Genesis 50

Genesis 50:1

በአባቱ ፊት ተደፍቶ

እዚህ ተደፍቶ የሚለው ፈሊጣዊ አባባል ተመስጦ ማለት ነው፡፡ አት “በአባቱ ላይ ተደፍቶ በሀዘን” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ባለመድኃኒት የሆኑ አገልጋዮቹ

አስከሬንን የሚያስተካክሉ አገልጋዮቹ

የአባቱን አስከሬን እንዲቀቡት

መቀባት ከቀብር በፊት አስከሬኑ እንዳይፈርስ የሚያቆዩበት ልዩ መንገድ ነው (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽን ይመልከቱ)

አርባ ቀን ወሰደባቸው

4ዐ ቀናት ወሰደባቸው (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

ሰባ ቀናት

7ዐ ቀናት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

Genesis 50:4

የሐዘኑ ጊዜ እንዳበቃ

“የማዘኑ ቀናት” ወይም “ለእርሱ የማልቀስ ቀናት”

ዮሴፍ ለፈርዖን ቤት ተናገረ

እዚህ የፈርዖን ቤት የፈርዖን ንጉሣዊ ፍርድ ቤት ወክል ባለሥልጣናት ያመለክታል ዮሴፍ ለፈርዖን ባለሥልጣናት ተናገረ (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

በፊታችሁ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ

ሞገስ ማግኘት የሚለው ሐረግ በአንድ ሰው ፊት ተቀባይነትን ማትረፍ የሚናገር ፈሊጣዊ አባባል ነው:: አት “በእናንተ ፊት ሞገስ ካገኘሁ ወይም በእኔ ደስተኞች ከሆናችሁ” (ፈሊጣዊ አባባልና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩልኝ ፤አባቴ አምሎኛል፤ እንዲህ ስል፤ እነሆ እኔ እሞታለሁ፤ በቆፈርሁትም መቃብር በከነዓን ምድር ከዚያ ቅበረኝ ፡፡ አሁንም ወጥቼ አባቴን ሊቅበርና ሊመለስ፡፡

ይህ ሁለት ደረጃና ሶስት ደረጃ ጥቅስ ይዞአል እነዚህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጹ ይችላሉ:: አት “በከነዓን ምድር በቆፈረው መቃብር እንዲቀብረው አባቴ በሚሞትበት ጊዜ እንዳመለኝ ለፈርዖን ንገሩልኝ:: አባተን እንዲቀብረውና ከዚያም ተመልሸ እንዲመጣ ፈርዖንን ጠይቁልኝ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

እኔ ልሞት ቀርበአለሁ

ሊሞት ነኝ

ልውጣ

ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደ ላይ መውጣት” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው፡፡

ፈርዖንም መለሰ

የመንግሥት ምክር ቤት አባላት ለፈርዖን ነገሩትና ከዚያም ፈርዖን ለዮሴፍ መለሰ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አባትህ እንዳማለህ

ለእርሱ እንደማልህለት

Genesis 50:7

ዮሴፍም… ወጣ

ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደ ላይ መውጣት” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው፡፡

የፈርዖን ሹማምንት በሙሉ የቤቱ ሽማግሌዎች/የቤተመንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የግብጽ ምድር ከፍተኛ ባለሥልጣናት

የፈርዖን ከፍተኛ መሪዎች ሁሉ የቀብሩን ሥነሥርዓት ተካፈሉ (የሁኔቶች ሥርዓት ይመልከቱ)

የቤቱ ሽማግሌዎች

የፈሪዖን ቤተምንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ያመለክታል

ከግብጽ ምድር ፤የዮሴፍ ቤተ ሰዎች ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰዎች

ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት “የግብጽ ምድር ፤ እንዲሁም የዮሴፍ ቤተ ሰዎች ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰዎች ከእርሱ ጋር አብረውት ሄዱ” (የሁኔቶች ቅደም ተከተል ይመልከቱ)

ሰረገላዎች

እዚህ በሠረገላዎች የተቀመጡ ሰዎችን ያመለክታል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)

እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ

እጅግ ብዙ ሰዎች ጉባኤ ነበር

Genesis 50:10

እነርሱም በመጡ ጊዜ

“እነርሱ” የሚለው ቃል በቀብር ሥነሥርዓቱን ይካፈሉ የነበሩ ሰዎችን ያመለክታል

የአጣድ አውድማ

ተገቢ ትርጉሞች 1) “አጣድ” የሚለው ቃል እሾህ ማለት ነው፤ አናም እጅግ ብዙ እሾሆች የሚበቅሉበት መሬት ሊባል ይችላል ወይም 2) “የአውድማው ባለቤት ስም ሊሆን ሊችላል:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ከፍተኛና መራራ ለቅሶ አለቀሱ

እጅግ መራራና ከፍተኛ ልቅሶ አልቅሰው ነበር

ሰባት ቀን

7 ቀን (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

በአጣድ አውድማ

ተገቢ ትርጉሞች 1) አጣድ የተባለው ሰው አውድማ ውስጥ ወይም 2) አጣድ በተባለው አውድማ ውስጥ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ይህ ግብጻዊያን እጅግ ያዘኑበት ጊዜ ነበር

የግብጻዊያን ልቅሶ መራራ ነበር

አቤል ምጽራይም

ተርጓሚዎች የሚከተለውን እንደ ግርጌ ማስታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ አቤል ምጽራይም የሚለው ስም የግብጻዊያን ሐዘን ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 50:12

ልጆቹም

የያዕቆብ ልጆችም

ልክ እንዳዘዛቸው

ልክ መመሪያ እንደሰጣቸው

ልጆቹም ተሸክመውት

ልጆቹም አስከሬኑን ተሸክመውት

ማክፌላ

ማክፌላ የቦታ ወይም የግዛት ስም ነው በዘፍጥረት 23፡9 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

መምሬ

የሔብሮን ከተማ ሌላ ስምዋ ነው በዚያ ይኖር በነበረው በአብርሃም ወዳጅ መምሬ ስም ሳትሰየም አትቀርም፡፡ በዘፍጥረት 13፡ 18 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ኬጢያዊው ኤፍሮን

ይህ የወንድ ሰው ስም ነው ኬጢያዊ የኬጥ ዘር ነው በዘፍጥረት 23፡8 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ወደ ግብጽ ዮሴፍ ተመለሰ

ዮሴፍ ወደ ግብጽ ተመለሰ

አብረውት የነበሩ ሁሉ

አብረውት የሄዱት ሁሉ

Genesis 50:15

ምናልባት ዮሴፍ ቂም ሊበቀለን ይሆናል

እዚህ ቂም ዮሴፍ በእጁ እንደምይዝ ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል አት ምናልባት ዮሴፍ የጠላን ይሆናል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ባደረግንበት ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል

እርሱን የበደለውን ሰው መበቀል አንድ ሰው ከሌላ ሰው የተበደረውን እንደመመለስ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “ባደረግንበት ክፋት ምናልባት ልበቀለን ይችላል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

አባትህ ገና ሳይምት እንዲህ ብሎ አዝዞአል ዮሴፍን እንዲህ በሉት እባክህ የወንድምችን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና

ይህ ሁለት ደረጃና ሶስት ደረጃ ጥቅስ ይዞአል እንደተዘዋዋሪ ጥቅስም ሊገለጹ ይችላሉ:: አት “አባትህ ከመሞቱ በፊት እኛ የበደልንህን ይቅር እንዲትለን እንድንነግርህ አዝዞናል” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

አባትህ ከመሞቱ በፊት አዝዞናል እንዲህ ስል

ያዕቆብ ለወንድማማቾች ሁሉ አባት ነው:: እዚህ ዮሴፍ አባቱ ለተናገረው ትኩረት እንዲሰጥ “አባትህ” ብለው ይናገራሉ:: አት “አባታችን ከመሞቱ በፊት”

በበደሉህ ጊዜ ያደረጉትን ኃጢአታቸውን

በአንተ ላይ ስላደረጉት ክፉ ነገሮች

አሁንም

ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው

የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል

ወንድሞቹ ራሳቸውን “የአባትህ አምላክ ባሪያዎች” ብለው ይገልጻሉ:: (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

ዮሴፍ ይህን ስሉት አለቀሰ

የሴፍ ይህን መልእክት በሰማ ጊዜ አለቀሰ

Genesis 50:18

በፊቱ ሰግደው

በፊቱ ወደ መሬት ጐንበስ በማለት ሰግደው፤ ይህ የትህትና እና ለዮሴፍ ክብርን የመስጠት ምልክት ነው፡፡ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?

ዮሴፍ ወንድሞቹን ለማደፋፈር ጥያቄ ይጠቀማል:: አት “እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ አይደለሁም” ወይም “እኔ እግዚአብሔር አይደለሁም” (አግናኝ ወይም ሽንገላ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

እናንተ ክፉ ነገር አስባችሁብኝ

እናንተ ክፉ ነገር አድርጋችሁብኝ

እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው

እግዚአብሔር ለመልካም አደረገው

ስለዚህ አሁንም አተፍሩ

ስለዚህ እኔን አተፍሩ

እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ

ሁል ጊዜ እናንተና ልጆቻችሁ በቂ ምግብ እንዲኖራችሁ አረጋግጣለሁ

አጽናናቸውም ልባቸውን ደስ አሰኛቸው

እዚህ ልቦች ወንድሞቹን ያመለክታሉ:: አት “አጽናናቸውም ደስም አሰኛቸው” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 50:22

መቶ አሥር ዓመት

11ዐ ዓመት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

የኤፍሬም ልጆች እስከ ሶስት ትውልድ

የኤፍሬም ልጆችና የልጅ ልጆች

ማኪር

ይህ የዮሴፍ ወንድ የልጅ ልጅ ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ

ይህ አባበል ዮሴፍ እነዚህን የማኪርን ልጆች የራሱ የልጅ ልጆች አድርጐ ተቀበላቸው ማለት ነው:: ይህም ዮሴፍን ለመውረስ ልዩ መብት አላቸው ማለት ነው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 50:24

በእርግጥ እናንተን ይጐበኛችኋል

በዘፍጥረት 5ዐ: 24./26 “እናንተ” የሚለው ቃል የዮሴፍን ወንድሞች ነገር ግን ደግሞ የእነርሱን ልጆች ያመለክታል፡: (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)

ወደ ምድራችሁ ከዚህ ምድር ያወጣችኋል

ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደ ላይ መውጣት” የሚለውን ቃለ መጠቀም የተለመደ ነው:: አት “ከዚህ ምድር ያወጣችኋል ወደ ምድራችሁ ይወስዳችኋል” (የክስተቶች ቅደም ተከተል ይመልከቱ)

110 ዓመታት

መቶ አሥር ዓመታት

እነርሱም በመድሃኒት ቀቡት

አንድን አስከሬን ከመቀበሩ በፊት እንዳይፈርስ ለማቆየት መድሃኒት መቀባት ልዩ የሆነ መንገድ ነበር በዘፍጥረት 5ዐ 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

ኖረ ወይም ተቀመጠ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት “አኖሩት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

በአስከሬን ሳጥን ውስጥ

“በሬሳ ሳጥን” ወይም “በሳጥን” ይህ ሳጥን የሞተ ሰው የሚቀመጥበት ነው::