Genesis 34

Genesis 34:1

አሁንም

በዚህ ይህ ቃል የታሪኩን አድስ ክፍል ለማመልከት ተጠቅሞአል፡፡

ዲና

የልያ ሴት ልጅ ነች በዘፍጥረት 3ዐ:21 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ኤዊያዊ

ይህ የብሔር ስም ነው:: በዘፍጥረት 1ዐ፡17 ኤዊያዊያን የሚለውን ቃል እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

የአገሩ ገዢ

ይህ ሴኬምን ሳይሆን ኤምርን ያመለክታል በዚህ ቦታ ገዢ የንጉሥ ልጅ ማለት አይደለም ይህም ኤሞር በዚያ ለሚኖሩ ሰዎች መሪ እንደነበር ነው

አስነወራት ከእርስዋም ጋር ተኛ

ሴኬም ዲናን ደፈራት (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል ወይም በተዘዋዋሪ አንድን ነገር የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ወደ ዲና ተሳበ

“በዲና ተማረከ” ዲናን እንደወደዳትና ከእርስዋ ጋር ለመሆን አንድ ነገር ወደ ዲና እንዲመጣ እንዳስገደደው ስለ ሴኬም ይናገራል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ከዲና ጋር ለመሆን እጅግ በጣም ፈልጐአል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ወይም ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

በጣፈጠ አንደበት አናገራት

እንደሚወዳትና እንዲትወደው ለማድረግ ሊያሳምናት በሚስብ መንገድ አናገራት ማለት ነው

Genesis 34:4

አሁንም ያዕቆብ

“አሁን” የተጠቀመው ከታሪኩ ወደ ያዕቆብ ዳራ መረጃ ለውጥ ማድረግን ለማመልከት ነው

ያዕቆብም … እርሱ … ሰማ

“እርሱ” የሚለው ቃል ሴኬምን ያመለክታል

አስነወራት

ሰኬም በጉልበት ከእርስዋ ጋር በመተኛት ዲናን እጅግ በጣም አዋረዳት ክብርዋን ነፈጋት ማለት ነው

ታግሶ ቆዬ

ያዕቆብ ስለ ጉዳዩ ምንም አላደረገም ወይም አልተናገረም ማለት ነው:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 34:6

ኤሞር ያዕቆብን ሊያነጋግረው ወጣ

ኤሞር ያዕቆብን ሊያነግረው ሄደ

የያዕቆብ ወንዶች ልጆች አዘኑ

ወንዶች ልጆች እጅግም ተቆጡ ወይም ደነገጡ

እስራኤልን አስነወረ

እዚህ እስራኤል የሚለው ቃል እያንዳንዱን የእስራኤል ቤተሰብ አባል ያመለክታል እስራኤል እንደብሔር ተደፍሮአል:: አት: “የእስራኤልን ቤት አዋርዶአል” ወይም “የእስራኤልን ስዎች አሳፍሮአል” (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘጥቤ ይመልከቱ)

የያዕቆብን ሴት ልጅ ስለደፈረ

የያዕቆብን ልጅ ስለደፈራት

ይህ ዓይነት ተግባር መደረግ አይገባውም

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እንደዚህ አስነዋሪ ነገር ማድረግ አይገባውም ነበር” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 34:8

ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው

ኤሞር ለያዕቆብና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ነገራቸው

በልጃችሁ ፍቅር ተነድፎአል

ፍቅር የሚለው ቃል በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚሆን ስሜታዊ ፍቅር ነው አት ወድዶአታልና ሊያገባት ይፈልጋል

ሚስት እንዲትሆነው እርሷን ስጡት

በአንዳንድ ባህሎች ልጆች ማግባት ያለባቸውን ወላጆች ይወስናሉ

በጋብቻ እንተሳሰር

በጋብቻ መተሣሠር ከሌላ ዘር ብሔር ባህልና ጐሣ ሰዎች ጋር መጋባት ማለት ነው:: አት: “በአናንተና በእኛ ሰዎች መጋባትን እንፍቀድ”

ምድሪቱ በእናንተ ፊት ናት

ምድሪቱ የእናንም ናት

Genesis 34:11

ሴኬም ደግሞ አባትዋን እንዲህ አለ

ሴኬም የዲናን አባት ያዕቆብን እንዲህ አለ

በእናንት ፊት ሞገስ ላግኝ እንጂ የጠየቅሁትን ሁሉ እሰጣለሁ

“ሞገስ ማግኘት” የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ማረጋገጥ የሚናገር ዘይቤያዊ አነጋገር ነው ደግሞም ዓይኖች ማየትን ሲወክሉ ማየት ሀሳብን ወይም ፍረጃን ያመለክታሉ:: አት: “እንደተቀበላችሁን ካረጋገጥሁ የሚትጠይቁኝን ሁሉ እሰጣለሁ”:: (ፈሊጣዊና ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ጥሎሽ

በአንዳንድ ባህሎች በጋብቻ ጊዜ ለሙሽሪቱ ቤተሰብ ሙሽራው በገንዘብ በንብረት በእንስሳትና በሌላም መልክ ስጦታ መስጠት የተለመደ ነው

የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም ለሴኬምና ለኤሞር የሚያታልል መልስ ሰጡ

ማታለል የሚለው ረቂቅ ስም መዋሽት እንደሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: ነገር ግን የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ለሴኬምና ለኤሞር በመለሱአቸው ጊዜ ዋሹአቸው (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)

ሴኬም ዲናን አስነውሮአታል

ከእርሱ ጋር እንዲትተኛ በመድፈሩ ሴኬም ዲናን እጅግ በጣም አዋርዶአታል አስነውሮአታል ማለት ነው:: በዘፍጥረት 34:5 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

Genesis 34:14

እነርሱም እንዲህ አሉአቸው

የያዕቆብ ወንድ ልጆች ለሴኬምና ለኤሞር እንዲህ አሉ

እኀታችንን ብንሰጥ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም

ዲናን በጋብቻ ሊንሰጥ አንስማማም

ይህም ለእኛ ውርዴት ነው

ይህም እኛን ያሳፍረናል:: እዚህ “እኛ” የያዕቆብን ወንዶች ልጆችንና የእስራኤልን ልጆች በአጠቃላይ ያመለክታል (የሚያካትትና የማያካትት እኛን ይመልከቱ)

ሴቶች ልጆቻችንን እንሰጣችኋለን የእናንተን ሴቶች ልጆች እንወስዳለን

ይህም ከያዕቆብ ቤተሰብ የሆነ ሰው በኤሞር ምድር የሚኖረውን ሰው ያገባል ማለት ነው

Genesis 34:18

ያቀረቡትም ሃሳብ ለኤሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታየቸው

ኤሞርና ልጁ ሴኬም የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ባቀረቡት ሃሳብ ተስማሙ

ያሉትን ለማድረግ

ለመገረዝ

የያዕቆብ ሴት ልጅ

የያዕቆብ ሴት ልጅ ዲና

ከአባቱ ቤተሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው

ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: እጅግ ስለሚያከብሩት ሌሎች ሰዎች ለመገረዝ እንደሚስማሙ ሴኬም እንደተረዳ ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “እርሱ በእነርሱ ዘንድ የተከበረ በመሆኑ የአባቱ ቤተሰብ ወንዶች ሰዎች ሁሉ ለመገረዝ እንደሚስማሙ ሴኬም ያውቅ ነበር” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)::

Genesis 34:20

ወደ ከተማቸው በር

ሕጋዊ ውሳኔ ለመወሰን በከተሞች በር መሰባሰብ በመሪዎች የተለመደ ነው

እነዚህ ሰዎች

ያዕቆብ ወንዶች ልጆቹና የእስራኤል ሰዎች

በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች

እዚህ “እኛ” ኤሞር ልጁንና የተናገሩአቸው በከተማው በር ያሉ ሰዎችን ሁሉ ያቀፈ ነው (ሁሉን ያቀፈ “እኛ” ይመልከቱ)

በምድራችን ይኑሩ ይነግዱበትም

በምድሪቱ ይኑሩ ይነግዱበትም

እነሆ ምድሪቱ በእርግጥ ሰፊ ናት

ለዐረፍተ ነገሩ ትኩረት ለመስጠት ሴኬም “በእርግጥ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል:: “እነሆ ምድሪቱ በእርግጥ ለእነርሱም ሰፊ ናት” ወይም “እነሆ ለእነርሱ የሚበቃ በቂ መሬት አለ”

ሴት ልጆቻቸውን እንውሰድ ለእነርሱም ሴት ልጆቻችንን እንስጥ

ይህ በአንዱ ቡድን ሴቶች በሌላው ቡድን ወንዶች መካከል የሚፈጸሙ ጋብቻዎችን ያመለክታል፡፡ በዘፍጥረት 34፡9 ተመሣሣይ ሀረጐችን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡

Genesis 34:22

አጠቃላይ መረጃ

ኤሞርና ልጁ ሴኬም ለከተማዋ ሽማግሌዎች መናገራቸውን ቀጠሉ

አንድ ሕዝብ ሆነን ከእኛ ጋር ይቀመጡ ዘንድ በዚህ ነገር ብቻ እሺ ይሉናል እነርሱ እንደተገረዙ ወንዶቻችንን ሁሉ ብንገርዝ

ሰዎቹ ከእኛ ጋር እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው አብረውን ለመኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደሆነ ብቻ ነው

ታዲያ እንዲህ ብናደርግ ከብቶቻቸው ንብረታቸው እንስሶቻቸው ሁሉ የእኛው ይሆኑ የለምን?

የያዕቆብ እንስሶችና ንብረቶች ለሴኬም ሰዎች እንደሚሆን ሴኬም ጥያቄ ምልክት በመጠቀም አበክሮ ይናገራል:: ይህ እንደዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “የእነርሱ እንስሳትና ንብረት ሁሉ ለእኛ ይሆናል” አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ::

Genesis 34:24

ወንዶች ሁሉ ተገረዙ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ስለዚህ ኤሞርና ሴኬም ወንዶችን ሁሉ የሚገርዙ ነበሩአቸው (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዘበት ዐረፍት ነገር ይመልከቱ)

በሶስተኛውም ቀን

ሶስት ተራ ቁጥር ሶስት ነው:: ያለ ተራ ቁጥር ሊነገር ይችላል:: አት: “ከሁለት ቀን በኋላ”

ሁሉም ቆስለው ሳሉ

የከተማው ወንዶች ቆስለው ሳሉ

እያንዳንዱ ሰይፉን መዝዞ

ሰይፋቸውን መዘው

ከተማዋን ወጉት

ከተማ ሰዎችን ይወክላል አት እነርሱ የከተማይቱን ሰዎች ተዋጉ (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ጥበቃ፤ እናም ወንዶችን ሁሉ ገደሉ

ይህ እንደአዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ጥበቃ፡ ስምዖንና ሌዊ የከተማይቱን ወንዶች ሁሉ ገደሉ፡፡”

Genesis 34:27

ሬሳዎች

የኤሞር የሴኬምና ወንዶች ስዎቻቸው ሬሳ

ከተማዋን ዘረፉ

በከተማይቱ ያለውን ጠቃሚ ነገር ሁሉ ወሰዱ

ሰዎች እህታቸውን ስላረከሱአት

ሴኬም ብቻውን ዲናን አርክሶአት ነበር ነገር ግን የያዕቆብ ልጆች የሴኬም መላው ቤተሰብና በከተማው ያለው ሁሉ ሰው ለዚህ ድርጊት ተጠያቂ አድርገው ቆጥረዋል

አረከሳት

ከእርሱ ጋር እንዲትተኛ በመድፈር ሴኬም ዲናን አዋረዳት ወይም ክብርዋን ነፈጋት/አሳፈራት ማለት ነው:: በዘፍጥረት 34: 5 አረከሳት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

መንጎቻቸውን ወሰዱ

የያዕቆብ ልጆች የሰዎችን መንጋ ወሰዱ

ሀብቶቻቸውን ሁሉ

ንብረታቸውንና ገንዘባቸውን ሁሉ ሕጻናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውን ሁሉ ማረኩ

Genesis 34:30

አስጨነቃችሁኝ

ለአንድ ሰው የጭንቀት ምክንያት መሆን ጭንቀት በአንድ ሰው ላይ እንደሚመጣና እንደሚቀመጥ ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል አት: “ትልቅ ችግሮችን ፈጥራችሁብኛል” (ዜይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ)

በዚህ አገር በሚኖሩ ዘንድ እንደጥንብ አስቆጠራችሁኝ

ያዕቆብ በዙሪያው በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ እንዲጠላ ማድረግ የያዕቆብ ልጆች እርሱን እንደ መጥፎ ሽታ እንዳደረጉ ተገልጾአል ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “በምድሪቱ በሚኖሩ ዘንድ የተጠላሁ እንዲሆን አድርጋችሁኛል” (ዜይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ)

እኔ በቁጥር አነስተኞች ነኝ ቢያጠቁኝ እኔንና ቤተሰቤን ያጠፋሉ

እዚህ “እኔ” እና “እኔን” የሚሉ ቃላት ያዕቆብን ቤተሰብ በአጠቃላይ ይወክላሉ:: ያዕቆብ የቤተሰቡ መሪ ከመሆኑ የተነሳ “እኔ” ወይም “እኔን” ይጠቀማል:: አት: “ቤተሰብ አነስተኛ ነው … ተባብረው ቢነሡብኝና ቢያጠቁኝ ሁላችንንም ያጠፋሉ::” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ተባብረ ይነሡና ያጠቁኛል

ሠራዊት ይፈጥሩና ያጠቁኛል ወይም ሠራዊት ይፈጥሩና ያጠቁናል

እኔም እጠፋለሁ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ያጠፉኛል ወይም ያጠፉናል ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ”

ሴኬም በሴተኛ አዳሪ/በጋለሞታ እንደሚደረግ በእኀታችን ያደርግባትን?

ሴኬም ያደረገው ጥፋትና ሞት እንደሚገባው አበክረው ለመግለጽ ሌዊና ስምዖን ጥያቄ ይጠቀማሉ:: አት: “ሴኬም እህታችንን እንደ ሴተኛ አዳሪ/ጋለሞታ አድርጐ ባልቆጠረ ነበር!” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)