Genesis 15

Genesis 15:1

እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም በተገለጠለት ጊዜ ምን ማበረታቻ ቃል ሰጠው?

እግዚአብሔር አምላክ አብራም እንዳይፈራ፣ ለአብራም ጋሻና እጅግ ታላቅ ዋጋው እርሱ መሆኑን ነገረው

አብራም የተጨነቀው ስለ ምን ጉዳይ ነበር?

አብራም እስካሁን ልጅ ስላልነበረውና የቤቱ መጋቢ ወራሹ ስለሆነ ተጨንቆ ነበር

አብራም የተጨነቀው ስለ ምን ጉዳይ ነበር?

አብራም እስካሁን ልጅ ስላልነበረውና የቤቱ መጋቢ ወራሹ ስለሆነ ተጨንቆ ነበር

Genesis 15:4

እግዚአብሔር አምላክ የተናገረው የአብራም ወራሽ ማን እንደሚሆን ነበር?

ከራሱ ከአብራም ሥጋ የሚወለደው ወራሹ እንደሚሆን እግዚአብሔር አምላክ ተናገረ

እግዚአብሔር አምላክ የተናገረው አብራም ምን ያህል ልጆች እንደሚኖሩት ነበር?

እግዚአብሔር አምላክ አብራም እንደ ከዋክብት የበዙ ልጆች እንደሚኖሩት ተናገረ

Genesis 15:6

ለእግዚአብሔር አምላክ ተስፋ የአብራም ምላሽ ምን ነበር? ከዚያስ እግዚአብሔር አምላክ ምን አደረገ?

አብራም እግዚአብሔር አምላክን አመነ፣ እግዚአብሔር አምላክም አብራምን ጻድቅ አድርጎ ቆጠረው

Genesis 15:9

አብራም ስለ መሬት እግዚአብሔር አምላክን የጠየቀው ምን ነበር?

አብራም እግዚአብሔር አምላክን፣ "እርሱን እንደምወርስ በምን አውቃለሁ"? ብሎ ጠየቀው

Genesis 15:12

ከዚያ አብራም እንዲያቀርብ በተነገረው እንስሳት ላይ ምን አደረገ?

አብራም እንስሳቱን አርዶ ለሁለት በመክፈል አንደኛውን በሌላኛው ፊት በትይዩ አስቀመጣቸው

ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ አብራም ምን ሆነ?

ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ አብራም አንቀላፋ፣ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማም ወደቀበት

እግዚአብሔር አምላክ የተናገረው የአብራም ዘሮች ለምን ያህል ጊዜ ባሪያዎች እንደሚሆኑና እንደሚጨቆኑ ነበር?

ዘሮቹ ለአራት መቶ አመታት ባሪያዎች እንደሚሆኑና እንደሚጨቆኑ እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም ነገረው

Genesis 15:14

እግዚአብሔር አምላክ የአብራምን ዘሮች ባሪያ ያደረጉ ሕዝቦች ምን እንደሚሆንባቸው ተናገረ?

እግዚአብሔር አምላክ በዚያ ሕዝብ ላይ እንደሚፈርድ ተናገረ

እግዚአብሔር አምላክ የተናገረው የአብራም ዕድሜ በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚያልቅ ነበር?

አብራም በመልካም ሽምግልና በሰላም እንደሚሞት እግዚአብሔር አምላክ ተናገረ

የአብራም ዘሮች ተስፋ ወደ ተሰጣቸው ምድር ከመመለሳቸው በፊት መጠኑን መሙላት የነበረበት ምንድነው?

የአብራም ዘሮች ከመመለሳቸው በፊት የአሞራውያን ኃጢአት መጠኑን መሙላት ነበረበት

Genesis 15:17

በዚያ ምሽት አብራም ባዘጋጃቸው ክፋዮች መካከል ምን ሆነ?

የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ

በዚያ ቀን እግዚአብሔር አምላክ ከአብራም ጋር የገባው ቃል ኪዳን ምን ነበር?

ይህቺን ምድር እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም ዘሮች እንደሚሰጥ ለአብራም ቃል ኪዳን ገባለት

በዚያ ቀን እግዚአብሔር አምላክ ከአብራም ጋር የገባው ኪዳን ምን ነበር?