Genesis 28

Genesis 28:1

አታግቡ

አታግባ

ተነሣ ሂድ

ወዲያውኑ ሂድ

ጳዳን አራም

ይህ የመስጴጦምያ ግዛት ሌላ ስሙ ሲሆን የአሁኑ ራቅ የሚገኝበት ቦታ ነው:: በዘፍጥረት 25:2ዐ ይህ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

ቤት

የሰውየው ትውልድ ወይም ሌሎች ዘመዶች: አት: “ቤተሰብ” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ባቱኤል

ባቱኤል የርብቃ አባት ነው በዘፍጥረት 22፡22 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

የእናትህ አባት

ወንድ አያትህ

ሴት ልጆች መካከል

ከሴት ልጆች

የእናትህ ወንድም

አጐትህ

Genesis 28:3

አጠቃላይ መረጃ

ይስሐቅ ለያዕቆብ መናገሩን ቀጠለ

ልጆች አፍራ ዘርህን ያብዛው

ያብዛው የሚለው ቃል እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዴት ፍሬያማ እንደሚያደርገው ይገልጻል:: አት: “ብዙ ልጆችንና ትውልድ ይሰጥሃል” (ድርብ ቃላት ይመልከቱ)

ለአብርሃም የሰጠውን በረከት ለአንተና ለዘሪህ ይስጥ

ይህ የሚናገረው አንድን ሰው ስለመባረክ ሲሆን በረከት አንድ ሰው ሊሰጥ እንደሚችል ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል ረቂቅ ስም “በረከት” “ይባርክ” በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት: “አብርሃምን እንደባረከ አንተንና ዘርህን እግዚአብሔር ይባርክ” ወይም “ለአብርሃም የገባውን ተስፋ ለአንተና ለዘርህ እግዚአብሔር ይስጥ”:: (ዜይቤያዊ አነጋገርና ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

ምድሪቱን ያወርስህ ዘንድ

እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር ለያዕቆብና ለዘሩ መስጠቱ ልጅ ከአባቱ ገንዘብ ወይም ሀብት እንደሚወርስ ተደርጐ ተገልጾአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

የሚትኖርበትን ይህችን ምድር

“እስከአሁን ያለህበትን ምድር”

እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠውን

እግዚአብሔር ለአብርሃም ተሰፋ የሰጠውን

Genesis 28:5

ጳዳን አራም

ይህ የመስጴጦምያ ግዛት ሌላ ስሙ ሲሆን የአሁኑ ራቅ የሚገኝበት ቦታ ነው:: በዘፍጥረት 25:2ዐ ይህ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

ባቱኤል

ባቱኤል የርብቃ አባት ነው በዘፍጥረት 22፡22 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

Genesis 28:6

አጠቃላይ መረጃ

ታሪኩ ከያዕቆብ ወደ ዔሣው ይዞራል

አሁንም

ይህ ቃል እዚህ የተጠቀመው ከተነገረው ታሪክ ወደ ዔሣው የሕይወት መረጃ ፍሰቱ መቀየሩን ለማመልከት ነው (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ይመልከቱ)

ጳዳን አራም

ይህ የመስጴጦምያ ግዛት ሌላ ስሙ ሲሆን የአሁኑ ራቅ የሚገኝበት ቦታ ነው:: በዘፍጥረት 25:2ዐ ይህ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

ሚስት ያግባ

ሚስትን ያግባ

እንዲሁም ደግሞ ይስሐቅም እንደባረከው አየ

እንዲሁም ይስሐቅ ያዕቆብን እንደባረከው ኤሣው አየ

የከነዓን ሴቶች

የከነዓን ሴት ልጆች ወይም የከነዓናዊያን ሴቶች

Genesis 28:8

አጠቃላይ መረጃ

የዔሣውን ታሪካዊ ዳራ ይቀጥላል

ዔሣው አየ

ዔሣው ተገነዘበ

ከነዓናውያን ሴቶች በአባቱ በይስሐቅ ዘንድ ተጠልተዋል

አባቱ ይስሐቅ የከነዓናውያንን ሴቶች አልተቀበለም

የከነዓን ሴቶች

የከነዓን ሴት ልጆች ወይም የከነዓናዉያን ሴቶች

ስለዚህም ሄዴ

በዚህ ምክንያት ሄዴ

በሚስቶቹ ተጨማሪ

ከነበሩ ሚስቶች ተጨማሪ

ማዕሌት

የእስማኤል ሴት ልጆች አንዷ ነች (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ነባዮት

ከእስማኤል ወንድ ልጆች አንዱ ነው (ስምችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 28:10

አጠቃላይ መረጃ

ታሪኩ እንደገና ወደ ያዕቆብ ይመለሳል

ወደ አንድ ሥፍራም ደረሰ ጸሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ

ወደ አንድ ሥፍራ ደረሰ ጸሐይም ጠልታ ስለነበር አዳሩን ከዚያ ለማድረግ ወሰነ

Genesis 28:12

እርሱም ሕልም ዐለመ

ያዕቆብ ሕልም ዐለመ

በምድር ላይ ቆሞ

ታችኛው አካል መሬትን በነካ መንገድ ቆሞ

ጫፉ ሰማይ የሚደርስ

ይህ እግዚአብሔር የሚኖርበትን ቦታ ያመለክታል

እነሆም

እነሆም የሚለው ቃል ለሚቀጥለው አስደናዊ መረጃ ትኩረት ለመስጠት ነው

እግዚአብሔር በጫፉ ላይ ቆሞ

ተገቢ ትርጉሞች 1 እግዚአብሔር በመሰላሉ ጫፍ ላይ ቆሞ 2 እግዚአብሔር በያዕቆብ ጐን ቆሞ

ለአብርሃም ለአባትህ

እዚህ “አባት” ቅድመ ዘር ማለት ነው:: አት: “አብርሃም ለዘርህ” ወይም “አብርሃም ለቅድመ አያትህ”

Genesis 28:14

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር ለያዕቆብ በሕልም መናገሩን ቀጠለ

ዘርህ እንደምድር አሸዋ ይሆናል

በቁጥር መብዛትን አግንኖ ለማሳየት እግዚአብሔር የያዕቆብን ዘር ከምድር አሸዋ ጋር ያነጻጽራል:: አት: “መቁጠር ከምትችሉት በላይ ብዙ ዘር ይሆንላችኋል” ተመሣሣይ አባባል/simile ይመልከቱ

እስከ ምዕራብ ትስፋፋለህ

ትስፋፋለህ በነጠላ የተቀመጠና ያዕቆብን ያመለክታል እዚህ ያዕቆብ ዘሩን ይወክላል:: አት: “መቁጠር ከሚትችለው በላይ ብዙ ዘር ይሆንልሃል” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ትስፋፋለህ

ይህም ሕዝቡ የምድራቸውን ድንበር የሰፋሉ እናም ብዙ ምድር ይወርሳሉ ማለት ነው

ወደ ምዕራብ ወደ ምሥራቅ ወደ ሰሜን ወደ ደቡብ

እንዚህ ሀረጐች በጣምራ “ወደ ሁሉም አቅጣጫዎች” የሚል ትርጉም ለመስጠት ተጠቅመዋል:: (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “በአንተና በዘርህ በምድር ያሉ ሕዝቦችን እባርካለሁ” (ተሻጋረ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተነገር ይመልከቱ)

እነሆ እኔ

ትኩረት ስጥ እኔ የሚናገረው እውነትና ጠቃሚ ነው፤ እኔ

አልተውህም ሁሉንም እፈጽምልሃለሁ

ሁሉንም እስከሚፈጽምልህ ድረስ አልተውህም

እጠብቅሃለሁ

“ደኀንነትህን እጠብቃለሁ” ወይም “እከላከልልሃለሁ”

እንደገና ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ

ወደዚህች ምድር እመልስሃለሁ

Genesis 28:16

ከእንቅልፉ ሲነሣ

ከእንቅልፉ ሲነቃ

የእግዚአብሔር ቤት … የሰማይ ደጅ

የሰማይ ደጅ የሚለው ሀረግ የሚገልጸው የእግዚአብሔር ቤት እና የእግዚአብሔር መኖሪያ መግቢያ ቦታ እንደሆነ ነው (ድርብ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)

ይህ የሰማይ ደጅ ነው

ይህ ስለ እግዚአብሔር መኖሪያ ቦታ መግቢያ የሚናገረው በአካል እንደሚታይ አንድ ሰው በር ከፍቶ ሰዎችን እንደሚያስገባው የመንግሥት ቤት ተደረጐ ተገልጾአል:: (ዘይቤያዊ አባባል ይመልቱ)

Genesis 28:18

ሐውልት

ትልቅ ድንጋይ ወይም በጫፉ ቅርጽ ያለበት ለማስታወሻነት የቆመ ሐውልት ነው

በላዩ ላይ የወይራ ዘይት አፈሰሰበት

ያዕቆብ ሐውልቱን ለእግዚአብሔር መቀደሱን የሚያመለክት ድርጊት ነው:: የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “ሐውልቱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ዘይት በላዩ ላይ አፈሰሰበት” (ምልክታዊ ድርጊት ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ቤተል

ቤተል ማለት የእግዚአብሔር ቤት የሚለውን ተረጓሚዎች እንደ ግርጌ ማስታወሻ ያስቀምጣሉ

ሎዛ

ይህ የከተማይቱ ስም ነው

Genesis 28:20

ስእለት ተሳለ

“ስእለት አደረገ” ወይም “በተለይ ለእግዚአብሔር ቃል ገባ”

እግዚአብሔር እንዲህ…. እግዚአብሔር አምላኬ ይሆናል

ያዕቆብ እግዚአብሔርን በሶስተኛ ሰው አገላለጽ ያናግረዋል ይህ በሁለተኛ ሰው አገላለጽ ሊገለጽ ይችላል:: አት: አንተ እንዲህ…የማመልከው አምላኬ ትሆናለህ” (ተዛማጅና ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

የሚበላውን እንጀራ ቢትሰጠኝ

እዚህ “እንጀራ” አጠቃላይ ምግብ ይገልጻል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ወደ አባቴ ቤት

“ቤት” ለያዕቆብ ቤተሰብን ይገልጻል አት ወደ አባቴና ወደሌሎች የቤተሰብ አባላት (ተዛማጅና ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

የተቀደሰ ድንጋይ

ድንጋዩ እግዚአብሔር የተገለጠበትን ቦታ ያመለክታልና ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት ቦታ ይሆናል