Genesis 38

Genesis 38:1

ይሁዳ ሚስት አድርጎ ያገባው የማንን ልጅ ነበር?

ይሁዳ ከከነዓናዊ የተወለደች ሴት ሚስት አድርጎ አገባ

Genesis 38:6

እግዚአብሔር አምላክ በይሁዳ የበኩር ልጅ በዔር ላይ ምን አደረገ? ለምን?

ክፉ ስለ ነበረ እግዚአብሔር አምላክ ዔርን ገደለው

Genesis 38:8

የይሁዳ ሁለተኛ ልጁ አውናን በዔር ስም የሚጠራ ልጅ ሳይተካለት የቀረው እንዴት ነበር?

አውናን ከትዕማር ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚያደርግበት ጊዜ የወንዴ ዘሩን በምድር ላይ ያፈሰው ነበር

እግዚአብሔር አምላክ በይሁዳ ሁለተኛ ልጅ በአውናን ላይ ምን አደረገ? ለምን?

ያደረገው ነገር ክፉ ስለ ነበረ እግዚአብሔር አምላክ አውናንን ገደለው

Genesis 38:11

ከዚያ በኋላ ይሁዳ ለትዕማር ምን ቃል ገባላት?

ሦስተኛው ልጁ ሴሎም በሚያድግበት ጊዜ ባል እንደሚሆናት ይሁዳ ለትዕማር ቃል ገባላት

Genesis 38:12

ከብዙ ጊዜ በኋላ ይሁዳ ሊጽናና ያስፈለገው ለምን ነበር?

ይሁዳ ሚስቱ ሞታ ነበርና ተጽናና

ይሁዳ ወደ ተምና እንደሚሄድ በሰማች ጊዜ ትዕማር ምን አደረገች?

ትዕማር የመበለትነትዋን ልብስ አወለቀች፣ መጎናጸፊያ ወስዳ ተሸፋፈነችና ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ተቀመጠች

ትዕማር ይህንን ያደረገችው ለምን ነበር?

ትዕማር ይህንን ያደረገችው የይሁዳ ሦስተኛው ልጅ ሴሎም ቢያድግም ሚስት ትሆነው ዘንድ ስላልተሰጠችው ነበር

Genesis 38:17

ይሁዳ ከእርሷ ጋር ከመተኛቱ በፊት ለክፍያው መያዣ የሚሆን ምን ተቀበለች?

ይሁዳ ቀለበቱን፣ አምባሩንና በትሩን ለክፍያው መያዣ እንዲሆናት ለትዕማር ሰጣት

Genesis 38:21

ይሁዳ ለሴተኛ አዳሪዋ ክፍያ የፍየል ጠቦት በመላክ መያዣውን ለማስመለስ በሞከረ ጊዜ ምን ተረዳ?

በዚያ አካባቢ የመቅደስ ሴተኛ አዳሪ እንደሌለች ይሁዳ ተረዳ

Genesis 38:24

ትዕማር እንደ ፀነሰች በሰማ ጊዜ ይሁዳ ምን ለማድረግ ፈለገ?

ትዕማር በሴሰኝነት ፀንሳለችና ይሁዳ በማቃጠል ሊገድላት ፈለገች

ትዕማር እንደ ፀነሰች በሰማ ጊዜ ይሁዳ ምን ለማድረግ ፈለገ?

ትዕማር በሴሰኝነት ፀንሳለችና ይሁዳ በማቃጠል ሊገድላት ፈለገች

ይሁዳ የራሱን ቀለበት፣ አምባርና በትር ባየ ጊዜ ምን አለ?

ትዕማርን ሚስት እንድትሆነው ለሴሎም አልሰጣትምና ከእርሱ ይልቅ ትዕማር ጻድቅ መሆኗን ይሁዳ ተናገረ

Genesis 38:27

ትዕማር ስንት ልጆች ወለደች?

ትዕማር መንትያ ወንዶች ልጆች ነበሯት

ከትዕማር መንትያ ልጆች አንዱ ከማህፀኗ እጁን ወደ ውጭ ባወጣ ጊዜ አዋላጂቱ ምን አደረገች?

ከትዕማር መንትያ ልጆች አንዱ ከማህፀኗ እጁን ወደ ውጭ ባወጣ ጊዜ አዋላጂቱ የፈትል ክር ወስዳ እጁ ላይ አሰረችና "ይህ በመጀመሪያ ወጥቷል" አለች

Genesis 38:29

ትዕማር የወለደቻቸው የሁለቱ ወንድማማቾች ስም ማን ነበር?

ትዕማር የወለደቻቸው የሁለቱ ወንድማማቾች ስም ፋሬስና ዛራ ነበር

ትዕማር የወለደቻቸው የሁለቱ ወንድማማቾች ስም ማን ነበር?

ትዕማር የወለደቻቸው የሁለቱ ወንድማማቾች ስም ፋሬስና ዛራ ነበር