዳው ስፍራ ላይ አትቆዩ። ወደ ተራሮች ሽሹ፤ አለበለዚያ ትጠፋላችሁ።" 18 ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ "ጌቶቼ ሆይ፣ 19 እኔ ባሪያችሁ በፊታችሁ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርጋችሁልኛል፤ እኔ እንደ ሆንኩ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል። 20 ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ቦታ ያለች ትንሽ ከተማ አለች ሸሽቼ ወደዚያ ብሄድ ሕይወቴን ማዳን እችላለሁ።" 21 እርሱም፣ "ይሁን እሺ፤ ልመናህን ተቀብብያለሁ፤ ያክካትንም ከተማ አላጠፋትም። 22 አንተ እዚያ እስክትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል በል ቶሎ ፍጠንና ወደዚያ ሽሽ" አለው። ስለዚህ ያቺ ከተማ ዞዓር ተባለች። 23 ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ወጥታ ነበር። 24 ከዚያ ያህዌ ሰዶምና ጎሞራ ላይ ድኝና እሳት አዘነበ። 25 እነዚያን ከተሞችና ረባዳ ቦታዎቹን፣ የከተሞቹ ነዋሪዎችንና እዚይ ኣያሉ ለምለም ነገሮችን ሁሉ አጠፋ። 26 ከኋላው የነበረችው የሎጥሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች። 27 አብርሃም ጠዋት ማለዳ ተነሥቶ ያህዌ ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። 28 ቁልቁል ሰዶምና ጎሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የነበረውን ምድር ተመለከተ። ከምድጃ የሚወጣ የመሰለ ጢስ ከምድሩ እየወጣ ነበር። 29 እግዚአብሔር በረባዳው ቦታ የነበሩ ከተሞችን ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው። ሎጥ የነበረበትን ከተሞች ቢያጠፋም፣ እርሱ ግን ከጥፋት መሐል አወጣው። 30 ሎጥ ግን በዞዓር መኖር ስለ ፈራ ከሁለት ሴቶች ልጆቹ ጋር ተራሮቹ ላይ ለመኖር ከዞዓር ወደ ላይ ወጣ። ስለዚህ እርሱና ሁለት ሴቶች ልጆቹ ዋሻ ውስጥኖሩ። 31 ታላቋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፣ "አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ከእኛ ጋር የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም። 32 ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር እናትርፍ።" 33 ስለዚህ በዚያ ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት። ታላቂቱ ልጅ ሄዳ ክአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቅም። 34 በሚቀጥለው ቀን ታላቂቱ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ "ትናንት ሌሊት እኔ ከእባቴ ጋር ተኛሁ። ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፣ ከዚያ አንቺ ሄደሽ ከእርሱ ጋር ትተኛለሽ፣ የአባታችንንም ዘር እናተርፋለን።" 35 ስለዚህ በዚያም ምሽት አባታቸውን ወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱ ልጅ ሄዳ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም። 36 ሁለቱ የሎጥ ልጆች ክአባታቸው አረገዙ። 37 ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ሆነ። 38 ታናሺቱም እንዲሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ሆነ።