Genesis 17

Genesis 17:3

እግዚአብሔር አምላክ ከአብራም ጋር የገባው ቃል ኪዳን ለማጽናት እንደገና በተገለጠለት ጊዜ የአብራም ዕድሜ ስንት ነበር‌?

እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም እንደገና በተገለጠለት ጊዜ አብራም ዘጠና ዘጠኝ ዓመቱ ነበር

የሕይወት አካሄዱን በሚመለከት እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም የሰጠው ትዕዛዝ ምንድነው?

እግዚአብሔር አምላክ፣ አብራም በእርሱ ፊት ያለ ነቀፋ እንዲመላለስ አዘዘው

Genesis 17:7

እግዚአብሔር አምላክ የአብራምን ስም ወደ ምን ለወጠው? ትርጉሙስ ምንድነው?

እግዚአብሔር አምላክ የአብራምን ስም ወደ አብርሃም ለወጠው፣ ይኸውም፣ "የብዙ ሕዝብ አባት" ማለት ነው

Genesis 17:9

እግዚአብሔር አምላክ የቃል ኪዳኑ አካል አድርጎ ለአብርሃም ዘሮች የሚሰጣቸው ምንድነው?

እግዚአብሔር አምላክ የቃል ኪዳኑ አካል አድርጎ ለአብርሃም ዘሮች የከነዓንን ምድር ሁሉ ሰጣቸው

እግዚአብሔር አምላክ በእርሱና በአብርሃም ዘሮች መካከል ምን ዓይነት ግንኙነት ይሆናል አለ?

እግዚአብሔር አምላክ ለአብርሃም ዘሮች አምላካቸው እንደሚሆን ተናገረ

እግዚአብሔር አምላክ በእርሱና በአብርሃም መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት የሚሆን ምን እንዲደረግ አዘዘ?

እግዚአብሔር አምላክ በእርሱና በአብርሃም መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት እንዲሆን ወንድ ሁሉ እንዲገረዝ አዘዘ

እግዚአብሔር አምላክ በእርሱና በአብርሃም መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት የሚሆን ምን እንዲደረግ አዘዘ?

እግዚአብሔር አምላክ በእርሱና በአብርሃም መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት እንዲሆን ወንድ ሁሉ እንዲገረዝ አዘዘ

Genesis 17:12

አንድ ሕፃን በስንት ዓመቱ መገረዝ ነበረበት?

አንድ ሕፃን በስምንተኛው ቀን መገረዝ ነበረበት

ከእግዚአብሔር አምላክ የቃል ኪዳን ቤተሰቦች ጋር የተቀላቀሉ እንግዶች ምን ማድረግ ነበረባቸው?

ከእግዚአብሔር አምላክ የቃል ኪዳን ቤተሰቦች ጋር የተቀላቀሉ እንግዶች፣ እነርሱም ደግሞ መገረዝ ነበረባቸው

ከእግዚአብሔር አምላክ የቃል ኪዳን ቤተሰቦች ጋር የተቀላቀሉ እንግዶች ምን ማድረግ ነበረባቸው?

ከእግዚአብሔ አምላክ የቃል ኪዳን ቤተሰቦች ጋር የተቀላቀሉ እንግዶች፣ እነርሱም ደግሞ መገረዝ ነበረባቸው

ያልተገረዘ ወንድ ሁሉ ምን ሆነ?

ያልተገረዘ ወንድ ሁሉ ቃል ኪዳን አፍርሶአልና ከእግዚአብሔር ሕዝብ ተለይቶ ጠፋ

Genesis 17:15

እግዚአብሔር አምላክ የሦራን ስም ወደ ምን ለወጠው?

እግዚአብሔር አምላክ የሦራን ስም ወደ ሣራ ለወጠው

እግዚአብሔር አምላክ ተስፋ የሰጠው በሣራ በኩል ምን እንደሚመጣ ነበር?

የአብርሃም ወንድ ልጅ በሣራ በኩል እንደሚመጣ እግዚአብሔር አምላክ ተስፋ ሰጠ

Genesis 17:17

ሣራን በሚመለከት እግዚአብሔር አምላክ ለሰጠው ተስፋ የአብርሃም ምላሽ ምን ነበር?

አብርሃም ሳቀ፣ በእድሜ በጣም ያረጁ ወንድና ሴት እንዴት ልጅ ሊወልዱ ይችላሉ በማለትም ጠየቀ

Genesis 17:19

እግዚአብሔር፣ በሣራ በኩል የሚመጣውን ወንድ ልጅ አብርሃም ማን ብሎ መጥራት አለበት አለ?

እግዚአብሔር፣ አብርሃም ልጁን ይስሐቅ ብሎ መጥራት አለበት አለ

እግዚአብሔር ከይስሐቅ ጋር እመሠርታለሁ ያለው ምንድነው?

እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ከይስሐቅ ጋር እንደሚመሠርት ተናገረ

እስማኤልን በሚመለከት እግዚአብሔር ምን ተስፋ ሰጠ?

እግዚአብሔር እስማኤልን ሊባርክ፣ ሊያበዛውና ታላቅ ሕዝብ ሊያደርገው ተስፋ ሰጠ

Genesis 17:22

እግዚአብሔር ከይስሐቅ ጋር እመሠርታለሁ ያለው ምንድነው?

እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ከይስሐቅ ጋር እንደሚመሠርት ተናገረ

Genesis 17:24

እግዚአብሔር ከተለየው በኋላ አብርሃም በዚያው ቀን ምን አደረገ?

አብርሃም በዚያው ቀን በቤቱ የነበሩትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ

እግዚአብሔር ከተለየው በኋላ አብርሃም በዚያው ቀን ምን አደረገ?

አብርሃም በዚያው ቀን በቤቱ የነበሩትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ

እስማኤል በተገረዘ ጊዜ ዕድሜው ስንት ነበር?

እስማኤል በተገረዘ ጊዜ ዕድሜው አሥራ ሦስት ነበር

እግዚአብሔር ከተለየው በኋላ አብርሃም በዚያው ቀን ምን አደረገ?

አብርሃም በዚያው ቀን በቤቱ የነበሩትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ

እግዚአብሔር ከተለየው በኋላ አብርሃም በዚያው ቀን ምን አደረገ?

አብርሃም በዚያው ቀን በቤቱ የነበሩትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ