Genesis 18

Genesis 18:1

አብርሃም በድንኳኑ በራፍ ተቀምጦ እያለ አሻግሮ ሲመለከት ምን አየ?

አብርሃም ሦስት ሰዎችን በእርሱ አቅጣጫ ቆመው አየ

Genesis 18:3

አብርሃም ለሰዎቹ ምን አቀረበላቸው?

አብርሃም ለሰዎቹ እንዲታጠቡበት ጥቂት ውሃና ጥቂት ምግብ አቀረበላቸው

Genesis 18:6

አብርሃም ለሰዎቹ ምን አቀረበላቸው?

አብርሃም ለሰዎቹ እንዲታጠቡበት ጥቂት ውሃና ጥቂት ምግብ አቀረበላቸው

Genesis 18:9

ጎብኚው ትንቢታዊ ቃሉን በሚሰጥበት ጊዜ ሣራ የት ነበረች?

ሣራ በድንኳኑ ውስጥ ነበረች

Genesis 18:11

አንደኛው ጎብኚ ሣራን በሚመለከት የሰጠው ትንቢታዊ ቃል ምን የሚል ነበር?

አንደኛው ጎብኚ፣ እርሱ በሚመለስበት ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ እንደሚኖራት ተናገረ

Genesis 18:13

ለጎብኚው ትንቢታዊ ቃል የሣራ ምላሽ ምን ነበር?

ሣራ ትንቢታዊውን ቃል በሰማች ጊዜ በልቧ ሳቀች

ጎብኚው እግዚአብሔር አምላክ፣ ስለ ሣራ ምላሽ ምን አለ?

እግዚአብሔር አምላክ ሣራ ለምን እንደ ሣቀች ጠየቀ፣ እንዲሁም፣ "ለእግዚአብሔር አምላክ የሚሳነው ነገር አለን"? አለ

Genesis 18:16

ሰዎቹ ከአብርሃም ቤት ከወጡ በኋላ በየት አቅጣጫ ሄዱ?

ሰዎቹ ከአብርሃም ቤት ወጥተው ወደ ሰዶም ሄዱ

እየተራመዱ እያሉ እግዚአብሔር አምላክ የጠየቀው ምን ዓይነት ጥያቄ ነበር?

እግዚአብሔር አምላክ፣ "እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን?" አለ

እግዚአብሔር አምላክ ለአብርሃም የሰጠውን ተስፋ እንዲፈጽም አብርሃም ምን ማድረግ አለበት አለ?

እግዚአብሔር አምላክ፣ አብርሃም ጽድቅንና ፍርድን እንዲያደርጉ ልጆቹንና ቤተሰቦቹን ማስተማር አለበት አለ

Genesis 18:20

ሰዎቹ ወደ ሰዶም የሄዱት ለምን ነበር?

ሰዎቹ ወደ ሰዶም የሄዱት የሰዶምና የጎሞራ ጩኸት ታላቅ ስለነበረና የከተሞቹ ክፋት ጩኸታቸው የሚያመለክተውን ያህል መሆኑን ለማየት ነበር

Genesis 18:22

ሰዎቹ ወደ ሰዶም የሄዱት ለምን ነበር??

ሰዎቹ ወደ ሰዶም የሄዱት የሰዶምና የጎሞራ ጩኸት ታላቅ ስለነበረና የከተሞቹ ክፋት ጩኸታቸው የሚያመለክተውን ያህል መሆኑን ለማየት ነበር

Genesis 18:24

አብርሃም ከእግዚአብሔር አምላክ ጋር ቆሞ ሳለ እግዚአብሔርን የጠየቀው ምን ነበር?

አብርሃም የጠየቀው፣ "ጻድቁን ከኃጢአተኛው ጋር ታጠፋለህን?" በማለት ነበር

Genesis 18:27

በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ቢኖሩ እግዚአብሔር አምላክ ምን እንደሚያደርግ ተናገረ?

እግዚአብሔር አምላክ በእነርሱ ምክንያት ስፍራውን ሁሉ እንደማያጠፋ ተናገረ

በከተማይቱ ውስጥ አርባ አምስት ጻድቃን ቢኖሩ እግዚአብሔር አምላክ ምን እንደሚያደርግ ተናገረ?

እግዚአብሔር አምላክ በእነርሱ ምክንያት ስፍራውን ሁሉ እንደማያጠፋ ተናገረ

Genesis 18:29

በከተማይቱ ውስጥ አርባ ጻድቃን ቢኖሩ እግዚአብሔር አምላክ ምን እንደሚያደርግ ተናገረ?

እግዚአብሔር አምላክ በእነርሱ ምክንያት ስፍራውን ሁሉ እንደማያጠፋ ተናገረ

በከተማይቱ ውስጥ ሠላሳ ጻድቃን ቢኖሩ እግዚአብሔር አምላክ ምን እንደሚያደርግ ተናገረ?

እግዚአብሔር አምላክ በእነርሱ ምክንያት ስፍራውን ሁሉ እንደማያጠፋ ተናገረ

በከተማይቱ ውስጥ ሃያ ጻድቃን ቢኖሩ እግዚአብሔር አምላክ ምን እንደሚያደርግ ተናገረ?

እግዚአብሔር አምላክ በእነርሱ ምክንያት ስፍራውን ሁሉ እንደማያጠፋ ተናገረ

Genesis 18:32

በከተማይቱ ውስጥ አሥር ጻድቃን ቢኖሩ እግዚአብሔር አምላክ ምን እንደሚያደርግ ተናገረ?

እግዚአብሔር አምላክ በእነርሱ ምክንያት ስፍራውን ሁሉ እንደማያጠፋ ተናገረ