Genesis 40

Genesis 40:1

ከዚህም በኋላ

ይህ ሀረግ የተጠቀመው በታሪኩ አዲስ ክስተት መጀመሩን ለማመልከት ነው፡፡ (አዲስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)

የመጠጥ አሳላፊ

ይህ ለንጉሡ መጠጥ የሚያቀርብ ሰው ነው

እንጀራ ቤቱ

ይህ ለንጉሡ ምግብ የሚያዘጋጅ ሰው ነው

ጌታቸውን በደሉት

ጌታቸውን አስቆጡት

የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ

ዋና የመጠጥ አሳላፊና ዋና እንጀራ እቅራቢ

በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው እስር ቤት አስገባቸው

በዘበኞቹ አለቃ በሚተዳደረው የቤት ውስጥ እስር ቤት አስገባቸው

አስገባቸው

ንጉሡ ወደ እሥር ቤት አላስገባቸውም ነገር ግን እንዲታሠሩ አዘዛቸው፡፡ አት “እነርሱ እንዲያስገቡ አደረጋቸው” ወይም “ዘበኛው እንዲያስገባቸው አዘዘ” (ተዛማጅ ምትክ አባባሎችን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ዮሴፍ ወደጋዘበት እስር ቤት

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ይህ ዮሴፍ የነበረበት ተመሣሣይ እስር ቤት ነው ወይም ይህ ጲጥፋራ ዮሴፍን ያስገባበት ተመሣሣይ እስር ቤት ነው (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 40:4

በእስር ቤት ጥቂት ጊዜ ቆዩ

በእስር ቤት አያለ ጊዜያት ቀን ተቀመጡ

Genesis 40:6

ዮሴፍ ወደእነርሱ ገባ

ዮሴፍ ወደ መጠጥ አሳላፊውና እንጀራ አቅራቢው ገባ

እነሆም አዝነው አያቸው

እነሆም የሚለው ቃል ባየው ነገር ዮሴፍ እንዴት እንደተገረመ የሚያሳይ ነው:: አት “እነርሱን አዝነው በማየቱ ተገረመ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አብረውት የነበሩ የፈርዖን ሹማምንት

ይህ የጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አቅራቢዎች አዛዥ ያመለክታል

በጌታው ግቢ በግዞት

በጌታው ግቢ በእስር ቤት፤ ጌታው የዮሴፍ ጌታ፤ የዘበኞች አለቃ የሚያመለክት ነው

ትርጓሜ ከእግዚአብሔር የማገኝ አይደለምን?

አጽንዖት ለመስጠት ዮሴፍ ጥያቄ ይመለከታል:: ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ትርጓሜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው! ወይም ለሕልሞች ትርጉምን መስጠት የሚችል እግዚአብሔር ነው” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

እስቲ ንገሩኝ

ሕልማቸውን እንዲነግሩት ዮሴፍ ይጠይቃቸዋል:: አት “ሕልሞቻችሁን እባካችሁ ንገሩኝ”

Genesis 40:9

የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ

ለንጉሡ መጠጦችን የሚያቀርብ ዋና ሰው ነው”” በዘፍጥረት 4ዐ: 2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

በሕልሜ እንሆ የወይን ዛፍ በፊቴ ሆና አየሁ

“በሕልሜ የወይን ጣፍ በፋቴ ሆና አየሁ!” የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ባየው ነገር እንደተደነቀና ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳየት “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል::

ዘለላዎችዋም በሰሉ

ዘለላዎችዋም ተንዠርግገው በሰሉ

ጨመቅሁአቸው

ከእነዚያ የጁስ ጭማቂ አወጣሁ ማለት ነው አት ከእነዚያ ጁስ ጨምቄ አወጣሁ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 40:12

የዚህ ትርጓሜ ይህ ነው

የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው

ሶስቱ ሐረግ ሶስት ቀን ነው

ሶስት ሐረጐች ሶስት ቀኖች ያመለክታሉ

በሶስት ቀኖች ውስጥ

እስከ ሶስት ቀኖች

ራስህን ከፍ ከፍ ያደርጋል

እዚህ ፊርዖን ከእስር ቤት የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃ የሚያወጣው ፈርዖን ከፍ ከፍ እንደሚያደርገው ተደርጐ ተነግሮአል:: አት “ከእስር ቤት ያወጣሃል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ወደ ቀድሞ ሹመትህ ይመልስሃል

ወደ ሥራህ ይመልስሃል

በነበርህበት ጊዜ

በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው

Genesis 40:14

ቸርነት አድርግልኝ

ቸር ሁንልኝ

ስለእኔም ለፈርዖን ንገርልኝና ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ

ዮሴፍም የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ስለእርሱ ለፈርዖን እንዲነግረው ከዚህም የተነሣ ፈርዖን ከእስር ቤት እንዲያስወጣው ማለት ነው:: አት: “ስለእኔ ለፈርዖን በመንገር ከእስር ቤት እንዲወጣ እርዳኝ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

በእርግጥ በአፈና ውስጥ ነኝ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “በእርግጥ ሰዎች አፍነው እምጥተውኛል” ወይም “በእርግጥ እስማኤላዊያን ይዘው አምጥተውኛል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ከዕብራዊያን ምድር

ዕብራዊ ሰዎች ከሚኖሩበት ምድር

አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም

እናም ደግሞ እዚህ በግብጽ በሚርበት ጊዜ በእስር ቤት እንዲጣል የሚያደርገኝን ምንም ነገር አላደረግሁም

Genesis 40:16

የእንጀራ ቤት አዛዡም

ይህ ለንጉሡ ምግብ የሚያቀርብ መሪ ሰው እንደሆነ ያመለክታል:: በዘፍጥረት 4ዐ:2 ይህ እንዴት እንደተተረጐመ ይመልከቱ::

እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ እናም

እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ እናም በሕልሜ

እነሆም ሶስት መሶብ እንጀራ በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር

ሶስተ መሶብ እንጀራ በራሴ ላይ ተሽክሜ ነበር! እዚህ የእንጀራ ቤቱ አዛዥ “እነሆ” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ባየው ሕልም መገረሙንና ዮሴፍም ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳየት ነው::

ለፈርዖን ከተዘጋጀው እንጀራ

ለፈርዖን ከተዘጋጀው ምግብ

Genesis 40:18

ፍቺው ይህ ነው

የሕልሙ ትርጉም ይህ ነው

ሶስቱ መሶቦች ሶስት ቀኖች ናቸው

ሶስት መሶቦች ሶስት ቀኖችን ይወክላሉ

ራስህን ከፍ ያደርጋል

ዮሴፍ በዘፍረት 4ዐ:13 ለመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ በሚናገርበት ጊዜ ደግሞ ራስህን ከፍ ያደርጋል የሚለውን ሀረግ ተጠቅሞአል እዚህ ግን የተለየ ትርጉም አለው አማራጭ ተገቢ ትርጉሞች: (1) በአንገትህ ገመድ በማሠር ራስህን ከፍ ያደርጋል ወይም (2) ራስህን በመቁረጥ ከፍ ያደርግሃል::

ሥጋ

የ “ሥጋ” ቀጥታ ትርጉሙ የአንድ ሰው አካል ክፍል ማለት ነው

Genesis 40:20

እንዲህም ሆነ በሶስተኛውም ቀን

ከዚያም በኋላ በሶስተኛውም ቀን እዚህ እንዲህም ሆነ የሚለው ሀረግ የተጠቀመው አዲስ ክስተትን ለማመልከት ነው (አዲስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)

ግብር አበላ

ግብዣ ነበረው

የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃ

ይህ ለንጉሡ መጠጥን የሚያዘጋጅና የሚያቀርብ መሪ ሰው ነበር፡፡ በዘፍጥረት 4ዐ፡2 እነዚህ ቃላት እንዴት እንደተተረጐሙ ይመልከቱ፡

የእንጀራ ቤት አዛዡን

ይህ ለንጉሡ ምግብን የሚያዘጋጅ መሪ ሰው እንደሆነ ያመለክታል:: በዘፍጥረት 4ዐ:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው

የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ሹመት ወይም ኃላፊነት እንደመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ሥራው እንደሆነ ያመለክታል አት ለመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ሥራውን መልሶ ሰጠው (ተዛማጅ ምትክ ቃላትን ስለመጠቀም ይመልከቱ)

ነገር ግን የእንጀራ ቤት አዛዡን ሰቀለው

ፈርዖን ራሱ አልሰቀለውም ይሁን እንጂ እንዲሰቀል አዘዘ አት የእንጀራ ቤት አዛዥ እንዲሰቀል አዘዘ ወይም ዘበኞቹ ወይም ጥበቃዎቹ የእንጀራ ቤት አዛዡን እንዲሰቅሉ አዘዘ (ተዛማጅ ምትክ ቃላትን ስለመጠቀም ይመልከቱ)

ልክ ዮሴፍ እንደተረጐመላቸው

ይህ ዮሴፍ ሕልማቸውን እንደተረጐመላቸው የሚለውን ያመለክታል አት የሁለቱን ሰዎች ሕልም ዮሴፍ እንደተረጐመላቸው እንዲሁ ሆነ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)