Genesis 4

Genesis 4:1

ቃየንና አቤል የሚሠሩት ምን ዓይነት ሥራ ነበር?

ቃየን ገበሬ ሲሆን አቤል በግ አርቢ ነበር

Genesis 4:3

ቃየን ለእግዚአብሔር አምላክ ያቀረበው መሥዋዕት ምን ነበር?

ቃየን ከምድር ፍሬ ጥቂቱን አቀረበ

አቤል ለእግዚአብሔር አምላክ ያቀረበው መሥዋዕት ምን ነበር?

አቤል ከበጎቹ በኩራትና ከስቡ ጥቂቱን አቀረበ

እግዚአብሔር አምላክ የቃየንን እና የአቤልን መሥዋዕት እንዴት ተመለከተው?

እግዚአብሔር አምላክ የአቤልን መሥዋዕት ተቀበለ፣ ነገር ግን የቃየንን መሥዋዕት አልተቀበለም

Genesis 4:6

እግዚአብሔር አምላክ የቃየንን እና የአቤልን መሥዋዕት እንዴት ተመለከተው?

እግዚአብሔር አምላክ የአቤልን መሥዋዕት ተቀበለ፣ ነገር ግን የቃየንን መሥዋዕት አልተቀበለም

የቃየን ምላሽ እንዴት ነበር?

ቃየን እጅግ ተናደደ፣ ፊቱም ጠቆረ

ቃየን ተቀባይነትን ያገኝ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ የነገረው ምን እንዲያደርግ ነበር?

ቃየን ተቀባይነትን እንዲያገኝ መልካም የሆነውን እንዲያደርግ እግዚአብሔር አምላክ ነገረው

ኋላ ሜዳ ላይ ቃየንና አቤል ምን ሆኑ?

ቃየን ተነሣና አቤልን ገደለው

Genesis 4:8

እግዚአብሔር አምላክ ወንደሙ ወዴት እንዳለ ቃየንን በጠየቀው ጊዜ ቃየን ምን አለ?

ቃየን፣ "አላውቅም፡፡ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?" አለ

Genesis 4:10

የእግዚአብሔር እርግማን በቃየን ላይ ምን ነበር?

የቃየን እርግማን፣ ምድር ኃይልዋን አትሰጠውም፣ ኮብላይና ተቅበዝባዥም ይሆናል

Genesis 4:13

ቃየንን ማንም እንደማይገድለው ለማረጋገጥ እግዚአብሔር አምላክ ምን አደረገ?

እግዚአብሔር አምላክ በቃየን ላይ ምልክት አደረገበት

Genesis 4:16

ቃየን ለመኖር የሄደው ወዴት ነበር?

ቃየን ከኤድን በስተምስራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ

Genesis 4:18

የቃየን ዝርያ የሆነው ላሜሕ ስንት ሚስቶች ነበሩት?

ላሜሕ ሁለት ሚስቶች ነበሩት

Genesis 4:23

ላሜሕ ስላደረገው ነገር ለሚስቶቹ የነገራቸው ምን ነበር?

ላሜሕ ለሚስቶቹ የነገራቸው ሰው መግደሉን ነበር

Genesis 4:25

ለአዳምና ለሔዋን የተወለደላቸው ሌላኛው ወንድ ልጅ ስሙ ማን ነበር?

የአዳምና የሔዋን ሌላኛው ወንድ ልጅ ስም ሴት ነበር

በሴት ልጅ በሄኖስ ዘመን ሰዎች ማድረግ የጀመሩት ምን ነበር?

ሰዎች የእግዚአብሔር አምላክን ስም መጥራት ጀመሩ