Genesis 43

Genesis 43:1

ራቡ በምድሪቱ ላይ እንደጸና ነበር

ከነዓን የሚለው ቃል የታወቀ ነው ይህ ሃሳብ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት በከነዓን ምድር ራቡ የጸና ነበር (ድብቅ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

እንዲህም ሆነ

ይህ ሀረግ የተጠቀመው የታሪኩን አድስ ክፍል መጀመሩን ለማመልከት ነው በቋንቋዎ ይህን መግለጽ የሚችሉበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)

በልተው ከጨረሱ በኋላ

ያዕቆብና ቤተሰቡ በልተው ከጨረሱ በኋላ

ያመጡትን

የያዕቆብ ታላቅ ልጆች ያመጡትን

ለኛ ሸምቱልን

እዚህ እኛ ያዕቆብን የያዕቆብን ልጆችና የቀሩ የቤተሰብ አባላትን ያመለክታል:: (ሁሉን አካታች “እኛ” ይመልከቱ)

Genesis 43:3

ይሁዳ እንዲህ አለው

ይሁዳ ለአባቱ ለያዕቆብ እንዲህ አለው

ያ ሰው

ይህ ዮሴፍን ነው የሚያመለክተው ነገር ግን ወንድምቹ ዮሴፍ መሆኑን አላወቁትም ነበር:: እነርሱም እርሱን ያመለከቱን እንደ “ያ ሰው” ወይም በዘፍጥረት 42:3ዐ እንደተነገረው “ያ ሰው የምድሪቱ ጌታ” ነው::

ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ፊቴን አታዩም ብሎ አስጠንቀቆናል

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል ይህም እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ታናሽ ወንድማችንን ይዘነው ካላመጣን ፊቱን ማየት እንደማንችል አስጠንቅቆናል” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

በጥብቅ አስጠንቅቆናል

እንዲህም በማለት በጥብቅ አስጠንቀቆናል

ፊቴን አታዩም

ወደ ግብጽ አገር ያለ ብንያም መመለስ እንደማይችሉ ለአባቱ ለማጽናት በዘፍጥረት 43፡ 4-5 ይሁዳ ይህን ሀረግ ሁለት ጊዜ ይጠቀማል:: ፊቴን የሚለው የዚያ ሰው የዮሴፍ ፊት ያመለክታል:: አት “ፊቴን አታዩም” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዜይቤ ይጠቀሙ)

ወንድማችን ከእኛ ጋር

ይሁዳ ራሔል ከመሞትዋ በፊት የወለደችውን የመጨረሻ ልጅ ብንያምን ያመለክታል

እኛም ወደዚያ አንወርድም

ከከነዓን ወደ ግብጽ ጉዞ በሚነገርበት ጊዜ “ወደታች መውረድ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው

Genesis 43:6

ለምን በደላችሁኝ?

ለምን ይህ ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?

ሰውየው አጥብቆ ጠየቀን

ሰውየው ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀን

ስለእኛ

እዚህ እኛ የሚለው በተለይ የሚያመለክተው ወደ ግብጽ የወረዱና ከሰውየው ጋር የተነጋገሩ ወንድሞችን ነው

አባታችሁ አሁን በሕይወት አለ? ሌላ ወንድም አላችሁ? ሲል ጠየቀን

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል አት አባታችን በሕይወት እንዳለና ሌላ ወንድም እንዳለን በቀጥታ ጠይቆናል:: (በጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

እኛም ለጥያቄዎቹ መልስ ሰጠን

የጠየቀንን ጥያቄዎች መለስንለት

…ይዛችሁ እንዲትመጡ እንደሚለን እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?

ሰውየው ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደሚነግር ልጆቹ አለማወቃቸውን አጽንተው ለመንገር ጥያቄ ይጠቀማሉ ይህ አግናኝ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል አት እንደዚህ … እንደሚለን አላወቅንም ነበር (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ወንድማችሁን ይዛችሁ ውረዱ ወይም አምጡ እንደሚለን

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል አት ወንድማችንን የዘን ወደ ግብጽ እንድንወርድ እንደሚነግረን (በጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

ወንድማችሁን ይዛችሁ ውረዱ

ከከነዓን ወደ ግብጽ ጉዞ በሚነገርበት ጊዜ “ወደታች መውረድ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው

Genesis 43:8

እኛና አንተ ልጆቻችንም ደግሞ እንድንድን እንዳንሞትም

እንድንድን እና እንዳንሞት የሚሉ ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: ይሁዳም በሕይወት ለመኖር ከግብጽ አህል መሸመት እንዳለባቸው በማጽናት ይናገራል:: አት “መላው ቤተሰባችን እንዲተርፍ ወደ ግብጽ ወርደን እህል መሸመት ይገባናል” (ተመሣሣይ ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)

እኛም ተነሥተን

እዚህ እኛ ወደ ግብጽ የሚጓዙ ወንድሞችን ያመለክታል:: (የሚያቅፍና የማያቅፍ እኛ ይመልከቱ)

እኛ እንተርፋለን

እዚህ “እኛ” ወንድሞች እስራኤልና መላውን ቤተሰብ ያመለክታል (የሚያቅ “እኛ” ይመልከቱ)

እኛ ሁለታችን

እዚህ እኛ ወንድማማቾችን ያመለክታል (የሚያቅፍና የማያቅፍ “እኛ” ይመልከቱ)

እኛ አንተም

እዚህ አንተ በነጠላ የተገለጸና እስራኤልን ያመለክታል (ሁለተኛ ወገን ሰው ወይም አንተ አጠቃቀም ይመልከቱ)

የእኛም ልጆች ወይም ልጆቻችን

እኛ ወንድሞችን ያመለክታል በረሀቡ ጊዜ ሊሞቱ የሚችሉ ትናንሽ ልጆችን ያመለክታል

እኔ ዋስ እሆንለታለሁ

“ዋስ” የተባለው ረቂቅ ስም እንደ “ተስፋ” የተባለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል፡፡ (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

ተጠያቂ እሆናለሁ

ያዕቆብ ይሁዳን እንዴት ተጠያቂ እንደሚያደረገው በግልጽ መነገር አለበት አት በብንያም ላይ በሚደርሰው ነገር ሁሉ ምላሽ እንዲሰጥ ታደርገኛለህ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)

እኔ ራሴ ኃላፊነትን እሸከማለሁ

ይህ አንድ ሰው እንደሚሸከመው ዕቃ ተደርጐ ኃላፊነትን መሸከም ይገልጻል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ባንዘገይ ኖሮ

ይሁዳ ቀድሞ መደረግ የነበረበት ነገር ግን ያልተደረገውን ነገር ይገጻል ተጨማሪ እህል ለመሸመት ልጆቹ ወደግብጽ ሳይሄዱ በመቆየታቸው አባቱን እንስራኤልን ይሁዳ በመውቀስ ይናገረዋል (የሚገመቱ ታሳቢ ሁኔታዎችን ይመልከቱ)

እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን

ሁለት ጊዜ መመላለስ በቻልን

Genesis 43:11

እንዲህ ከሆነ ይህን አድርጉ

ይህ ብቸኛ ምርጫችን ከሆነ ይህን አድረጉ

ተሸክማችሁ ውረዱ

ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ መውረድ የሚለውን ቃል መጠቀም የተለመደ ነበር

በለሳን

ቆዳን ለማከምና ለመከላከል የሚጠቀሙበት ጣፊጨነት ያለው ቅባታማ ፍሬ ነው:: በዘፍጥረት 37:25 ይህን ቃል እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት “መድኃኒት”

ቅመማ ቅመሞች

የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች በዘፍጥረት 37:25 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

ለውዝ

ትናንሽ አረንጓዴ ተክል ለውዞች (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ተምር

ጣፋጭ ጣዕም ያለው የዛፍ ፍሬ (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

በእጃችሁ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ

እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰውን ይወክላል አት ዕጥፍ ገንዘብ ውሰዱ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

በየስልቾቻችሁ አፍ የተገኘውን የተመለሰውን ብር በአጠፌታ አድርጋችሁ በእጃችሁ ውሰዱ

እዚህ እጅ ሙሉ ሰውን ይወክላል በስልቼቻችሁ አፍ የተመለሰው ብር የተባለው ሀረግ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አንድ ሰው በስልቾቻችሁ የጨመረውን ብር መልሳችሁ ወደ ግብጽ ውሰዱ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤና ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 43:13

ወንድማችሁንም ውሰዱ

ብንያምንም ደግሞ ውሰዱ

ሂዱ

ተመለሱ

ሁሉም የሚችል አምላክ በዚያ ሰው ፊት ምሕረትን ይሰጣችሁ

ምሕረት የሚለው ረቂቅ ስም ርኀራኄ በሚለው ቅጽል ሊተረጐም ይችላል:: አት “ሁሉን የሚችል አምላክ ያ ሰው እንዲራራ ያድርግላችሁ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

ሌላውንም ወንድማችሁንም

ስምዖንን

እኔም ልጆቼን እንዳጣሁ አጣሁ

ልጆቼን ካጣሁ ያው አጣሁ ያዕቆብ ልጆቹን ቢያጣ እንዳጣ ሊቀበል አውቆታል ማለት ነው

በእጃቸው … ወሰዱ

እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰውን ይወክላል:: አት እነርሱም … ወሰዱ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ወደ ግብጽም ወረዱ

ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደዚያ ወረደ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር

Genesis 43:16

ከራሳቸው ጋር ብንያምን

ብንያም ከዮሴፍ ታላቅ ወንድሞች ጋር

የቤቱን አዛዥ

የቤቱ አዛዥ የዮሴፍን ቤት ተግባራትን ለማሰተዳደር ኃላፊነት ነበረው

እነዚህን ሰዎች አመጣቸው

እዚህ “አመጣቸው” እንደ “ወሰዳቸው” ሊተረጐም ይችላል:: (“መጣ” እና “ሄደ” አጠቃቀም ይመልከቱ)

ወደ ዮሴፍ ቤት

ወደ ዮሴፍ ቤት ውስጥ

Genesis 43:18

ሰዎቹም ፈሩ

የዮሴፍ ወንድሞች ፈሩ

ወደ ዮሴፍ ቤት ስለተወሰዱ

ይህ ተሻጋሪ ግስ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፤ አት “ወደ ዮሴፍ ቤት ይሄዱ ነበር” ወይም “የቤቱ አዛዥ ወደ ዮሴፍ ቤት ይወስዳቸው ነበር” (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)፡፡

ቀደም ስል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት የቤቱ አዛዥ እየወሰደን ያለው ያነ አንድ ሰው በስልቾቻችን በጨመረው ብር ሰበብ ነው (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ሰውዬው በዚህ አጋጣሚ ሊተነኰልብን ይሆናል ሊያሥረንም ይችላል

ይህ እንደ አድስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት “ሊከሰን እጋጣሚ እየጠበቀ ስላለ ሊያሰረን ይሆናል”

Genesis 43:21

አገናኝ ዐረፍተ ነገር

ወንድሞቹ ለቤቱ አዛዥ መናገር ቀጠሉ

እንዲህም ሆነ

ይህ ሀረገ በታሪኩ ዋና ክተት ለማመልከት ተጠቅሞአል በቋንቋዎ ይህን የሚገልጹበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ::

ወደምናድርበት ቦታ በደረስን ጊዜ

ለአዳር በሠፈርንበት ቦታ በደረስን ጊዜ

እነሆ

እዚህ “እነሆ” የሚለው ቃል ወንድሞቹ ባዩት ነገር እንደተገረሙ ለማሳየት ተጠቅሞአል::

እያንዳንዳችን በስልቾቻችን አፍ ብራችንን ሙሉውን አገኘነው

እያንዳንዳችን በየስልቾቻችን ሙሉውን ብሮቻችንን አገኘው

መልሰን በእጃችን አመጣነው

እዚህ እጆች ሙሉውን ሰው ይወክላሉ አት ብሮቻችንን መልሰን የዘነው መጣን (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ደግሞም እህል መሸመቻ የሚሆነንን ተጨማሪ ገንዘብ ይዘን መጥተናል/ወርደናል

እዚህ እጆች ሙሉ ሰው ይወክላሉ:: አት “ደግሞም እህል መሸመቻ የሚሆነንን ብር ይዘን መጥተናል” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ይዘን ወርደናል

ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደዚያ ወረደ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር

ሰላም ለእናንተ ይሁን

ረቂቅ ስም ሰላም እንደ ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ዘና በሉ ወይም ተረጋጉ” (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)

አምላካችሁና የአባታችሁ አምላክ

የቤቱ አዛዥ ሁለት የተለያዩ አምላኮችን እየተናገረ አይደለም አት “አምላካችሁ አባታችሁ የሚያመለከው”

Genesis 43:24

እግሮቻቸውን የሚታጠቡበት

ይህ ባህል ረጅም ጉዞ ተጉዘው ከመጡ በኋላ የደከሙ መንገደኞች ድካማቸው እንዲቀል የሚረዱበት ነው:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልክቱ)

ለአህዮቻቸው የሚበሉትን ገፈራ ሰጣቸው

ገፈራ ለከበቶች የሚሆን ድርቆሽ ነው

Genesis 43:26

በእጃቸው ያመጡአቸውን እጅ መንሻዎች አበረከቱለት

“እጅ” ሙሉን ሰው ይወክላል:: አት “ወንድሞች ያመጡአቸውን እጅ መንሻቸውን” (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

በፊቱም ወድቀው ሰገዱለት

ይህ ክብርና አክብሮት የሚገለጽበት መንገድ ነው:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

Genesis 43:28

አገልጋይህ አባታችን

አባታቸውን እንደ “አገልጋይህ” ማመልከታቸው አክብሮታቸውን ለማሳየት ነው አት “አባታችን የሚያገለግልህ”

አጐንብሰው ሰገዱለት

እነዚህ ቃላት በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው በሰውየው ፊት ጐንበስ በማለት አክብሮታቸውን ገለጹ:: አት “በፊቱ ሰገዱለት” (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

ዮሴፍም ዐይኑን ሲቃኝ

ቀና ብሎ ሲመለከት ማለት ነው ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ

የእናቱን ልጅ እናም አለ

ይህ በአድስ ዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “የእናቱን ልጅ.. አየ:: ዮሴፍም አለ፤”

ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን?

ተገቢ አማራጭ ትርጉሞች 1 ይህ ሰው ብንያምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ዮሴፍ በውኑ ይጠይቃቸዋል ወይም 2) ይህ አግናኝ ጥያቄ ነው:: “ደግሞ ይህ ታናሽ ወንድማችሁ …. “ (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ልጄ

ይህ አንድ ሰው በዝቅተኛ ደረጃ ላለ ሌላ ሰው በጓደኝነት መንገድ የሚጠራው አጠራር ነው:: አት “ወጣቱ”

Genesis 43:30

ፈጥኖ ከክፍሉ ወጣ

ተቻኩሎ ከክፍሉ ወጣ

ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለተነካ

ስሜቱ በጥልቀት የሚለው ሀረግ አንድ መልካም ነገር ሲከሰት የሚሰማ ታላቅ ስሜትን ያመለክታል:: አት “ለወንድሙ የመራራት ጠንካራ ስሜት ነበረው” ወይም “ለወንድሙ ጠንካራ የናፍቆት ስሜት ነበረው” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

አለ

ዮሴፍ እንደሚናገር ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት “እናም ለአገልጋዮቹ አላቸው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ማዕድ ይቅረብ

ሰዎች እንዲመገቡ ምግብን ማቅረብ ማለት ነው፡፡

Genesis 43:32

አገልጋዮችም ለዮሴፍ ለብቻው ለወንድሞቹም ለብቻቸው አቀረቡላቸው:: ከእርሱ ጋር ለሚበሉ ግብጻዊያን ደግሞ ለብቻቸው አቀረቡላቸው::

ይህም ዮሴፍ ወንድሞቹና ሌሎች በአንድ ክፍል በተለያየ ቦታ ተቀምጠው ይመገባሉ ማለት ነው አገልጋዮችም ለዮሴፍ ለብቻው ለመንድሞቹም ለብቻቸው እናም ከእርሱ ጋር ለሚበሉ ግብጻዊያን ደግሞ ለብቻቸው አቀረቡላቸው

ከእርሱ ጋር ለሚበሉ ግብጻዊያን ለብቻቸው

እነዚህ ምናልባት ከእርሱ ጋር የሚበሉ የግብጽ ባለሥልጣናት ይሆናሉ ነገር ግን ከዮሴፍና ከዕብራዊያን ወንድሞቹ ተለይተው ተቀምጠዋል

ግብጻዊያን ከዕብራዊያን ጋር መመገብ አይሆንላቸውም ምክንያቱም ያ ለግብጻዊያን መርከስ ነውና

ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል ይህንን ያደረጉበት ምክንያት ግብጻዊያን ከዕብራዊያን ጋር መመገብ ጸያፍ አድርገው ያስባሉ

አብረው እንጀራ አይበሉም

እዚህ እንጀራ ጠቅላላ ምግብ ይወክላል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ወንድምቹ በእርሱ ፊት ተቀመጡ

እያንዳንዱ ወንድም የት መቀመጥ እንዳለበት ዮሴፍ እንዳዘጋጀ ሊገመት ይገልጻል የተገለጸውን መረጃ ግልጽ ማድረግ ይቻላል አት የሚቀመጡበት ቦታ በተዘጋጀላቸው መሠረት በሰውየው/ዮሴፍ ፊት ወንድሞቹ ተቀመጡ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)

በፊቱም በኩሩ እንደታላቂነቱ ታናሹም እንደታናሽነቱ

“በኩር”ና “ታናሽ” የተጠቀሙት ሁሉም ወንድሞች በአንድነት እንደየዕድሜያቸው በተርታ እንደተቀመጡ ለመግለጽ ነው::( ነጠላ ነገር በብዙ የመግለጽ ዘይቤ/merism/ ይመልከቱ)

ሰዎቹም/ወንድሞቹም በአንድነት ተገረሙ

ይህን ባወቁ ጊዜ ሰዎቹ በጣም ተገረሙ

የብንያም ድርሻ ከሌሎች ወንድሞች አምስት እጥፍ ነበር

አምስት እጥፍ የሚለው ሀረግ በአጠቃላይ ብዙ በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት “ብንያም የተቀበለው ድርሻ ወንድሞቹ ከተቀበሉት በጣም ብዙ ነበር”