Genesis 25

Genesis 25:1

አብርሃም ሚስቱ ሣራ ከሞተች በኋላ ምን አደረገ?

አብርሃም ኬጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ

Genesis 25:5

አብርሃም ሃብቱን ያከፋፈለው እንዴት ነበር?

አብርሃም ለቁባቶቹ ልጆች ስጦታ ሰጣቸው፣ የነበረውን ሁሉ ደግሞ ለይስሐቅ ሰጠው

አብርሃም ሃብቱን ያከፋፈለው እንዴት ነበር?

አብርሃም ለቁባቶቹ ልጆች ስጦታ ሰጣቸው፣ የነበረውን ሁሉ ደግሞ ለይስሐቅ ሰጠው

Genesis 25:7

አብርሃም ስንት ዓመት ኖረ?

አብርሃም አንድ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ

Genesis 25:9

አብርሃምን ማን ቀበረው?

ይስሐቅና እስማኤል ሁለቱም አብርሃምን ቀበሩት

Genesis 25:17

አሥራ ሁለቱ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ከእርስ በእርሳቸው ጋር የኖሩት እንዴት ነበር?

አሥራ ሁለቱ የእስማኤል ልጆች እርስ በእርሳቸው በጠላትነት ኖሩ

Genesis 25:21

ርብቃ ልጅ ስላልነበራት ይስሐቅ ምን አደረገ?

ይስሐቅ ስለ ሚስቱ ወደ እግዚአብሔር አምላክ ጸለየ፣ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰማው፣ ርብቃም ፀነሰች

Genesis 25:23

በርብቃ ማኅፀን ውስጥ ስለሚጣሉት ሁለት ልጆች እግዚአብሔር አምላክ ምን ብሎ ነበር?

ሁለት ሕዝቦች በማኅፀኗ ውስጥ እንዳሉ፣ አንደኛው ሕዝብ ከሁለተኛው እንደሚበረታና ታላቁ ታናሹን እንደሚያገለግል እግዚአብሔር አምላክ ተናገረ

Genesis 25:24

በመጀመሪያ የተወለደው ማን ነበር? እርሱ ምን ይመስል ነበር?

በመጀመሪያ ኤሳው ተወለደ፣ እርሱ እንደ ፀጉራም ልብስ ሁለመናው ቀይ ነበር

ቀጥሎ የተወለደው ማን ነበር? በሚወለድበት ጊዜስ ምን ሲያደርግ ነበር?

ቀጥሎ የተወለደው ያዕቆብ ነበር፣ በሚወለድበት ጊዜ የኤሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር

Genesis 25:27

ኤሳው ምን ዓይነት ሰው ነበር?

ኤሳው አደን የሚያውቅ የበረሃ ሰው ሆነ

ያዕቆብ ምን ዓይነት ሰው ነበር?

ያዕቆብ ጊዜውን በድንኳን ውስጥ የሚያሳልፍ ጭምት ሰው ነበር

Genesis 25:29

ይስሐቅ ማንን ይወድ ነበር? ርብቃስ?

ይስሐቅ ኤሳውን ወደደው፣ ርብቃ ደግሞ ያዕቆብን

የኤሳው ሌላው ስሙ ማን ነበር?

ኤዶም የኤሳው ሌላ ስሙ ነበር

Genesis 25:31

ኤሳው ርቦት ስለ ነበረ ለመብላት ለፈለገው ቀይ ወጥ ያዕቆብ በምላሹ ምን ጠየቀ?

ያዕቆብ፣ በቀይ ወጡ ምትክ ኤሳው ብኩርናውን እንዲሰጠው ጠየቀ

ለያዕቆብ ጥያቄ የኤሳው ምላሽ ምን ነበር?

ኤሳው ማለለትና ብኩርናውን ለያዕቆብ ሸጠ

ለያዕቆብ ጥያቄ እንዲህ ያለ ምላሽ በሰጠ ጊዜ ኤሳው ብኩርናውን አንዴት አየው?

ለያዕቆብ ጥያቄ እንዲህ ያለ ምላሽ በሰጠ ጊዜ ኤሳው ብኩርናውን አቃለለ