Genesis 33

Genesis 33:1

እነሆ

“እነሆ” የሚለው ቃል ለሚያስደንቀው ለታሪኩ አድስ ክፍል ትኩረት እንዲንስጥ ያደርጋል

አራት መቶ ሰዎች

400 ሰዎች (ቁጥሮች ይመልከቱ)

ያዕቆብ ልጆቹን ….. ለሴት አገልጋዮች አከፋፈላቸው

ይህ እያንዳንዷ ሴት ተመሣሣይ ቁጥር ልጆች እንዲኖራት ያዕቆብ ልጆቹን አከፈላቸው ማለት አይደለም እያንዳንዱ ልጅ ከእናቱ ወይም ከእናትዋ ጋር የሆን ዘንድ ያዕቆብ ለጆቹን አከፋፈላቸው (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ሴት አገልጋዮች

“አገልጋይ ሚስቶች” ዘለፋንና ባላን ያመለክታል

እርሱ ራሱ ቀድሞአቸው ሄደ

እዚህ ራሱ የሚለው ያዕቆብ ራሱ በሌሎች ፊት ቀድሞ እንደሄደ ትኩረት ይሰጣል (ተጣቃሽ ተውላጤ ስም ይመልከቱ)

ጐንበስ ብሎ እጅ ነሣ

ጐንበስ ማለት አንድን ሰው በትህትና መቀበልንና ማክበርን ይገልጻል (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

Genesis 33:4

ሊገናኘው

ያዕቆብን ሊገናኝ

ዐቀፈው በአንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው

ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ዔሣው በያዕቆብ ላይ እጆቹን ጠምጥሞ አቀፈው እናም ሳመው”

ከዚያም ሁለቱ አለቀሱ

ይህ በግልጽ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ከዚያም እንደገና በመተያየታቸው ተደስተው ዔሣው ያዕቆብ አለቀሱ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ሴቶቹንና ልጆቹን አየ

ከያዕቆብ ጋር ያሉ ሴቶቹንና ልጆቹን አየ

እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው

የአንተ አገልጋይ የሚለው ሀረግ ያዕቆብ ራሱን በትህትና ያቀረበው መንገድ ነው:: አት: “እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

Genesis 33:6

አገልጋይ ሴቶች

ሴት አገልጋዮች፡፡ ባላንና ዘለፋን ያመለክታል፡፡

ጐንበስ አለ

በሌላ ሰው ፊት ትህትናንና አክብሮትን የሚያሳይ ምልክት ነው:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)

ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድን ነው?

“ይህ ሁሉ” የሚለው ሀረግ ያዕቆብ በየቡድኑ በባሪያዎች ለዔሣው የላከውን ስጦታዎች ያመለክታል:: አት: “እነኛ የተለያዩ ቡድኖች ሁሉ እንዲገናኙኝ ለምን ላክሃቸው?”

በጌታዬ ፊት ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው

ሞገስ ማግኘት የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ማረጋገጥ የሚል ትረጉም የያዘ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው እንዲሁም ደግሞ ፊት ፍርድን ወይም ግማገማን ይወክላል አት አንተ ጌታዬ እንዲትደሰትብኝ ነው (ፈሊጣዊና ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ጌታዬ

ጌታዬ ዔሣው በትህት መንገድ ዔሣው የተገለጸበት ነው:: (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

Genesis 33:9

እኔ በቂ አለኝ

እንስሳት ወይም ንብረት የታወቁ ቃላት ናቸው:: አት: “በቂ እንስሳት አለኝ ወይም በቂ ንብረት አለኝ” (ድብቅ አገላለጽ ይመልከቱ)

በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ

ሞገስ ማግኘት የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ሰለማኘት የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው እዚህ ዓይን የማየት ምትክ ቃል ሲሆን ማየት ግምገማውን የሚገልጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው:: አት: “በእኔ የተደሰትህ እንደሆነ” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የሊጣዊና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እጅ መንሻዬ

“እጅ” ያዕቆብን ያመለክታል አት ይህ ለአንተ የሚሰጠው እጅ መንሻዬ ነው (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

በውኑ እጅ መንሻዬ

እንደ አድስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “በእርግጥም እጅ መንሻዬ”

የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና

ይህ ተመሣሣይ አባባል ግልጽ አይደለም ተገቢ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው 1 እግዚአብሔር ይቅር እንዳለለት ዔሣውም ይቅር እንዳለው ያዕቆብ ደስተኛ ነው ወይም 2 ያዕቆብ እግዚአብሔርን በመገናኘቱ እንደተደነቀው ሁሉ ዔሳውን በመገናኘቱ ተደንቆአል 3 ያዕቆብ በእግዚአብሔር መገኘት ራሱን እንዳዋረደው ሁሉ በዔሣው ፊት ራሱን ያዋርዳል (ተመሣሣይ አባባሎችን ይመልከቱ)

ፊትህን አይቻለሁ

እዚህ ፊት ዔሣውን ያመለክታል ይህ ፊት በመባል ሊተረጐም ይችላል፤ ምክንያቱም “ፊት” የሚለው ቃል በዘፍጥረት 32:3ዐ “የእግዚአብሔር ፊት” እና “ፊት ለፊት” ለመግለጽ ተጠቅሞአል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ይህችንም ያመጣሁልህ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ይህም አገልጋዮቼ ያመጡልህ” (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

እግዚአብሔር በቸርነቱ አሟልቶ ስለሰጠኝ

እግዚአብሔር በቸርነቱ ስለመለከተኝ ወይም እግዚአብሔር እጅግ በጣም ስለባረከኝ

ያዕቆብም አጥብቆ ስለለመነው ዔሣው እጅ መንሻውን ተቀበለ

አንድን ሥጦታ ላለመቀበል መገዳደር ነገር ግን ከዚያ በኋላ ሰጪው እንዳያዝን መቀበል የተለመደ ባህላዊ መንገድ ነው

Genesis 33:12

ጌታዬ ያውቃል

ይህ በትህትናና በመደበኛ መንገድ ዔሣውን ማመልከት ነው:: አት: “አንተ ጌታዬ ታውቃለህ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

ልጆች የጠኑ አይደሉም

ትርጉሙም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አት፡ “በፍጥነት ለመጓዝ ልጆች ገና የጠኑ አይደሉም”:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)

አንዲት ቀን እንኳ በጥድፍያ ቢነዱ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ለአንድ ቀን እንኳ በፍጥነት እንዲጓዙ ቢናጣድፋቸው” (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ጌታዬ ከባሪያው ቀድሞ ይሂድ

ይህ ያዕቆብ ራሱን በመደበኛና በትህትና መንገድ የሚገልጸው ነው:: አት: “ጌታዬ እኔ ባሪያህ ነኝ” (ከፊቴ ቀድመህ ሂድ አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

በሚነዱአቸው እንስሳት እርምጃ ልክ

“በሚነዱአቸው እንስባት እርምጃ ፍጥነት መጠን”

ሴይር

በኤዶም ግዛት የሚገኝ ተራራማ ሥፍራ ነው፡፡ በዘፍጥረት 32 3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)

Genesis 33:15

ለምንድር ነው?

ዔሣው ሰዎቹን መተው እንደሌለበት ለማጽናት ያዕቆብ ጥያቄን ይጠቀማል:: አት: “ይህን አታድርገው” ወይም “ይህን ማድረግ አይገባህም” (አግናኝ ጥያቄዎች ይመልከቱ)

ጌታዬ

ይህ በመደበኛና በትህትና ዔሣውን የሚግለጽ ነው:: አት: “አንተ ጌታዬ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

ሱኮት

ተርጓሚዎች እንደግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ ሱኮት የሚለው ስም መጠለያዎች ማለት ነው ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ

ለራሱ ቤትን ወይም መጠለያን ሠራ

ይህ የተሠራው ቤት ለቤተሰቡም እንደሆነ ያመለክታል፡፡ አት፡ “ለራሱና ለቤተሰቡ ቤት ሠራ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ለመንጋው

ለሚጠብቁአቸው እንስሳት

Genesis 33:18

አጠቃላይ መረጃ

ይህ አድስ የታሪኩን አካል ይጀምራል በሱኮት ካረፈ በኋላ ያዕቆብ ምን እንዳደረገ ጸሓፊው ይገልጻል

ያዕቆብ ወደ ጳዳን አራም በመጣ ጊዜ

ያዕቆብ ….. ደረሰ ….. ሠፈረ

ይህ ያዕቆብ የቤሰቡ መሪ ስለሆነ እርሱን ብቻ ይጠቅሳል::

የእርሱም ቤተሰብ ከእርሱ ጋር እንደነበር ግልጽ ነው (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አጠገብ ሠፈረ

በቅርበት ሠፈረ

ከፊል መሬት

ከፊል ቦታ

ኤሞር

የአንድ ሰው ስም ነው

የሴኬም አባት

ሴኬም የሰውዬውና የከተማይቱ ስም ነው

አንድ መቶ

1ዐዐ (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

ኤል ኤሎሄ እስራኤል

ተርጓሚዎች የግርጌ ማስታወሻ እንደሚከተለው ሊጨምሩ ይችላሉ አት ኤል ኤሎሄ የሚለው ቃል እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)