Genesis 11

Genesis 11:1

ከጥፋት ውሃ በኋላ ወዲያውኑ፣ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ስንት ቋንቋዎች ነበሩ?

ከጥፋት ውሃ በኋላ ወዲያውኑ፣ በምድሪቱ ሁሉ ላይ አንድ ቋንቋ ነበረ

Genesis 11:3

ሕዝቡ ከተማና ግንባቸውን የሠሩት የት ነበር?

ሕዝቡ ከተማና ግንባቸውን የሠሩት በሰናዖር ምድር ነበር

Genesis 11:5

ሕዝቡ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው በምድር ላይ ከመበተን ይልቅ ምን ለማድረግ ወሰኑ?

ሕዝቡ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው በምድር ላይ ከመበተን ይልቅ ከተማና ግንብ ለመሥራት ወሰኑ

ሕዝቡ ለራሳቸው ምን ለማድረግ ፈለጉ?

ሕዝቡ የራሳቸውን ስም ለማስጠራት ፈለጉ

እግዚአብሔር አምላክ ወርዶ በሕዝቡ ላይ ያደረገው ምን ነበር?

እግዚአብሔር አምላክ ወርዶ የሕዝቡን ቋንቋዎች ደበላለቀው

እግዚአብሔር ይህንን ያደረገው ለምን ነበር?

እግዚአብሔር ቋንቋዎቻቸውን ያደበላለቀው እርስ በእርሳቸው እንዳይግባቡ ነበር

Genesis 11:8

እግዚአብሔር ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ አደረጋቸው?

እግዚአብሔር አስቀድሞ እንዳዘዛቸው በምድር ፊት ሁሉ ላይ እንዲበተኑ አደረጋቸው

ሕዝቡ ለመገንባት የሞከሩት ከተማ ስም ማን ይባላል?

የከተማው ስም ባቢሎን ይባላል

Genesis 11:24

በዚህ ምዕራፍ የተጠቀሱት የኖኅ የየትኛው ልጁ ትውልዶች ናቸው?

በዚህ ምዕራፍ የተጠቀሱት የኖኅ ልጅ የሴም ትውልዶች ናቸው

የአብራም አባት ማን ነበር?

የአብራም አባት ታራ ነበር

Genesis 11:27

ታራ ይኖር የነበረው የት ነው?

ታራ ይኖር የነበረው በከለዳውያን ዑር ነው

Genesis 11:29

የአብራም ሚስት ስሟ ማን ነበር?

የአብራም ሚስት ስሟ ሦራ ነበር

የአብራም ሚስት ምን ችግር ነበረባት?

የአብራም ሚስት ሦራ መካን ነበረች፣ ልጅም አልነበራትም

Genesis 11:31

ታራ ከአብራም፣ ሦራና ሎጥ ጋር የተጓዘው ወዴት ነበር?

ታራ ከአብራም፣ ሦራና ሎጥ ጋር ወደ ከነዓን ምድር ተጓዘ