Genesis 40

Genesis 40:1

የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊውንና እንጀራ ጋጋሪውን በወህኒ ያኖራቸው ለምን ነበር?

በድለውት ስለ ነበረ በወህኒ አኖራቸው

Genesis 40:4

ጠጅ አሳላፊውና እንጀራ ጋጋሪው በተመሳሳይ ምሽት ምን ሆኑ?

ጠጅ አሳላፊውና እንጀራ ጋጋሪው ሁለቱም በአንድ ምሽት ሕልም አለሙ

Genesis 40:6

ጠጅ አሳላፊውና እንጀራ ጋጋሪው በማግስቱ ያዘኑት ለምን ነበር?

ሕልማቸውን ሊተረጉምላቸው የሚችል ባለማግኘታቸው ሁለቱም አዝነው ነበር

ጠጅ አሳላፊውና እንጀራ ጋጋሪው በማግስቱ ያዘኑት ለምን ነበር?

ሕልማቸውን ሊተረጉምላቸው የሚችል ባለማግኘታቸው ሁለቱም አዝነው ነበር

ዮሴፍ፣ ሕልም መተርጎምን የሚሰጥ ማነው አለ?

ዮሴፍ፣ ሕልም መተርጎምን እግዚአብሔር ሊሰጥ ይችላል አለ

Genesis 40:12

ዮሴፍ፣ የጠጅ አሳላፊው ሕልም ትርጉሙ ምንድነው አለ?

ዮሴፍ፥ የሕልሙ ትርጉም ፈርዖን በሦስት ቀናት ውስጥ የጠጅ አሳላፊውን ወደ ቀድሞው ሹመቱ ይመልሰዋል ማለት ነው አለ

ዮሴፍ፣ የጠጅ አሳላፊው ሕልም ትርጉሙ ምንድነው አለ?

ዮሴፍ፣ የሕልሙ ትርጉም ፈርዖን በሦስት ቀናት ውስጥ የጠጅ አሳላፊውን ወደ ቀድሞው ሹመቱ ይመልሰዋል ማለት ነው አለ

Genesis 40:14

ዮሴፍ የሕልሙን ፍቺ ከነገረው በኋላ ለጠጅ አሳላፊው ያቀረበው ጥያቄ ምን ነበር?

የጠጅ አሳላፊው እንዲያስበው፣ ስለ እርሱ ለፈርዖን እንዲነግርለትና ከወህኒም እንዲያወጣው ዮሴፍ ለመነው

Genesis 40:18

ዮሴፍ፣ የእንጀራ ጋጋሪው ሕልም ምንድነው አለ?

ዮሴፍ፣ የሕልሙ ትርጉም ፈርዖን በሦስት ቀናት ውስጥ እንጀራ ጋጋሪውን በእንጨት ላይ ይሰቅለዋል ማለት ነው አለ

ዮሴፍ፣ የእንጀራ ጋጋሪው ሕልም ምንድነው አለ?

ዮሴፍ፣ የሕልሙ ትርጉም ፈርዖን በሦስት ቀናት ውስጥ እንጀራ ጋጋሪውን በእንጨት ላይ ይሰቅለዋል ማለት ነው አለ

Genesis 40:20

ከሦስት ቀን በኋላ ምን ልዩ ሁነት ተከናወነ?

ከሦስት ቀን በኋላ የፈርዖን የልደት በዓል ነበረ

በዚያ ቀን፣ ፈርዖን በጠጅ አሳላፊውና በእንጀራ ጋጋሪው ላይ ምን አደረገ?

ዮሴፍ እንደ ተረጎመላቸው፣ ፈርዖን የጠጅ አሳላፊውን ወደ ሹመቱ መለሰው፣ እንጀራ ጋጋሪውን ግን ሰቀለው

በዚያ ቀን፣ ፈርዖን በጠጅ አሳላፊውና በእንጀራ ጋጋሪው ላይ ምን አደረገ?

ዮሴፍ እንደ ተረጎመላቸው፣ ፈርዖን የጠጅ አሳላፊውን ወደ ሹመቱ መለሰው፣ እንጀራ ጋጋሪውን ግን ሰቀለው

ዮሴፍ ባቀረበለት ጥያቄ መሠረት ጠጅ አሳላፊው አሰበው?

አይደለም፣ ጠጅ አሳላፊው ዮሴፍን ለመርዳት አላሰበውም፣ ይልቁንም ረሳው እንጂ