Genesis 13

Genesis 13:1

አብራም ከግብፅ ወጥቶ ወዴት ተጓዘ?

አብራም ወደ ኔጌብ ተጓዘ

Genesis 13:3

አብራም ከራሱ ጋር ምን ይዞ ወጣ?

አብራም ከራሱ ጋር ብዙ ከብት፣ ብዙ ብርና ወርቅ ይዞ ወጣ

Genesis 13:5

አብራም ከራሱ ጋር ምን ይዞ ወጣ?

አብራም ከራሱ ጋር ብዙ ከብት፣ ብዙ ብርና ወርቅ ይዞ ወጣ

Genesis 13:8

በአብራምና በሎጥ መንጋ ጠባቂዎች መካከል ጠብ የሆነው ለምንድነው?

አብራምና ሎጥ የነበራቸው እጅግ ብዙ ነበርና በአንድነት ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቸውም፣ በዚህ ምክንያት ጠብ ሆነ

አብራም ለሎጥ ምን ምርጫ አቀረበለት?

አብራም፣ ሎጥ የሚኖርበትን እንዲመርጥና እርሱም ከሎጥ ተለይቶ ወደሚኖርበት ለመሄድ ምርጫ አቀረበ

Genesis 13:10

ሎጥ ለመኖር የመረጠው የት ነበር? ለምን?

ሎጥ ወደ ምስራቅ ለመሄድና ውሃ የሞላበት ስለ ነበር በዮርዳኖስ ሸለቆ ለመኖር መረጠ

ሎጥ ለመኖር የመረጠው የት ነበር? ለምን?

ሎጥ ወደ ምስራቅ ለመሄድና ውሃ የሞላበት ስለ ነበር በዮርዳኖስ ሸለቆ ለመኖር መረጠ

Genesis 13:12

ከዚያ አብራም የት ኖረ?

አብራም በከነዓን ምድር ኖረ

በሰዶም እንዴት ያሉ ሰዎች ይኖሩ ነበር?

የሰዶም ሰዎች በእግዚአብሔር አምላክ ፊት ክፉዎችና ኃጢአተኞች ነበሩ

Genesis 13:14

በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም ምን እንደሚሰጠው ተናገረ?

አብራም ከቆመበት ስፍራ ጀምሮ የሚያየው ምድር ሁሉ እንደሚሰጠው እግዚአብሔር አምላክ ተስፋ ሰጠ

በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም ምን እንደሚሰጠው ተናገረ?

አብራም ከቆመበት ስፍራ ጀምሮ የሚያየው ምድር ሁሉ እንደሚሰጠው እግዚአብሔር አምላክ ተስፋ ሰጠ

Genesis 13:16

እግዚአብሔር አምላክ የተናገረው አብራም ምን ያህል ዘር እንደሚኖረው ነበር?

አብራም ሊቆጠር የማይችል ዘር እንደሚኖረው፣ "ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛል" በማለት እግዚአብሔር አምላክ ነገረው

ከዚያ አብራም የተጓዘው ወደ የትኛው ከተማ አቅራቢያ ነበር?

አብራም ወደ ኬብሮን ከተማ አቅራቢያ ተጓዘ