Genesis 12

Genesis 12:1

አብራም በካራን ሲኖር ሳለ እግዚአብሕሔር ምን እንዲያደርግ ነገረው?

እግዚአብሔር አምላክ አብራም የአባቱን ቤተሰብ ትቶ እርሱ ወደሚያሳየው ምድር እንዲሄድ ለአብራም ነገረው

እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም ምን ተስፋ ሰጠው?

እግዚአብሔር አምላክ አብራምን እንደሚባርከው፣ ትልቅ ሕዝብ እንደሚያደርገውና በእርሱ በኩል የምድር ቤተሰቦች በሙሉ እንደሚባረኩ ተስፋ ሰጠው

Genesis 12:4

እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም ምን ተስፋ ሰጠው?

እግዚአብሔር አምላክ አብራምነ እንደሚባርከው፣ ትልቅ ሕዝብ እንደሚያደርገውና በእርሱ በኩል የምድር ቤተሰቦች በሙሉ እንደሚባረኩ ተስፋ ሰጠው

Genesis 12:6

ከአብራም ጋር የተጓዘው ማን ነበር?

አብራም ከሚስቱ ከሦራና ከወንድሙ ልጅ ከሎጥ ጋር ተጓዘ

አብራም የተጓዘው ወደ የትኛው ምድር ነበር?

አብራም ወደ ከነዓን ምድር ተጓዘ

እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም በተገለጠ ጊዜ ለአብራም ምን ተስፋ ሰጠው?

ዘሮቹ በከነዓን ምድር እንደሚኖሩ እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም ተስፋ ሰጠው

Genesis 12:8

አብራም ለእግዚአብሔር አምላክ አምልኮን ያቀረበው እንዴት ነበር?

አብራም ለእግዚአብሔር አምላክ መሠዊያን ሠራ፣ የእግዚአብሔር አምላክንም ስም ጠራበት

Genesis 12:10

አብራም ከነዓንን ትቶ የተጓዘው ወዴት ነበር?

አብራም ከነዓንን ትቶ ወደ ግብፅ ተጓዘ

አብራም ወደ ግብፅ በመግባት ላይ እያለ ያሰጋው ጉዳይ ምን ነበር?

አብራም፣ ሚስቱ ሦራ ቆንጆ ስለ ነበረች ግብፃውያን እርሱን ገድለው እርስዋን እንደሚወስዱበት በማሰብ ሰግቶ ነበር

Genesis 12:14

አብራም ሦራን የጠየቃት ለግብፃውያኑ ስለ ራስዋ ምን እንድትነግራቸው ነበር?

የአብራም እህት መሆኗን ለግብፃውያኑ እንድትነግራቸው አብራም ሦራን ጠየቃት

ወደ ግብፅ በገቡ ጊዜ ሦራ ምን ሆነች?

ፈርዖን ሦራን ወደ ቤቱ ወሰዳት

Genesis 12:17

በዚህ ጊዜ ፈርዖን ምን ሆነ?

እግዚአብሔር አምላክ ፈርዖንና ቤተሰቡን በታላቅ መቅሰፍት መታቸው

ፈርዖን አብራምን ምን ጥያቄ ጠየቀው?

ሦራ ሚስቱ ሆና ሳለች ለምን እህቱ እንደሆነች አድርጎ እንደ ነገረው ፈርዖን አብራምን ጠየቀው

ፈርዖን አብራምን ምን ጥያቄ ጠየቀው?

ሦራ ሚስቱ ሆና ሳለች ለምን እህቱ እንደሆነች አድርጎ እንደ ነገረው ፈርዖን አብራምን ጠየቀው

ፈርዖን አብራምና ሦራን ምን አደረገ?

ፈርዖን አብራምና ሦራን ከሀገሩ አስወጣቸው