Genesis 38

Genesis 38:1

በዚያም ወራት ይሁዳ

ይህ ስለ ይሁዳ የሚናገረውን አድስ የታሪኩን ክፍል ያስታውቃል (አድስ ክስተት መጀመር ስለማስታወቅ ይመልከቱ)

ኤራስ ወደተባለ ዓዶሎማዊ

ኤራስ በዓዶሎም የሚኖር ወንድ ሰው ስም ነው (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

ሴዋ

ሴዋ ይሁዳን ያገባች ከነዓናዊ ሴት ነች (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

Genesis 38:3

እርስዋም ጸንሣ

የይሁዳ ሚስት ጸንሣ

ዔር ተብሎ ተሠየመ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “አባቱ ዔር ብሎ ሰየመው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ስሙንም … ጠራው

ሰየመው

ክዚብ

የቦታ ወይም የሀገር ስም ነው (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

Genesis 38:6

ዔር

ይህ የይሁዳ ወንድ ልጅ ስም ነው:: በዘፍጥረት 38:3 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር

በእግዚአብሔር ፊት የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር የዔርን ክፋት እንደአየው ያመለክታል:: አት: “ክፉ ነበርና እግዚአብሔር አየው” (ፊሊጣው አነጋገር ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ቀሠፈው

ክፉ ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር ቀሠፈው:: ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “ስለዚህ እግዚአብሔር ቀሠፈው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 38:8

አውናን

ይህ ከይሁዳ ወንድ ልጆች የአንዱ ስም ነው በዘፍጥረት 38፡4 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

ወደ ወንድምህ ሚስት ግባ

ይህ ታላቅ ወንድም አግብቶ ሳለ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ተከታይ ወንድሙ ወደ መበለትዋ በመግባት ሩካቤ ሥጋ በመፈጸም ዘርን የማስቀጠል ባህል እንደሆነ ያመለክታል መበለትዋ የመጀመሪያ ወንድ ከወለደች ያ ወንድ ልጅ የሞተው ወንድም ልጅ እንደሆነ በመቆጠር የሟቹን ሀብት ይወርሳል::

በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር

በእግዚአብሔር ፊት የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር የአውናን ክፋት እንደአየው ያመለክታል:: አት: “ክፉ ነበርና እግዚአብሔር አየው” (ፊሊጣው አነጋገር ይመልከቱ)

እንዲሁም ደግሞ እግዚአብሔር ቀሠፈው

ያደረገው ነገር ክፉ ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር ቀሠፈው:: ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “ስለዚህ እንዲሁ ደግሞ እግዚአብሔር ቀሠፈው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 38:11

ምራቱ

የታላቅ ወንድ ልጁ ሚስት

ወደ አባትሽ ቤት

ይህም ማለት በዚህ በአባትዋ ቤት እንዲትኖር ነው:: አት “እናም በአባትሽ ቤት… ቢትኖሪ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ

ይሁዳ ትዕማር ሴሎም ለአካለመጠን በደረሰ ጊዜ እንዲታገባው ያስባል፡፡ አት “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን በደረሰ ጊዜ ሊያገባሽ ይችላል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ሴሎም

ይህ ከይሁዳ ወንድ ልጆች የአንዱ ስም ነው በዘፍጥረት 38፡5 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ

ሴሎም ትዕማርን ቢያገባ እንደ ወንድሞቹ ይሞትብኛል ብሎ ይሁዳ ሠግቶአል:: አት “እርሱ እርስዋን ካገባ እንደወንድሞቹ ይሞትብኛል ብሎ ስለሠጋ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 38:12

ሹዓ

ይህ የወንድ ሰው ስም ነው በዘፍጥረት 38፡2 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

ይሁዳ ከሀዘኑ ተጽናና

ይሁዳም ሀዘኑን ባቆመ ጊዜ

የበጎቹን ጸጉር ወደሚሸልቱት ሰዎች ወደ ተምና

ተምና የበጎቹንነ ጸጉም የሚሸልቱ ስዎች ወዳሉበት ሥፍራ

ተምና … ኤናይም

እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

እርሱና የእርሱ ጓደኛ ዓዶላማዊው ሒራ

ከዓዶላም ጓደኛው ሒራ አብሮት ሄደ

ሒራ ዓዶላማዊው

ሒራ የወንድ ሰው ስም ነው እናም ዓዶላም እርሱ የሚኖርበት ቀበሌ ስም ነው፡፡ በዘፍረት 38፡1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ትዕማር ተነገራት

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “አንድ ሰው ለትዕማር ነገራት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

እይው አማትሽ

ስሚ ፤ እዚህ “እይው” የሚለው ቃል የትዕማርን ትኩረት ለመሳብ ተጠቅሞአል፡፡

አማትሽ

የባልሽ አባት

የመበለትነት ልብስ

መበለቶች የሚለብሱት ልብስ

ሻሽ

ሴቶች ፊታቸውንና ጭንቅላታቸውን ለመሸፈን የሚጠቀሙት ከስስ ጨርስ የተሰራ ልብስ

ራስዋን ተከናንባ

ይህም ሰዎች እንዳያውቃት ራስዋን በልብስ በመከናነብ ሸፈነች ማለት ነው ሴቶች ራሳቸውን መከናነብ የሚያስችላቸው ሰፋፊ ልብሶች በባህሉ የተለመዱ ናቸው አት ሰዎች እንዳያውቃት በሰፋፊ ልብሶች ተከናነበች (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

መንገድ ዳር

በመንገድ ዳር ወይም በመንገድ

ለእርሱ ሚስት ሆና አልተሰጠችም ነበር

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ይሁዳ ለሴሎም ሚስት አድርጐ አልሰጣትም ነበር” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 38:15

ፊትዋን ስለሸፈነች

ይሁዳ እንደ ጋለሞታ ያሰባት ፊትዋን ስለሸፈነች ብቻ ሳይሆን በከተማው መግቢያም ስለተቀመጠች ነው አት ጭንቅላትዋን ስለሸፈነችና ጋለሞቶች በሚቀመጡበት ቦታ ስለተቀመጠች ነበር (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ወደ እርስዋም አዘነበለ

ትዕማር በመንገዱ ዳር ነበረች አት እርስዋም ወደተቀመጠችበት ወደ መንገዱ ዳር ሄደ ወይም አዘነበለ(ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

እባክሽ ነዪ

እባክሽ ወደ እኔ ነዪ ወይም እባክሽ አሁነ ነዪ

ምራቱ

የልጁ ሚስት

Genesis 38:17

ከመንጋዬ

ከፍዬሎች መንጋዬ

ማኀተም ቀለበት ከነማሰሪያው …. በትር

ማኀተም ብር መሣይ በላዩ ላይ ቅርጽ የተቀረጸበት የቀለጠ ሰም ለመቅረጽ የሚጠቀምበት ነው ቀለበት ማኀተም ያለበትና ባለቤቱ በአንገት የሚያደረገው ነው በትር ከረጅም እንጨት የተሠራና በአዳጋች በመንገድ የሚጠቀሙበት ነው

ለእርሱም ጸነሰች

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “እርሱም እርሷን አስረገዛት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 38:19

ሻሽ

ሴቶች ፊታቸውንና ጭንቅላታቸውን ለመሸፈን የሚጠቀሙት ከስስ ጨርስ የተሰራ ልብስ ነበር:: በዘፍጥረት 38: 14 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

የመበለት ልብስዋን ለበሰች

መበለቶች የሚለብሱትን ልብስ ለበሰች:: በዘፍጥረት 38: 14 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

አዶሎማዊ

በአዶሎም ቀበለ የሚኖር ሰው በዘፍጥረት 38፡ 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

መያዣ የሰጣትን

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “መያዣውን ለማስመለስ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ከሴቲቱ እጅ

እዚህ እጅ የሚለው ቃል በእርስዋ ቁጥጥር ሥር እንደሆነ አበክሮት ይሰጣል:: የሴቲቱ እጅ ሴቲቱን ይወክላል:: አት “ከሴቲቱ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 38:21

አዶሎማዊ

በአዶሎም ቀበለ የሚኖር ሰው በዘፍጥረት 38 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

የአገሩ ሰዎች

በዚያ ከሚኖሩ ሰዎች እንዳንዶች

ቤተ ጣዖት ዝሙት አደሪዋ

በቤተ ጣዖት የሚታገለግል ዝሙት አዳሪ

ኤናይም

ይህ የቦታ ስም ነው በዘፍጥረት 38፡14 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

አለዚያ መሳቂያ እንሆናለን

የሆነውን ነገር ሰዎች ከሰሙ በይሁዳ ይስቁበታል ይሣለቁበታል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ወይም ደግሞ የሆነውን ሰዎች ካወቁ ይስቁብናል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ እና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 38:24

እንዲህም ሆነ

ይህ ሀረግ የታሪኩን አድስ አካል ጅማሬ ያመለክታል (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)

ለይሁዳ ተነገረው

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አንድ ሰው ለይሁዳ ነገረው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ምራትህ ትዕማር

ትዕማር የታላቅ ልጅህ ሚስት

ከዚህም የተነሣ ጸነሰች

ከዚህ የሚለው ቃል ከዝሙት ከፈጸመችው ዝሙት ማለት ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከዚህም አረገዘች” ወይም “አረገዘች” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

አምጡአት

አውጡአት

በእሳት ትቃጠል

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እንዲትሞት እናቃጥላታለን” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

እርስዋም ባወጡአት ጊዜ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እነርሱ ባወጡአት ጊዜ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

አማትዋ

የባልዋ አባት

ማኀተም ቀለበት ከነማሰሪያው …. በትር

ማኀተም ብር መሣይ በላዩ ላይ ቅርጽ የተቀረጸበት የቀለጠ ሰም ለመቅረጽ የሚጠቀምበት ነው:: ቀለበት ማኀተም ያለበትና ባለቤቱ በአንገት የሚያደረገው ነው በትር ከረጅም እንጨት የተሠራና በአዳጋች በመንገድ የሚጠቀሙበት ነው:: (በዘፍጥረት 38: 18 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ)

ሴሎም

ይህ ከይሁዳ ወንድ ልጆች የአንዱ ስም ነው:: በዘፍጥረት 38፡5 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

Genesis 38:27

በዚያን ጊዜ

ይህ ሀረግ የታሪኩ አድስ ክፍል መጀመሩን ያመለክታል (አድስ ክስተት ስለማታወቅ ይመልከቱ)

እነሆ

እነሆ የሚለው ከዚህ በፊት ያልታወቀው ትዕማር መንታ ልጆችን እንደተሸከመች እንድንገረም ለማድረግ ተጠቅሞአል

ስትወልድም እንዲህ ሆነ

እንዲህ ሆነ የሚለው ሀረግ በታሪኩ ዋና ክስተት ያመለክታል በቋንቋዎ ይህን የመሰለውን የመግለጽ አባባል ካለ ይጠቀሙ

አንደኛው እጁን አወጣ

ከሕጻኖች አንደኛው እጁን አወጣ

አዋላጅ

አንድ ሴት በሚትወልድበት ጊዜ የሚረዳት ሰው ነው በዘፍረት 35:17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

ቀይ ክር

ደማቅ ቀይ ክር

በእጁ

በአምባሩ ዙሪያ

Genesis 38:29

እነሆ

እነሆ የሚለው ቃል ለሚከተለው የሚያስገርም መረጃ ትኩረት እንድንሰጠው ነው

እንዴት ጥሰህ መጣህ!

ይህ ሁለተኛው ሕጻን ቀድም ሲወጣ አዋላጅዋ በማየት የተደነቀችውን የሚያሳይ ነው:: አት “እንዴት የራስህን መንገድ ጥሰህ ወጣህ!” ወይም “ሰንጥቀህ ቀድመህ ወጣህ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመለከቱ)

ስም ተሰጠው ወይም ተሰየመ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት “እርስዋ ስም ሰጠችው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ፋሬስ

የወንድ ልጅ ስም ነው ተርጓሚዎች እንደሚከተለው የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ:: ፋሬስ የሚለው ስም ጥሶ መውጣት ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ዛራ

ይህ የወንድ ልጅ ስም ነው ተርጓሚዎች እንደሚከተለው የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ:: ዛራ የሚለው ስም ቀይ ክር ወይም ደማቅ ቀይ ክር ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)